April 30, 2012

በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ መጓዛቸውን ኢሳት ዘገበ፣

  •   "ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል” ብሏል የኢሳት ዜና፤
(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 23/2004 ዓ.ም፤ April 30/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦፦ “በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ መትመማቸውን እንዲሁም ሁለት ነጮች መገደላቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን” ኢሳት የተባለው ብቸኛው ከአገር ውጪ የሚገኝ ነጻ የዜና ተቋም በሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም  ዘገባው አስታወቀ። “የገዳሙ አባቶች ለሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እስከ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኙ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ አካባቢው መትመማቸውን ተከትሎ ሁለት ነጮች መሞታቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ እኛ ከህዝብ ጋር አንጣላም በማለት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል” ያለው ዜና ተቋሙ የሟቾቹ እና አካባቢውን ለቀው የወጡት ነጮች ምዕራያን ይሁኑ የቻይና ዜጎች አልታወቀም” ሲል አክሏል።


ዘገባው ቀጥሎም “ከ5ሺ ያላነሱ የአካባቢው ነዋሪዎች በዋልድባ ተገኝተው ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን፣ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላትም ርምጃ ለመውሰድ ፈርተዋል። ሁኔታው እጅግ አስፈሪ ነው፣ መንግትና ዝቡ ተፋጠዋል፣ የአካባቢው ወጣቶችም ወደ አካባቢው ለመጓዝ እየተመካከሩ ነው ሲል አንድ ጉዳዩን በቅርብ ሆኖ የሚከታተል ሰው ለኢሳት” መግለጡን አብራርቷል።

“ሰራተኞቹ እኛ ለዝብ ልማት ይውላል ተብሎ ነው የመጣነው፣ እናንተማ ካልፈለጋችሁት እኛ እዚህ ምን እናደርጋለን?” በማለት አካባቢውን ለቀው በመውጣታቸው፣ በአሁኑ ጊዜ ራው ሙሉ በሙሉ ቆሟል።” ያለው ኢሳት “መንግራው ተቋርጧል በማለት ለአካባቢው ነዋሪዎች ቢናገርም፣ ዝቡ ግን ሚጢቆ በሚባል ቦታ ላይ የተተከሉት ሁለቱ የኤሌክትሪክ ጄኔሬተሮች ካልተነሱ ራው መቋረጡን ከልብ አምነን ለመቀበል  አንችልም የሚል መልስ ሰጥቷል” ብሏል።


የአካባቢው ዝብ አሁንም ጄኔሬተሮቹ እስኪነሱ ድረስ በትግስት በአካባቢው ተገኝቶ እየጠበቀ ነው። ዝቡ በስንቅ እጦት እንዳይቸገር እርስ በርሱ  እየተተካካ እንደሚጠብቅ ለማወቅ ተችሏል” ሲል ኢሳት አብራርቷል። የገዳሙ አባቶች ይማኖት ወዲያ ምን አለ፣ ለይማኖት መሞት ጽድቅ ነው።” በማለት ሰሞኑን ዝቡን እየዞሩ ሲያስተምሩ ነበር። ያለው ኢሳት “መንግት የተወሰኑ መነኮሳትን አፍኖ መውሰዱም ታውቋል” ብሏል። “አሁን በሚታየው ስሜት የዋልድባ የስኳር ግንባታ ተፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል አንድ የአካባቢው ሰው ለኢሳት ተናግረዋል። የዝቡ ቁጣ ከመጠን እያለፈ ነው ያሉት እኝህ ሰው፣ መንግት ከዝቡ ጋር እልህ ውስጥ የሚጋባ ከሆነ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችላል ሲሉ” ማስጠንቀቃቸውን ጠቅሶ “የመንግት ባለስልጣናት በግንባታው ዙሪያ የሀይማኖት አባቶች ስምምነታቸውን ሰጥተዋል ቢሉም፣ ዝቡ ግን የሚቀበለው አልሆነም” ብሏል። 

25 comments:

galela said...

amlake hoy hezebehen asebe

lamelame europe said...

abatoche yamayalefe sera sero

Anonymous said...

lebe latote lebe yesetelene

Anonymous said...

