March 23, 2012

“እሳት በመንደርም ይነሣል፤ በቤተ ክርስቲያን ሲሆን ለምን ይገናል?” (የጠ/ ቤተ ክህነቱ መግለጫ)


(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 14/2004 ዓ.ም፤ ማርች 23/2012. READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ሁሉም ሓላፊዎች በዋልድባ ገዳማት፣ በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአባ ሳሙኤል ገዳም እና በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከተፈጠረው ችግር ጋራ በተያያዘ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምላሽ ተመጣጣኝና ፈጣን እንዳልሆነ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ላይ የሚሰነዘረውን ወቀሳ በማጣጣል አስተባብለዋል፡፡


ንት ከቀትር በኋላ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአስተዳደር አዳራሽ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው የተመራው በምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ የኋላ እሸት ነው፡፡ ከእርሳቸውም ጋራ የአጣሪ ቡድን አባላት በመሆን ወደ ዋልድባ እና ዝቋላ የተጓዙት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ እና የአስተዳደር መምሪያ ሓላፊው ቀሲስ ዮሐንስ ገብረ መስቀል፤ ወደ አሰቦት ሄደው የነበሩት የካህናት አስተዳደር መምሪያ ሓላፊው መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም እና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ምክትል ሓላፊ ሊቀ ኅሩያን ዳዊት ታደሰ በመግለጫው ላይ ዘገባዎቻቸውን አቅርበዋል፤ ለጥያቄዎችም ምላሽ ለመስጠት ሞክረዋል፡፡

“የምንመሰክርላችሁ ያየነውን ነው” ያሉት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች በዋልድባ ገዳማት ጉዳይ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናትና የገዳሙ ማኅበረሰብ ጋራ ከተደረገው ውይይትና በመስክ ከተመለከቱት ‹እውነታ› በመነሣት “ልማቱ በገዳሙ ክልል እንደማይካሄድና ገዳሙን እንደማይነካ አረጋግጠናል፤ ልማቱን እንደ ስጋት የሚያራግቡት ገዳሙን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግና ሕዝበ ክርስቲያኑን የማደናገር ዓላማ ያላቸው መነኰሳት ናቸው፤” ብለዋል፡፡ ይልቁንስ “ግድቡ ለገዳሙ ልማት ዕድል /Opportunity/ በመሆኑ የገዳማት አስተዳደሩ በዚህ ዙሪያ መሥራት አለበት፤” የሚል ማሳሰቢያም ሰጥተዋል፡፡

በብዙ ተፋልሶዎች በተሞላውና ለጋዜጠኞች አሰልቺ በነበረው በዚሁ ጋዜጣዊ ጉባኤ “የዋልድባ ገዳም ትውፊቱን ጠብቆ መሄድ አለበት፤” ያሉት ሓላፊዎቹ ከገዳማዊ ሥርዐቱና ትውፊት ጋራ የሚጋጩ ምላሾችን ሲሰጡ ተስተውለዋል፡፡ ‹ልማቱ› ለገዳሙ ዕድል ስለመሆኑ ባብራሩበት ምላሻቸው፡- “ግድቡ ገዳሙን የመክበብ ቅርጽ አለው፤ ይህም የግድቡን ውኃ ለመጠቀም ያስችለዋል፤ በዚህም የዓሣ ርባታና መስኖ ልማት ያካሂዳል፤” ብለዋል፡፡

ከዘላቂ ሥነ ልማት ኀልዮት አኳያ በቂ ወይም ትክክለኛ ትንተና ያልተሠራበት የስኳር ልማቱ ግዙፍነት የአካባቢውን ተፈጥሯዊ ገጽታ፣ ማኅበረ - ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በመሠረቱ በመለወጥ የሚፈጥረው ግዙፍ የከተሜነት ተጽዕኖ ከገዳማውያኑ ጥብቅ የምንኩስና ሥርዐትና ትውፊት ጋራ የዕሴት ግጭት እንደሚፈጥር የገባቸው መነኰሳቱ ግን በደብዳቤያቸው እንደገለጹት፣ በብዙኀን መገናኛም ቀርበው እንደተናገሩት በመንግሥትም ይሁን በቤተ ክህነቱ መግለጫ እንደማይስማሙ ነው - “የተቀደሰችው የዋልድባ ገዳም ኀጢአት የማይሻገርባት፣ ዘር የማይዘራባት፣ እህል የማይበላባት ናት፡፡”

በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች መግለጫ መሠረት በ‹ልማቱ› ምክንያት የሚነሡት አብያተ ክርስቲያን ቁጥርም ሁለት መሆኑ ተገልጧል፡፡ እኒህም ቢሆኑ የገጠር አብያተ ክርስቲያን እንጂ የገዳሙ አካላት አይደሉም፡፡ በአንጻሩ በመንግሥት ሳይቀር የተነገረውና በገዳማውያኑ መግለጫ የተቀመጡት አብያተ ክርስቲያን ቁጥር አራት ነው፡፡ እኒህ አብያተ ክርስቲያን ምእመኑ ከቦታው ቃል ኪዳን የተነሣ የሚሰጣቸው ከፍተኛ መንፈሳዊ ዋጋ በሓላፊዎቹ መግለጫ ውስጥ ተገቢው ቦታ አልተሰጠውም ወይም አልገባቸውም፡፡ ከጀርመን ድምጽ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉ አንድ የመንግሥት ሐላፊ “ተራ አብያተ ክርስቲያናት” በሚል ሲገልጿቸው እንደተሰሙት ማለት ነው።

