April 5, 2012

የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት አብያተ ክርስቲያናት የአቡነ ፋኑኤልን ማስፈራርያ እንደማይቀበሉ አረጋገጡ

·         አቡነ ፋኑኤል የሀ/ስብከቱን ፀሐፊ ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝን “ክህነቱን ይዣለኹ” ያሉበትን ደብዳቤ በተሐድሶዎች ብሎግ ላይ አወጡ፤
·         ይህ ሥርዓት የሌለው “ሥልጣነ ክህነትን ማገድ” ሊቀ ጳጳሱን ከማስገመት ውጪ ትርጉም የለውም ተብሏል፤
 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 27/2004 ዓ.ም፤ ኤፕሪል 5/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት አብያተ ክርስቲያናት “ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካ ተመድበው ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ አብያተ ክርስቲያናቱ ያቀረቡትን ጥያቄ ባለመቀበል የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር በሚያናጋ መልኩ፤ የፓትርያርኩ ስም በጸሎተ ቅዳሴ እንዳይነሳ በመገፋፋት፤ ሰዎች በፈለጉት መንገድ እንጂ በቃለ ዐዋዲ የሚመራ ቤተ ክርስቲያን እንዳይኖር፤ የካህናትን ክብር የሚያቃልል የቦርድ አስተዳደር በቤተ ክርስቲያን እንዲስፋፋ ጥረት በማድረግ፤ በትልቅ ትጋት ሀገረ ስብከቱን ለዚህ እድገት ያበቁትን ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ቀርበው ተመድቤ መጥቻለሁ ብለው ኃላፊነትን ከመቀበል ይቅ “የአብርሃምን ድንኳን” አፈርሳለሁ በሚል ስሜታዊ አዋጅ ተነሳስተው ሀገረ ስብከት የሚባል የለም  ብለው በአሜሪካ ድምጽ እስከመናገር” ደርሰዋል ሲሉ  በድጋሚ ወቀሱ። 


ቅዳሜ መጋቢት 22/2004 ዓ.ም፤ ማርች 31/2012 የተሰበሰቡት በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት፤ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት ፤ የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፤ ምክትል ሰበካ ጉባኤ ሊቃነ መናብርት፤ የሰንበት ት/ቤት፤ የካህናትና የምእመናን ተወካዮች የተገኙበት ባወጡት የአቋም መግለጫ “አብያተ ክርስቲያናቱ  የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ይጠበቅ በማለታችን  የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ነኝ የሚል አባት ሊደሰት ሲገባው፤ ይህንን አቋም በመጥላት፤ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ለማዳከም መነሳሳት ከብፁዕ  አቡነ ፋኑኤል በተግባር እያገኘነው  ያለ ምላሽ ነው። ብፁዕ  አቡነ ፋኑኤል በተደጋጋሚ ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤና አብያተ ክርስቲያናት የቀረበላቸውን “ወደ መንበርዎ ይመለሱ” የሚል ጥያቄ  አልቀበልም በማለት፤ በተቃራኒ መልኩ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ጠብቀው የሚያገለግሉ ካህናትን  በመደወልና በስሜታዊ ንግግር በመናገር የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት እንዲያከናውኑ የተሰጣቸውን ክህነት የፈለጉትን መፈጸም የሚችሉበት የግል ሥልጣን አድርገው በመውሰድ የቤተ ክርስቲያን መመሪያ ከሚፈቅደው ውጭ እውነትን ይዘው የተከራከሩ ካህናትን ሥልጣነ  ክህነት እይዛለሁ” ሚል መስመር በመጓዝ ላይ ይገኛሉ” ብለዋል።

