March 22, 2012

ስለ ዝቋላ እሳት ጉዳይ - ምስጋና እና ስጋት


(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 12/2004 ዓ.ም፤ ማርች 21/2012/ READ IN PDF)፦ ስጋቱ - ዛሬ አዳሩን ከምሽቱ 300 ገደማ የቅዱሳን ከተማ በሚባለው ስፍራ ሲጤሱ የዋሉ የገመኑ (የተቃጠሉ) ጉቶዎችና ግንዶች ምሽቱን እሳት መቀስቀሳቸው ተሰምቷል፡፡ የእሳቱ መጠን ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ለጊዜው ማወቅ ባይቻልም÷ በየአቅጣጫው ሁኔታውን በንቃት እየቃኙ በነበሩት መናንያን በተሰማው ደወል በገዳሙ አዳራሽ የነበረው ምእመን እንዲጠራ ተደርጎ፣ በተራራው ላይ የመከላከሉን ተግባር በከፍተኛ ደረጃ ሲያግዙ ከነበሩት የፌዴራል ፖሊስ እና የመከላከያ ኀይሎች ጋራ የተቀሰቀሰውን እሳት ለማጥፋት እየተረባረቡ መሆኑ ተገልጾልናል፡፡

ንት ሌሊቱንና ዛሬ ውሎውን የቃጠሎው መዛመት ተግ ብሎ ከጋራው ግርጌ በኩል የሚጤሱ የጋሙ ጉቶዎች ጢስ ብቻ ነበር የሚታየው፡፡ ማምሻውን የተቀሰቀሰው እሳት በቃጠሎው ብዛት የገመኑት ግንዶችና ጉቶዎች የፈጠሩትን ፍሕም ጨርሶ ለማጥፋት በአየር የሚረጨው ኬሚካል በእጅጉ አስፈላጊ እንደ ሆነ ያለማቋረጥ እየቀረበ ያለውን ጥያቄ ትክክለኛነት የሚያስረግጥ ነው፡፡ በመሆኑም በጎ አድራጊ አካላት ለዚህ ተፈጻሚነት እንዲተባበሩ ተጠይቋል፡፡
ከዚህ ውጭ ያለው አማራጭ የነፍስ ወከፍ የውኃ ርጭት ነው፡፡ ይሁንና ገዳሙ ከቀድሞም ባለበት የውኃ እጥረትና ከፍሕሙ መብዛት የተነሣ በቂ ውኃ ለማግኘትይችልም፡፡ እስከ ኀሙስ ገበያ ድረስ ለመምጣት የቻለው ውኃም እየተቀዳ ቃጠሎውን ለማጥፋት ለተሰማሩት ወገኖች ነው የተከፋፈለው፡፡ በመሆኑም በዚህም በኩል በጎ አድራጊ አካላት ውኃና ውኃ የሚያቀርቡ ተሽከርካሪዎችን በማቅረብ እንዲራዱ ተጠይቀዋል፡፡
እስከ አሁን - የገዳሙ መነኰሳት እስከ አሁን የተደረገውን ቃጠሎውን የመከላከል ጥረት እንደሚከተለው ገልጸውታል፡- ‹‹በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በምእመኑ ብዛት እሳቱ ጠፍቷል፤ አሁን ባለበት ርቀት  የሚበላውን ያህል በልቶ ስለጨረሰ ከዚህ በኋላ ሊስፋፋ አይችልም፡፡
ሕዝበ ክርስቲያኑ፣ መከላከያው፣ ፖሊሱ፣ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ባለሞያዎች ወደ ገዳሙ መዳረሻ በሆኑ መንገዶች አፈሩን እየቆፈሩ ጉድጓዶችን በማውጣት፤ አፈሩን፣ ቅጠሉንና ግንዱን በመከመር ቃጠሎው ወደ ጠበሉ እንዳይገባ አድርገውታል፡፡
አሁን የቃጠሎው ስጋት ያለው ጢሱ በሚታይበት ተራራ ግርጌ፣ በአዱላላ በኩል ጊዳ መሥመር እየተባለ በሚታወቀው አቅጣጫ ነው፡፡ ሌሊት መናንያን ሁኔታውን በንቃት ይጠብቃሉ፡፡ የሚያሰጋ ከሆነ ደወል ይደውላሉ፡፡››
የገዳማውያኑ ምስጋና - ‹‹ለቦታው ተቆርቋሪ ከሆነው ወገን የቀረ ሰው የለም፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪው፣ የከተማው ወጣት፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ ፖሊሱ፣ መከላከያው በአጠቃላይ ሕዝበ ክርስቲያኑ እዚሁ ነው ያለው፡፡ በተለይ ወጣቱ ለቦታው ታላቅ ባለውለታ ነው፡፡ ሃይላንዳቸውን ብቻ ይዘው ተራራውን ወጥተው ከዚህ መድረሳቸው ብቻ ለእኛ አለኝታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሐሳባቸውን ያስፈጽምላቸው፡፡ ውለታቸው በሰው ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ቦታውን ታድገውታል፡፡››

ቸር ወሬ ያሰማን

አሜን

4 comments:

stloius said...

አሜን ቸር ወሬ ያሰማን!!! እኔስ አፈርኩ መንግስትና የሐይማኖት መሪ ለካ እናት ሐገሬ የላትም ለካ ለራስ መሆን አይቻልም አዝናለሁ ለጦርነት ሲባል የንጹህ ሰው ደምን ለማፍሰስ 1ኛ ቀዳሚዎች እናንተ ናችሁ እግዚአብሔር ፍርድ ይስጥ ይፍረድባችሁ!!!!

Anonymous said...

Amen! God bless them

Anonymous said...

God Of Elias will protecte our mother church we have only one identity ond life that is EOTC church and it her Monastries.holy Spirit will save us from earthly fire.a great lent will bring to Us joy.yet we have to pry strongly.any one who help this government will destroy Himself particulary abba pawlos He makes our church PLC(pawlos limited caompan)
from seattel

Anonymous said...

we have to help ethiopian sunday school studentes,MK,Yetemket temelash wetatoche jornalistes,nuns and monks.

theotokos will be with us.
from Arat killo

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)