የዋልድባ ገዳማትን የመጀመሪያ ዜና ከደጀ ሰላም በማግኘት ወደማጣራቱ መግባታቸውን ቢናገሩም ደጀ ሰላምን ጨምሮ፣ የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮን፣ የጀርመን ድምፅ ሬዲዮንና የማኅበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣን በ‹አራጋቢነት› እና በ‹ማስጮኽ› ወንጅለዋል፡፡ በምእመናኑ ‹ይግባኝ› የተባለባቸው ሚዲያዎቹ “እነርሱ ናቸው የቤተ ክርስቲያን አሳቢዎች!!” በሚልም ተላግጦባቸዋል፡፡

ሓላፊዎቹ አቤቱታውን ለማቅረብ በመላው የገዳሙ ማኅበር ስምምነት ተወክለው ወደ አዲስ አበባ የመጡትንና በእኒህ ሚዲያዎች ቀርበው ቃላቸውን የሰጡትን ተወካዮችንም “ማንነታቸውን ማወቅ አልቻልንም” ሲሉ ክደዋቸዋል፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች የማኅበረ መነኰሳቱን ሙሉ ስምምነት አግኝተው የተላኩትን ተወካዮች እንዲህ ካሏቸው ተነጋግረናል የሚሉት ከማን ጋራ ነው? ፈጣን መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው፡፡

ከአቤቱታ አቅራቢዎቹ አንዱ የሆኑትና “እውነተኛ መነኩሴ አይደሉም፤ በገዳሙም አይኖሩም” በሚል የተዘለፉት አባት ከቀናት በፊት ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት በሰጡት ምላሽ ግን “የእኔ ቆብ ከመርካቶ የተገዛ አይደለም፤ እውነተኛ መነኩሴ ነኝ፤ ያመነኮሱኝም አባት በገዳሙ ይገኛሉ፤ በማኅበሩ የተላኩት ጥያቄውን አድርስ ተብዬ ነው፤ ለሚዲያም የተናገርኹት ሃይማኖቴ አስገድዶኝ ነው፤” ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ይህንኑም ቃላቸውንም መምህር አባ ገብረ ክርስቶስ የተባሉ የገዳሙ የቀድሞ አበምኔት አረጋግጠዋል፡፡

በአሰቦት ገዳም በቃጠሎ የደረሰውን ጉዳት የማኅበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ “ተቃጠለ ብሎ በመሥራት አጩኾታል” ያሉት አንድ ሓላፊ “ችግሩን ለመፍታት ቀድመን ወደ ስፍራው ሄደናል፤” ብለዋል፡፡ በቅርቡ በገዳሙ መንፈሳዊ ትምህርት የሚከታተል የሰባት ዓመት ልጅ በአካባቢው ታጣቂ ጎሳዎች መገደሉንም አስታውሰዋል፡፡ ከአፋር፣ ከሶማሌ እና ከኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ጋራ በጉዳዩ ላይ መነጋገራቸውንና በአካባቢው የሚታየው የጎሳዎች የርስ-በስ ግጭት ለክልሎቹም አሳሳቢ መሆኑን ጠቅዋል፡፡

ገዳሙን ለቃጠሎም ይሁን ለእንዲህ ዐይነቱ የግፍ ግድያ ያጋለጠው ከዐፄ ኀይለ ሥላሴ ጀምሮ ለገዳሙ ይደረግ የነበረው ቋሚ የፖሊስ ጥበቃ ባለመኖሩ በመሆኑ ወደፊት የጋራ ግብረ ኀይል ተቋቁሞ ለገዳሙ ቋሚ የፖሊስ ኀይል በሚመደብበት ሁኔታ ላይ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ወርቅነህ ገበየሁ ጋራ ንግግር እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በተያያዘ ጉዳይ በዕለቱ በተሸጠው መግለጫ ላይ ነጭ ውሸት ሆኖ የተገኘውና “ለችግሮቹ ሁሉ ቀድመን ተገኝተናል” የሚለውን የቤተ ክህነቱን መቃወሚያ የሚያስተባብለው የዝቋላ ገዳምና አካባቢው እሳት በደጀ ሰላም ቀዳሚ ዜና እንደተገለጸው መጋቢት ስምንት ሳይሆን መጋቢት 10 ነው መባሉ ነው፡፡ በአሰቦት ገዳም የካቲት 20 ቀን የጀመረው ቃጠሎ ለሁለተኛ ጊዜ በተደገመበት የካቲት 23 ቀን በመድረሳቸው “ቀድመን ተገኝተናል” እንዳሉት ሁሉ!!

ቢደርሱስ ይህ ነው የሚባል የገቢ ምንጭ ከሌለው ከዚሁ ገዳም አበል መጠየቅስ በመሠረቱ አግባብ ነውን? እነርሱ አበል ከጠየቁ በበጎ ፈቃድ (በራሳቸው ወጭ) በእግርም በተሽከርካሪም ገስግሰው መጥተው ቃጠሎውን እናጠፋለን ሲሉ የእሳት እና የኢሳዎች ጥይት ራት ሊሆኑ የነበሩት ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን ምን ይከፈላቸዋል?!

ለማንኛውም የዝቋላው ቃጠሎ የተነሣበት ቀን መጋቢት 10 ነው መባሉ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሐላፊዎች መጋቢት 11 መሄዳቸውን ምክንያታዊ ለማድረግና ዘግይታችኋል ከሚለው ተወቃሽነት ለመዳን ታስቦ ይመስላል - ማስተባበያቸው ከእነርሱ ጉዞ አራት ቀናት አንሥቶ የወደመውን ሀብት ባይመልሰውም!!

