April 5, 2012

ከክህነት ስለሚያስሽሩ ምክንያቶች አንዳንድ ነጥቦች ከፍትሐ ነገሥት


ካህናትን ከክህነታቸው ስለሚያሽሩ ምክንያቶች
አንዳንድ ነጥቦች ከፍትሐ ነገሥት
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 27/2004 ዓ.ም፤ ኤፕሪል 5/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አዲስ ሊቀ ጳጳስ ተሹሞ ተልኳል ከተባለበት ከጥቅምት ወር 2004 ዓ.ም ጀምሮ በችግር ላይ ይገኛል። ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በሀ/ስብከቱ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በቃለ ዓዋዲው መሠረት የመረጡትን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አልቀበልም ከማለት አልፈው ካህናቱን በሙሉ ማስፈራራት እና አንዳንዶቹንም “አውግዣለሁ” ማለት ጀምረዋል። ይህም መነሻ ሆኖን “ካህናትን ከክህነታቸው ስለሚያስሽሩ ምክንያቶች”፣ በደፈናው ከመሬት ተነሥተው “ክህነት ይዣለሁ” ስለሚሉ አቡነ ፋኑኤልን ስለመሳሰሉ ጳጳሳት አስቀድመው በቅዱሳን አበው የተሠራውን ሕግ በተመለከተ ፍትሐ ነገሥቱ የሚለውን ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን።

+++
ክህነ መዓረጉ ምጡቅ፣ ምሥጢሩ ረቂቅ ነው፡፡ የሰማያዊው ንጉሥ የእግዚአብሔር ወኪል ከመሆን የበለጠ ሥልጣን የለምና፤ ይህ ሥልጣን በሰማይም በምድርም የሚሠራ ነው፡፡ ስለዚህ ከምድራዊው ሥልጣን የላቀ ነው፡፡ ይህን ሥልጣን ለመቀበል ሊሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች እንደመኖራቸው ሥልጣኑን ያለ አግባብ ሲጠቀሙበት የተገኙ ወይም የክህነት ሥልጣን ከሚፈልገው ሕግና ሥርዓት ውጭ ሆነው የተገኙ ተሿሚዎች ክህነታቸው የሚያዝበት ወይም ከክህነት የሚሻሩበት ቀኖናም ተቀንኑዋል፡፡ ይህ ክታብ ለመጀመሪያ ዜ በ1958 ዓ.ም በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ በ1995 ዓ.ም በትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት የታተመውን ፍትሐ ነገሥት ንባብና ትርጓሜውን መሠረት ያደረገ ነው በዚህ ክታብ ላይ ለመዳሰስ የተሞከረው በፍትሕ መንፈሳዊ ካህናት ከሹመታቸው ስለሚሻሩበት ሁኔታ የተገለጸውን ለመጠቆም ነው፡፡
+++
በእንተ ጳጳሳት

ጵጵስና የክህነት የመጨረሻው ደረጃ ነው፡፡ እዚህ ደረጃ ላይ የሚደርሱ አባቶች በሁሉ ነገር የተመሠከረላቸው ነቅ የሌለባቸው ሊሆኑ እንደሚገባ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ያዛል፡፡ ዳሩ ግን አንዳንድ ጊዜ ሳይገባቸው በተለያየ ምክንያት እዚህ መዓረግ ላይ የሚደርሱ አሉ፡: የጵጵስና ማዕረግ ላይ ደርሶ ሳለ ከሕግና ከሥርዓቱ ውጭ ሆኖ የተገኘ ከክህነቱ ይሻራል፡፡ አንድ ጳጳስ ከጵጵስናው ከሚሻርባቸው ብዙ ምክንያቶች የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ተኛው ክፍል በአንጾኪያ የተሰበሰቡ ሊቃውንት በአሥራ ሰባተኛው አንቀጽ ሊቀ ጳጳስ፣ ጳጳስ፣ ኢጲስ ቆጶስም ቢሆን በሥራ በመሾም በመሻር በማጥመቅ በማቁረብ በማስተማር አንድ ናቸው፡፡ ከተሾመ እኒህን መዓረጋት ከተቀበለ በኋላ ቤተ ክርስቲያን የማያገለግል ካህን አንድ ዕለት አንድ ሰዓትም ቢሆን ይሻር፡፡

