April 30, 2012

በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ መጓዛቸውን ኢሳት ዘገበ፣

  •   "ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል” ብሏል የኢሳት ዜና፤
(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 23/2004 ዓ.ም፤ April 30/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦፦ “በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ መትመማቸውን እንዲሁም ሁለት ነጮች መገደላቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን” ኢሳት የተባለው ብቸኛው ከአገር ውጪ የሚገኝ ነጻ የዜና ተቋም በሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም  ዘገባው አስታወቀ። “የገዳሙ አባቶች ለሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እስከ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኙ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ አካባቢው መትመማቸውን ተከትሎ ሁለት ነጮች መሞታቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ እኛ ከህዝብ ጋር አንጣላም በማለት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል” ያለው ዜና ተቋሙ የሟቾቹ እና አካባቢውን ለቀው የወጡት ነጮች ምዕራያን ይሁኑ የቻይና ዜጎች አልታወቀም” ሲል አክሏል።

April 28, 2012

ዋልድባ አሁንም አወዛጋቢነቱ እንደቀጠለ ነው (ጥልቅ ሪፖርታዥ)

READ THIS ARTICLE IN PDF.
·         ማኅበረ ቅዱሳን በዋልድባ ጉዳይ ከፓትርያሪኩ እና ከመንግሥት ጋራ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል። 
·     ማኅበሩ የወልቃይት ስኳር ፕሮጀክት በዋልድባ ገዳም ላይ ስለሚያደርሰው ተጽዕኖ ያጠናቀረውን ሪፖርት አስመልክቶ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል::
·     “እስከ 20 ሄ/ር የገዳሙ መሬት በግድቡ ውኃ ይሸፈናል፤ ፕሮጀክቱ የገዳሙን 40% የምርት ገቢ 60% የምእመናን ድጋፍ ያሳጣዋል” (የማኅበሩ አጥኚ ቡድን ሪፖርት)::
·       ማኅበሩ የፕሮጀክቱ አካባቢ ከሚለወጥበት እስከ ዲዛየን ማሻሻያ የሚደርስ የጥናት አማራጭ እንዲያቀርብ፣ ገዳማውያኑ ስለ ፕሮጀክቱ ማኅበራዊ እና አካባቢያዊ ተጽዕኖ ያላቸው ሐሳብ የሚደመጥበት አቋማቸውንም ያለጫና የሚያሳውቁበት መድረክ እንዲያመቻች ተጠይቋል::
·        የስኳር ኮርፖሬሽኑ በፕሮጀክትና ፋብሪካ ማኔጅመንት የአቅም ማነስ ችግር እንዳጋጠመው አስታውቋል::
·     “ወደ ፕሮጀክቱ ትግበራ ከመግባታችን አስቀድሞ መነኰሳቱን እንደ መንግሥት በአለማነጋገራችን አጥፍተናል፤ እነርሱን [የቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳትን] ማማከር ነበረብን፡፡” (የፕሮጀክቱ ሓላፊዎችና የወረዳው ባለሥልጣናት)::
·         መንግሥት የፕሮጀክቱን የጥናት ሰነዶች ይፋ ያድርግ(አንድ የኢንቫይሮመንታል ዲዛይን ምሁር)::
(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 19/2004 ዓ.ም፤ April 27/2012 )፦ መንግሥት በክልል ትግራይ ምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ በሚገኘው የዛሬማ፣ ዱቁቆ እና ተከዜ ሸለቆ በሚያካሂደው የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት የተነሣ ከአገራችን ታላላቅና ቀደምት ቅዱሳት መካናት አንዱ በኾነው በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ የተጋረጠው አደጋ ለብዙኀን መገናኛ ዘገባ ከዋለ ድፍን ሁለት ወራት ተቆጥረዋል፡፡

April 27, 2012

በስዊዲን “አዲስ ቤተ ክርስቲያን ይከፈታል" መባሉን ምዕመናን ተቃወሙ


(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 19/2004 ዓ.ም፤ 4/27/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በስዊዲኗ የስቴክሆልም ከተማ በመጪው እሑድ “ይከፈታል” የተባለ ቤተ ክርስቲያንን አስመልክቶ ምእመናን ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። የተቃውሟቸውን እና ምክንይቱን ዝርዝር እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን 