የዝቋላን ቃጠሎ ለማጥፋት ለአየር ኀይሉ የሄሊኮፕተር ርዳታ ጥያቄ ማቅረባቸውን የተናገሩት ሓላፊዎቹ፡- ሄሊኮፕተሮች ለሌላ ግዳጅ መሰማራታቸው፣ ሄሊኮፕተሮቹ ቢኖሩም ለዚህ ዐይነቱ የቃጠሎ መከላከል ተግባር የተዘጋጁ አለመሆናቸውንና ቃጠሎውን ለማጥፋት የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎች አለመኖራቸውን፣ ከዚህ ቀደም የተከሠቱትን ተመሳሳይ ችግሮች ለመከላከል የተቻለው ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት በተደረገው እገዛ መሆኑን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሐላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ቃጠሎው በሰው ኀይል (በምእመናን፣ በኦሮሚያ ፖሊስ፣ በፌዴራል ፖሊስ) ርብርብ ለመከላከል እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

ማለፊያ! ቃጠሎውን አስመልክቶ ከሓላፊዎቹ ንግግር በእጅጉ የሚነካውና ጆሮን ጭው የሚያደርገው ግን “እሳት በመንደርም ይነሣል፤ በቤተ ክርስቲያን ሲሆን ለምን ይገናል?” የመባሉ እብሪት ነው !!! አንቶኒዮሙላቱ የተባሉ የፌስቡክ ፀሐፊ እንዳሉት “ታዲያ ይህ ኮሚቴ አጣሪ ወይስ አደናጋሪ” ኮሚቴ?

ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡

30 comments:

Gebre Z Cape said...

በጣም የሚያሳዝን መግለጫ ነው:: ቤተክህነት ጠበቃ ካልሆናት ማን ጠበቃ ይሆነናል? እውነቴ ነው የምላችሁ: ይህ መግለጫ አልገባኝ አልዋጥልህ እያለኝ ነው:: ሥራውን እንካን ሰርተው ምን አለ ይህ ያጋጥማል (መንደር ላይም ሳት ይነሳል): ይህ አንዳንድ ሽብር ለማስነሳት የሚፈልጉ አካላት ተጽኖ ነው ቢሉ:: ገዳሙ በእሳት እየወደመ እየታየ 3 እና 4 ቀን ዝም ብለው ቆይተው ይሄዱና, ጠፍታል ምንም ይችግር የለም ይህ ያጋጥማል ይሉናል::

ቤተክህነት እኮ ሁለት ነገሮችን እኮ ነው ያሳጣን::

1)- የራሱን እርዳታ (እሳቱን በማጥፋት)::
2)- ትክክለኛውን መረጃ ወይም መግለጫ ባለመስጠት (ከቤተ/ያን አካል የሚጠበቀውን)::

ሁለቱን እንካን ብናጣ, እንዴት ቁጥር አንድን ልናጣ እንችላለን? ቁጥር ሁለትን እንደፈለጉት ያድርጉት:: መንግስትና ሃይማኖት ካልተለያዩ በስተቀር ሁሌም ሃይማኖታዊ መግለጫዎች በፖለቲካ መቀባታቸው አይቀርም:: ይህ የሚለወጠው ግን መንግስት ሲስተካካል ወይም ሲለወጥ ነውና እዚህ ላይ ዝም ልበል::

ቤተክህነት ለቤተ/ያን ለውጥ የማይፈልግ ስለሆነ, ወይ መስተካከል ወይም መለወጥ ይኖርበታል:: እንዴት እኔ እንጃ? ምናልባትም በመጀመሪያ ግልጽ የሆነ ውይይት ማድረግ:: ካልተሳካ በሰላማዊ መንገድ በሰላማዊ ሰልፍ አቀምን ማሳወቅ::

አምላክ ቤ/ያን በትልቅ ፈተና ውስጥ ናትና እርዳን: አሜን::

Gebre Z Cape said...

በጣም የሚያሳዝን መግለጫ ነው:: ቤተክህነት ጠበቃ ካልሆናት ማን ጠበቃ ይሆነናል? እውነቴ ነው የምላችሁ: ይህ መግለጫ አልገባኝ አልዋጥልህ እያለኝ ነው:: ሥራውን እንካን ሰርተው ምን አለ ይህ ያጋጥማል (መንደር ላይም ሳት ይነሳል): ይህ አንዳንድ ሽብር ለማስነሳት የሚፈልጉ አካላት ተጽኖ ነው ቢሉ:: ገዳሙ በእሳት እየወደመ እየታየ 3 እና 4 ቀን ዝም ብለው ቆይተው ይሄዱና, ጠፍታል ምንም ይችግር የለም ይህ ያጋጥማል ይሉናል::

ቤተክህነት እኮ ሁለት ነገሮችን እኮ ነው ያሳጣን::

1)- የራሱን እርዳታ (እሳቱን በማጥፋት)::
2)- ትክክለኛውን መረጃ ወይም መግለጫ ባለመስጠት (ከቤተ/ያን አካል የሚጠበቀውን)::

ሁለቱን እንካን ብናጣ, እንዴት ቁጥር አንድን ልናጣ እንችላለን? ቁጥር ሁለትን እንደፈለጉት ያድርጉት:: መንግስትና ሃይማኖት ካልተለያዩ በስተቀር ሁሌም ሃይማኖታዊ መግለጫዎች በፖለቲካ መቀባታቸው አይቀርም:: ይህ የሚለወጠው ግን መንግስት ሲስተካካል ወይም ሲለወጥ ነውና እዚህ ላይ ዝም ልበል::

ቤተክህነት ለቤተ/ያን ለውጥ የማይፈልግ ስለሆነ, ወይ መስተካከል ወይም መለወጥ ይኖርበታል:: እንዴት እኔ እንጃ? ምናልባትም በመጀመሪያ ግልጽ የሆነ ውይይት ማድረግ:: ካልተሳካ በሰላማዊ መንገድ በሰላማዊ ሰልፍ አቀምን ማሳወቅ::

አምላክ ቤ/ያን በትልቅ ፈተና ውስጥ ናትና እርዳን: አሜን::

Orthodoxawi said...