በተለይም ብፁዕነታቸው “ሥልጣነ ክህነታቸውን ይዣለሁ” ያሏቸውን ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝን በተመለከተ የአብያተ ክርስቲያናቱ ተወካዮች ባሰሙት ሐሳብ በአንድ ድምጽ ከቀሲሱ አገልግሎት ጋር መሆናቸውን አበክረው የገለፁ ሲሆን ስብሰባ በተደረገ ማግስት ሊቀ ጳጳሱ በቃል ያሰሙት የነበረውን ማስፈራሪያ ወደ ጽሑፍ በመቀየር የውግዘት ደብዳቤያቸውን ሥልጣነ ክህነትን በማይቀበሉ ተሐድሶዎች ድረገጽ ላይ አውጥተዋል። ሥልጣነ ክህነቱ መሻር ከነበረበት ነገሩ መዞር የነበረበት ወደራሳቸው ወደ ሊቀ ጳጳሱ መሆኑን ያወሳው ጉባኤው “ሰዎችን ሊያሳዝናቸውና ፈርተው እንዲገዙለት ፈልጎ በማይገባ ቢያስር ቢያወግዘውም እርሱ (ጳጳሱ) ከእግዚአብሔር ዘንድ  የታሰረ ይሁን። ካህናትም በእውነት ይቋቋሙት” (ፍትሐ ነገሥት  አንቀጽ ፻፹፬  ረስጠብ ፳፬) የሚለውን ሕገ ቤተ ክርስቲያን የመግለጫው መሪ ቃል አድርጎ አቅርቧል።

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በተደጋጋሚ ደብዳቤዎቻቸውን የቤተ ክርስቲያንን እምነት በሚያራክሱ፣ ቅዱሳንን በሚሳደቡ፣ ገዳማት በእሳት መቃጠላቸውን በሚደግፉ፣ ሥልጣነ ክህነትን (የራሳቸውን ጵጵስና ይጨምራል) በማይቀበሉ የተሐድሶ የጡመራ መድረኮች (ብሎጎች) ላይ ማውጣታቸው ብዙዎችን እያስገረመ ነው። “የአጋጣሚ ወይስ ሆን ተብሎ? ከተሐድሶዎቹ ጋር ግንኙነት አላቸው ወይስ አብረዋቸው የሚሠሩ ተሐድሶዎች አሉ?” የሚሉ ጥያቄዎች በመንሸራሸር ላይ ናቸው። ሊቀ ጳጳሱ ከሐዋሳ ግርግር ጀምሮ ከተሐድሶዎች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በሰፊው ሲወራ የቆየ ቢሆንም እርሳቸው ብቻ ሊልኳቸው በሚችሏቸው ደብዳቤዎች ጉዳይ ግን ነገሩ ግልጽ እየሆነ መምጣቱን ብዙዎች እየተቀበሉት መጥተዋል።
ሊቀ ጳጳሱ ሀ/ስብከታቸውን እና መንበረ ጵጵስናውን ሳይቀበሉ ሌላ ማረፊያ ካዘጋጁ ጀምሮ “ገለልተኞችን አቀርባለሁ” በሚል ፈሊጥ በሀ/ስብከቱ ውስጥ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እና ካህናት ጋር ከመሥራት ይልቅ በራሳቸው መንገድ መሔድ መምረጣቸው ይታወቃል። የሚያሳዝነው ደግሞ “አቀርባቸዋለኹ” የሚሏቸው “ገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት” በይፋ የእርሳቸውን ተልዕኮ ባለመቀበል ይልቁንም እንዳይመጡባቸው ማዕቀብ በመጣል ከሁለት ያጣች ጎመን እንዲሆኑ አድርገዋቸዋል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ ሁኔታ ባለበት ወቅት አቡነ ፋኑኤል “ክህነት ይዣለሁ” ብለው የጻፉት ደብዳቤ ያላቸውን ዕውቀት መጠን ፍንትው አድርጎ ያጋለጣቸው ከመሆኑም በላይ “እዚህ ዘመን ላይ እንድረስ? ጵጵስና እንዲህ ይሁን?” የሚል ቁጭትን አጭሯል።

የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።  

ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡

16 comments:

desalew said...

ABO! yetewgezuna eirsachew aba melaku nathew!!! besewm be eigizabherm zenid!!!

