April 24, 2012

አቡነ ፋኑኤል አዲስ አበባ ናቸው


አቡነ ፋኑኤልን ለጵጵስና ያበቃቻቸው ንግግር (ቪዲዮውን ይመልከቱ)


·         በጉጉት የሚጠብቁትን ደብዳቤ ከፓትርያርኩ አግኝተዋል፤ 

(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 14/2004 ዓ.ም፤ 4/22/2012, READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ አወዛጋቢው የአሜሪካ ሁለት አህገሩ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቅዳሜ አዲስ አበባ ገብተዋል፤ በመላው አሜሪካ የተነሣባቸውን ተቃውሞ ለማድበስበስ እና ከአሜሪካ እንዳይነሡ ለማድረግ እንደተዘጋጁ የደጀ ሰላም ምንጮች አስታወቁ። በአሜሪካ የተቀሰቀሰባቸውን ተቃውሞ የሚያበርድ ደብዳቤ ከፓትርያርኩ አግኝተዋል።


አርብ ተነሥተው ቅዳሜ ሚያዚያ 13 አዲስ አበባ የገቡት ብፁዕነታቸው ከሳምንት አስቀድመው የተልዕኮዋቸው የቀኝ እጅ እና “አባ ሰላማ” ከተባለው የተሐድሶ ድረ ገጽ እና የተሐድሶ ክንፍ ጋር ድልድይ ሆኖ የሚያገናኛቸው እንዲሁም በአሜሪካ የጀመሩትን “አዲስ ሀገረ ስብከት እና ከእውነተኛ ኦርቶዶክሳውያን የጸዳ ቡድን” የማቋቋም ዘመቻ መሐንዲስ ነው የሚባለውን ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁንን ወደ አዲስ አበባ ልከዋል። ዲያቆኑ የቅዱስ ፓትርያርኩ ጥብቅ ወዳጅ እና ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተቋቋመውና እንዲፈርስ ቢታዘዝም በፓትርያርኩ እና በአቡነ ፋኑኤል እምቢተኝት በመንቀሳቀስ ላይ ያለው  “የውጪ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ባለሙሉ ሥልጣን ኃላፊ” ነው። የግለሰቡ ተልዕኮ አቡነ ፋኑኤል በአሜሪካ የገጠማቸውን ተቃውሞ ለማለዘብ ከቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ አስቀድሞ ብፁዓን አባቶችን ማግባባትና ሎቢ ማድረግ ነው ተብሏል።

በፓትርያርኩ ብቸኛ መሪነት ልዩ ተልዕኮ ሰጥቷቸው አሜሪካንን ልክ እንደ ሐዋሳው በማመስ ላይ የሚገኙት አቡነ ፋኑኤል መንግሥት እና ፓትርያርኩ ሊደሰቱባቸው ይችላሉ፣ በዚህም የሹመቴን ዕድሜ ያራዝማሉ ያሏቸውን ንግግሮች ሲናገሩ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ሲያስቀዱ ሰንብተዋል ተብሏል። በዋልድባ ጉዳይ ተቃውሞ የሚያሰሙት “ፖለቲከኞች ናቸው”፤ ፓትርያርኩ አኩሱም ላይ የጀመሩት የሙዚየም ግንባታ የቤተ ክርስቲያኒቱ ትልቅና ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ስለሆነ ገንዘብ አዋጡ እያሉ በቀጥታ ለቪዲዮ ካሜራዎች የሚናገሩባቸው ንግግሮች ተቀድተው የተዘጋጁ ሲሆን ለፓትርያርኩ እጅ መንሻ ሆነው እንደሚቀርቡ ምንጮች ለደጀ ሰላም አብራርተዋል።

