March 30, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ምጥን ዘገባ (ክፍል አንድ)


·         ስብሰባ የጎንደርን ካህናትና ምእመናን እንደማይወክል ተገለጸ
·         “ዋልድባ ቅዱስ ገዳማችን ነው፤ እንዲነካ አንፈልግም፤ እኛም እንደ ክልል እነ ኣባይ ፀሃዬ ጉዳዩን የት እንዳደረሱት እንከታተላለን፤ ሁላችሁም ሄዳችኹ አይታችኹ እውነታውን ማረጋገጥ ትችላላችኹ” (አቶ አያሌው ጎበዜ፤ የክልሉ ፕሬዚደንት)።
 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 20/2004 ዓ.ም፤ ማርች 29/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ “የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት” በዋልድባ ገዳም ህልውና እና ክብር ላይ የጋረጠውን አደጋ በተመለከተ “የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ካህናትና ምእመናን የሚያነሡትን ሐሳብ ለመስማት” የሚል ስብሰባ ትንት መጋቢት 19 ቀን 2004 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ዐምባ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

የስብሰባው አዘጋጅ የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሲሆን ለተመረጡ ሰዎች በየስማቸው የተሰራጨው የጥሪ ካርድ ደግሞ በጎንደር ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ሓላፊ የተፈረመበት እና እንደ ሰርግ ካርድ “የጥሪው ካርድ እንዳይለይዎ” የሚል ማሳሰቢያም የሰፈረበት ነው፡፡
ጥሪው በአንድ በኩል የሀገረ ስብከቱን የአድባራት አስተዳዳሪዎችን፣ የሰበካ ጉባኤ አባላትን፣ የጉባኤ መመህራንና ሰባክያነ ወንጌልን አለማካተቱ በአንጻሩም በቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸው አቋም አጠራጣሪ የሆኑ ግለሰቦች ከየቀበሌው የተጠሩበት መሆኑ የስብሰባው ዓላማ ከጅምሩ ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ማድረጉ ተዘግቧል፡፡

ስብሰባው የተመራው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ ነው፡፡ ከእርሳቸውም ጋራ የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ግዛት ዐብዩ በመድረኩ የተገኙ ሲሆን ለጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሞከሩት ዋነኛው ተናጋሪ ደግሞ የስኳር ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ኣባይ ፀሃዬ ናቸው፡፡

ከጠዋቱ በ2፡30 እንደሚጀመር ቀጠሮ የተያዘለት ስብሰባ ከረፋዱ 4፡15 የተጀመረ ሲሆን እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ ከዘለቀ በኋላ እንዲህ ባሉት ስብሰባዎች ድራማዊ በሆነ መልክ የሚዘጋጁ “የጋራ አቋም መግለጫዎች” ሳይነበቡበት ተጠናቋል፡፡ የዚህም ምክንያቱ ከቤቱ የሚቀርቡ አብዛኞቹ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረክ ከሚሰጡት ምላሾች ጋራ አለመጣጣማቸው የተሳታፊዎችን ስሜት እያካረረው በመሄዱ እንደሆነ ተገልጧል፡፡

የስብሰባውን ሂደት የታዘቡ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት በገለጻ ረጅም ጊዜ የወሰዱት አቶ ኣባይ በአብዛኛው ያተኰሩት በመነኰሳቱም ይሁን በምእመኑ ባልተነሡና ደካማ በሆኑ ነጥቦች ላይ ነው - “ገዳሙ በውኃ አይጥለቀለቅም፤ ሸንኮራ አገዳ አይተከልበትም፤ ሕዝብ አይሰፍርበትም” በሚሉ ጉዳዮች፡፡ በመሆኑም ተሳታፊዎቹ አቶ ኣባይ ጥያቄያቸውን እየመለሱ እንዳልሆነ በማስገንዘብ “የገዳሙ መሬት በመንገድ ሥራ ይሁን በእርሻ ተነክቷል ወይስ አልተነካም፤ የቅዱሳን ዐፅም ተቆፍሮ ወጥቷል ወይስ አልወጣም፤ የሚፈርሱ አብያተ ክርስቲያን አሉ ወይስ የሉም?” ለሚሉት ሦስት ዐበይት ጥያቄዎች ቀጥተኛ ምላሽ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋቸዋል፡፡ ሚኒስትሩ ግን አለባብሰው ከማለፍ ውጭ የሰጡት ቀጥተኛ ምላሽ አልነበረም፡፡