ቦታውን /መንበሩን/ ትቶ ቢሔድ እሺ ብሎ ወደ ቦታ እስኪመለስ ድረስ የሀገሩ ሰዎች /በሀገረ ስብከቱ ያሉ ካህናት ምዕመናን/ ይማልዱት ለምነውት አልመለስም ቢል ከምእመናን አንድነትም ይለይ፡፡ የሀገሩ ሰዎች /የሀገረ ስብከቱ ካህናት ምእመናን/ ከለመኑት በኋላ ካልተመለሰ ይሰደድ፡፡ አንድም የሀገሩ ሰዎች ከለመኑት በኋላ ቢመለስ ከእነርሱ ዘንድ ሊያኖሩት ቢወዱ ስሙንም በጸሎት ሊያነሱ ቢወዱ ፈቃድ አላቸው፡፡ ካልወደዱ ግን ስሙንም በጸሎት አያንሱ፡፡ እሱ እንደጸለየላቸው ሊጸልዩ ይገባልና፡፡ እሱ እንዳልጸለየላቸው ሊጸልዩለት አይገባምና፡፡  (መንፈሳዊ ፍትሐ ነገሥት ገጽ 1ዐዐ)

ሐዋርያት በሦስተኛው ቀሌምንጦስ 62ኛው አንቀጽ ሁለት ጊዜ የተሾመ ይሻር እንዳልን ሳይሾም ሁለት ሚስት አግብቶ የተገኘ ተሿሚው ሿሚውም ይሻር፡፡ ሿሚው ሁለት ሚስት ማግባቱን ያላወቀ ቢሆን ተሿሚው ብቻ ይሻር፡፡
ሠለስቱ ምዕት በኒቂያ በጻፉት መጻፍ በሠለሳ አምስተኛው አንቀጽ ፈጽሞ ቂም የሚይዝ ሁል ጊዜ እስከ ማውገዝ ደርሶ ፈጥኖ የሚቆጣ ኤጲስ ቆጶስ ቢኖር ይህን ቂሙን የማይተው፣ ሊያከብሩት የሚወድ ቂሙን የማይረሳ ሁል ጊዜ ፈጥኖ እንዳያወግዝ ከሹመቱ ይሻር ከማዕረጉ ይዋረድ፡፡

ሐዋርያት በሁለተኛው ምንጦስ በሃያ አራተኛው አንቀጽ ሕዝቡን የሚያስተምራቸው የሚመክራቸው በውግዘት ያይደለ ሕማማተ መስቀልን አስተምሮ አንድ የሚያደርጋቸው መምህር ይሁን አሉ፡፡ በማይገባ አይሠር፣ አያውግዝ፡፡ በማይገባ ቢያሥር ቢያወግዝ ሰዎችን ሊያሳዝናቸው በድለናል ብለው ሊገዙለት ወዶ ይህን ቢያደርግ እሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታሠራ የተወገዘ ይሁን፡፡

ካህናቱ በእውነት ነገር ይክሰሱት ሥራት ቢያጸናባቸው ሥራውን ለሊቀ ጳጳሱም ቢሆን ያስታውቁ፡፡ በእውነት ይነሱበት፡፡ ክርስቶስ በወርቅ ደሙ የተዋጃቸው ምእመናንን ይበድላቸው ዘንድ በሹመት ጸንቶ ሊኖር አይተዉት፡፡ እንዳያሳዝናቸው እግዚአብሔርን ወደ መስደብ ወንጌልን ወደመንቀፍ እንዳያደርሳቸው በሹመት ጸንቶ ይኖር ዘንድ አይተዉት፡፡ በሹመቱም አይዘዝ፡፡ ለሱ እንደሚገባው መጠን በደሉን አምኖ ቀኖናውን ተቀብሎ በበጎ ነገር ጸንቶ ይኑር፡፡ አንድም በበጎ ነገር ቀኖናውን ተቀብሎ ጨዋ ሆኖ ይኑር፡፡  /መንፈሳዊ ፍትሕ ነገሥት ገጽ 12/