በዕድሜ ለጋ፣ በሥራ ልምድ አናሳ ከሆኑትና በዘመነ አቡነ ጳውሎስ ልማድ ተደርጎ የተወሰደው የወጣት ጳጳሳት ሹመት ውጤት የሆኑት አቡነ ፋኑኤል ይህንን ጉድለታቸውን ለማሟላት በጥበብ ከመጓዝ ይልቅ ከሐዋሳ ጀምሮ አሜሪካ እስከ ሔዱበት ጊዜ ድረስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዕድሜ ጠገብ ተቋማት በማፍረስ  ሥራ ላይ ተጠምደው ቆይተዋል። ይህ ጉዳይ ሲያስደምመን ቆይቶ ከተደመምንበት ድማሜ፣ ከገባንበት መደነቅ ሳንወጣ፣ ጭራሽ በይፋ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከሚያዋርዱ እና ክብረ ቅዱሳንን ከሚያቃልሉ ግለሰቦች እና ድረ ገጾች ጋር እጅና ጓንት ሆነው በይፋ መሥራት ጀምረዋል። የሚጽፏቸውን ደብዳቤዎችም የራሳቸው ድረ ገጽ አዘጋጅተው ማውጣት ሲችሉ ወይም ሌላ መንገድ መፈለግ ሲገባቸው በተሐድሶ ድረ ገጾች በመጠቀም በቤተ ክርስቲያናችን ብፁዓን አበው ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ አሳፋሪ ተግባር መፈጸም ጀምረዋል።

ማንም ሰው የራሱን ስም እና አገልግሎት የሚያሰናክል ተግባር ለመሥራት የማይፈልገውን ያህል አቡነ ፋኑኤል ለራሳቸው ስምና ክብር መቃብር ለመቆፈር መታተራቸውን የሚያዩ አባቶች “ከጀርባቸው አይዞህ እያለ ወደ ጥፋት የሚመራቸው ሰው አለ” ሲሉ የቆዩ ሲሆን ብዙዎቹ ደግሞ “ፓትርያርኩ ናቸው” በሚለው ይስማማሉ። ፓትርያርኩ አቡነ ፋኑኤልን ያቀረቡ በመምሰል ከዚህ በፊት ፓትርያርኩን ለመቃወም ባደረጉት ሙከራ እየተበቀሏቸው ነው ሲሉ ያትታሉ። ይህንን አመክንዮ በሚያስረዳ መልኩ ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአቡነ ፋኑኤል እና “ሾምኳቸው” ላሏቸው ሰዎች እውቅና በመስጠት ደብዳቤ የጻፉ ሲሆን የተሐድሶዎቹ ድረ ገጾችም የፓትርያርኩን የግል ደብዳቤ “ከቅዱስ ሲኖዶስ የመጣ” በማስመሰል ለመጻፍ ሞክረዋል። እውነቱ ግን ይህ እንዳልሆነ ይታወቃል። ለማንኛውም የሊቀ ጳጳሱን እና የፓትርያርኩን ደብዳቤዎች ከዚህ በታች አስቀምጠናቸዋል። ለታሪክ። (ደብዳቤዎቹን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

ይህ በእንዲህ እንዳለ አቡነ ፋኑኤል ሊቀበሉት ፈቃደኛ ያልሆኑበት የዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት በሥሩ የሚገኙትን አብያተ ክርስቲያናት እንደያዘ አቤቱታውን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት በማሰማት ላይ ሲሆን ይኸው አቤቱታ እንዳይሰማ የፓትርያርኩ ጠንካራ አስተዳደር እጅ ሳይጫነው እንዳልቀረ ምንጮች ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ግንቦት ላይ በሚደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ በአጀንዳነት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ እንዳይሆን ደግሞ አቡነ ፋኑኤል “ያላቸውን ኃይል ሁሉ አጠራቅመው” ሄደዋል ተብሏል። የተጠራቀመው ኃይል ምን እንደሆነ ሁላችን ይገባናል። ቤተ ክርስቲያን በዚህ ከአሜሪካ ተጭኖ በሚሄደው “ኃይል” እስከመቼ እንደምትዘወር ትልቅ ጥያቄ ነው። ብፁዓን አባቶች በቅ/ሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ በጥብዓት ሐሳባቸውን ከሰጡ የአሜሪካ ምእመናን ከገቡበት የሐዋሳ ዓይነት ፈተና እና መከራ ይታደጓቸዋል።
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን     

23 comments:

yemelaku bariya said...

where are the letters?

Unknown said...

Open the attachments.

Dn haile Michael said...