ከአቶ ኣባይ ቀደም ሲል የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ጨምሮ ከደባርቅ፣ ወገራ፣ ጃናሞራ እና ከመሳሰሉት አጎራባች ወረዳዎች የተውጣጣ ልኡካን ቡድን ወደ ፕሮጀክቱ ስፍራ በመሄድ ያደረገውን ቆይታ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ቀርቦ ታይቷል፡፡ የልኡካን ቡድኑ አባላት ከተሳታፊዎች ለተነሡ ጥያቄዎችም ምላሽ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡

ከእነርሱም መካከል የጩጌ ማርያም ገዳም አበምኔት አባ ወልደ ገብርኤል እና የኮሶዬ /ወገራ/ በኣታ ለማርያሙ ካህን የሰጡት ምስክርነት ከሌሎቹ ለየት ያለ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ የኮሶዬ /ወገራ/ በኣታ ለማርያሙ ካህንምቤተ ክርስቲያን እንደሚፈርስ ተነግሮናል፤ በሚፈርሱት አብያተ ክርስቲያን ቁጥር ለእያንዳንዳቸው አንድ ሚልዮን ብር ካሳ እንሰጣችኋለን ሲሉ ሰምቻለሁ” ማለታቸው ተዘግቧል። ከሁለቱ የልኡካን ቡድኑ አባላት በተፃራሪ የጎንደር በኣታ እና የአዘዞ ሚካኤል አስተዳዳሪው አባ ብርሃነ መስቀል በዘጋቢ ፊልሙ ላይ የእሳት ጎረቤት እንጂ የውኃ ጎረቤት አይጎዳችሁም እያሉ መነኰሳቱን ሲያግባቡ ታይተዋል፡፡ ለዚህ አነጋገራቸው ከቤቱ ጃፓንን የጎዳት የውኃ ሱናሚ አይደለም ወይ? እንዴት የውኃ ጎረቤት አይጎዳም ትላለህ? የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡ 
አርእስተ ጉዳይ፡-
·         በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀረበው ‹የሀገረ ስብከቱ ልኡካን ቡድን› ዘገባ ከእውነታው ፈጽሞ የተለየ ስለ መሆኑ በስብሰባው ላይ ተጋልጧል፡፡ የልኡካን ቡድኑ አባል የነበሩ አንድ አባት በተለያዩ አካባቢዎች ከ500 ሜትር እስከ ሦስት ሰዓት መንገድ የሚሆን የገዳሙ መሬት ታርሶ መመልከታቸውን መስክረዋል፡፡
·         የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ከቀድሞ የተለየና ያልተጠበቀ አቋም ማሳየታቸው ብዙዎችን አስከፍቷልከቤተ ክህነቱና ከመንግሥት ሓላፊዎች በተደረገባቸው ጫና ሳይደረግባቸው አልቀረም ተብሏል።
·         የመንግሥት ባለሥልጣናት በማይ ፀብሪ፣ በማይ ገባ፣ በዓዲ አርቃይ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳት ላይ የሚፈጽሙትን ልዩ ጫናና ማስፈራሪያ እንዲያቆሙ ተጠይቋል፡፡ የቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳቱ በልማቱ ላይ እንደተወያዩ በኢ.ቴቪ የተላለፈውን ዘገባ ተቃውመዋል፤ ወደ ቦታው ሄጃለሁ፤ አይቻለሁ፤ ያየሁትን እናገራለሁ፤ ፊልሙ ተቆራርጦ ነው የቀረበው፡፡ ገዳማችንን ደፍራችሁታል፡፡ እዚያ መነኰሳቱን ስንጠይቃቸው ለእኛ የነገሩንገዳማችንን ደፍራችሁታል፤ ምነው በእኛ ዘመን ይህን አመጣብን ብለን እያዘንን፤ እየጸለይን፤ እያለቀስን ነው ያለነው፡፡ ጥያቄያችንን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ልከን መልስ እየጠበቅን ነው፡፡ ልማቱን ስለመደገፍ ሲጠየቁም እኛ የልማት ፀሮች አይደለንም ነው ያሉት፡፡ ነገር ግን በዓዲ አርቃይ፣ በማይ ፀብሪ፣ በማይ ገባ የቤተ ሚናስ መነኮሳትን ስታስጨንቋቸው፣ ስታስፈሯሯቸው፣ ስትጫኗቸው አይቻለሁ፡፡ የቴሌቪዥኑ ጋዜጠኛ ከቆመበት በላይ ወደ ገዳሙ እስከ 500 ሜትር ታርሶ አይቻለሁ፡፡ አባ ነፃ በሚባለው የአትክልት (ሙዝ) ስፍራ እስከ ሦስት ሰዓት የእግር መንገድ የሚሰድ ርቀት ታርሶ አይአለሁ፡፡
·         “በአባቶቻችን አፍረናል” በማለት የተናገሩ የስብሰባው ተሳታፊዎች የቡድኑን አባላት እነርሱ እንዳልመረጧቸው፣ ሊወክሏቸውም እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡
·         “በፕሮጀክቱ 50,000 ሰው የሥራ ዕድል ያገኛል፤ 5000 መኖርያ ቤቶች ይሠራሉ ብላችኋል፡፡ መነኰሳቱኮ ዋልድባ ድረስ የሄዱት ዓለምን ጥለው ጥሞናን ሽተው ነው፡፡ ታዲያ እናንተ የገዳሙን ክልል ከተማ ማድረጋችኹ አግባብ ነው ወይ?” /ከተነሡት ጥያቄዎች አንዱ/
·         ለተሳታፊዎች ጥያቄ ምላሽ ያልሰጡት አቶ ኣባይ ፀሃዬ አበው መነኰሳቱን ‹ፖሊቲከኞች› ገዳሙንም ‹የፖሊቲከኞች መሸሸጊያ› በሚል መናገራቸው በኢሕአዴግ አገዛዝ የቀጠለው ቤተ ክርስቲያንን የመናቅና መዳፈር አስተሳሰብና ተግባር አካል መሆኑ በተሰብሳቢዎቹ ተነግሯቸዋል
·         አቶ ኣባይ የዋልድባ መሬት ‹ለአፈር ምርመራ› በሚል መታረሱንና ዐፅሞችም መነሣታቸውን ያመኑ ሲሆን በገዳሙ ክልል ውስጥና ውጭ ‹ከሕዝቡ ጋራ በመነጋገር› የሚፈርሱ አብያተ ክርስቲያን እንዳሉ አስታውቀዋል፡፡
·         የጠ/ቤ/ክህነቱ ም/ዋ/ሥ/አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ውብሸት እና የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ሽሬ እንዳሥላሴ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ተስፋይ ተወልደ ወደ አዲስ አበባ ተልከው የሄዱ መነኰሳትን “መዋቅር ያልጠበቁ ሕገ ወጦች ናቸው” በማለት ዘልፈዋቸዋል፡፡
·         አቶ ኣባይንና አወያዩን አቶ አያሌው ጎበዜን ሳይቀር ደስ ያላሰኘው የአቶ ተስፋዬ ‹ውዳሴ ኢሕአዴግ› በተሰብሳቢው ተቃውሞ ተቋርጧል፡፡
·         በዕለቱ በስብሰባ አመራራቸው የተወያዮቹ መጽናኛ የሆኑት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ “ዋልድባ ቅዱስ ገዳማችን ነው፤ እንዲነካ አንፈልግም፤ እኛም እንደ ክልል እነ ኣባይ ፀሃዬ ጉዳዩን የት እንዳደረሱት እንከታተላለን፤ ሁላችሁም ሄዳችኹ አይታችኹ እውነታውን ማረጋገጥ ትችላላችኹ፤” በማለት ተሳታፊዎች ያነሷቸው ‹ስጋቶች› በምክክር እና ውይይት መፈታት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
·         ቅዱስ ሲኖዶስ የራሱን አጣሪ ቡድን ልኰ የገዳሙን ህልውና የሚያስጠብቅ አቋም እንዲወስድ፤ መንፈሳውያን ማኅበራት ትክክለኛውን መረጃ ይዘው ገዳሙን የማስጠበቅ እንቀስቃሴ እንዲያካሂዱ፣ መንግሥትም ቀስ በቀስ በይፋ እያመነ የመጣቸውን መረጃዎች በተሟላ ይዘታቸው (እውነታቸው) ለሕዝቡ ግልጽ በማድረግ ተነጋግሮ የማስማሚያ ነጥብ እንዲያቀርብ ተጠይቋል፡፡