AMELAKA GIORGIES YEREDANE
AMEN

ሰጠችኝ ማርያም said...

ክርስትና በተግባር የሚተረጎምበትጊዜ ላይ ነን

Tesfa said...

Oh my God! Is that true. May God give those people and the fathers strength and determination. May God also give a good heart for the politicians and church leaders. Please let us pray?

Aba Haregewoyne, Gojam said...

ጃንሆይን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች (እነ አቶ መለስ) ገለበጡ።
ዛሬ ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ግብ ግብ ከገጠሙ አቶ መለስን የሚገለብጣቸው የእግዚአብሔር ሃይል ነው። ኢትዮጵያ ከጥንት ከአዳም ጀምራ እግዚአብሔር በክርስትና ያስቀመጣት አገር ነች። ሌሎች እምነቶች ከጥቅምና ከጥገኝነት ጋር በተያያዘ ሁኔታ የተቀበለቻቸው እንግዶችዋ ናቸው። ስለዚህ ኢትዮጵያ የክርስቲያን ሀገር ነች ክርስቲያን መንግስት ብቻ ነው የሚያስተዳድራት። ይህን አንቀበልም የሚል እንግዳ ካለ ኢትዮጵያ በመልካም አሸኛኘት ወደ መረጡት መንግስት ሀገር ልትሸኛቸው ሁል ጊዜም ዝግጁ ነች። አቶ መለስና ጥቅመኛ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ብታስቡበት መልካም ነው፤ እየተከተላችሁ ያለውን መንገድ እንደገና ብትቀይሱት ይሻላል። ክርስትና እና ሰሜን አሜሪካ ክብር ይሻሉናነው።

Berhanu Melaku said...

Ethiopia is stretching out her hands to GOD again.
Here is the fact. Ethiopia is the first African nation to appreciate and worship the One True GOD of Old Testament and adopted the Judaic element (1,000 B.C.). Even history said that the idea of worship of one God has been in existence by Ethiopians earlier. This was confined to a limited number of families. Later this disappeared when a segment of the population strayed to all forms of worship.
One faith - One country - One GOD.

Anonymous said...

Those of you who are in Ethiopia, in whichever part of the country, please join them. but try to make it peacefully as much as possible. That is good action. Just go there like the Gondar people, Occupy the space and pray in group. This is what I was wishing.

Deje Selam, We will be happy if you can organize us (those out of Ethiopia) how to help them. For example, We can contribute in different ways like collecting money to supply them with food. From my side, I am very very willing to contribute at least 20,000 Ethiopian birr to supply food for the people and/or to cover transportation for others who have lack of money to travel to Waldba. I contribute more (maximum up to 40,000 Birr), if necessary. This is the issue of our identity, the country's identity. Please try to organize us.

Haile

መላኩ said...

ሰላም፡ እንደምን ሰነበታችሁ!

በተለይ ውጭ አገር የሚገኙ አባቶች ወደ ዋልድባ የመሄጃቸው ጊዜ አሁን ነበር። ለፈረንጅ የምርምር ዒላማ ከሚሆኑ ወደ ገዳሞቻችን አምርተው ለኛም አርዓያ ቢሆኑ ምን ያህል ታሪክ ባወደሳቸው። ለማንኛውም እግዚአብሔር አምላክ ሥራውን እየሠራ ነውና በቅርቡ ሁሉንም ገላልጦ ያሳየናል። እኛም አናማርር፡ ችግር፤ ስቃይና በደል ለክርስቲያን ፀጋ በረከትም ነውና።

Anonymous said...

deje selam bilachihu bilachihu ke esat metikes jemerachihu? esey esey...

Anonymous said...

እግዚአብሄር ከኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል በገዳም ያሉ አባቶቻችን ጸሎት ተሰማ ክርስትያኑ መንፈስ ቅዱስ እያነሳሳው ነው የጎንደር ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ክርስቲያን ለዝህ ለተቀደሰ አላማ መነሳት አለበት ቤ/ክቲያን ለትውልድ ማስተላለፍ የኦርቶዶክሳዊያን ሃላፊነት ነው:: ቃለህይወት ያሰማልን

Anonymous said...