ስጀምር አቡነ ፋኑኤልና ፓትርያርኩ ጸረ ቤተክርስቲያንና ተሐዲሶ አለመሆናቸው መች ተረጋገጠና ነው ሌላ የሚትሉን :: እንደ ግብጽ ቤተክርስቲያን የእኛ ቤተክርስቲያን ምእመናን እስከ መቼ ነው በቤተክርስቲያን ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፍ የመይሆኑት? እስከ መቼስ ነው አስመሳዮችና አጽራረ ቤተክርስቲያን የሚፈነጩባት ?
ከድቁና ጀምሮ ጳጳሳትም ሲሾሙ ለምንድ ነው ከምእመናን ስለ መልካም ጠባያቸው: በመንፈስ የሞቁ ስለመሆናቸው ሐዋርያት ሰባቱ ዲያቆናትን ለመሾም ከምእመናን ምስክርነትን እንደተቀበሉ ከምእመናን ምስክርነት የመቀበል ሥርዓት የማይኖረው? ፓትርያርኩስ በጉቦና በዝምድና ቤተክርስቲያንን የሚያለሙትን ሳይሆኑ የሚያጠፉትን ስሾሙ ዝም የሚንለው?
ሳይቀጠል በቅጠል እነዲሉ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ከእጃችን ሳይወጣ ሳንቀደም ብንቀድም::
ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በጡመራ መድረኩ “ውሾቹ ይጮሃሉ ግመሎቹም ይሔዳሉ “እንዳለ እኛ የውሾቹ ጩሀት ግመሎቹን እንዳያስቆም ለውጥ የማያመጣ ጩሀት ስንጮህ ግመሎቹ ፓተርያርኩና ወያኔ በቤተክርስቲያናችን ጉዳይ እንዳንወያይ አቤቱታ እንዳናቀርብ ሐሳባችንን እንዳንገልጽ ጠፍረውን እያጠፉ ነው::
ስትራቴጂ መቅረጽና ቤተክርስቲያንን የመታደግ ሥልት መስቀመጥ ለሕዝቡ ማዳረስ ከእናንተ ከደጀ ሰላማውያንና ከሌሎችም ጦማሪዎች ይጠበቃል::
እመሰ ረሳይኩኪ እየሩሳሌም ወይርሳእ የማንየ
እየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ

lamelame europe said...

enamenalane baretetane enetsaley enjea AMELAKACHEN enda awasawe yeradanale.
ayezochohe Usa enaneta kaawassawe memane atanesome....

galela said...

yaletadalo abate bayaheadobate....

Anonymous said...

Do some thing on the ground. Some thing on the ground. Some thing on the ground. Who is Aba paulos to do all these things against the church. He, the beyonce's Guide and has no moral ground to lead the church !!! And the holy synod, I am sory to say it, has become incapacitated and is no more functional. If the holy synod needs to talk about this problem, it has to be about stripping Aba paulos of his patriarchate and Fanuel from his priest hood. We must not beat around the bush. Aba paulos is the cancer cell and he needs to be removed. If the holy synod is not going to adress this issues I suggest it better not make the meeting. We have to stand up together like the christains of Russia. To do this we have to work some thing on the ground. thanks djeselam and other sites for empowering us with truthfull information.

Anonymous said...