እጅግ በጣም አሳዛኝ መግለጫ ነው
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን በቸርነቱ ይጠብቅልን

Anonymous said...

ወይ ሊቀ ህሩያን አይ የቤተ ክርስትያን ማዕረግ መርከስ ዝም ብሎ ከሜዳ የተነሳ መሀይም ሁሉ ሊቀ ምናምን ፣መላከ ምናምን ፣ መጋቤ ምናምን እየተባለ ይጠራና ይሾም ጀመረ ስለ ዳዊት ታደስ ጥራዝ ነጠቅ እዉቀት አንዴ ፖለቲከኛ አንዴ ሀይማኖተኛ በል ሲለዉ ደግሞ አራዳ የከተማ ልጅ እየሆነ ስልጣንና ገንዘብ ለማሳደድ እዚህና እዚያ ሲረግጥ እንዳልኖረ አሁን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሹመኛ ሆኖ ተግኘ፡፡
ስለ ዳዊት ታደሰ የቀድሞ ህይወት የአምቦና የጉደር ምዕመናን አሳምረን እናዉቃለን ቤተ ክርስቲያን ሲመቸዉ ሲገባ ሲጎልበት ሲወጣ እናዉቃለን፡፡
ስልጣንና ገንዘብ ፍለጋ ሲያደርገዉ የነበረዉን ሩጫና የማይፈነቅለዉ ድንጋይ ስላለመኖሩም ቀድሞ በመምህርነት ሲሰራባቸዉ የነበሩ ከገጠር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ ባኮ እንዲሁም እስክ የአምቦ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ያሉ ባልደረቦቹ ቢናገሩ ጉድ እንሰማ ነበር፡፡
በእርግጥ በ1985 ከሟቹ አቡነ ተክለሀይማኖት የድቁና መዓረግ መቀበሉ ይታወቃል ለአንድ ቀንም ቀድሶበት ባያዉቅም እንዲሁም ከአምቦ እርሻ ኮሌጅ ዲፕሎማ እንዳለዉ እናዉቃለን ነገር ግን ለቤተ ክርስቲያኗ የመመሪያ ሀላፊነት የሚያደርስ መንፈሳዊ እዉቀትም ስነ ምግባርም አግባብነትም የለዉም ታዲያ እንደነ ዳዊት ታደሰ አይነት ሰዎች አጣርተነዉ መጣን ብለዉ የሰጡት መግለጫ ምኑ ነዉ የሚታመነዉ፡፡
አይ ዳዊት በል እንግዲህ አዞልሀል በቤተ ክህነት ስም ደግሞ ብላ መቼም ለመብላት የተፈጠርክ ነህ፡፡
ዳዊትን ጠንቅቀን ከምናቅ የአምቦ ነዋሪዎች

Anonymous said...

How can we consider these to be the management of the church. They are there to demoralize and then destroy our church. They may or may not know it. They are totally focused on the money they receive, like the allowance they demand from financially poor monasteries(but very rich spiritually). We ought to think about what next?

Gebre Z Cape said...

Can you please post the link from Dire Tube so that I can also listen to what they said on ETV. It is not easy to find the news on Diretube using search engine.

Thanks

MAN YAZEWAL said...

