May 25, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ ‹በቦታው› የተገኘበት ስብሰባ እና መግለጫ

ማጠቃለያ ሪፖርታዥ (READ IN PDF)

·   የመግለጫው የመጀመሪያ ረቂቅ ምልአተ ጉባኤው ያልመከረባቸውን ዐበይት ጉዳዮች ያካተተ እንደነበር ተጠቁሟል፤ የዋልድባ እና የነ አባ ፋኑኤል የሐሰት ስኬት በሥርዋጽ ገብቶበት ነበር
·     አባ ጳውሎስ ምልአተ ጉባኤው ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ውሳኔ ባስተላለፈበት ቃለ ጉባኤ ላይ አልፈርምም ብለዋል፤ ስለማኅበሩ በመግለጫው ላይ የሰፈረውን አንቀጽም አላነብምየሚል አተካራ ውስጥ ገብተው ነበር
·     ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ከኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስነት አንሥቶ ወደ ጉጂና ቦረና ሊበን ዞኖች ሀ/ስብከት ለማዛወር በፓትርያ የቀረበው ሐሳብ ውድቅ ተደርጎ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ደርበው እንዲመሩ ተወስኗል
·      አገር ዓቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መሥራች ጉባኤ ከግንቦት 26 - 27 ቀን 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

May 23, 2012

የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ


(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 15/2004 ዓ.ም፤ May 23/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ቅዱስ ሲኖዶስ ሲያካሒድ የሰነበተውን ጉባኤ ባለ አሥር ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀቀ። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ይመልከቱ። ዝርዝሩን እንመለስበታለን።

ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!!
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡ 

ጽጌ ስጦታውና ሰባት ግለሰቦች ማዕርገ ክህነታቸው ተገፎ እንዲወገዙ ተወሰነ


የቅዱስ ሲኖዶስ ዐሥረኛ ቀን የቀትር በኋላ ውሎ

·         ቅዱስ ሲኖዶስ በውሳኔው መግለጫ ዝግጅት ላይ ጥንቃቄ አድርጓል፤ በመላው ዓለምየሚሠራጨውን መግለጫ በጽሑፍ የሚያዘጋጁት ከምልአተ ጉባኤው የተመረጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።
·      አባ ሰረቀ በተጠየቁበት ጉዳይ እምነታቸውን በጽሑፍ ይገልጣሉ፤ ለ”እውነትና ንጋት” ሌላ ማስተባበያ መጽሐፍ እንዲጽፉ ተወስኗል።
·        ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ለፕሮቴስንታንት ቤተ እምነት የጻፉት ደብዳቤ የእርሳቸው ላለመኾኑ በጽሑፍ ያረጋግጣሉ።
·        በጋሻው ደሳለኝ ተጨማሪ ስሕተቶቹ ተመርምረውና ራሱም ተጠይቆ የውሳኔ ሐሳብ እንዲቀርብ ተወስኗል።

የቅ/ሲኖዶስ (2004) ጉባኤ መግለጫ Synod Genbot 2004 Meglecha

“ደጀ ሰላም” የማ/ቅዱሳን ናት በሚል “ኢትዮፕያንሪቪው” ላይ ለተስተናገደ ጽሑፍ የተሰጠ ማስረጃዊ ምላሽ


(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 14/2004 ዓ.ም፤ May 22/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ደጀ ሰላም የማ/ቅዱሳን ናት በሚል የተለያዩ የተሐድሶ መናፍቃን ብሎጎች (ባለጌዎች) ሲጽፉ ከመቆየታቸውም በላይ ኢትዮጵያን ሪቪው ላይ ጽሑፋቸውን እስከማውጣት ደርሰዋል (ጽሑፉን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)። ለብልግናቸው መልስ መስጠት ባይገባንም “ማስረጃ” ብለው ያቀረቡትን ማታለያ ግን ዝም ብለን ልናልፈው አልፈቀድንም።

May 22, 2012

ሰበር ዜና - ቅዱስ ሲኖዶስ በተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅቶች ላይ የቀረበውን ጥናታዊ መግለጫ እና የውሳኔ ሐሳብ አጸደቀ