Anonymous said...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሐድሶ መጫወቻ ልትሆን አይገባትም የሚሉትን እውነተኛና ቆራጥ ኦርቶዶክሳውያንን በማስፈራራት ከሕዝብ ጋር ተገናኝተው ቃል እንዳያስተምሩ፣ መልእክት እንዳያስተላልፉ፣ እውነት እንዳይናገሩ እና ተሐድሶን በግልጽ እንዳይቃወሙ “ክህነታችሁን እይዛለሁ” በማለት የተነሱት አቡነ ፋኑኤል ያለ ምንም ጥርጥርና ተጨማሪ ጥናት የተሐድሶ አቀንቃኝ መሆናቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው። በገንዘብ ጵጵስናን የተቀበለ ሰው የጵጵስናን ምንነት ያውቀዋል ተብሎ ወትሮም ስለማይገመት ፍየል ከመድረስዋ ቅጠል መበጠስዋ እንዲሉ የቅዱስ ሲኖዶስን መመሪያ ጥሰው የፓትርያርክ ስም በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንዳይጠራ ማድረጋቸው አንሶ የቤተ ክርስቲያን መዋቅርን እናስጠብቃለን ብለው ደፋ ቀና የሚሉትን አገልጋዮች ከተሐድሶዎች ጋር ግንባር ፈጥረው ካህኑን ያለ ምንም ጥፋት አውግዤዋለሁ ብለው መጻፋቸው ብቻ ሳይሆን የሚያስወቅሳቸው ከጽሑፉ ጀርባ በርቱ፤ ግፉበት በማለት የገፋፏቸው የቤተ ክርስቲያን ውለታ ግድ የማይላቸው ተሐድሶዎች ረዳታቸው ሆነው መቆማቸው ነው። በመሠረቱማ ጳጳስ ድርሻው ማውገዝ ብቻ ቢሆን ኖሮ አቡነ ፋኑኤል አባ መላኩ የሚባለውን ስም ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት ጀምሮ አይጠሩበትም ነበር። አንድ ጳጳስ በየተመደበበት አገረ ስብከት ዓይንህን ለአፈር እየተባለ እንዴት ይቀመጣል? በአገር ውስጥም በውጭም ባሉ ኢትዮጵያውያን ተቀባይነት ካጡ ችግሩ ከእኔ ዘንድ ነው ብሎ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር አስፈላጊ ይሆናል። የአዋሳው ቁስል ሳይደርቅ እና ንዴቱ ከልብ ሳይወጣ ሌላ ተጨማሪ እሳት ከአገር ውጭ ወጥቶ ማንደድ ምን ይሉታል? ትናንት ዝቋላ ተቃጠለ፤ ዋልዳባ ታረሰ ብሎ ወገን ሲጮህ ድምፅ ያላሰማ ጳጳስ ብጠራው አልመጣልኝም ብሎ ክህነት መያዝ መሳቂያ ያደርገዋል እንጂ ደፋር አያሰኘውም። ከተሐድሶ ጋር የዋለ ማስተዋሉን እንደሚነጠቅ የታወቀ ነው። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ደብዛዋን ሊያጠፉ ከተነሱ የዘመኑ ከሐዲዎች ጋር ግንባር መፍጠር አስፈላጊ አልነበረም። አሁንም ልብ ያለው ልብ ይበል በማለት መልእክቴን አጠናቅቃለሁ።

zewdumesfin said...

FIRST OF ALL ABA FANUEL HAS NO POWER BECOUSE HEIS tahadiso dont worruy kese!!!! JUST SERVE LORD

Anonymous said...

gizitu enqwa keld honowal. meches yihe lebego new, yemiyastemiren neger yinoral. ye alama liyunet newuna mebertat new. beteley tikit yekirb gize papasat bahiriy eyehone new. masferarat, mabarer, maged, siltan meyaz. lib yistachew!!!!

Gebre Z Cape said...

Thanks for the information. Amilak lehulachinim asiteway libona yisiten. Ayi Yebetekiristian Fetena malekiya yelewum eko.

Man yazewal said...