ሲኖዶሱና ሙጅሊሡ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂ ሲል ፍትህ ጋዜጣ የተናገረው ለካ እውነት ነው ። ቤተ ክርስቲያናችን የምትመራው በቤተ ክርስቲያን ሰዎች ሳይሆን ማነነታቸው በውል በማይታወቅ ለሆዳቸው ባደሩ ሰዎች መሆኑን ያየነበት መግለጫ ነው።ለመሆኑ ይህን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ሰዎች እነማን እንደሆኑ ሊታወቅ ያ ስፈልጋል። ጎበዝ በቤተ ክህነት ታሪክ ውስጥ እንደዚህ
ዓይነት መግለጫ በእንደነዚህ ዓይነት ምናምንቴ ሰዎች ሲሰጥ የመጀመሪያው ነው። ብዙውን ጊዜ መግለጫ ሲሰጥ የምናየው በፓ ርያርኩ በኩል እንደሆነ የሚታወቅ ነው ።
መግለጫውን ያቀረቡ ሰዎች እነማን ናቸው ብለን ብንጠይቅ ቤቤተ ክህነታችን ውስጥ የመንግስትን ሥራ የሚሰሩ ካድሬዎች ናቸው። ሊቀ ማዕምራን በሚል ሽፋን ስም ወደቤተ ክህነት የገቡት ኃይለ ሥላሴ በአዲስ አበባ በድሬ ደዋና በፍቼ ሀገረ ስብከት ከመንግስተ የተሰጣቸው ተልዕኮ በማስፈጸም የሠሩ ዛሬም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ከሐይማኖታዊ ሥራ ይልቅ የፖለቲካው ን ሥራ በሰላይነት የሚሰሩ ናቸው። አቶ ተስፋዮ የተሻለ ሕሊና ያለው የፓርቲው አባል ሲሆን በትንሳኤ ዘጉባኤ ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ ለብዙ ጊዜ የሰራ ሰው ነው። እስክንድር ምንም ዓይነት የቤተ ክርስቲያንም ሆነ የዘመናዊ ዕውቀት የሌለው ካድሪ ነው። ቤተ ክህነቱን ከሚሰልሉትና አባቶች እንዲደበደቡ ያደረጉ የመንግስት ቅጥረኖች ናቸው። እንኩና ከነዚህ የመንግስት ቅጥረኖች ከአባት ተብየው ምንም በማንጠብቅበት በዚህ ፈታኝና አስቸጋሪ ወቅት ይህን መግለጫ ስሙ የቤተ ክህነት ተብሎ ቢወጣ የመንግስት መግለጫ ነው። የሚደንቀኝ ቤተ ክርስቲያኗ ገፍተኛ ገንዘብ እያወጣች የምታስተምራቸው የከፍተኛ መንፈሳዊ ምህርት ቤት ተማሪዎች እያሉ እንደነዚ ዓይነቱ በሁለት ቢላ የሚበሉ ሰዎችን በቤተ ክህነቱ ውስጥ መኖራቸውን ሳይ በቅርቡ ፍትህ የተባለ ጋዜጣ ሲኖዶሱና ሙጅሊሡ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ ያለው ለካስ እውነቱ ነው። በዚህ ሰዓት እናንተ ዝም ብትሉ እነዚህ ድንጋዮች ያመሰግናሉ እንዲል። ሃላፊነት ላይ ያሉ የእግዚአብሔርን ሥራ መሥራት አቅቶቸው በሚገኙበት ሰዓት እግዚአብሔር ከተናቁት ጋር ከወጣቱና ከምእመኑ ጋር እየሰራ መሆኑን ዓይናችን ያየው ዝቋላ ላይ ነው። መንግስት እንደነዚህ ዓይነ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መሰግሰጉ ሕገ መንግቱ ሐይማኖትና መንግስት የተለያዩ ናቸው የሚለውን አንቀጽ እያፈረሰ ከመሆኑም በላይ በደርግ ሥርዓት እንኩን ይህን ያህል ያልተደፈረቸው ቤተ ክርስቲያን ለመድፈር መነሳቱ ከማን ጋር እየታገለ መሆኑን ሊረዳ ያስፈልጋል። በእነደዚህ ዓይነት ቅጥፈት ማጭበርበር በተሞላበት ዓይን አውጣነት አካሄድ ሕሊናቸውን የቁራሽ እንጀራ የሸጡ ካዴሬዎችን በተቀደሰው ሥፍራ ገብተው የእግዚአብሔርን ቤት እንዲያረክሱ መደረጉ ፍጻሜው ጥፋት ነው።

Anonymous said...

i donot know who is who in this picture. just in case who knows, why dont you put ther names accordingly.

Abel said...