 ማ/ቅዱሳን ከሰ/ት/ቤቶች መምሪያ ሥር እንዲወጣና ራሱን እንዲችል ወሰነ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዐሥርኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎ
·  በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ግለሰቦች ላይ የቀረበውን ጥናታዊ መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ ደግሞ ከሰዓት በኋላ በመነጋገር እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል:: (READ THE DOCUMENT from HERE)
   ·    ማኅበረ ቅዱሳን በአወቃቀሩ ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ወጥቶ ለዋና ሥራ አስኪያጁ ተጠሪ እንዲኾን ቅዱስ ሲኖዶሱ ወስኗል::
·    በእሳታዊው ዘመን ወደ እሳታዊው ቤተ ክህነት - ቀልጦ መቅረት ወይም ነጥሮ በመውጣት የተቋማዊ ለውጥ አብነት መኾን!!
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 14/2004 ዓ.ም፤ May 22/ 2012/ READ THIS IN PDF)፦ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዐሥርኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው በስምንት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ድርጅቶች ላይ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና የሊቃውንት ጉባኤ አባላት ጥምር ኮሚቴ ያቀረበውን ጥናታዊ መግለጫ እና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ አጽድቋል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዘጠነኛ ቀን ውሎ


ቅዱስ ሲኖዶስ የማኅበራት መተዳደርያ ደንብ ጥናት ዳግመኛ ተጠንቶ እንዲቀርብ አዘዘ
አርእስተ ጉዳይ-
·        በማኅበራት መተዳደሪያ ደንብ ዝግጅት ላይ የቀረበው ጥናት የጽዋ፣ የጉዞና የስብከተ ወንጌል ማኅበራት፤ የጽርሐ ጽዮን አንድነት ማኅበር፣ የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበረና የማኅበረ ቅዱሳን ህልውና እንዲከስም የሚጠይቅ ነው
·        የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበዋል
·        የሰንበት /ቤቶች / ሊቀ ጳጳስ ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተና ጸሐፊውለመሪያው የማይመጥኑበሚል ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ጠይቀዋል
·        ዕንቍ ባሕርይ በማ/ ላይ ተጨማሪ የክስ ደብዳቤ ለምልአተ ጉባኤው አሰራጭቷል፤ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ እና የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች ዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት ቀርበው ያስረዳሉ

May 21, 2012

WHAT WE WROTE LAST YEAR


“ነጻው ሚዲያ” ስለ ቤተ ክርስቲያን ባለው አመለካከት “ነጻ” መሆኑን ያሳይ
  • ኦርቶዶክሳዊ ፀሐፊዎች እየመሰሉ፣ በመግቢያቸው “ወያኔ ይውደም” የሚል ማባበያ ቃል እየጨመሩ ነገር ግን “ቤተ ክርስቲያን ትውደም” የሚለውን ግብ ያነገቡ ጽሑፎች በየዕለቱ ማንበብ ይዘናል።
(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 26/2011፤ ጥር 18/2003 ዓ.ም)፦በተለምዶ “ነጻ ሚዲያ” እየተባለ የሚጠራው ከመንግሥት ቁጥጥር ውጪ የሆነውና በተለያዩ ግለሰቦች እና ቡድኖች የሚንቀሳቀሰው ሚዲያ ነው። “ሚዲያ” ያልነውን ራሱን ከለተመለከትነው ደግሞ የሕትመት ውጤቶችን ማለትም ጋዜጣና መጽሔቶችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያውን ማለትም ሬዲዮና ቴሌቪዥኑን፣ እንዲሁም ድረ ገጾችን ሁሉ ያጠቃልላል። እነዚህን ሁሉ ጠቅልሎ በማጥናት ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የሚያስተላልፉትን ለመመልከት ብዙ ጊዜ እና የሰው ኃይል እንዲሁም ገንዘብ የሚጠይቅ ቢሆንም በመጠነኛ የወፍ በረር (Birds Eye-view) ቅኝት ያገኘነውን ሐሳብ መነሻ አድርገን ትዝብታችንን ለመጠቆም እንደማይከለክለን እንረዳለን።