በተያያዘ ጉዳይ፦
·         ማኅበረ ቅዱሳን ወደ ዋልድባ ገዳም አምርቶ የፕሮጀክቱን ተጽዕኖ በመገምገም ይፋዊ ሪፖርት የሚያቀርብ የባለሞያዎች ቡድን ለመላክ መዘጋጀቱ እየተነገረ ነው፡፡
·         መጋቢት 27 ቀን በዋልድባ አብረንታንት መድኃኔዓለም  ክብረ በዓል (በዓለ ንግሥ) ነው፡፡ በርካታ የጎንደር ከተማ ምእመን በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከነገ መጋቢት 21 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስፍራው መጓዝ ይጀምራል -  አንድም ለአክብሮ በዓል በሌላም በኩል ለገዳሙ ያለውን አለኝታ ለመግለጽ፡፡ ጉዞው ከጎንደር እስከ ዓዲ አርቃይ በተሽከርካሪ ከዚያ በኋላ የ18 ሰዓታት የእግር መንገድ ነው፡፡
·         “ዋልድባ ዓለም አቀፍ ገዳማችን ነው፤ የትግሬው ወይም የአማራው ብቻ አይደለም !!” (ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ አንድ የዞኑ የደኅንነት መኰንን ዋልድባ በትግራይ ክልል የሚገኝ በመሆኑ በልማቱ ላይ ጥያቄ ማንሣት እንደማይችሉ ለተናገራቸው ቃል የመለሱለት)

የአርእስተ ጉዳዮቹ ዝርዝር እንደረሰልን የምናቀርብ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡

16 comments:

Anonymous said...