ማስተዋል ለጎደላቸዉ
“እየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” እየሩሳሌም (ሀገረ ሰላም) የህሊና እረፍት ፣ የወስጥ ሰላም እና የመንፈስ እርካታ ማግኛችን ይህች ሀገረ ሰላም ቤተ ክርስቲያን መሆንዋን ማንም አይክድም። የሚገርመዉ ግን የሰላምን ሀገር የሚደፈርሱ የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ተሿሚዎች ናቸዉ። ጠ/ሚ መለስ ዜናዊና ቤተ ክረስቲያናችንን የሚያምሱ የግብር ልጆቻቸዉ በትንሹም ይሁን በስደት ዓለም በነበሩበት ወቅት ከሰለጠነዉ ዓለም ትንሽ በጎ ነገር ሳይማሩ ወይም ደግሞ ሳይሰሙ አሊያም ደግሞ በጨረፍታ ሳያዩ አይቀርም። ትዉልድን በሥነ-ምግባር ኮትኩተዉ የሚያሳድጉ ማኅበራት እንደሚበረታቱና ከመንግሥት ድጎማ ሁሉ እንደሚደረግላቸዉ ባያዩ ይሰማሉ እላለሁ። በፖለቲካ የሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም ታዲያ ግጭትና ጸብ መፍትሔ ይሆናል ከተባለ ቅዠትና እብደት ነዉ። ግጭት ጊዜ ይፍጅ እንጂ ያፈናቅላል። ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵይ ምድር ይህን አደረገ ትዉልዱን በሥነ-ምግባረ አነጸ፣አልፎ ተርፎም የቤተ ክርስቲያኗ መሪ ተቢየዎች ያልሠሩትንና ሊሠሩ ያላሰቡትን ማከናወኑ ሊያስመሰግነዉ እደግ ተመንደግ ሊያስብለዉ ሲገባ የሌለ ስም እየሰጡ መናተፍ ለትዝብት ከመዳረግ ባሻገር ፈይዳ ቢስ ነዉ።
የማኀበረ ቅዱሳን አባላትኮ በየትኛዉም የኑሮ መስክ በመንፈሳዊዉም ሆነ በሥጋዊዉ ኑሮን በህይወት መልኩ መኖር እንደሚችሉ ልብ ሊሉ ይገባል። እንደ ተስፋዬ መቆያ አባባል “ዉዳሴ ማርያምን ደግሞ ያደገ ፊዚክስን፣ኬሚስትሪን መሥራት አያቅተዉም”፤ እንደ አባ ፋኑኤል አባባል “የእነሱን ድግሪ እኛ ማግኘት አያቅተንም የእኛን ክህነት እነርሱ ማግኘት አይችሉም” እንደ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ አባባል ደግሞ “አክራሪ” እያሉ ጊዜ ከማባከን በሰከነ መንፈስ ከታሰበ ለሀገር እና ለህዝብ የሚጠቅሙ በደሀይቱ ሀገራችን ገና ሊሠሩ የሚገቡ ብዙ ክፍት ቦታዎች ስላሉ በሌሎች ቀንተን ለእኛ በሌለን ነገር ከመወረፍ ታቅበን በሰከነ መንፈስ ሳይረፍድ ወደ ሥራ እናዝግም። ድሮ ልጅ እያለሁ ትዝ ይለኛል “ጊዜ ታክሲ አይደለም አይጠብቅም ቆሞ” እንል ነበር። ጠ/ሚ በሃይማኖት ጉዳይ ገብተዉ ዋልድባን ለስኳር ከማሳረስ የአባይ ጉዳይ በጅምር እንዳይቀር ቢተጉ፣ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የተገባ ሥራ ተሰጥቷችሁ የተሰጣችሁን ኃላፊነት በወጉ ሳትወጡ ገና በእንጭጩ ሹመት የጠማችሁና በተበለጥን በመደናበር በማያገባችሁ ገብታችሁ ምእመኑንና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚማስኑትን የምታዉኩ የአሉባልታ ሱሰኞች እዉነት ቅናተ ቤተ ክርስቲያን አቅጥሏችሁ ከሆነ ክፍተቱን እየፈለጋችሁ ሸፍኑ። በተረፈ የአሁኑ ዝላይ ለመሰበር ካልሆነ ለድኅነት አይሆናችሁም።
ለአባ ፋኑኤል የንስሐ ዕድሜ ይስጣቸዉ። ለጠ/ሚ መለስ ዜናዊ እዉነትን የሚያቀብሉ የደኅንነት ሠራተኛ እና ለሙያዉ የተገዛ እዉነት የሚዘግብ ጋዜጠኛ ይስጣቸዉ።ሌሎች ለጥናትና ምርምር የሚያግዛቸዉ ዕዉቀት ለመጨመር ትምህርት ቤት ይግቡ በበለጠ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል እንዲረዳቸዉ ። የካዱትም ተምረዉ ይመለሱ፤ ከለየላቸዉም የለዩ ከእየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ይዉጡ…. ብዕሩ ዘ-አትላንታ

ብዕሩ ዘ-አትላንታ said...