የአንጾኪያ ሊቃውንት በጻፉት መጽሐፍ በአሥራ ሁለኛው አንቀጽ ተሿሚ አልፎ ሲሔድ ወደ ሌላ ሀገር ቢደርስ በዚያ ቦታ ቅስና ወይም ዲቁና ሊሾም ቢወድ የሀገሩ ጳጳስ፣ ኢጲስ ቆጶሳት ይሾም ዘንድ ሹም ብለው ካልጻፉለት በራሱ ፈቃድ ቢሾም የሾማቸው ሰዎች ይሻሩ፤ ሿሚውም ይሻር፡፡

በዕንቁራ የተሰበሰቡ ሊቃውንት በጻፉት መጽሐፍ በአሥራ ስድስተኛው አንቀጽ በሀገሩ ኤጲስ ቆጶስነት የተሾመ የሀገሩ ሰዎች ባይቀበሉት ወይም ከእነሱ ብዙዎች ባይቀበሉት በሥራው ሁሉ ጠብ ክርክር ቢሆን እሱ ከተሾመ አገር ጥለን እንሔዳለን ቢሉ /ሀገረ ስብከቱ እንለያለን/ ቢሉ በሀገሩ ቀድሞ የተመውን ቢጣሉት ይሻር፡፡

በሃያ ሦስተኛ ሐዋርያት በሦስተኛው ቀሌምንጦስ በስልሳ አራተኛው አንቀጽ ደጋግ ምእመናን ኤጲስ ቆጶሱን ቢከስሱት ኤጲስ ቆጶሳቱ ወደ ጉባኤ ሊጠሩት ይገባል፡፡ መጥቶ በደሉን ቢያምን በሠራው ሥራ ይቅጡት፡፡ ይፍረዱበት፡፡

ሐዋርያት በሁለተኛው ቀለምንጦስ፣ በሃያኛው፣ ሠለስቱ ምዕት በኒቂያ በጻፉት መጽሐፍ በሃምሳ ሦስተኛው፣ ባስልዮስ በጻፈው መጽሐፍ በአርባ አምስተኛው አንቀጽ ይችን ማዕረገ ክህነት መማለጃ ሰጥቶ የተሾማት ኤጲስ ቆጶስ፣ ቄስ፣ ዲያቆን ይሻር  አሉ፡፡ መማለጃ ተቀብሎ የሾመውም ይሻር፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡

9 comments:

Anonymous said...

egzer yihen liyasawuken new endih yehonew. sti bezih zuria sefa adrigachihu astemirun. beyebotawko temesasay chigir new yalew.

Anonymous said...

"ሐዋርያት በሁለተኛው ቀለምንጦስ፣ በሃያኛው፣ ሠለስቱ ምዕት በኒቂያ በጻፉት መጽሐፍ በሃምሳ ሦስተኛው፣ ባስልዮስ በጻፈው መጽሐፍ በአርባ አምስተኛው አንቀጽ ይችን ማዕረገ ክህነት መማለጃ ሰጥቶ የተሾማት ኤጲስ ቆጶስ፣ ቄስ፣ ዲያቆን ይሻር አሉ፡፡ መማለጃ ተቀብሎ የሾመውም ይሻር፡፡"

ይሄ ሕግ ቢከበር ቤተ ክርስቲያናችን ከብዙ መከራ ትድን ነበር::

Anonymous said...

leKahin mistiru endih hono sale, sewoch lemin yaguremerimalu. Ene eko yemigermegn Abune Fanuel, min eyaregu new. Min ale endeAbat esachewin tewu biluachew. Alebeleziya gin yih tiwilid mawared bicha ayidelem sisedibachew new yeminorew. kezih yisewiren. EgziO

Anonymous said...

"ካህናቱ በእውነት ነገር ይክሰሱት፤ ሥራት ቢያጸናባቸው ሥራውን ለሊቀ ጳጳሱም ቢሆን ያስታውቁ፡፡ በእውነት ይነሱበት፡፡ ክርስቶስ በወርቅ ደሙ የተዋጃቸው ምእመናንን ይበድላቸው ዘንድ በሹመት ጸንቶ ሊኖር አይተዉት፡፡ እንዳያሳዝናቸው እግዚአብሔርን ወደ መስደብ ወንጌልን ወደመንቀፍ እንዳያደርሳቸው በሹመት ጸንቶ ይኖር ዘንድ አይተዉት"

Aresema said...