April 24, 2012

አቡነ ፋኑኤል አዲስ አበባ ናቸው


አቡነ ፋኑኤልን ለጵጵስና ያበቃቻቸው ንግግር (ቪዲዮውን ይመልከቱ)


·         በጉጉት የሚጠብቁትን ደብዳቤ ከፓትርያርኩ አግኝተዋል፤ 

(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 14/2004 ዓ.ም፤ 4/22/2012, READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ አወዛጋቢው የአሜሪካ ሁለት አህገሩ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቅዳሜ አዲስ አበባ ገብተዋል፤ በመላው አሜሪካ የተነሣባቸውን ተቃውሞ ለማድበስበስ እና ከአሜሪካ እንዳይነሡ ለማድረግ እንደተዘጋጁ የደጀ ሰላም ምንጮች አስታወቁ። በአሜሪካ የተቀሰቀሰባቸውን ተቃውሞ የሚያበርድ ደብዳቤ ከፓትርያርኩ አግኝተዋል።

April 23, 2012

65,000 gather in Moscow ‘to pray for Church & defend faith’

Here is a news about the opposition of Russian Orthodox Christians against the desecration of their Church. Ethiopian Orthodox Tewahedo Chirstians should learn a lesson from this.
Deje Selam
+++

(by OCP on APRIL 23, 2012/ in FEATURED NEWS,NEWS):- Tens of thousands of Orthodox Christians have joined a service outside Moscow’s main church, the Cathedral of Christ the Savior, in defense of their faith, sacred objects and the Church itself, following recent numerous attacks on Christian relics. The Sunday service has gathered around 65 thousand worshippers, according to official police data. It comes in response to what the church says is a series disrespectful acts against Orthodoxy and religious faith over the past few months.­

መንፈሳዊ ሙግት በመንፈሳዊ ፍርድ ቤት


(Reporter Newspaper):- ይህ ወቅት በክርስትና እምነት ተከታዮች የትንሳኤ በዓል የሚከበርበት ጊዜ ነው፡፡ ይህንን ወቅት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን መንፈሳዊና ትውፊታዊ በሆኑ ሥርዓቶች ያከብሯቸዋል፡፡ በትንሳኤው ዕለት ነጭ መልበስ፣ ያሬዳዊ ዜማ መዘመር፣ ጧፍና ሻማ ማብራት የበዓሉ መገለጫ ናቸው፡፡ ትውፊታዊ ሥርዓቶችም አሉ፡፡ በበዓለ ሆሳዕና ዘንባባ መታሰሩ፣ በዕለተ ሐሙስ የእግር እጥበት ሥርዓት መኖሩ፣ ጉልባን የመመገብ ሥርዓት ወዘተ በዚህ ወቅት የሚታዩ መንፈሳዊ ሥርዓቶች ናቸው፡፡ የትንሳኤ በዓል ከሌሎቹ መንፈሳዊ በዓላት የሚለየው መንፈሳዊ ይዘቱ ከፍ ያለ በመሆኑ ነው፡፡ በገና የገና ጨዋታ፣ በጥምቀት መተጫጨትን የመሳሰሉ ልማዶች በዘመነ ፋሲካ አይስተዋሉም፡፡ የትንሳኤን መንፈሳዊ አከባበር ካነሳን ደግሞ የሥርዓቱ ፈጻሚዎች፣ አገልጋዮችና መምህራንን ማሰብ አይቀርም፡፡ በዚህ ጽሑፍም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንንና የመንፈሳውያን ግንኙነት የሚዳኙበትን ሁኔታ፣ በመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት የተሰጡ ውሳኔዎቻችንና በሕገ መንግሥቱ መሠረት ያላቸውን ቦታ በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡

April 20, 2012

Ultimate Plan, Aedas win Orthodox Church mega conference hall design


(Capital/ Monday, 16 April 2012):- Ultimate Plan Private Limited Company won together with a United Kingdom firm Aedas a design architecture re-tender for the planned Ethiopian Orthodox Tewahdo Church (EOTC) mega conference hall with a combined capacity of 13,000 seats.
The building is expected to be constructed at the EOTC’s Patriarch palace located in Arat Kilo, Arada district. It is planned to be powered by solar energy in addition to hosting outside facilities such as landscaping, access roads and footpaths.