እግዚአብሄር ከኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል በገዳም ያሉ አባቶቻችን ጸሎት ተሰማ ክርስትያኑ መንፈስ ቅዱስ እያነሳሳው ነው የጎንደር ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ክርስቲያን ለዝህ ለተቀደሰ አላማ መነሳት አለበት ቤ/ክቲያን ለትውልድ ማስተላለፍ የኦርቶዶክሳዊያን ሃላፊነት ነው:: ቃለህይወት ያሰማልን

Ruth Ayano said...

Egziabiher hoy kefit kidem!!!!

Anonymous said...

I am simply a christaian, I am currently out of Ethiopia. I will soon go back and like to dye there at Waldiba. Diginified death. Martyrdom ! If you are willing follow me. Our cause is just, on earth and heaven !!!

Mahidere said...

Its really hard to consider ESAT as a reliable source. I am puzzled that dejeselam use ESAT as a source; I would imagine it would be easy for dejeselam to get the information themselves. BUT, I will be happy the news is true indeed. Dejeselam,please DONOT USE ESAT as a source in the future or you might loose credibility also.

Anonymous said...

I am so sorry for what happened to our church, but your news is biased. it doesn't help for any discussion with officials. i can say you are being a tool for others and their agenda.

yared said...

ESAT.... the one and only ''free TV''... don't you think that you are kidding when you call it 'free'

Andadirgen said...

... እኔ ያልገባኝ ነገር ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤›› ብሎ ማመን እንዴት አክራሪ ክርስትያን ያስብላል ? ‹‹አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።››ዮሐንስ ራእይ 22፤13 ይላል አንድ ጌታ ብለን እናምናለን ፤ አንዲት እውነተኛ እምነት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብለን እናምናለን ፤ አንዲት ጥምቀት ብለንም እናምናለን ታዲያ የኦርቶዶክስ አክራሪዎች እንባላለን? ...

... ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤›› ብለው ወጣቶች የሚለብሱት ቲሸርት ላይ የተጻፈው ጥቅስ ማህበረ ቅዱሳን የጻፈው ጥቅስ አይደለም ፤ ማህበሩ ገና 20 ዓመት አልሞላውም ፤ ጥቅሱ ግን 2000 ዓመት አለፈው ፤ ይህ እስከ ህይወታችን መጨረሻ የምንታመንበትና የምናምንበት የወንጌሉ ቃል ነው

http://andadirgen.blogspot.com/2012/04/blog-post_1357.html

Berhanu Melaku said...

“አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት” የኤፌሶን መልእክት ም. 4 ቁ. 5

ታዲያ በዚህ ከ 2000 አመት በላይ በሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ማኅበረ ቅዱሳንን ከአክራሪነት ጋር ማገናኘት ለምን አስፈለገ? ምናልባት አቶ መለስ አንዳንድ በንዋይ ፍቅር የታነቁትን የቤተ ክርስቲያኗ አባቶች ለማስደሰት ብለው ይመስላል ማኅበረ ቅዱሳንን ከአክራሪነት ውስጥ የመደቡት። አዎ ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያኗ መዋቅር፣ ዶግማ እና ቀኖና እንዲከበር ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
ማኅበረ ቅዱሳን “እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከበርበት” ሰላማዊ ለእምነቱ ታማኝ ማኅበር ነውእንጅ አክራሪ ሊባል አይገባም። ገዳማትንና አብነት ት/ቤቶችን ከጥፋት መታደግ አክራሪነት ነውን? ወጣቱ ትውልድ ሃይማኖቱን አውቆ በሥነ ምግባር ታንጾ አገሩንና ቤተ ክርስቲያኑን በቅንነት እንዲያገለግል ማድረግ አክራሪነት ነውን? በገንዘቡ፣ በዕውቀቱና በጉልበቱ በነጻ የትውልድ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚሞክር ትውልድ መፍጠር አክራሪነት ነውን?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ልጆች ዝንብን እንኳ የእግዚአብሔር ፍጡር ናት በማልት በእጃቸው አያጠፉም፤ በጭራ ያባርሯታል እነጂ። የአክራሪነትን (የአጥፍቶ ጠፊን) ምንነት ለመረዳት መስከረም ፩ (September 11)ን፣ የሎንዶኑን የባቡር ጣቢያ ፍንዳታ፣ የጅማውን ጭፍጨፋ፣ የኒው ዴልሒን የሽብር አደጋ፣ አል፡ሸባብ በየጊዜው በሶማሊያ የሚፈጽመውን መመልከት ያስፈልጋል። ትርጉሙና ምንነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ያለቦታው ይህንን ቃል መጠቀም ሕዝቡ ቃሉ ያዘለውን ቁምነገር እንዳይረዳ ከሚያደርገው በስተቀር ውጪ ሌላ ምንም ጥቅም የለውም።
ስለዚህ አቶ መለስ ይህ አባባልዎ በአንድ ወቅት "ባንዲራ ጨርቅ ነው" ብለው ካሉት እኩል ስለሆነ ጊዜ ሳይሰጡ ቶሎ ብለው ይቅርታ ቢጠይቁ መልካም ነው።
አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት !!!

መላኩ said...

ሰላም!

አንድ የረሳሁት ነገር፡ ይህ "ኢሳት" እያል እራሱን የሚጠራው ጣቢያ አነሳሱና አመሠራረቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልክ ጸረ-ኢትዮጵያ የሆነ አጀንዳ ያለው፡ የኢትዮጵያውያንን ማንንነት ለማጥፋት ከተቋቋሙት ድርጅቶች አንዱ መሆኑን አትጠራጠሩ። ለእስላም ሰባኪያን ማይክሮፎን የሚሰጥ ድርጅት ወይ ከአረቦች ገንዘብ ያገኛል፣ ወይ ለሃቅ ያልቆመ ወሽካታ ድርጅት ነው።

መላኩ said...

@andadrigen

ለክርስቲያን "አክራሪ" መባሉ እኮ መጥፎ ነገር ሊሆን አይገባውም፡ የክርስቲያን አክራሪ እንድ ክርስቶስ ዓይነት ነው ማለት ሲሆን የሙስሊሞች አክራሪነት ደግሞ እንደ ሙሀመድ ማለት ነው። ክርስቶስ የፍቅር አክራሪ፣ ሙሀመድ ደግሞ የጥላቻ አክራሪ ያስብላቸዋል። ስለዚህ አክራሪ ክርስቲያንነቱን በደስታ ነው መቀበል ያለብን፡ አይመስልዎትም?

Haile Michael zemerahe berhanat said...

http://www.youtube.com/watch?v=vXohWPxzmYE&sns=fb


Please listen from VOA about the current situation around Waldiba Monastery.
Let us ask ourselves what we are contributing for our church while those around Waldiba are going to sacrifice themselves to safeguard our church.

“እመሰ ረሳእኩኪ ኢየሩሳሌም ለትርሳእ የማንየ
ወይጥጋእ ልሳንየ በጉርኤየ ወለእመ ኢተዘከርኩኪ
... ወለእመ ኢበጻእኩ በቀዳሚ ትፍስሕትየ’
ኢየሩሳሌም ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ
ባላስታውስሽ ከደስታየ ሁሉ ባላስቀድመሽ ምላሴ ከትናጋ ትጣበቅ
መዝ 136 :5 _6”

Unknown said...

I am really touched by this news! Those of you diaspors please help us in any ways...i appreciate the guy who express z amount of money he can contribute..
I can see God will consider ur motive as if you already paid off the sum you pledged!
Lets organize and keep our church from zis junta EPRDF!
They are so ambitious that they want to reach civilization in 5 years... Poor woyane i feel sorry for you!!

Anonymous said...

Egiziabiher beselam yiftaw yetesfawan hager emebetachin titebek. Abetu Getahoy fetineh teradan.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)