“ነካክተው ነካክተው የተኛውን በሬ አደረጉት አውሬ “
ደጀሰላማዌያንን እጅግ በጣም ላመስግን እውዳልሁ
‘ማንነቱን ለማውቅ ጛደኞቹን ማወቅ” ይባልየለ
ለሳቸ ው ትልቅ ሰው እና አዋቂ አቶ ሐይለየሱስ ነው
የሚገር መኝ የማይነካን ሰው መንካት ምንየሚሉት ጨዋታነው
ሐይማኖ ያላቸውን እያወገዙ መናፍቁን አማካሬ ማድረግ አሁን
ምየ የሚሉት ቀልድነው ምእመኑ አንደሚበልጣቸው አለማወቃው ይገርማል
እንኳን ክርስቲያኑን አህዛብ በምራት አይችሉም ይልቁኑ በጊዜ ይቅርታይጠይቁ
ለነገሩ በአባጰውሎስ ዘመነግዛት ምን የማይሆን ነገር
አለ ? ድሮ ቀረ በቅዱሳኑ ዘመን ጵጵስና፤ ያሁን ዘመን፤
ገንዘብ ያለው ወይም ንብረት ያለው በዘር አንድ የሆነ
ያሳዝናል፣የሚገርመው በአብይ ፆም በሱባኤው ቢያንስ የተጣላ ይታረቃል እንጅ
ያወግዛ ትርጉሙን የሚያቁት አይመስለኝም፣የቀበሌ ሊቀመንበር የሆኑ መሰላችው፣ካልቻሉበት አስኬማችን ይመልሱልን
ድሮውም አላግባብ ነው የተቀበሉት ፣አሁንም ይረፉ ፣ዝም ማለት ትግስት እንጅ ፍራቻ አይደለም
ገና ጉዱ ይወጣል፣ thank you for technology you con not stop it.

Anonymous said...

ለመሆኑ ይህንን ሥርዓት ያውቀት ይሆን? ለነገሩ ቢያውቁት ኖሮማ እንዲህ ዓይነት አሳፋሪ ድርጊት ባልሰሩ ነበር።

Anonymous said...

እባካችሁ ለ አባ ፋኑኤል የቅርብ ሰዉ የሆናችሁ የፍትሐ ነገስት መጠሐፍ ገዝታችሁ ስጠአቸዉ። ለነፍሳችሁ ይሆናሉ ባለማወቅ እየተጎዱ ነዉ ቤተክርስትያንንም እያሳፈሩ ነዉ ... "ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም"...

Berhanu Melaku said...

አይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቁንጮዎች፤ ምነው ቤተክርስቲያኒቱን ካለችበት ፈተና ለማውጣት ብትጥሩ። አሁን ይህ ድርጊት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ይጠቅማታል? ምእመናን አባትን በማክበርና በሀዋሳ ልይ የሆንውን ግብግብ ችግር ላለመድገም ብለን ዝም ብንል ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል
እንደተባለው ጳጳሱ እየጮሁ አላስቀምጥ አሉን። ከእንግዲህስ ወዲያ ዝምታው እየከበደን ነው።

ብጹእነትዎ እስኪ የሚከተሉት ጥያቄወች የእርስዎን መምጣት በጉጉት እየጠበቅን ላለነው ለምእመናን ይመልሱልን።

፩. ዛሬ እርስዎ ስልጣንዎን በመጠቀም እያስፈራሩአቸውና እየወነጅሉአቸው ያሉት ካህናት በጥያቄ ቁጥር ፬ ላይ በተዘረዘሩት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የእርስዎን መምጣት
በጉጉት እየጠበቅን ያለነወችን ምእመናን አሰባስብው ቀደም ብሎ በብጹእ አቡነ አብረሃም የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድ በተመሰረተው ሃገረ ስብከት
ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማና ቀኖና በመጠበቅ በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ስር በመሆን ምእመናን እንዳይበተኑና ቤተ ክርስቲያ
እንዳትበደል በማገልገል ላይ ያሉ መሆናቸውን ጠንቅቀው ያውቃሉን?
እርስዎን ሊጠቅም የማይችል ድርጊት በእነዚህ አባቶች ላይ ባይፈጽሙ መልካም ነው።

፪. ለመሆኑ ይህንን ውሳኔ ሲወስኑ ከየትኛው መንበር ላይ ቁጭ ብለው ነው ???