“በአባት ስም“ የቤተክርስቲያን ጠባቂዎች ነን ባዮች፤ ምን አለ ለራሳችሁ ስትሉ ልቦና ብትገዙ?
ቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ የሆነ መከራና ችግርን ስታሳላፍ ቆይታለች። አሁንም መከራውን እየቀመሰች ነው። ይህ የነበረ ወደ ፊትም የሚኖር ነው። የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናንም ይህ ለምን ሆነ ብለው አያምርሩም። መከራና ስቃይን ከእርሱ ከጌታችን ተምረዋልና። አሁን አሁን ግን አባት መሳይ “አባቶች “ ከቤተክርስቲያኒቱ የላይኛው ወንበር ላይ በመፈናጠጥ የሚያደርሱት አስነዋሪ ስራ ምዕመኑን እያንገሸገሸው ነው። ለሚፈጠረው ችግር ጋዝ ጨማሪ መሆናቸው ጥቃቅን ነገሮችን እንኳ በቀላሉ መፍታት አልተቻለም። አንዳንዴ የሚሰጡት መግለጫ፤ የሚያወጡት ደረቅ ውሸት ብዙ ጥያቄ እንድናነሳ ያደርገናል። እየዋሹ ለመኖርም፤ መቀመጫ ቦታ ያስፈልጋል። አሁን መቀመጫቸው በተለያየ ዝባዝንኬ ምክንያት ሲጠፋ፤ ቢያንስ ለምን ማለት ነበረባቸው። እንዲህ ጀሮ ዳባ ልበስ እያሉ፤ ከችግሩ ጋር የማይገናኝ “የኦሪት ፍየል ፍለጋ“ መሄድ ነገ ራስን ለመከራ ማዘጋጀት መሆኑን ምን አለ ቢያስቡበት? “ቆብን“ እያስተካከሉ፤ “መስቀልን“ እያወዛወዙ ለማደናበርም እኮ መቀመጫ የሆነ ቤተክርስቲያን፤ የእምነቱም ተከታይ ምዕመን ያስፈልጋል። “የአበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይቀልድም“ የሚባለውን የሐገራችን ተረት መተግበር ያስፈልጋል። ተመሳሳይ ችግሮች በሌሎች ሃገራት ተከስተው ነበር። በወቅቱ መልስ መስጠት የተሳናቸው “አባቶች“፤ ትውልዱ በእምነቱ ተስፋ እንዲቆርጥ፤ የሰይጣን መጨዋጫ እንዲሆን፤ አብያተ ክርስቲያናትም መደነሻና ወደ ንግድ ተቋማትነት እንዲቀየሩ ነው ያደረጋቸው። ለዚህም በአውቶፓና በአካባቢው ተከስቶ የነበረውንና ያስከተለውን ችግር ጠይቆ ወይም አንብቦ መረዳት በቂ ነው። በአሁኑ ሰዓት በሃገራችን ያሉ አንዳንድ የበላይ “አባቶች“ የሚፈጽሙት ግፍ መጨረሻው የአውሮፓውን ክስተት መድገም ነው የሚሆን። ይህ ድርጊታቸው ባዶ “ቀሚስና መስቀላቸውን“ ይዘው እንዲቀሩ ነው የሚያደርጋቸው። ምን አለ ልቦና ቢገዙ! ቢያንስ ማድረግ ካልቻሉ በአርምሞ ቢያልፉት? በቁስላችን ላይ ለምን የጋለ ብረት ይሰዳሉ? እውነት ልማቱ ከልብ ከሆነ 113 ሚሊዮን ሄ/ር የሚጠጋ የቆዳ ስፋት ያላት ሃገር፤ ከእዚህም ውስት ከ60 ሚሊዮን ሄ/ር በላይ ለእርሻ ያመቻል የሚባልባት አገር ይዘን፣ የቤልጀየምን አገር ስፋት የሚያህል መሬት ለአንድ ኩባንያ በ“ሊዝ“ መልኩ አሳልፈን እየሰጠን፣ መንግስት በቢልዮን የሚቆጠር ልማት ለማፍሰስ ያን ድንጋያማ፤ ደረቃማና ወጣ ገባ ውስጥ ያለ በጣም አስከፊ የሆነውን የዋልባ አካባቢ ለዚህ ግዙፍ ኢንቨስትመንት ለምን መምረጥ አስፈለገ? አባይ ጸሐዬ ጉዳዩ የፓለቲካ ነው እንጅ ገዳሙን ማንም አይነካም ብለው ባደባባይ ከመደስኮር መረጃ አስደግፈው ለምን ያ አካባቢ ተመረጠ ለሚለው መልስ ቢሰጡ መልካም ነው። የፓለቲካ ያደረጉት እርሳቸው ናቸው። ማንም ልማትን አይጠላም። ነገር ግን በልማት ስበብ አገር፤ሕዝባና እምነት ከጠፋ የልማቱ ተጠቃሚ፤ ማን ሊሆን ነው? ከመርካቶ በተገዛ “ቆብ ና መስቀል“ ማናችንም አንሸወድም። እውነትን የያዘ ቆብና መስቀል ሳያሰፈልገው ሊያስረዳንና ሊያሳምነን ይችላል። ካልሆነ ግን እውነት እውነት ናት! ገዳማቶቻችን በግርግር ሲጠፉ አናይም! እኛ እንኳን ዝም ብንል የሰራዊት ጌታ ዝም አይልም! ስራውን ይሰራል። በእምነት አምላካችንን ይዘን እስከ መጨረሻው እንፋለማችዃለን። አሸናፊ ማን ሆኖ እንደሚወጣ ታዩታላችሁ። አባት መሳይ “በአባች“ ግን ካልቻላችሁ ፤ ቢያንስ በአርምሞ እለፉት። አታድሙን።

Anonymous said...

I am sorry for the unbelievable words they spoke. Whom we trust? Please, forget the so called "Bete Tiknet"
but you MK, Dejeselam and devoted citizens God bless you.Thank you very much in reporting the truth,helping the destitute people,expending your money and time. History never forget such devotions.

It is high time to say the so called Patriarch "you are not father of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church". Instead, he too fast to announce government sayings. In addition to this, the government of Ethiopia is also showing negligent to the many distractions occurring frequently. So, for how long we carry such burdens and distractions?

May God bless Ethiopia.

Anonymous said...

ለካ ታይቶ በማይታወቅ ጭንቅ የምንታመሰው እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች በስልጣን አስቀምጠን ነው? አበል መጠየቅስ ምን ይሉታል? አሁን የማንተኛበት ግዜ ነው ጎበዝ፣ አምላከ እስራኤልም የውስጣችን ጉዳት እየተመለከተ ነው:: በተነሳንበት ብርታት መቀጠል አለብን!

Anonymous said...

To all krstians, I thik this condition is from God. By this time most of us are wz 'sin'. God may give this time for sacrification and to get salivation. But how we involve? Who lead us? Where we pay sacrification?

Anonymous said...

Why are you expect good deeds from bete kihinet; bete kihinet has already changed to bete tikinet and bete neger. May God bless all the brethren and the true fathers of the church. The statement “እሳት በመንደርም ይነሣል፤ በቤተ ክርስቲያን ሲሆን ለምን ይገናል? suggests that the Holy Church of God is administered by some alien individuals who care for their carnal passions. The very statement shows that they are not true members of the Holy Church. What did Jude did more than this wicked did; he betrayed his Lord and these sons of him also follow his footstep and betrayed the Holy Church of Christ the Lord and by this they disobey Him. Woe to them! They are shame to the Church. Min albat esatu arat kilo yimeta yihonal!

Anonymous said...

they are memebers of EPDREF.Eskender was Yeka sub city temerach in 1997 tesfaye Arada sub city and H/Selassie was good war fghter in 1980's around mekell.be shure it is governmental press confaernce tahn spirtual.way not the holy Synod members attend the press conference? Dawit eskender Tesfaye they are modern and legal LEBOCH

y said...

"...በወንዝ ፍርሃት፥ በወንበዴዎች ፍርሃት፥ በወገኔ በኩል ፍርሃት፥ በአሕዛብ በኩል ፍርሃት፥ በከተማ ፍርሃት፥ በምድረ በዳ ፍርሃት፥ በባሕር ፍርሃት፥ በውሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርሃት..." እግዚአ!

esrael said...