April 17, 2012

ሪፖርታዥ፦ የዋልድባ መድኃኔዓለም ተሳላሚዎች ምስክርነት


  • READ THIS ARTICLE IN PDF.
  • ገዳሙ በከፍተኛ የፖሊስ ኀይል ስምሪት ውስጥ ወድቋል
  •  መነኰሳት በአባትነታቸው አይከበሩም፤ ይዘለፋሉ፤ ይታሰራሉ፤ ጸሎተ ምሕላ በማኅበር እንዳያደርሱ ተከልክለዋል
  • ከአንድ ኪ.ሜ ያላነሰ የገዳሙ መሬት የፕሮጀክቱ አካል ኾኗል
  •  “ስለሚታረሰው አያገባችኹም፤ ስለተተኮሰባችኹና ስለተደበደባችኹት አያገባንም” /አቡነ ኤልሳዕ ለተሳላሚዎቹ ጥያቄ የሰጡት ምላሽ/። 
  •  “እውነቱን ከማኅበረ ቅዱሳን ልኡካን ሪፖርትና መግለጫ እንጠብቃለን” /ተሳላሚ ምእመናኑ/

(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 8/2004 ዓ.ም፤ April 16/2012)፦ መጋቢት 20 ቀን 2004 ዓ.ም፤ የመድኃኔዓለምን በዓል በአብረንታንት ዋልድባ ገዳም ለማክበር ወደዚያው ለማምራት ተዘጋጅተናል፡፡ መነሻችን ከጎንደር ከተማ ነው፡፡ ካለፉት ዓመታት ጋራ ሲነጻጸር ዘንድሮ  የተሳላሚው ቁጥር አንሶ ይታያል፤ ከጉዟችን በፊት መንገዱ እንደሚዘጋና በርካታ የፌዴራል ፖሊስ ኀይል እንደተላከ አብዝቶ በመሰማቱ የቀረው ሰው ብዙ ነው፡፡

“እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ፤ አደረሰን።”


“እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ፤ አደረሰን።” 

April 7, 2012

ለቪኦኤ የተናገሩት የዋልድባው አባት በፖሊስ እየታደኑ ነው


·         ያሉበትን ካልጠቆማችኹ በሚል ሦስት ገዳማውያን ታስረው ተፈተዋል::
·         እስሩና ‹አደኑ› የቤተ ሚናስ መነኰሳት በተለይም ከ1997 ዓ.ም ወዲህ ለሚደርስባቸው ልዩ ጫና ግልጽ አመልካች ነው ተብሏል::
·         በ1980 ዓ.ም የገዳሙን ሰሜናዊ ክፍል (በእንስያ ወንዝ) የጦር ካምፕ ለማድረግ የተቃጣው ሙከራ ኅቡኣን አበው ኵናት መወገዱ ተነግሯል::
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 29/2004 ዓ.ም፤ April 7/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የመንግሥት ባለሥልጣናት በዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳት ላይ ከሚያደርሱባቸው ወከባና ማስፈራሪያ እንዲታቀቡ እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሦስት የገዳሙ ማኅበር አባላት በፖሊስ ታስረው መፈታታቸው ተሰማ፡፡ መነኰሳቱ ለእስር የተዳረጉት “ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት አባ የት እንዳሉ ተናገሩ” ከሚል የፖሊስ ጥያቄ ጋራ በተያያዘ መሆኑን ምንጮቻችን ከስፍራው ዘግበዋል፡፡ እንደ ምንጮቹ መረጃ ኮማንደር በየነ በሚባል የፀለምት ወረዳ ፖሊስ መጋቢት 23 ቀን 2004 ዓ.ም ከገዳሙ የተወሰዱት ሦስቱም ታሳሪዎች በገዳሙ በዲቁና የሚያገለግሉ ሲሆኑ ከሦስቱ ሁለቱ መናንያን መሆናቸው ተገልጧል፡፡

April 6, 2012

(ማስታወቂያ) በዋሽንግተን ዲሲ:- መንፈሳዊ የውይይት መድረክ

“ የአባቶቼን ርስት እሰጥ ዘንድ ከእኔ ይራቅ”
(መጽ. ነገሥት ቀዳ. ፳ ፥ ፫) 
 የዋልድባ ገዳምን ለመታደግ የሰላማዊ ሰልፍ ያስተባበረው ኮሚቴ ሁለተኛውን ክፍልና ቀጣዩን ሂደት ለመጠቆም እና ለመወያየት ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ታላቅ ስብሰባ የሆሳዕና ዕለት ተዘጋጅቷል። እርስዎም በቦታው ተገኝተው የበኩልዎን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