An'd andu ayinebebim, This article is /post/ is almost unreadable. Please repost it again.It might Help.

TEHA

Anonymous said...

AYi Anchi hager .. endawu mechereshash nafekegne
Amlak hoye ethiopian tebiki

Anonymous said...

I know Ato Abay will not try to change his mind because he has the mind of TPLF. Ato Ayalew Gubeze is better but I afraid he does not have the power. MK's plan is good but the politicians may not give ears. The best option is to keep on the pressure from christians!!!

Anonymous said...

መነግሥት በየውይይት መድረኩ ባለፉት ሥርዓቶች ተጠቃሚ የነበረ ሃይማኖት ነው እያለ ኦርቶዶክሳውያንን አንገት ለማስደፋት በማያገባውና በማያውቀው ስዘባርቅ ከነበረው ይሀንንም አቶ ተፈራ ዋልዋ በ1997 ዓ/ም ቤተክርሰቲያንን በይፋ ከተሳደቡበት ፡ከወያኔ መሥራች አንዱ የሆኑት አረጋዊ በርሔ የወያኔን ታሪክ በጻፉበት ወያኔ ትግራይን ለመገንጠል የኢትዮጵያን ሕዝብ በብዙ ነገር አስተሳስራ ያለችውንና ብሔራዊ መንፈስን የሚታስተምረውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በቅድሚያ ማዳከም እንዳለበት አቅዋም ይዞ መነሳቱን (A Political History of the Tigray People’s Liberation Front ፡ Neutralizing the Church and Mobilizing Muslims፡“A combination of factors made relations between TPLF and the EOTC church difficult …the church taught its followers to respect their allegiance to the Ethiopian state and was, in effect , a school for national consciousness, using national symbols such as the flag in all religious and social events. No church ever conducted major ceremonies without hoisting the Ethiopian flag – an act also regularly observed …’ page 244

“The pragmatic TPLF understood the church’s role in village social life and its support for the unity of the country .It also understood a possible alliance between the Church with its forces that stood against socialism and nationalization of the land as well as separatism .The church was viewed as a force standing in the way of TPLF. …there was no doubt that it wanted to subordinate the church to its cause” page 245) እና በተለያዩ አካላት በቤተክርስቲያን የሚፈጸመውን ተጽእኖ ስናይ ይህ ሁሉ የሚፈጸመው በመንግሥት ይሁንታ እነደሆነ እናረጋግጣለን፡፡

በዝህም ብቻም አያበቃም የወያኔ ሤራ ፡፡ቤተክርስቲያንን ለማዳከም ይህን አጀነዳ እነደያዙ በቤተክርስቲያን መዋቅር በቀጥታ መሳተፍም ጀምረዋል፡፡

በቅርቡ የአድዋ ድል የትግራይ ሕዝብ ብቻ እንደ ነበረ ጽፈው በትግራይ ክልል ወጣቱ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ያለው አመለካከት እንድለወጥ(To Brainwash) ያሰራጩትንና ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቁትን ገብረ ኪዳን ደስታን መጥቀስ ይቻላል::

እነደ ጩሉሌ ነጣቂ አስመሳይ መነኮሳት መብዛታቸው ከተሐዲሶ መናፍቃን ባሻገር የዚህ ሤራ አካል ሳይሆን አይቀርም::ሰሞኑን ዋልዲባ ገዳምን አስመልክቶ የተሰጠው የቤተክህነቱና የቤተመንግሥቱ መግለጫ “የዐይጥ ምስክር ድንቢጥ” ዓይነትና ከእውነት የራቀ የሆነው አንዱ የዚህ ሤራ ይመስለኛል::

እስኪ አቡነ ጳውሎስና ጋሻ ጀግሬዎቻቸው እስካሁን ከቤተክርስቲያን የዘረፉትን ገንዘብ ገምቱ: የት እየሄደ ነው ?

Anonymous said...