ማስተዋል ለጎደላቸዉ
“እየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” እየሩሳሌም (ሀገረ ሰላም) የህሊና እረፍት ፣ የዉስጥ ሰላም እና የመንፈስ እርካታ ማግኛችን ይህች ሀገረ ሰላም ቤተ ክርስቲያን መሆንዋን ማንም አይክድም። የሚገርመዉ ግን የሰላምን ሀገር የሚያደፈርሱ የሀገርና የቤተ ክርስቲያን ተሿሚዎች ናቸዉ። ጠ/ሚ መለስ ዜናዊና ቤተ ክርስቲያናችንን የሚያምሱ የግብር ልጆቻቸዉ በትንሹም ይሁን በስደት ዓለም በነበሩበት ወቅት ከሰለጠነዉ ዓለም ትንሽ በጎ ነገር ሳይማሩ ወይም ደግሞ ሳይሰሙ አሊያም ደግሞ በጨረፍታ ሳያዩ አይቀርም። ትዉልድን በሥነ-ምግባር ኮትኩተዉ የሚያሳድጉ ማኅበራት እንደሚበረታቱና ከመንግሥት ድጎማ ሁሉ እንደሚደረግላቸዉ ባያዩ ይሰማሉ እላለሁ። በፖለቲካ የሥልጣን ዕድሜ ለማራዘም ታዲያ ግጭትና ጸብ መፍትሔ ይሆናል ከተባለ ቅዠትና እብደት ነዉ። ግጭት ጊዜ ይፍጅ እንጂ ያፈናቅላል። ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵይ ምድር ይህን አደረገ ትዉልዱን በሥነ-ምግባረ አነጸ፣አልፎ ተርፎም የቤተ ክርስቲያኗ መሪ ተቢየዎች ያልሠሩትንና ሊሠሩ ያላሰቡትን ማከናወኑ ሊያስመሰግነዉ እደግ ተመንደግ ሊያስብለዉ ሲገባ የሌለ ስም እየሰጡ መናተፍ ለትዝብት ከመዳረግ ባሻገር ፈይዳ ቢስ ነዉ።
የማኀበረ ቅዱሳን አባላትኮ በየትኛዉም የኑሮ መስክ በመንፈሳዊዉም ሆነ በሥጋዊዉ ኑሮን በህይወት መልኩ መኖር እንደሚችሉ ልብ ሊሉ ይገባል። እንደ ተስፋዬ መቆያ አባባል “ዉዳሴ ማርያምን ደግሞ ያደገ ፊዚክስን፣ኬሚስትሪን መሥራት አያቅተዉም”፤ እንደ አባ ፋኑኤል አባባል “የእነሱን ድግሪ እኛ ማግኘት አያቅተንም የእኛን ክህነት እነርሱ ማግኘት አይችሉም” እንደ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ አባባል ደግሞ “አክራሪ” እያሉ ጊዜ ከማባከን በሰከነ መንፈስ ከታሰበ ለሀገር እና ለህዝብ የሚጠቅሙ በደሀይቱ ሀገራችን ገና ሊሠሩ የሚገቡ ብዙ ክፍት ቦታዎች ስላሉ በሌሎች ቀንተን ለእኛ በሌለን ነገር ከመወረፍ ታቅበን በሰከነ መንፈስ ሳይረፍድ ወደ ሥራ እናዝግም። ድሮ ልጅ እያለሁ ትዝ ይለኛል “ጊዜ ታክሲ አይደለም አይጠብቅም ቆሞ” እንል ነበር። ጠ/ሚ በሃይማኖት ጉዳይ ገብተዉ ዋልድባን ለስኳር ከማሳረስ የአባይ ጉዳይ በጅምር እንዳይቀር ቢተጉ፣ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የተገባ ሥራ ተሰጥቷችሁ የተሰጣችሁን ኃላፊነት በወጉ ሳትወጡ ገና በእንጭጩ ሹመት የጠማችሁና በተበለጥን በመደናበር በማያገባችሁ ገብታችሁ ምእመኑንና ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚማስኑትን የምታዉኩ የአሉባልታ ሱሰኞች እዉነት የቤተ ክርስቲያን ቅናት አቅጥሏችሁ ከሆነ ክፍተቱን እየፈለጋችሁ ሸፍኑ። በተረፈ የአሁኑ ዝላይ ለመሰበር ካልሆነ ለድኅነት አይሆናችሁም።
ለአባ ፋኑኤል የንስሐ ዕድሜ ይስጣቸዉ። ለጠ/ሚ መለስ ዜናዊ እዉነትን የሚያቀብሉ የደኅንነት ሠራተኛ እና ለሙያዉ የተገዛ እዉነት የሚዘግብ ጋዜጠኛ ይስጣቸዉ።ሌሎች ለጥናትና ምርምር የሚያግዛቸዉ ዕዉቀት ለመጨመር ትምህርት ቤት ይግቡ በበለጠ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል እንዲረዳቸዉ ። የካዱትም ተምረዉ ይመለሱ፤ ከለየላቸዉም ይለዩ ከእየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ይዉጡ… ብዕሩ ዘ-አትላንታ

Anonymous said...