Minim bihon betekiristian eyetefach egna zim bilen enikemetalen bilachihu asibachihu kehone sihitet new mikiniatum hiliwinachen betekiristianachin nech ena

Anonymous said...

Instead to talk too much prey for your part for this church donot acuse any body. Do you know about this all things happening b/c of our sin? It's better come our mined no t to acuse any body. see ur self Amoment what you are doing do you have plastics altitude for the another person ? It is always un answerd question .

Anonymous said...

Enezih sewoch be Nabute lay endemesekerut Minamintewoch nachewu min yasdeniqal. Hodachew amlakachew kibrachewu benewurachewu new.

Anonymous said...

“እሳት በመንደርም ይነሣል፤ በቤተ ክርስቲያን ሲሆን ለምን ይገናል?” የሚል ሰው ሐይማኖት ምን እንደሆነ የማይገባው ሰው ብቻ ነው:: እግዚአብሔር የለም የሚሉ ሰዎች እንደዚህ አይነት ጥያቄ ያነሳሉ ምክንያቱም በነሱ አስተሳሰብ ሁለቱም ቤት ነው:: ሐይማኖት ምን እንደሆነ ለሚያውቅ ሰው ግን ሁለቱ በፍጹም አይነጻጸሩም:: ለጥያቄያቸው መልሱን ከፈለጉት ግን መልሱ በጣም ቀላል ነው:: መንደር የአለም ጉዳይ ነው; የስጋ ነገር ነው; ጊዜያዊ መኖሪያ ነው መንደር ወይም የግላችን ቤት:: ቢበዛ አንድ ሰው በምድራዊ ቤቱ ሊኖር የሚችለው 80 አመት ነው ምናልባት እስከ 100ም አመት:: ቤተክርስቲያን ግን ዘላለማዊ ቤታችን ናት; የነፍስ ጉዳይ ናት; መተኪያም የላትም:: መንደር ቢቃጠል ግን ገንዘብ ነው የሚቃጠለው:: እናንተ ለገንዘብ ያላችሁ ፍቅር ከምንም በላይ ስለሆነ ጊዜያዊ መንደራችንን (ቤታችንን) ከነፍሳችን ቤት (ከዘላለማዊ ቤታችን) ጋር አነጻጸራችሁት ለእኛ ግን ሁለቱ በፍጹም አይወዳደሩም:: ቤታችንን መንግስት ወይም ሌላ አካል ሊነጥቀን ቢሞክር የምንችለውን ያክል ከመታገልና ከመከራከር በቀር ምንም ማረግ አንችልም:: ህይወታችንን ለመንደራችን (ለምድራዊ ቤታችን) አሳልፈን አንሰጥም:: ከአቅም በላይ የሆነ ጉዳይ በምድራዊ ቤታችን ጉዳይ ቢያጋጥመን አሳልፈን እንሰጣለን:: ለዘላለማዊው ቤታችን (ለቤተከስቲያን) ጉዳይ ግን ህይወጣችንን አሳልፈን ለመስጠት የምንፈራው ነገር የለንም:: እናንተ የምትተማመኑበት መሳሪያዎችም ስለዘላለማዊው ቤታችን (ስለቤተክርስቲያን) ስንል አንፈራውም አትጠራጠሩ:: ጊዜውን ጠብቆ በራሱ ጊዜ የሚፈርሰውን ስጋችንን እንጂ ነፍሳችንን መግደል በፍጹም አትችሉም:: ለጊዜያዊ ቤታችሁና ለገንዘባችሁ ብቻ እየተጨነቃችሁ ነፍሳችሁ እንዳትወሰድ ለንስሐ እንዲያበቃችሁ መልካም ምኞቴ ነው::

Anonymous said...

ENEZIH YEBETEKERSTIYANENA YE MENDER LIYOUNET LEYETEWU YEMAYEKU "CHEWAWOCH" MAEREGENA SIME YALEWAGA SETEN SHUMENACHEWU KEZI LELA MENE ENDILU NEWU YEMENETEBEKEWU?!? ESTI TEWUWACHEWU ENESU YEBELU EGNA LE BETEKERSTIYANACHEN KE KIDUS EGEZIYABEHER GAR SERA ENESERA.WETATOCHACHENEN GULEBET ENA BEREKETUN YADELELEN!

ታዘበው said...

በ "እርኩስ የሚመራ ቅዱስ ህዝብ" ውድ የተዋህዶ ልጆች መቼም ከቀን ወደቀን እየባሰ እንጂ ምንም አይነት መሻሻል የማይታይበት የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ ከዚህ ዘመን በፊት ብዙ ፈተናዎችን ብታሳልፍም ይኸኛው የባሰ ብቻ ሳይሆን እጅግ የተቀነባበረ ስልታዊ እንቅስቃሴ ነው በውጭ የሚታገዝ የተዋህዶ ጸር የሆኑ የመንግስት ባለስልጣኖቻችንና የአባቶችን ስራ ሲሰሩ የማይታዩት ነገር ግን አባቶቻችሁ ነን የሚሉን ሁሉ የተቀመጡት በተዋህዶ አንቀልድም ይህስ ሲሆን ዝም ብለን አንመለከትም ብለው በፍቅርና በቁጭት የተነሱትንና የሚነሱትን የተዋህዶ ልጆችን ለማደናገር ነውና ስልታዊ ስራቸውን በመመርመር እየተደረገ ያለውን የፍቅር እንቅስቃሴያችንን ይዘን እንበርታ ያለምንም ጥርጥር እናሸንፋለን ምክንያቱም "ከኛ ጋራ ያለው ከነርሱ ይበልጣልና" እናስተውል የ"ዮዲት"እና የዘመናችን የሃይማኖት መሪዎቻችንን አንድነትና ልዩነታቸውን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ተዋህዶን ይታደግልን!!!

asbet dngl said...