May 19, 2012

በብዙ ጫና ውስጥ ያለው ማ/ቅዱሳን መንግሥት በዋልድባ አካባቢ ስለሚገነባቸው ፕሮጄክቶች ሪፖርቱን አቀረበ


  •    ሪፖርቱ የጠ/ቤተ ክህነት ሓላፊዎች “አቀረብን” ካሉት በይዘትም በተአማኒነትም የተሻለ ነው።
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 10/2004 ዓ.ም፤ May 18/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ማ/ቅዱሳን መንግሥት በዋልድባ አካባቢው ሊሠራው ስላቀደው ግዙፍ ሮጄክት “አጠናሁት” ያለውን ሪፖርት አቀረበ፤ ከመንግሥት ጋር መነጋገሩንም ገለጸ። ዛሬ ይፋ የተደገው የማኅበሩ ሪፖርት የቤተ ክህነቱ አዳዲስ ተሿሚዎች ማኅበሩን በዋልድባ ጉዳይ በከሰሱ ማግስት የቀረበ ሲሆን ለእነርሱ ክስ የተሰጠ አፋጣኝ ምላሽ ይሁን አይሁን ወደፊት የሚታይ ይሆናል።

May 18, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሰባተኛ ቀን ውሎ ሪፖርታዥ


·         አባ ጳውሎስ በእመቤታችን ንጽሕና ላይ እምነታቸውን እንዲገልጡ ቢጠየቁ አንደበታቸው ተሳሰረ፤ ለጥያቄው መነሻ የኾነው ፓትርያርኩ በአባ ሰረቀ ‹መጽሐፍ› ላይ ስለተጠቀሰው የዶክትሬት ጽሑፋቸው ዝምታን በመምረጣቸውና ኮሚቴውም የእርሳቸውን ምላሽ ወይም አቋም አለመመርመሩ ነው - “አባ ሰረቀ ጽሑፍዎን ጠቅሰው መጽሐፍ ከጻፉ በኋላ ለምን ዝም አሏቸው? ኮሚቴውስ ለምን አልጠየቀም? ይሉኝታ ነው ወይስ ተመሳስሎ ለመኖር ነው?” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም - ነደ ‹ተሐድሶ›/
·         አባ ጳውሎስ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ ኮሚቴው ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ “አልቀበልም፤ ኮሚቴው በትክክልና በጥራት አልሠራም” በሚል ያመጡትን ተለዋጭ ሐሳብ ቅዱስ ሲኖዶሱ ውድቅ በማድረግ ሪፖርቱ ተባዝቶ እንዲደርሰው አዝዟል፤ ከዛሬ ጀምሮ በእያንዳንዱ የውሳኔ ሐሳብ ላይ በጥንቃቄ እየተወያየ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል

May 17, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ስድስተኛ ቀን ውሎ ሪፖርታዥ

·      ኮሚቴው ፍጹም ውግዘት የሚገባቸውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ለይቷል - ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት፣ አሸናፊ መኰንን፣ አግዛቸው ተፈራ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ ይገኙባቸዋል።
·         “ሃይማኖቴ እንደ አባቶቼ ነው” ያሉት የአባ ሰረቀ እና “የቅን ልቦና የመንፈሳዊና የፈውስ አገልግሎትን ያቋቋምኹት ልጆቼን የማበላቸው ስለተቸገርኹ ነው” ያሉት የ‹ሊቀ ካህናት› ጌታቸው ዶኒ ጉዳይ ያለውሳኔ ሐሳብ ለምልአተ ጉባኤው ውሳኔ ቀርቧል።
·    አባ ጳውሎስ ከጥንተ አብሶ ጋራ በተያያዘ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕና እንዲመሰክሩ ሊጠየቁ ይችላሉ።

ማ/ቅዱሳን በዋልድባ አካባቢ ስለሚገነባው የስኳር ፕሮጄክት “መልካምነት” ባለመዘገቡ ተጠየቀ፤ መልስ እንዲሰጥ ይጠበቃል


(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 9/2004 ዓ.ም፤ May 17/ 2012/ READ THIS IN PDF)፦ ማ/ቅዱሳን መንግሥት በዋልድባ አካባቢው ሊሠራው ስላቀደው ግዙፍ የስኳር ሮጄክት “መልካምነት” ባለመዘገቡ ሊወነጀል ነው። አዲስ በተሾሙት የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ኃላፊ በመምህር ዕንቁ ባሕርይ ተከስተ ተፈርሞ የወጣውና “በዋልድባ አካባቢ መንግሥት ሊሠራ ያቀደውን ግዙፍ የስኳር ፋብሪካን በማስመልከት በዋልድባ ይዞታ ላይ ያደረሰው ተጽእኖ መኖር አለመኖሩን የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ ተፈላጊውን የማጣራት ሥራ አከናውኖ” ከተመለሰ በኋላ “ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠቱና … የማኅበረ ቅዱሳን ጋዜጠኞች መከታተላቸው መሣተፋቸውና የሚፈልጉትን ጥያቄ በይፋ አቅርበው ምላሽ መሰጠቱ”ን በመጥቀስ ይጀምራል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ስድስተኛ ቀን ውሎ (አርእስተ ጉዳይ)