From Nekefa Yebica

Dejeselam PLEASE! PLEASE post something which helps people to develop their spiritual education. We can get those kinds of news (politics) from other news papers. What we need is the words of God and something which helps us to live as a christians.

Anonymous said...

አቡነ ፋኑኤል ላለሁበት ቤተ-ክርስቲያንም አባት ቢሆኑም፤ እያነበብኩና እየታዘብኩ የመጣሁት ያያዛቸው ነገር ግን ብዙም የሚጥም አልመሰለኝም (የፓትሪያርኩ አሰራር እንዳለው ሆኖ)።
1- በእልህና በአላማ ውስጥ ያሉ
2- የአስተዳደር ችሎታ ውስንነታቸው
3- ከአንድ አባት የሚጠበቅ የተሸናፊነት ባህሪ ማጣት
4- በፓትሪያርኩ ለመወደስ የሚተጉ
5- .. ሌላም ሌላ

ለቤተ-ክርስቲያናችን የቀደሙት አባቶች (አቡነ ኤዎስጣጢዎስና አቡነ አብርሃም) እየመሰረቱ ለነበረው ሰላም ክፉኛ እንቅፋት!.ከዚህ ሌላ፤ የደብዳቤዎቹ አላማ ‘ለቤተ-ክህነት ጥሩ ገጽታ’ ከፓትሪያርኩም ‘ቡራኬን’ ለመቀበል ካልሆነ .... በአጠቃላይ ውቅሩ ‘ከብት በሌለ ኩበት ለቀማ’ !!


እንጸልይላቸው።

ወጣት ኤልያስ /ዳላስ-ቴክሳ/

peter said...

for nekefa yibka

it is not nekefa, deje selam just telling us the truth. creating awareness!! read church history. we have to stand for our church and the truth. real christians feels so much love, burn inside for their church and all kinds of injustices. when waldiba changing to sugar factory or ziquala set on fire , u can not just sit idle and say "oh"
that is politics. God give us the wisdom to see the truth. please help us to feel the pain of our church and stand up together to help our church. deje selam thank you and God bless u all.

Anonymous said...

Kebatari hulu , Abune Fanueal btam
teliq abat nachew. Awaqina tiru
Abat. Egziabher yikr yiblachu.
yemitnagerutn atawqumna.

Anonymous said...

Ye Dejeselam Azegajoch Wondimoche ebakachihu sile sew atmezigibulin yibka Kebad yehone fetena eyametsan new Abune Fanueilm Honu Abune Pawlos & Abune Abirham yalfalu yematalfew bete kirstiyan tefetenech yemitamen tsefa hulum asadag hone Ahunim YIkirbin Btselot enberta Melyayet yibka elalehu

Anonymous said...

let us do something befor the holy sinodos start meeting ginbot 12 ,like sunday school did. Russia orthodox church is good example. We have 2 stand 4 our church. It is shame 4 us transfer our church 2 the next generation with these complected problem. Let us stand 4 beloved orthodox church.

Anonymous said...

Min honachihu new ? Papas mehon Yemichalew Bengigir-Begenzeb -Bepoletika-Bezer new eyalu Memezgeb Min Malet New ?Menafikanu Min Yibelu ? Aba Selam Yetbalew Bilogg Bimezegibew yishalal Menafik Silemimesil enante yetewahedo lijoch nachihu Azegajochinm Awkalehu tadiya Papasatin -kahinatin -menekosatin- Diyakonatin Metechewtin lehizibu yihinn ayinet were manafes min Malet new ?
Abune Fanueil Yeteshomut Bemnfes Kidus Fekad new Yastemralu- Dha Yiredalu-Yikedsalu -yibarkalu Yaseralu Yelmat sew nachew Ke Abune Gebireilna Kelelochu Bemin Yansalu ?enante siletselachihachew bicha Mesedeb Alebachew ?yasazinal Ahuns ye enante mehone asazeneg -asfereg

Anonymous said...

dejeselam
negerutruaidelm
AbBA dabilosyemisert
ereylmeonu mindenugudu

Anonymous said...