ቤተ ክርስቲያን በምን ዓይነት ሰዎች እንደምትመራ ያሳየ ወፈገዝት ግዝት የሆነ መልእክት ነው። አንዳንድ ቄሶች እንዲህ ካላደረጋችሁ አወግዛለሁ እያሉ ፍላጎታቸውን ለማሟላት እንደሚሉት የሳቸውም ግዝት ወፈ ገዝት የሆነ ግዝት ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ለመሆኑ ለዚህ ከንቱ ለሆነ ተግባርዎ የጠቀሱት ፍትሐ ነገስት የሚጠቅመው ለእርስዎ ብቻ ነው። እርስዎስ ያለ ሀገረ ስብከትዎ እየገቡ ክህነት ሲሰጡ ቤተ ክርስቲያን ሲባርኩ በሥራዎ መጽሐፉ የተወገዙ ያደርግዎታል። ደግሞ ካላከበረከኝ ብሎ አወግዛለሁ ማለት ምን ማለት ነው።የግል ፍላጎትዎን ለማሟላትና ተልዕኮን ለመፈጸም በሁለት በኩል ተሰለው የሚገኙትን እንደርሶዎ በቤተ ክርስቲያን ሃብት ላይ ኅሊናቸውን ሽጠው እንደፈለጉ ለመሆን ሳይሆን ያላቸውን ትተው ቤተ ክርስቲያንን በንጹህ ኅሊናቸው በማገልገል ላይ የሚገኙትን ቀሲስ ዶ ክተር ምስፍንን አውግዥለሁ ማለትዎ የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዓት ጬርስዎ አለማወቅዋን ያሳያል። እባክዎ ን ብጹዕ አባታችን ዛሬም ጊዜ አልዎትና አንዴ መቼም በምንእንደሆነ ባይታወቅም ለዚህ ክብር በቅተዋልና ሊቃውንትን ጠይቀው ቢያንስ እንኳን አንድ ሊቀ ጳጳስ ምን መሆንና መምሰል እንዳለበት ለመማር ይሞክሩ። መቼም ለእርስዎ ይህ ምክር የሞት ያህል ሊከብድዎ ይችላል ግን ጊዴለም አባታችን ቢያንስ በምእመናን ሲመዘኑ ቀለው እንዳይገኙ ያደረግዎታል።

Anonymous said...

“ጥይት እንደሌለው ጠመንጃ፣ ሥልጣን የሌለው ‘ውግዘት’”
የሚከተለውን መልዕክት ከአንድ አስታያየት ሰጪ ምዕመን የደረሰን ነው::
በቤተ ክርስቲያን ውግዘት ሁለት ዓይነት ነው። በክህነት የሚተላለፍ ውግዘት እና አስቀድሞ የተወገዘ ድርጊት። በርዕሱ “ጥይት እንደሌለው ጠመንጃ ሥልጣን የሌለው ውግዘት” ያልኩት በተወገዘ ድርጊት የተሠማሩ ባለሥልጣን ነን ባዮች የሚያስተላልፉትን ‘ውግዘት’ ነው።
በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን የተወገዙ ድርጊቶችን የሚያደርግ ውጉዝ ወይም የተወገዘ ነው። በፍትሐ ነገስት ከሥልጣነ ክህነት የሚያሽሩ ወይም የተወገዙ ድርጊቶችን ከምዕመናን እሰከ ጳጳሳት ያሉትን ይመለከታል። በተለይ ካህናትን እና መነኮሳትን አስመልክቶ፦
1. መነኩሴ በገዳም ተወስኖ እንዲኖር
2. ካህን ያለ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ያለ ጳጳስ ፈቃድ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንደፈለገ እንዳይዘዋወር
3. ጳጳስ ከሀገረ ስብከቱ ውጪ በሌላው ሀገረ ስብከት ያለፈቃድ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን በተለይም ሢመተ ክህነትን እንዳይፈጽም
ያዛል።