እጅግ በጣም አሳዛኝ መግለጫ ነው
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን በቸርነቱ ይጠብቅልን

MelkameKene said...

“እሳት በመንደርም ይነሣል፤ በቤተ ክርስቲያን ሲሆን ለምን ይገናል?” Because church is special than any-other.

Anonymous said...

በአባቶቼ አዘንኩ እሳት በመንደርም ይነሳል የቤተክረስቲያን ሲሆን ለምን ይገርማል አሉ በእውነት የሚያስተዳድረን መንፈሳዊ አባት ወይስ የመንግስት ጥገኛ በመንፈሳዊ ሥም የሚነግድ?

Anonymous said...

Abet adenen! we shamed of them(bete-kehenet)they let us dowen every day and they need only protect there own privet life,but God ve time! pls guys we ve to do something,we ve responsibility.it's not helping if we say only this or that.pls dejeselamoch zenawun endasemachehun yehone neger enedenaderg aderegu,malet bemaheber sewu hulu beiehageru yalew tebabero yemiserabeten neger amechachulen bians begenezeb metebaber aleben specialy wuchi lemenenor sewoch betam yasefelegenalena pls.we don't ve to only read the news.it's not right.let us do something christianoch bakachu,ahezab betekerestianachenen likerametuat new.God help us

ድሉ ዘእግዚአብሔር said...

የአካል ሁሉ አንቀሳቃሽ ሞተር ራስ ላይ ነው ያለው። ለዚህም ነው ''የእሳ ግማቱ ? ከአናቱ።" የሚባለው ምሳሌአዊ አባባል። እናም ራስ ጤናማ ካልሆነ የራስ ጥገኛ የሆኑት ሌሎች አካላት ጤናማ እንደማይሆኑ የታወቀ ነው።
ስለዚህ በሽተኛው ራስ በጤናማ ራስ ካልተተካ በስሩ ያሉ አካላቱ ከበሺተኛ ራሳቸው ተለይተው ጤናማ ይሆናሉ ብለን አንጠብቅ ። ምን ለማለት እንደፈለኩ ትረዳላችሁ ብየ እገምታለሁ።

Anonymous said...

የጥፋት እርኩሰት በተቀደሰዉ ሥፍራ ስታዩ ዘመኑ እንደቀረበ አውቃችሁ ትጉና ጸልዩ ::
ሰው ሆይ የክነትህ ምንጭ የሆነች ለቤተክርስቲያን እንዳታስብ ማንአዚም አደረገብህ::
እኔ የሚገርመኝ ዘመኑ ይሆን ሰው ገንዘብ ሥልጣን ይወዳል:: ዋናውን የሰማያዊዩ ን ነገር ግን ረሳው::

ቸሩ መዳህኔ ዓለም እንደሆን ይሁዳ ለሞት ቢሸጠው ከሙታን ተነስቶ እኛን ወደ ሕይወት አሸጋገረን ::ይሁዳ ግን 30 ብር አየ ተቀበለ እንጂ አልተጠቀመበትም::

ታዲያ ዛሬ መንግሥት ደስ እንዲለው ሥልጣን እንድናገኝ ሀብት እንድናካብት ብለን የክህነታችን ምንጭ ሆና እንድንከበር ያደረገችንን ቤተክርስቲያንን ለምን ከፋንባት::

ጉዳቱ በራሳችን እንደሆነ ላለማወቅ የእውቀት መጉደል ያለብን አይመስለኝም::

እመቤታ ድንግል ማሪያም ሆይ ኧረ ያስራት ሀገርሽን ኢትዮጵያንና ቤተክርስቲያንን ጠብቂልን::
ኧረ ፈጣሬ አለማት ክርስቶስ ሆ ይ ውሸት የኢትዮጵያ መገለጫ የሆነበት ጊዜን ስለተመረጡት ብለህ አሳጥርልን::ሚዲያው ከዋሸ ቤተክህነት ከዋሸ ማን እውነት ይናገር

Dawit said...

በርቱ!እንዲህ ነው እንጅ አባት። ምን አለባችሁ-ጃንጥላ ተዘቅዝቆ፣ ምንም ከሌለው ምዕመናን ጉሮሮ ላይ ተቁሞ በተሰበሰበ ገንዘብ ትኖራላችሁ። ይህ አልበቃ ብሎ ደግሞ ባደባባይ መዝለፍ ያዛችሁ። ዋ ይች ቀን ታልፍና!ምን ይዉጣችሁ ይሆን? "መታሰሩን ታሰር ነገ ትፈታለህ፤ ወዳጅና ጠላት ትለይበታለህ።" ተብላ የተቋጠረችዋ ስንኝ እንደ እናንተ ያሉትን ለመለዬት ሳይሆን አይቀርም። ከማን ወገን እንደሆናችሁ ብግልጽ ስለነገራችሁን እናመሰግናለን። የሰራዊት ጌታ ልዑል እግዚአብሔር ስራችሁን ይስጣችሁ። ማንም የዘራውን ስለሚያጭድ፤ ለፍቶ መና አያድርጋችሁ። የዘራችሁትን ስታጭዱ በአይናችን ለማሳዬት ያብቃን!

lele said...

yekere balane

Anonymous said...

lebetu yemateteqemuten werebelawoche egeziahbear neqelo yawetachehu...

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)