/ ሲኖዶስ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ የተዘጋጀውን ሪፖርት አዳመጠ
 (ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 8/2004 ዓ.ም፤ May 16/ 2012/ READ this news IN PDF)፦
·        ኮሚቴው ፍጹም ውግዘት የሚገባቸውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ለይቷል - ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት፣ አሸናፊ መኰንን፣ አግዛቸው ተፈራ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ ይገኙባቸዋል

በሩቅ ምሥራቅ የሚገኙ “የኢ/ኦ/ተ ምእመናን ጉባኤ” ለቅዱስ ሲኖዶስ መልእክት ጻፈ


(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 8/2004 ዓ.ም፤ May 16/ 2012/ READ THIS IN PDF)፦ በሩቅ ምሥራቅ የምንገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ጉባኤ” የተባለና በትምህርትና በሥራ በሩቅ ምሥራቅ በዝርወት ተበትነው ባሉ ምእመናን ያቋቋሙት ጉባኤ ለቅዱስ ሲኖዶስ መልእክት ላከ፤ በቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገን ላይ የተፈፀመውን ሕገ ወጥ ተግባር ተቃወመ።

May 15, 2012

“በሕገወጦች በጨለማ የተዘጋጀው ደብዳቤ ተበተነ” (ማ/ቅዱሳን)

(ማ/ቅዱሳን፤ ግንቦት 7/2004 ../) READ IN PDF):- ከጥቂት ቀናት በፊት ማኅበረ ቅዱሳን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ማእከላዊ አስተዳደር ተገዥ ካለመሆን አልፎ የተቋሙን ሕልውና ወደ መፈታተን እንደ ደረሰ በማተት የሚከስ ደብዳቤ ለሕግ ተገዢ ባልሆኑ ግለሰቦች በጨለማ ተረቅቆ በመምሪያው ሓላፊ እንዲፈረም ተደርጎ ሊወጣ እንደ ነበር፤ ነገር ግን በመምሪያው ሓላፊው በቆሞስ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ መታገዱን ገልጸን ነበር፡፡

የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣን ጽሑፎች የሚመረምር ኮሚቴ ተቋቋመ


·        አባ ጳውሎስ በጉባኤው ላይ እንዲቀርቡ ለተጠሩት አዘጋጆች በተፈለጉበት ጉዳይ ዙሪያ ሲመክሩና ነገር ሲያስጠኑ አምሽተዋል፤ አዘጋጆቹን አቅርቦ ለመጠየቅ የነበረው ዕቅድ ተሰርዞ እንዳይገቡ ተደርገዋል::
·        “እኔ የግል ቤት የለኝም፤ መኪና የለኝም፤ ሲኖዶሱ መወሰንና ርምጃ መውሰድ አለበት” (ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)
·        “ለቤተ ክርስቲያን አደጋ ነው፤ መወሰን አለብን” (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ)
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 7/2004 ዓ.ም፤ May 15/ 2012/ READ THIS IN PDF)፦ ዛሬም ለተከታታይ ሁለተኛና ሙሉ ቀን በዜና ቤተ ክርስቲያን ጽሑፎች ላይ ሲወያይ የዋለው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ

በዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ላይ ያተኮረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አራተኛ ቀን ውሎ

READ THIS IN PDF.
·        አባ ጳውሎስ ጉዳዩ አጀንዳ እንዳይኾን ተቃውመው ነበር
· እትሙ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውን ቅዱስ ሲኖዶስ ክብር የሚያቃልልና መጥፎ አርኣያነት ያለው መኾኑ በጉባኤው አባላት አጽንዖት ተሰጥቶበታል
·        የጋዜጣው ተጠሪነት ለማን እንደ ኾነ አልታወቀም
·        የጋዜጣው ዋና እና ምክትል አዘጋጆች፣ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና እና ምክትል ሓላፊዎች ዛሬ ቀርበው ይጠየቃሉ
·      የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ንብረት ጉዳይ በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳነት ተይዞ ለቋሚ ሲኖዶስ ተመርቶ ነበር
·  ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝ ቅ/ሲኖዶስ ፍርድና ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)