ትዕዛዛቱ ሁሉ ቢዘረዘሩና የዛሬ ካህናትና ጳጳሳት በፍትሐ ነገስቱ ሕግና ሥርዓት ቢመዘኑ አብያተ ክርስቲያናቱ ያለ ካህናት አህጉረ ስብከቶቹ ያላ ጳጳሳት ሊቀሩ እንደሚችሉ ያሰጋል። እውነተኞች ካህናትና ጳጳሳት የሉም ማለት ግን አይደለም።
ከብዙ በጥቂቱ ከተረዘሩት የውግዘት ተግባሮች አባ ፋኑኤል ሁሉንም የፈጸሙ ሰው ናቸው። በፍትሐ ነገስቱ እንደተደነገገውና ሐዋርያት በዲድስቅልያ እንደ ደነገጉት በምዕመናን ፈቃድና ምስክርነት ነው አንድ ካህን ለኤጲስ ቆጶስነት የሚሾመው። እኚህ ሰው ግን በምዕመናን ያልተመሰከረላቸው ባለሥልጣን፣ በሕገ ወጦች የተመሰከረላቸው ሕገ ወጥ ናቸው። ታዲያ እኚህ ሰው እንኳን ውግዘታቸው አንደበታቸው ለምዕመናን ጆሮ የሚስማማ አይደለም።
አባ ፋኑኤል ‘አወገግዝኩ፣ ገዘትኩ’ ቢሉ የሚደንቅ አይደለም። ቤተ ክህነቱ ሕገ ወጦች የሚሾሙበት እውነተኞች የሚሰደዱበት የወንበዴ ዋሻ ሆኖአል። ስለዚህ የሚደንቀው እውነተኞችን ቢሾሙ፡ ሕገ ወጦችን ቢያወግዙ ነበር። ወደ አሜሪካ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የሚሠሩት ሁሉ ሕገ ወጦችን በርቱ እያሉ መሾምና የሀገረ ስብከቱ ሕግና ደንብ ይከበር የሚሉትን ማሳደድ የዕለት ተግባራቸው ሆኖአል።
ክህነት የተሰጠው ለሰዎች ድህነት እንጂ ለውግዘት እንዳልሆነ አለማስተዋላቸው፣ ኤጲስ ቆጶስነት መንጋውን ለመጠበቅ እንጂ ለመበተን እንዳልሆነ አለመገንዘባቸው ይደንቃል።
የሚያወግዝ ጠፋ እንጂ በቤተ መቅደሱ ጣዖት ባቆሙ ጊዜ በሰው ሳይሆነ በእግዚአብሔር የተወገዙ እንኳን በሌሎች ካህናት ይቅርና በእኛ በተራ ምዕመናን እንኳን ሥልጣን እንደሌላቸው ሊያውቁት ይገባል!

Anonymous said...

ለካ እንደዚህ ጠንካራ የሆኑ አብያተ ክርስቲያናት አሉ። ካህናቱም በብዙ ካህናት ዘንድ ያለውን ፍርሃት አሰወግዳችሁ ለቤተ ክርስቲያናችሁ ዘብ በመቆም እንደዚህ ዓይነቱን ወፈ ገዝት ግዝት በመቃወማችሁ ለቤተ ክርስቲያናችን ያላችሁን ለኝታነት አሳይታችኃል። ቀሲስ ዶ ክተር ምስፍን ለሚሰሩትና ለሰሩት መልካም ሥራ ሁሉ ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን መሪ ከሆኑ ከአባ ፋኑ የተላለፈልዎ ወረቀት ካለ ይቅደዱት። ትላንት በሓዋሳ ምእመናን እንባ ሲጫወቱና ሲደነፉ ነበረ አሜሪካን እንዲህ አደርጋለሁ ብለው ከሆነ ብልጥ ነበሩ ምነው ዛሬ ተሞኙ ለካስ ብልጥ ያለ አንዴ አይበልጥ የሚባለው ለዚህ ነው።

Anonymous said...

Wei menafikan. Endezih erasachun badebabay tagalitu ere nisiha gabtachihu kabatoch tareku. Yeha kihidetina elihegnnet tegebi aydelem

Anonymous said...