እንደ እኔ እምነት በተለያየ ሚዲያ አውርተን ወዲያው ዝም ማለታችንና ተገቢውን ጥያቄ በተገቢ መልክ ለመጠየቅ አለመንቀሳቀሳችን ለመንግ ሥትና ለአጽራረ ቤተክርስቲያን የልብ ልብ እንድሰማቸው ያደረገ ይመስለኛል:: እንዲህ አውርተን ፈሪዎች መሆናችንን ከሚናስመሰክር ዝም ብንል ይሻላል ::ምክንያቱም ዝም ብንል ቢያንስ ከሰሙ ………….. እየተባለ እንዲህ በንቀትና በግልጽ በድፍረትም በቤተክርስቲያን አይዘበትም ነበረ::ከተነጋገርን ከሰማን ካየን ወደ መፍትሔ እንሂድ ወይ አናውራ ዝም እንበል::አሁን የቤቱ ግድግዳው ተበልቶ አልቆአል ::የቀረው እያንዳንዳችንን ማተብ በጥስ ሃይማኖት ለውጥ የሚል አዋጅ የጣሪያው መቃጠል ነው፡፡

ስለዚህ ብንዘገይም የባሰ ሳይመጣ አሁን ወደ መፍትሔ እንሂድ:-

1) አባቶቻችን ካህናት ይህን ሁሉ ጥፋት ላያዉቁ ይችላሉ፡ ቢያዉቁም አቡነ ጳውሎስና መንግሥት እጅና ጉዋንት ስለሆኑ (ለመንግሥት ህልውና ቅድሚያ ስለሚሰጡ) ካህናቱም በብዛት ቤተሰብአቸውን የሚመሩት ከቤተክርሰቲያን ከሚያገኙት ገቢ ስለሆነ ከፊት መሆን ልከብዳቸው ይችላል::

2) ስለዚህ በሰበካ ጉባኤ በሰንበት ትምህርት ቤት በአባልነት ያለን በተላይም ዲያቆናት እንቀሳቀስ ::

3) እስካሁን ያዩትና የሰሙት ከበቂ በላይ ቢሆንም መረጃ ለመእመናን በማዳረስ ረገድ በርትተን እንሥራ: ይህንንም መረጃ በቀላሉ ልዳረስ በሚችልባቸው አከባቢዎች በተለይም በዩኒቨርሲቲዎች በኮልጆች በቴክኒክና ሙያ ተቁዋማት እናተኩር ::

ነገሩ ወደ ውጤት ከመምጣቱ በፊት ለማስፈራራት እንዳይጠቀሙት ጥያቄያችንን በአንድነት እስከምናቀርብበት ቀን ድረስ በጥንቃቄ እንሥራ ይህንንም እስካሁን በቤተክርስቲያን ላይ በመንግሥት በአጽራረ ቤተክርስቲያን የደረሱ ግፎችን በመረጃ በማጠናከርና በመላክ የሰሙትም እንዲሰሙና የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጅነት ግድታቸውን እንድወጡ በማሳሰብ በfacebook እናስታውቅ በemail እንላክ::

በቤተከርስቲያን ላይ እስካሁን የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን የጥፋት ሤራ በመረጃና በዝርዝረ በማስቀመጥ መፍትሔ በፍጥነት እንድሰጥባቸው ቢያንስ ፈርማ ለማሰባሰብ እንቀሳቀስ፡፡ይሀንንም በሰበካ ጉባኤ በሰንበት ትምህርት ቤት እንጀምር፡፡ ምክንያቱም የሰበካ ጉባኤ አባል ያልሆነ ቤተሰብ የለምና፡፡ የሰበካ ጉባኤ አመራር አባላትም ከምእመናን ከሰንበት ትምህርት ቤት ከካህናት የተወጣጡ ናቸውና ፡፡

ይህን ስንል ፖለቲካ የሚመስላቸው ልኖሩ ይችላሉ: በእርግጥ በፖለቲካው ዐይን ካዩ ፖለቲካ ልሆንባቸውም ይችላል::

እሱማ ዐራት ኪሎ ጠቅላይ ቤተክህነት ለተለያየ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ትንሽ ብዛት ያለው ሰው ከተገኘ ሁሉ ለመንግሥት ፖለቲካ መምሰል ከጀመረ ቆይቶአል::“.....

ታስታ

ውቅ ከደረቱዋ ትታጠቅ’” እንዲሉ :: እዉነት ፍትሕ ካለ ይህን ያህል ምን አስፈረው: መንግሥትን!?

መንግሥት መጣብን እነጂ እኛ አልሄድንበት::

ከጸሎት ባሻገር ሰማዕትነትን

እነደ አግባቡ መክፈል ተገቢ ባይሆን ኖሮማ የዋልድባ መነኮሳት”…….. የሚትሠሩት በእኛ መቃብር ላይ ነው::” በማለት ስብሰባ ረግጠው ባልወጡም ነበር ::መቼም ከመነኮሳቱ በላይ መንፈሳዉያን ነን እንደማንል እርግጠኛ ነኝ::

እኛ በፋሽስት ጣሊያን ጊዜ የነበርን ቢሆን “አይ እግዚአብሔር ከሰማይ መቅሰፍት አውርዶ እስኪያጠፋቸወ ዝም እንበል” ሳንል አንቀርም ::“ እግዚኦ እግዚእነ ኢታርዕየነ ሙስናሃ ለቤተክርስቲያን”

Anonymous said...