April 5, 2012

ከክህነት ስለሚያስሽሩ ምክንያቶች አንዳንድ ነጥቦች ከፍትሐ ነገሥት


ካህናትን ከክህነታቸው ስለሚያሽሩ ምክንያቶች
አንዳንድ ነጥቦች ከፍትሐ ነገሥት
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 27/2004 ዓ.ም፤ ኤፕሪል 5/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አዲስ ሊቀ ጳጳስ ተሹሞ ተልኳል ከተባለበት ከጥቅምት ወር 2004 ዓ.ም ጀምሮ በችግር ላይ ይገኛል። ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በሀ/ስብከቱ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በቃለ ዓዋዲው መሠረት የመረጡትን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አልቀበልም ከማለት አልፈው ካህናቱን በሙሉ ማስፈራራት እና አንዳንዶቹንም “አውግዣለሁ” ማለት ጀምረዋል። ይህም መነሻ ሆኖን “ካህናትን ከክህነታቸው ስለሚያስሽሩ ምክንያቶች”፣ በደፈናው ከመሬት ተነሥተው “ክህነት ይዣለሁ” ስለሚሉ አቡነ ፋኑኤልን ስለመሳሰሉ ጳጳሳት አስቀድመው በቅዱሳን አበው የተሠራውን ሕግ በተመለከተ ፍትሐ ነገሥቱ የሚለውን ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን።

የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት አብያተ ክርስቲያናት የአቡነ ፋኑኤልን ማስፈራርያ እንደማይቀበሉ አረጋገጡ

·         አቡነ ፋኑኤል የሀ/ስብከቱን ፀሐፊ ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝን “ክህነቱን ይዣለኹ” ያሉበትን ደብዳቤ በተሐድሶዎች ብሎግ ላይ አወጡ፤
·         ይህ ሥርዓት የሌለው “ሥልጣነ ክህነትን ማገድ” ሊቀ ጳጳሱን ከማስገመት ውጪ ትርጉም የለውም ተብሏል፤
 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 27/2004 ዓ.ም፤ ኤፕሪል 5/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት አብያተ ክርስቲያናት “ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካ ተመድበው ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ አብያተ ክርስቲያናቱ ያቀረቡትን ጥያቄ ባለመቀበል የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር በሚያናጋ መልኩ፤ የፓትርያርኩ ስም በጸሎተ ቅዳሴ እንዳይነሳ በመገፋፋት፤ ሰዎች በፈለጉት መንገድ እንጂ በቃለ ዐዋዲ የሚመራ ቤተ ክርስቲያን እንዳይኖር፤ የካህናትን ክብር የሚያቃልል የቦርድ አስተዳደር በቤተ ክርስቲያን እንዲስፋፋ ጥረት በማድረግ፤ በትልቅ ትጋት ሀገረ ስብከቱን ለዚህ እድገት ያበቁትን ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ቀርበው ተመድቤ መጥቻለሁ ብለው ኃላፊነትን ከመቀበል ይቅ “የአብርሃምን ድንኳን” አፈርሳለሁ በሚል ስሜታዊ አዋጅ ተነሳስተው ሀገረ ስብከት የሚባል የለም  ብለው በአሜሪካ ድምጽ እስከመናገር” ደርሰዋል ሲሉ  በድጋሚ ወቀሱ። 

April 3, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ዘገባ (ክፍል ሁለት)


·        በዋልድባ ጉዳይ የጎንደር ወጣቶች ሊቀ ጳጳሱን አነጋገሩ::


·        በሊቀ ጳጳሱ አቋም ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ተይዟል::
·        በዋልድባ ወጣቶች ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ እንዳይደርሱ በፖሊስ ታግደዋል::
·        የማኅበረ ቅዱሳን አጥኚ ቡድን ነገ ወደ ዋልድባ ያመራል::

 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 24/2004 ዓ.ም፤ April 2/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የጎንደር ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች ጥምረትና የጥምቀት በዓል አከባበር ወጣቶች ማኅበራት ጥምረት ኮሚቴዎች፣ በማኅበረ ቅዱሳን የስድስቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት ሥራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም የጎንደር ማእከል ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ጋራ መነጋገራቸው ተሰማ፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)