፫. በብጹእ አቡነ አብረሃም መልካም አባታዊ መሪነት የተገዛውንና በቅዱስ ሴኖዶስ የሚታወቀውን የሃገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ለምን አልተረከቡም?

፬. በቅዱስ ሴኖዶስ የታወቁትንና ሊቀ ጳጳስ ተመድቦላቸው በብጹእ አቡነ አብረሃም ይተዳድሩ የነበሩትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አብያተ ክርስቲያናት ለምን አልተረከቡም?

፩ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ባልቲሞር
፪ ምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አሌክሳንደሪያ
፫ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
፬ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ሉዊቪል
፭ አንቀጸ ምህረት በዓታ ለማርያም ሻርለት
፮ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አትላንታ
፯ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ወአቡነ አረጋዊ
፰ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ታምፓ
፱ ደብረ ዕንቁ ቅድስት ማርያም ሜምፊስ
፲ ደብረ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ካንሳስ ሲቲ
፲፩ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኦክላሆማ ሲቲ
፲፪ የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ቨርጂኒያ
፲፫ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ቨርጂኒያ ቢች

፭. ለምንስ በቪ.ኦ.ኤ በሰጡት መግለጫ "አሜሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት መተዳደሪያ ደንብ የላቸውም፣ ሃገረ ስብከት የለም" አሉ?

ከላይ የተጠቀሱት አብያተክርስቲያናት በሙሉ የምንጠቀመው መተዳደሪያ ደንብ ቃለ አዋዲ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከቃለ አዋዲ የተለየ እርስዎ የሚያውቁት መተዳደሪያ ደንብ አውጥታለች?

፮. እርስዎ ከመምጣትዎ በፊት የሃገረ ስብከቱ አስተዳዳሪ የነበሩትን ብጹእ አቡነ አብረሃምን ለምን ሸሹ ለምን የርክክብ ስርአት አልተደረገም?

፯ በግንቦቱ የቅዱስ ሴኖዶስ ምላተ
ጉባኤ ላይ ከብጹእ አቡነ አብረሃም ጋር በግንባር ለመወያየት ፈቃደኛ ነወት?

፰ በአሁኑ ሰዓት እርስዎ እየመራኋቸ ነው የሚሏቸውን አብያተ ክርስቲያናት ስምና ቦታ በዝርዝር ለምእመናን ቢያስረዱን?

፱ በግ፣ ፍየል እና ተኩላ አንድ ላይ ደባልቄ ካልመራሁ ብለው ከሆነ እረኛ ሁነው ከፊት ሲመሩ በጎችን ተኩላ እንድሚጨርሳቸው ያውቃሉን ተኩላዎችን ለመመገብ አስበው ከሆነ ፍየሎች ያጋልጡወታል

ቅዱስ እግዚአብሔር መልካም እረኛ የሚያደርግና መልካሙን መንገዱን እንዲገልጽልዎ እየጸለይኩ መልስዎን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
ያቅርቡልኝ ስል በጥህትና እጠይቃለሁ።

ግልባጭ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቁንጮ ለሆነው ቅዱስ ሴኖዶስ::

Anonymous said...

melkam new. yezemenu papasat genzebin ena kibrin filega tinkolawunim endemitekemu eyayen new. enezih degmo dikunawun syacherisu papas yetebalut be 5th patriarich new. ene yemaznew le miemenan ena lebetekirstian new. hulunim be-ejachew adrigew eyegezuniko new. beteley
abune funauel
abune sawiros
abune yaecob
tetekash nachew. yihen sil degag abatoch yeleum malete aydelem. ende eliyas demenan azizew zinab yazenebu (be kidisina) alulin. gin albereketulinim.
egzer betekirstianin bekash yibelat!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)