በቃ
በዚያ ሰሞን ቤተ ክህነቱ ውስጥ ያሉ ጉዶች “እሳት በመንደርም ይነሳል በቤተ ክርስቲያንም ይነሳል፡፡ ለምን የቤተ ክርስቲያን ሲሆን ይገናል፡፡” በማለት በድፍረት እና በንቀት ነግረውናል፡፡ ልብ ይስጣቸው ከማለት በቀር ሌላ ምንም ምን የምለው ነገር የለም፡፡ ነገር ግን በዚህ አጋጣሚ አለቅላቂነታቸውን ለማረጋገጥ የሞከሩት የገዥው ፓርቲ በቀቀን በመሆንና ጋሻ ጃግሬነታቸውን ባሳየ መልኩ መሆኑ አሳዛኝ ነው፡፡ ይህም ውስጥ ያሉትን ጉዶች በገሃድ ስላሳያን በጣም በጣም እናመሰግናለን፡፡
ሌላው ልቀበለው እየከበደኝ እና እያስቸገረኝ የመጣ አባይ ጸሐዮ የተባሉ ስማቸው እና ምግባራቸው ያልተገናኘ ሰው ጉዳይ ነው፡፡ ድፍረታቸው እጅግ በጣም ጣራ ስለነካ ዋልድባ ገዳም ውስጥ ፖለቲከኞች ተሰግስገዋ አሉ፡፡ እዚህ ላይ አቶ አባይ አንድ ነገርን አስታወሱኝ፡፡ በትጥቅ ትግላቸው ወቅት የህውሓት ሰዎች ይከተሏቸው ከነበሩ ስልቶች አንዱ የቆሎ ተማሪ መምሰል፣ ቄስ መምሰል፣ እብድ መምሰል ወዘተ ነበሩ፡፡ እና እነሱ አድርገውት ያለፉትን ሌላውም የሚያደርገው ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ድፈረታቸውም የመጣው ከሌላ ከምንም አይደለም ከጥንት አብሯቸው ከነበረው የድፍረት ተሞክሮ ነው፡፡ ሳይሆኑ ይመስሉ ስለነበር፡፡
አንድ ነገር መናገር እፈልጋለሁ፡፡ ለእኔ ሐይማኖቴ ሀገሬ ናት፡፡ ሀገሬም ሐይማኖቴ ናት፡፡ እና በእነዚህ በሁለቱ በኩል የመጣን አካል ተው ከማለት አልቆጠብም፡፡ አሁንም እላለሁ አቶ አባይ አምባገነንነትዎን እዛው የለመዱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ፡፡ እዛው ጋዜጦች ላይ፡፡ አሁን የመጡት እራሰዎን ወደ እሚበላ መንገድ እና እሳት ነው፡፡ አሁን የበቃ ይመስለኛል፡፡ ሐይማኖታችንን በገሀድ መሳደቡን ከዛሬ ነገ ትተዋላችሁ እያልን ጠበቅን እንጅ በትዕግስት ሞተን አይደለም፡፡ በ1997 ምንም የማያውቁት አቶ ተፈራ በገሀድ ተሳደቡ ዝም አልን፡፡ ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ በመጽሀፍ ሰደበን ዝም አልን፡፡ አሁን ግን በቃ…. ከዚህ በላይ መታገስ በአንገት ላይ ሰይፍ ማስዞር ስለሆነ በቃ እንላለን፡፡ እጅግ በጣም በዛ….. የግፍ ጽዋው ሞልቶ ፈሰሰ….
ከዚህ በኋላ ስለ ዋልድባ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን አጠቃለይ ሐይማኖታችንን በተመለከተ እጁን እንዲያነሳ የምናሳስብበት ጊዜው አሁን ነው፡፡ ከዚህ በላይ ምን ያድርጉን፡፡ አይናችን እያየ እያዩ ቤተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ ፍትህ የለም፡፡ የገዳማት ደኖች ተቃጠሉ መልስ የለም፡፡ ሁለት ታላላቅ ትምህርት ቤቶች ተቃጠሉ ምክንያቱ አልታወቀም…. ወዘተ… ከዚህ በላይ ምን ያድርጉ…. እንዳለ በጅምላ እስኪያቃጥሉን እንጠብቅ…. እንዴት ነው ነገሩ…. በቃ ማለት ያለብን አሁን ነው፡፡ እጅግ በጣም በዛ… ስለዚህ በቃ…. በቃ…. በቃ…..