Dear Dejeselam,

I don’t know why you post this video now – we know what you are trying to transmit . I think it looks like you’re following the steps of Ato Mirchaw, who is trying to put a character assassination. The only thing we know about Abune Fanuel is his strong and dedicated character. He deserve the title - He changed and pull many young Ethiopian people to the church through his nice spiritual education. We couldn’t deny his BIG again BIG contribution to Debre Meheret Kidus Michael church. We all know when he said “ME” he meant as a leader not to say he did it everything by himself . Above all the “ CHURCH MEMBERS “ already understand what he meant. PLEASE, PLEASE, PLEASE don’t exaggerate things and split hair to create unnecessary conflict . As a Christian we don’t expect things like this from you – instead we want to hear words like our God “ Don’t Judge people and don’t try to revenge” since those are not our duties. Finally I hope you’ll post this and would like to say “ SEGA LEB YESTACHU”
Amen.

Anonymous said...

Answer to Peter

I didn’t mean about Waldiba and other monasteries. What I wanted to say was commenting our spiritual fathers – especially about Aba Fanuel. Do you think God is happy about commenting his disciples – we think we are the one who can give judgment – we are taking the duties of God. Our share is to pray for all that way our problem will be solved. Our share is to create peace among our spiritual leaders not trying to take side and dismantle them. Please let us follow the word of God. I hope Deje Selam will accept this suggestion and we thought they are way better than Aba Selama regarding our Church. Let us leave judgment for the other Blog (Aba Selama) since I don’t expect this from you.
Thanks

lelr said...

yasazenale.....meneme manager alechalekom

lelr said...

yasazenale.....meneme manager alechalekom

yemelaku bariya said...

ዝም ብለን ነው እየደከምን ያለነው:: ዘመኑ ምን አይነት እንደሆነ ማገናዘብ አቅቶናል ይመስለኛል:: እነዚህን ክፉዎች ከመዋጋት ጎንለጎን ማኅበረሰባችን ከሚደርስበት የሞራል ድቀት እና ተስፋ መቁረጥ ስሜት መታደግ ግድ ይለናል:: በኃይማኖታችን እንደተማርነው አቡነ ጳውሎስን፣ አቡነ ፋኑኤልን የመሳሰሉ እንክርዳዶች በየማሳው ማየት ግድ እንደሆነ ማወቅና ማሳወቅ አለብን በዚህ ክፉ ዘመን ውስጥ እንኳ ለክፉ አሳልፎ የማይሰጠን በሕይዎቱ የገዛን ከባርነት ያወጣን ከድንግል የተወለደው ክርስቶስ እንዳለን ለዓይን ጥቅሻ ቅጽበት ያክል እንኳ እንዳንዘናጋ መረዳት አለብን:: እንክርዳድ ዘመኑ ሲደርስ ይበጠራል እናም ይህ ሁሉ ችግር ከሱ ከእየሱስ ክርስቶስ ነገድ ነጥሎ እንዳያወጣን ጠንክረን መጸለይ እና አቅም ያለን ሌሎቹንም መርዳት ነው:: ክፉዎች በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የክፋት ኃይላቸውን ቢያወርዱም እሷ ሳትሆን የምንጎዳው እኛ ነንና ከክፋታቸው የሚበልጠውን ጥንካሬ በሚሰጠው ኃይማኖት እንጸና ዘንድ ግድ ነው:: ቤተ ክርስቲያንማ ቃል ኪዳን አላት የሚወረወረው ፍላጻ ሁሉ እየነጠረ መመለሱ አይቀርም ይልቅስ እኛ አንድ ጊዜ ከእቅፏ ውስጥ ሌላ ጊዜ ከእቅፏ ዉጭ ስንራወጥ ፍላጻው እንዳያገኘን በመከላለያዋ በእቅፏ ውስጥ መሆናችንን እናረጋግጥ::

Anonymous said...

It is extremely sad to see such kind of gangsters in our church even as ordinary follower let alone under Arch Bishop capacity. The more fake religious leaders we have the greater is the risk to drive people out of religion. How can we call this guy and his supporters religious leaders?

Frezer said...

Meche yhon sew mamlek yemntewew??

Amlak libona yisten!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)