March 17, 2012

ሰበር ዜና - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ አረፉ

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 8/2004 .ም፤ ማርች 17/2012/ PDF) ተወዳጁ የቅብጥ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ ሺኖዳ ሣልሳዊ በተወለዱ 88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የአገሪቱን ሬዲዮ የጠቀሰው ቢቢሲ ዘግቧል። ለእረፍታቸው ምክንያት የሆነው ምን እንደሆነ ያልተገለጸ ቢሆንም በዕድሜ አረጋዊ የኾኑት ቅዱስነታቸው  ለረዥም ጊዜ ሲታመሙ መቆየታቸው ይታወቃል። 
የግብጽ ኦርቶዶክስ ምእመናን  80 ሚልዮን የአገሪቱ ሕዝብ 10 እጅ (10%) ብቻ ሲሆኑ በአክራሪዎች በሚደርስባቸው ተደጋጋሚ አደጋ ምክንያት ፖፕ ሺኖዳ መንግሥት የበለጠ ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ሲማጠኑ ቆይተዋል።ከዚህ በፊት በደጀ ሰላም ላይ ባቀረብነው አንድ ዘገባችን ፖፑ “በልቤ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ መናገር አልችልም። ዝምታዬን እግዚአብሔር ይሰማዋል” ካሉ በኋላ ምእመናኑ ፊት ሲያነቡ ታይተዋል።  ከጻድቁ ፖፕ ከአቡነ ቄርሎስ ቀጥለው በመንበረ ማርቆስ የተሰየሙት 117ኛው ፖፕ  አቡነ  ሺኖዳ በተለይም በኢትዮጵያ ምእመናን ዘንድ በመጽሐፎቻቸው የበለጠ ታዋቂ እና ተወዳጅ ሆነዋል። ኢትዮጵያን ለመጎብኘት በመጡበትም ወቅት ሕዝቡ ከቦሌ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል እንዳደረገላቸው ይታወሳል።
የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን፤ ይደርብን፤ ለግብጽ ቤተ ክርስቲያንም የብፁዕ ወቅዱስ አቡነነ ሺኖዳን ዐይነት አባት ይተካላቸው፤ ይስጣቸው። አሜን

10 comments:

Anonymous said...

ነፍስዎን ይማርልን አባባ ሾኖዳ።
ይህ ሞት የሚሉት ለምን ያዳላል ???
እንዴት ኢትዮጵያን ልፎ ወደ ግብጽ ሄደ እውነትም ፰ኛ ሸህ ደርሶ ነው መሰለኝ እግዚአብሔር ልጆቹን እየሰብሰበ ያለው። በስሙ እየነገዱ ምድርን የሚበጠብጡትንማ ደስታቸው በመሬት ላይ ብቻ እንዲሆንላቸው ብሎ እነርሱ የምድር ኑሮ እስኪሰልቻቸው ዝም ብሎ እያያቸው ነው። ኧረ ባክህ እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አንድ በልልን !!! ?

ርብቃ ከጀርመን said...

ለግብጾች ብቻ አልነበረም አባትነታቸው ለኛም የሚያጽናና አባት ላጣነው በስብከታቸውና በሚጽፉዋቸው መጻህፍት የመከሩን ያስተማሩንና የገሰጹን የ21ኛው ክፍለዘመን ታላቅ አባት ነበሩ ለሳቸውስ እረፍት ነው ያብርሀም አምላክ ተፍሳቸውን በክብር ያሳርፍ አሜን

Anonymous said...

WHAT A BAD NEWS IS THAT? IT IS REALLY SO SAD!RIP!!!

Tenaye Araya

Yodit said...

Oh no no noooooo! OMG, what a distress! i am so very sorry
for our loss! just wanna cry loud...

Anonymous said...

Wow, Today is one of my saddest moment in my life....
As an Ethiopian orthodox church follower I am deeply saddened by the News. The POP was one of the holly men that the church has to offer. In this critical time when the Egypt churches needed the holy Father the most to hear this bad news was difficult for me. I said to the copt orthodox church people all around the world Remember God is always with you and the Blessed Virgin Mary will bring the Holy one, the anointed one to lead in the POP Shinoda foot steps
Keep on Praying and We will pray with you. God bless

Anonymous said...

I would like to express my heartfelt condolences to the late lovable His Holliness Pop Shinoda.We Ethiopians who has been benefiting from His Blessings have also lost Him.For Him is Rest with His ascendants who fell doing the righteous.

መላኩ said...

ብዙ ስቃይና በደል ያዩ አባት ነበሩ -- አምላክ ከቅዱሳን ጎን ያሰልፋቸው! በእስራኤል ላይ የነበራቸው አቋም ግን በጣም ስህተት ነበር፡ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚላቸው አልጠራጠርም። ግብጻውያን ክርስቲያን ወንድሞቻችን በርጉም ሙስሊሞች በከፋ ሁኔታ የሚበደሉበት ዘመን እየመጣ ነው።

Anonymous said...

የብጹእ አባታችን በረከት ይድረሰን! ደግ አባት ያድለን በመጣፍም በቃልም በሕይወትም የሚያስተምር

Anonymous said...

betamm tegeremalachehuu tasekalachehummmmm le ethiopia abatotochh mot telemenalachehuuu ere ebakachehu asteyayet setetsfuuu asteuluuu wey keresetena yerasewan satawek yesew mademek min yelutal abatachenen nefesachew beabreham ategeb yanurelen

Anonymous said...

Le Anonymous March 18, 2012 12:23 PM
Eney endemeselegn Tsehafiw malet yefelgut Ethiopia sayasfelegate 2 patriarks aluwate, Yehulunem leeb Seytan adenedenebachew. Yehenen betemelekete አባባ ሾኖዳ Aba Pawlosn betam bezu mekrewache neber. Tadia ya sayderege Enia abat temertew hedu, enihe abat mertew keru. Bemalet eniam legeletse ewodalhu. Tegbabane? Awo tiru.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)