Anonymous said...

I hope Ato Ayalew will keep his good fame. He does have a good leadership for the people of Amhara.

Gebre Z Cape said...

Thanks for always updating us. The time is media supported by evidences. Try your best to find evidences where ever is important. I am looking in to your detail news for you "ariste Zena". Specifically, አቶ ኣባይ የዋልድባ መሬት ‹ለአፈር ምርመራ› በሚል መታረሱንና ዐፅሞችም መነሣታቸውን ያመኑ ሲሆን በገዳሙ ክልል ውስጥና ውጭ ‹ከሕዝቡ ጋራ በመነጋገር› የሚፈርሱ አብያተ ክርስቲያን እንዳሉ አስታውቀዋል፡፡

I am telling you all Orthodox Christians, this is the right time for us to fight for our church. I can see our government leaders are telling lies here and there. We should keep pressuring them so that they can act on our biggest issues immediately.

Amilak yiradan engi min enilalen.

Anonymous said...

ገብር ኄር
እኮ ስትነግሩን ገብርኄር ብላችሁ
ደግ መሥራትን ጫፉን አስይዛችሁ
የመልካም እረኛ ምሳሌ ሆናችሁ
እምነት ካለ ምግባር ባዶ ነዉ እያላችሁ
እኛን የመራችሁ፤
ሰላሳ፣ሰድሳ ፣መቶ እንድናፈራ
ያሳደጋችሁን በወንጌል አዝመራ
መክሊቱ የት አለ?
እንድታተርፉበት አበዉ የሰጧችሁ
ከግበበ ምድር ፣ዋሻ ሥር ሆነዉ አደራ ያሏችሁ።
ግብሩ ወዴት ጠፋ እናንተስ የት ናችሁ?
ዋልድባ ሲነጠቅ ዝቋላ ሲቃጠል ከቶ ያረመማችሁ።

መልካሙ ዕረኛ የበጎች ጠባቂ
ዝም የማይለዉ ሲመጣ ነጣቂ
ከመቅደሱ ገርፎ ዉጡ ሂዱ ያላቸዉ
ነጋድያን ፣ለዋጮችን፣ ወንበዴዎችን ነዉ።

እና በዋልድባ ዛሬ የተዘመተዉ
ለስኳር ማምረቻ ቦታ ጠፍቷቸዉ ነዉ?
ወይስ የ1519 ዓመት ታሪክ ከስኳር አንሶ ነዉ:፡
በምዕራቡ ዓለም፣ በምድረ አፈረነጅ በሰለጠኑት
አንዲት ተራ ጎጆ መቶ ዓመት ከሞላት
ከቅርስ ተዘግባ ጥበቃ ሲሰጣት
በእኛ ግን … የታሪክ ማሕደር ቅርስ የሚወድምበት
ስኳር ሆኖ መጣ… አደራ በሊታ ዳኛ በቅሎበት።


መጽሐፉም ታጠፈ ካህኑም አረመመ
በስኳር በሽታ ሊቁ ሁሉ ታመመ።
ኢትዮጵያዊ ክብሩን ታሪኩን ለዉጦ
የባዕድ ቀላዉጦ ማንነቱን ሸጦ
እየሞተ ይኖራል፤ እየሄደ ሳይሄድ
አንጀቱን ታቅፎ እየታከክ የግድ።
የዘመኑ ትዉልድ አረም ያበቀለ
ለሥጋዉ አድልቶ ከዐላዉያን ነገሥታት ብርክ ሥር ዋለ
ሀገረ ክርስቶስን ተዋህዶን ጣለ።

እስኪ ይጠየቅ ተጠየቁና እንጠይቅ
ዬት ነዉ የበቀለዉ እንዲህ ያለ ትዉልድ
እንዲህ የጠየመ ሀገሩን የማያዉቅ።
ለአንዲት ኩርማን እንጀራ ክብራችን ጎድፎ ሀገር ከምትወድቅ
ይበጠር፣ ይወቀጥ፣ ይፈጭ፣ ይሰለቅ
ፍሬዉ ከገለባ ተለይቶ ይታወቅ።
የዋልድባ መነኮሳት እግዚአብሔር ያጥናችሁ
የአክሊለ ሦኩ ምሥጢር የገባችሁ።
ዛሬም
የአክሊለ ሦኩን ክብር የተጎናጸፋችሁ
የክርስቶስን መስቀል በእጅ የያዛችሁ
ከልብ የሆነ ፍቅሩን ይስጣችሁ::
እንደ ጥንቶቹ አበዉ ወኔ ያድላችሁ።
እንደ አንዲት ተዋህዶ አንድ አካል ያድርጋችሁ።
ከዐቢይ ጾም ሰናብት አንዱ/ ገብር ኄር ነዉና
መክሊቱን ቀብራችሁ እንዳትሆኑ ወና
ትጉና አትጉን እንደ ትናንቶቹ ዛሬም እንደገና።

Anonymous said...