Hey why u guys wory For Aba Fanueal Esachew eko be ewuketachew lik eyaderegu yalu sew nachew. Enen yasazenegni Ye'Ethiopia orthodox betekirstiyan Papas teblo meteratachew new enji esachew Tifat nurobachew sayihon ye'ewuket chiger new. Aschegari new sew ande kemayiwetabet elek wust kegeba mewucha yelewum mekiniyatum shinfet silemimeslew. Esachewum yeziwu ayinet neger agatimochew enji. wedew ayidelem yih demo kesachew kerto kande yenebite tera sew yemayitebek new.

Anonymous said...

bezih wekit smina selot new einji einidih ayinet neger mefesem ayigebam betechale meten lebetekirisitiyan eiyasebin bihon melikam new << ahiya biraget yemigodaw meretu new >> eindetebalew betekirisitiyan benanite mikiniyat simuwa menesatu yasazinal

Anonymous said...

sewuyewun endih kmalet biyans 1 subae enditemequ lemin atadergum ! betenako aydelem endih yemihonute mazen newu ymigeban

Anonymous said...

Sharing negn

1.Who is Abune Fanuel after all as long as he does not abide by the rule of the Church and the word of God.

He can follow his own doctrine if he doesn't have the belief in orthodox church but it is shame to try to change the church using the church's property like some viruses do to human being and devil covers himself in the body of snake.There are many spiritual priests and the like to lead the church. Those who are just thinking you are the best are the least. Even a single child without any spiritual maturity has better good mind than you.

2.Orthodox Christians please be awake and watch what is going on on our church in regards to the word of God . Do not trust some wolfs covered by the hide of sheep. They are milking the church being covered by our innocent people who respect priests and others without judging them.All those who are challenging ,do not think you are being smart

3. This era is the end of the world, where so many unexpected things happen even to those chosen by God. They do not have the spiritual capability to defeat Devil and they do not have the spiritual maturity to lead the people.

4.All orthodox people please pray for yourself, for our church and learn as much as possible about the church. The church expects more from miemenan
than the leaders.And nowadays the miemen is better than the leaders, please continue to struggle to get rid of the inside enemies of the church.And follow up on their life and make it clear to the public since they could not listen when they are told secretly by discussing with the appropriate people before telling their sins. Tell them first, if they say no , then tell to the public to protect the public and to protect them from doing more evil work and continue on their sin.

5. Do not be discouraged by the evil work of the leaders, but be strong
and read the word of God and learn the church's doctrine and preaching
as well lead your life with the word of God. Pray for each other and for all people.

mskin girl said...

አብነ ፋኑኤል መጀመሪያ ለቀሲሲ ዶክተር መስፍን ባውጡት የሞኝ ማስጠንቀቂያ ቀሲስ ዶከተር ምስፍንን ቀሲስ የሚለው ባወጡት ደብዳቤ አልጨመሩም ነበር ታድያ ያላመኑበትን ቅስና እንዴት አግዱት ውይ አብነ ፋኑኤል የሚስሩት ነገር የለዋትም እነ ቀሲስ ዶክተር በጣም ብዙ የቤተ ክርስቲያን ስራ አለባቸው እባኮት ይስሩብት አይብጥብጡ የርሶ ማርፊያ የት ይሆን? የስላም አምላክ የሂሊና እረፍት ይስጦት አሜን!!

Anonymous said...

