March 19, 2012

ስለ ዝቋላ ገዳም አሁን የደረስንበት … የዝቋላ ገዳም ቃጠሎ ግራ አጋቢ (ተኣምራዊ?) ትዕይንት እየታየበት ነው


 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 10/2004 ዓ.ም፤ ማርች 19/2012/ PDF)፦  
·         እሳቱ በአንድ አካባቢ ኀይሉ ሲቀንስ/ሲገታ በሌላ ሥፍራ ድንገት እየተቀሰቀሰ የመከላከሉን ጥረት አድካሚና ግራ አጋቢ አድርጎታል፡፡
·         “በምዕራብ ስናጠፋው በምሥራቅ እየዞረ፣ በምሥራቅ ስናጠፋው በምዕራብ እየዞረ፣ በተለይም ዐርብ ረቡዕ በሚባለው የተራራው ገጽ በኩል፣ ጠበል ሜዳን (ጠበሉ የሚገኝበትን ጥቅጥቅ ያለ ጫካ) እየከበበ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከገዳሙ በማእከላዊ ግምት ከ300 - 400 ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡”
·         በእሳት አጥፊ አውሮፕላን ወይም ሄሊኮፕተር በሚረጭ ኬሚካል ካልሆነ በቀር ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ ባፈር በቅጠሉ በሚደረገው የነፍስ ወከፍ መከላከል ጥረት ጨርሶ ሊጠፋ ወይም መጥፋቱ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡
·         እሳቱ ጠበሉ ወደሚገኝበት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ከገባ ገዳሙ የነበር ታሪክ ይሆናል፡፡
·    የተወሰኑ የአየር ኀይል እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ምእመናኑና ገዳማውያኑ ከሚያደርጉት ውጭ የተለየ መከላከል ሊያደርጉ አልቻሉም፡፡
·         የውኃ እጥረት እና የተራራው አቀበትነት ትግሉን አስቸጋሪ አድርጎታል።
·         ዛሬ ቀን ላይ በሦስት መኪኖች ከአዲስ አበባ ተጉዘው ከስፍራው በመድረስ በተለይም እሳቱ አስቀድሞ በተነሣበት ምሥራቃዊ አቅጣጫ (አዱላላ) ጥረት ሲያደርጉ ያመሹት ቁጥራቸው እስከ 300 የሚገምቱ በበጎ ፈቃድ የተሰበሰቡ የሰንበት ት/ቤት፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እና በተለይም የአውቶቡስ ተራ አካባቢ ወጣቶች ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ ናቸው፡፡ ወጣቶቹ፣ “ቃጠሎው በአንድ ቦታ ኀይሉ ሲቀንስ/ሲገታ ባልታሰበ ሌላ አቅጣጫ ድንገት የመቀስቀስ ግራ አጋቢ እና ተኣምራዊ ጠባይዕ ያለው ነው፤” ብለዋል፡፡
·         የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ለመንግሥት ደብዳቤ መጻፉ ተሰምቷል፡፡ ደብዳቤው ቃጠሎውን ለመከላከል መንግሥት እገዛ እንዲያደርግና መንሥኤው እንዲጠና የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡
·         ይህ በእንዲህ እንዳለ በጥንታውያን ገዳሞቻችን ህልውና እና ክብር ላይ እየተጋረጠ በሚገኘው አደጋ በቂ ወይም ምንም ጥረት እንዳላደረጉ እየተወቀሱ የሚገኙት ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ነገ፣ መጋቢት 11 ቀን 2004 ዓ.ም፣ በይፋ እንደሚፈጸም በሚጠበቀው የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን 117ኛ ፖፕ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሲኖዳ የቀብር ሥነ ሥርዐት ላይ ለመገኘት ዛሬ ማምሻውን ወደ ግብጽ እንደሚጓዙ ተዘግቧል፡፡ ከፓትርያኩ ጋራ አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሌሎች ሁለት የፓትርያኩ ፕሮቶኮል ሰዎች አብረዋቸው ይጓዛሉ፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን

አሜን


4 comments:

Ewunet Tenagari said...

Does The Ethiopian Orthodox Church have Synod? patriarch? Arch Bishops? Administration? Organizations? Sad! Walidiba is being ploughed,Asebot forest burnt,now The Monastry of Ziqual is being threatened by conflagration of its forest,many Other Churches were burnt to ash,Christians were slaughtered and shot to death,do we really haveSynod? patriarch? Arch Bishops? Administration? Organizations? Sad!

Anonymous said...

Thanks to mahibere kidusan we are all made cowards. While people who do not care about the church head the church and embezzel its property, we keep quite. The only solution this time is revolution against the so called 'patriarch' more appropriately the beyonce guide. He is fast to make visites abroad but is incapable and not willing to do any thing at home.His attendance on funeral of his hollines popshinoda seems simply window dressing. Because he has no unity with pope shinoda. they are entirly different personalities. Any way late him go and see how egyptians love their father.

wub said...

Egziabher hoy mihretihn laklin.

Anonymous said...

This is so sad!!! Amlak hoy, ante kehulu belay neh, Bante hulu yechalale!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)