አባ ጳውሎስ ከእውነተኛው የቤተክስቲያን አባት ከአቡነ ሸኑዳ ሃዋርያዊና የወንጌላዊነት ስራና ህይወት
ምነው ትንስ ቢማሩ
ከአቡነ ሸኑዳ ገዳማት በማዳበር በመንከባከብ እራሳቸውም በየጊዜው በገዳማት ለሱባዔ ለጸሎት ብዙ ግዜ
ያሳልፉ ነበር
በግብፅ ቤተ ክርስቲያን አንድ ሰው ክህነት እንደተቀበለ ወደ ገዳም ገብቶ ክህነቱ እንደ ሃዋርያት የተቀደሰ እንዲሆን አገልግሎቱ እንዲቃና እንዲባረክ ለ40 ቀናት በሱባዔ በጸሎት ይወሰናል ከዛ በተጨማሪ በየጊዜው ገዳም ገብቶ ክህነቱ ያበረክታል እነአባ ጳውሎስ ገዳማትን ማዳበር መንከባከብ ሳይሆን አባቶቻችን የመሰረቱት ሲዳከም ሲወድቅ ቤተ መንግስት ሆነው በድሎት ያፍዋጫሉ

Tesfa said...

I appreciate Dejeselam's effort on this. Those Meamenans who spoke the truth, God bless you. May God initiate our fathers heart to stand up for the church and speak out the way that favours the church, not temporary politicians. May God give EPRDF the heart and ears to listen to the people and refrain from deadful mind set. AMEN

lamelame europe said...

yamaderegoten ayawekomena yekere balachawe.

Anonymous said...

ጊዜው የሰማዕትነት ነው፣ ጾሙ እስኪያልቅ እንጸልይበትና ወደእርምጃ እንገባለን። ወይ እኛ ወይ ኢህአዴግ አንዳችን እናሸንፋለን። መቼም ገድሎ አይጨርሰን። ደም መጠጣት የለመዱ ስለሆኑ እነዚህ ሰዎች በጉልበት ካልሆነ በውይይት አይገባቸውምና.....

Anonymous said...

kezih belay wurdet bewunu ale? Christianu hizib min eyetebeqin new? lemin aninesam?

20 amet mulu betechristianachinin adakemuat. Ahun degmo wanaw lay metubin.

Min eskibal new minitebiqew?

asbet dngl said...

ጊዜው የሰማዕትነት ነው፣ ጾሙ እስኪያልቅ እንጸልይበትና ወደእርምጃ እንገባለን። ወይ እኛ ወይ ኢህአዴግ አንዳችን እናሸንፋለን። መቼም ገድሎ አይጨርሰን። ደም መጠጣት የለመዱ ስለሆኑ እነዚህ ሰዎች በጉልበት ካልሆነ በውይይት አይገባቸውምና..... ይህ አባባል እውን ይሆን ይሆን? አዎ አንድ ቀን እውን ነው:: ለመሆኑ አንድ የሃይማኖት አባት መስቀል ይዞ ተነሣ ምእመን ለማተብህ ለሃይማኖትህ የሚል እንዴት ይጥፋ ምን እስክንሆን ይሆን የሚጠብቁን ያለ?? ይገርማል:: ዲ/ዳንኤል ክብረት ትምህርት ላይ "እግዚአብሔር ሰው አለው"ሲል ያስተማረውን በማሰብ᎒ ከእለት ተእለት ጾለቴ እንዲህ ብየ እጸልይ አለሁ᎓ አባት አባት ሆይ እባክህ ይህን ቀን እሩቅ አታርገው:: ለዚች አገርና ለዚህ ምእመን ለሐይማኖታችን በአንድ ልብና በቀና መንፈስ የሚያስብ በፍጥነ ላክላት ። አሜን

Aresema said...

የቅዱሳን አምላክ ይታደገን ከአሁን በሗላ ጥሩ ነገር የምንሰማው
የፈረደበት ማህመረ ቅዱሳን(የቁርጥቀን ለጆቿ) የሚያቀርብልን ብቻነው
ምንም አይነት ነገር ቢመጣ በናት ቤ/ክ/ቲ ያን ቀልድ የማያውቅ
ታላቁ አርበኛ ምንግዚም ማህበረ ቅዱሳን የቅድሳን አምላክ ይጠብቃቸው
ቸር ወሬ ያሰማን አሚን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)