አይ ይህቺ ጊዜ ስንቱን ታሳየን!!! ታሰማን!!! ቤተክርስቲያናችን የሲሆል ደጆች አይችሏትም የሚባለዉ ለዚህ ነው። በሌላት አቅሟ አስተምራ ለዚህ አድርሳ ተመልሰው ሲያጠቈት ከማየት በላይ የሚያሳዝን ነገር የለም። ይህ ደግሞ የማን ተግባር እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው የአዳባባይ ሚስጥር ነው። የነ ተረፈ አሪዮስ አለዚያም የነ መሐመዳዊያን ግብር ውጤት ነው፡; የዋሽንግተንና አካባቢ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለአቡነ ፋኑኤል ተረ ወረቀት የመለሱት ምላሽ የሚያረካ ነው። መልዕክቱ በጣም የሚያስተምርና ትምህርት ሰጭሚ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። መጽሐፉን አጋላብጠው፣ ፍትሀ ነገስቱን አመሳክረው ከአባቶቻቸው በተማሩት መሰረት የቤተክርስቲያኗን ስርዓትና ቅኖናን ጠብቆ የተመለሰ ምላሽ በመሆኑ ሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት የነዚህን አብያተ ክርስቲያናት ፈለግ ተከትለዉ ለተዋህዶ ሃይማኖታቸው ዘብ መቆም እንዳለባቸው ጥሩ አርሃያ ሆነውናል፡; የቤተክርስቲያኗን መዋቅር ይከበር ብላችው የተነሳችዉ የክርስቶስ አገላጋይ ካህናት ሁሉ በያዛችዉት ዓላማ ያጽናችዉ፤ በተራና ባሉባልታ ወሬ አትሸበሩ፤ ወንጌሉን ስበኩ፤ የቤተክርስቲያኗንም መዋቅር በጀመራችዉት እስከመጨረሻው አድርሱት። ክርስትና መንገዷ አልጋ በአልጋ አለመሆኗ ከኔ በላይ ታውቁታላችዉና በርቱ። አቡነ ፋኑኤልና ተባባሪዎቻቸው በመጀመሪያ አቡነ ፋኑኤል የዋሽንግተንና አካባቢውን ሀገረ ስብከትና ቤተክርስቲያናችንን በምንም መልኩ አይወክሉም። ምክንያቱም ስልጣነ ክህነቱን ባንድም በሌላም ተቀብለው ስልጣኑን abuse እያደረጉት ይገኛሉ። ያገልግሉ አያገልግሉ ባይታወቅም ባሉበት ቅ/ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እንካ የፓትርያርኩን የማይጠሩና ቅኖናና ስርዓቱ በሚያዘው መሰረት የያዙት አብያተ ክርስቲያናት ሳይኖሩን ክህነቱኝ አለኝ በማለት በማይወክሉበት ቤተክርስቲያንን ገብተው መበጥበጥ ምን የሚሉት ነገር ነው? ሲጀመርም ዓላማዎት ምን እንደሆነ በጣም ጠንቅቀን ስለምናውቅ በሚያደርጉት ተግባር ብዙም አልተደነቅንም። ያው ሀገር ቤት የጀመሩት የማን አለብኝነት ተግባር ስለሆነ እግዚአብሄር ልቦና ያድሎት ከማለት ውጭ ምን ይባላል? አባትነታቸውም ከምግባራቸው ተመልሰው ከሀገረ ስብከቱ ጋር እስካልሰሩ ድረስ በተለይ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ያለንን አብያተ ክርስቲያናት ስለማይወክሉ ብዙም በይደክሙ ይመረጣል፤ የተሰጣቸውንም ክህነት ተራ ክህነት አለመሆኑን ተገንዝበው ኦርቶዶክሳዊ አካሄድ ቢኖራቸው መልካም ነው በማለት ሀሳቤን እቆጨለሁ።

Anonymous said...

ለአቡነ ፋኑኤል እግዚአብሔር ልባቸውን ወደ ቤተክርስትያን ይመልስ በኛ ላይ የፈፀሙት ሁከትና ሽብር እንዲሁም ብጥብጥና ለቅሶ በውጪ ያሉት ምእመናን ላይ ለማድረግ ነበር ነገር ግን እግዚአብሔር ገትቶአቸዋል በዚያ ያላችሁ የቤተክርስትያን ልጆች በርቱ እላለሁ ያኔ የአዋሳ ክርስትያን በለቅሶ እና በዋይታ ሲታመስ ጩኸታቸውን እንደባግራወንድ ነው የማየው እኔ የአሜሪካን ሀገር ሁሉን ያየሁ አባት ነኝ ብለው ሲመፃደቁ የነበሩ አባት ናቸውና አሁን እንባችን ታብሶ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብተናል እሳቸውን ግን በእውነት ከቤተክርስትያናችን ማውገዝ ነው እላለሁ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)