March 29, 2012

በዋልድባ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሕዝባዊ ውይይቶች ቀጥለዋል


·         ምእመናን ለቤተ ክርስቲያናቸው መቆም ያለባቸው ጊዜ ላይ መደረሱ ተወስቷል፡፡
·         ሰላማዊ ሰልፎች ማድረጉ ይቀጥላል።
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 20/2004 ዓ.ም፤ ማርች 29/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በዋልድባ እና በጠቅላላው የቤተ ክርስቲያን ህልውና ጉዳይ የተቀሰቀሰው ቁጣ በሕዝባዊ ውይይቶች ታጅቦ እየቀጠለ መሆኑን የሰሜን አሜሪካ ምንጮቻችን ገልጸዋል። በመላው የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በስልክ ኮንፈረንስ ሐሳባቸውን እንዲሰጡ እያደረገ ባለው በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ የምእመናን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ስለ ዋልድባ ይዞታ መደፈር ወይም ስለ ዝቋላ እና አሰቦት ገዳማት የእሳት አደጋ ብቻ ሳይሆን “በጠቅላላው ስለ ቤተ ክርስቲያን ህልውና ነው መነጋገር ያለብን” ወደሚለው ገዢ ሐሳብ በመምጣት ላይ ናቸው ተብሏል።


በዚሁ በፈቃደኛ ምእመናን በተጠራው እና በልባቸው በየቤታቸው ሲቃጠሉ የነበሩ ምእመናንን እየቀሰቀሰ በመጣው የስልክ-ጉባኤ አያሌ መሠረታዊ ጥያቄዎች በመነሣት ላይ ናቸው። “እኔ ምንም የሌለኝ አንድ ደካማ ሰው ነኝ” ሲሉ የጀመሩ አንድ ምእመን እንዲህ አሉ። “ስለ ዋልድባ ጉዳይ የአካባቢው ባለሥልጣን ሲናገሩ ሰምቻለኹ። መነኮሳቱም ሲናገሩ ሰምቻለኹ። እንግዲህ ይህ ገዳም ለሁለት ሺህ ዓመት የቆየ ነው። እንዲያው ምንም ችግር ከሌለ እንዴት ገዳማውያኑ እስከ አዲስ አበባ፣ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ድረስ ለመሔድ ይነሣሉ?” ሲሉ ተጠየቃዊ ሐሳብ አቅርበዋል። አክለውም “እኔ ስለዋልድባ ብቻ አይደለም የምናገረው። ከዚህ በፊት አኩሱም ላይ ችግር ተፈጥሮ ነበር። ከዚያ ሰው ሞተ። የሚገርመው ገዳዩ ማን ነው ሳይባል ሁከቱን የቀሰቀሰው ማን ነው? ይቅርታ ይጠይቅ የሚል ነገር ተነሣ። ይህ መንግሥት (ኢሕአዴግ) ስለ ቤተ ክርስቲያን ያለውን ሀሳብ መጠየቅ አለብን። በዚህ በ20 ዓመት ውስጥ የሌሎች እምነቶች ንብረቶች እንዲህ ሆኑ ሲባል ሰምቼ አላውቅም። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብቻ ነው የሚጠፋው። የሚቃጠለው። ይህ እኮ ሕጋዊ ጥያቄም ነው። መንግሥት ለእምነቶች ጥበቃ የማድረግ ግዴታ አለበት። ለዜጎች። የዋልድባ መነኮሳት ከተማን ሸሽተው፣ ዓለምን ንቀው ነው የሄዱት። ለከተማ ለከተማማ በየከተማው ባሉ አብያተ ክርስቲያናት መኖር ይችሉ ነበር እኮ። እነርሱም ዜጋ ናቸው። መንግሥት ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል” ሲሉ ልብ የሚነካ ንግግር አድርገዋል።

“ሥር ነቀል የምእመናን እንቅስቃሴ ነው የሚያስፈልገው” ያሉ ሌላ ተናጋሪም ኮፕት ቤተ ክርስቲያንን በአብነት በመጥቀስ ምእመኑ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት፣ አባቶችን ብቻ በመጠበቅ ጊዜው እንዳያልፍበት፣ እስካሁን ጠብቆ ምንም ያገኘው ነገር አለመኖሩን፣ በመላው ዓለም ያሉ ኦርቶዶክሳውያን በአንድነት በመነሣት ቤተ ክርስቲያናቸውን መጠበቅ እንደሚገባቸው አስረድተዋል። “ስደተኛ፣ ገለልተኛ፣ በአገር ቤት አስተዳደር ስር ያለ እያልን ተበታትነን ቀረን። የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ፖለቲካ እየሠሩ ነው። እኛ እነርሱን ተከትለን መጥፋት የለብንም” ካሉ በኋላ “አሁንም በፍፁም ንጽህና ፣ በንፁህ ልብ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ መሥራት አለብን። ፖለቲከኞች አሁን እኛን ተዉን። ፖለቲካችሁን ሌላ ቦታ ውሰዱ። እኛ የምንሠራው ለቤተ ክርስቲያን ነው” ብለዋል።

አክለውም “ሁላችሁንም በእግዚአብሔር ስም አንድ ነገር እለምናችኋለሁ። ከዘረኝነት ራሳችንን እናጽዳ። ዘር ለዱባና ለድንች እንጂ ሁላችን ከአንድ ከክርስቶስ ከማይጠፋው ዘር የተወለድን ነን” ሲሉ በሰሜን አሜሪካ ትልቅ በሽታ የሆነውን የዘረኝነትን ጉዳይ በቀጥታ አንሥተዋል።ሌሎች ተናጋሪዎችም በይዘት ከዚሁ ጋር የሚያያዝ ብዙ ሐሳብ ጠቅሰዋል።

ጉባኤው በዚሁ ቀጥሎ ሰላማዊ ሰልፎችን መቀጠል እንደሚገባ፣ በየአካባቢው የምእመናን አስተባባሪ ኮሚቴዎችን ማቋቋም እንደሚያስፈልግ፣ ይህ ሁሉ ችግር በእግዚአብሔር ቸርነት ይወገድ ዘንድ እና የተጀመረው እንቅስቃሴም ፍሬ እንዲያፈራ የምሕላ ጸሎት መደረግ እንዳለበት፣ ጊዜያዊ ችግር ያለባቸው ለዝቋላ እና ለደብረ አሰቦት ዓይነት ገዳማት የተጀመረው ርዳታ ማስተባበር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በረዥም ጊዜም ዓለም አቀፍ የሆነ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ፋውንዴሽን መቋቋም እንዳለበት የቀረበው ሐሳብ በዓላማነት ተቀምጧል።

ይኸው የምእመናን መነሣሣት እና ሕዝባዊ ውይይት በሌሎች አህጉሮች ማለትም በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያ፣ በአፍሪካ እና በአረብ አገሮች ወዘተ ባሉ ምእመናን ዘንድም ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

ር ወሬ ያሰማን
 አሜን፡፡

9 comments:

Anonymous said...

አሜን! ቸር ወሬ ያሰማን፡፡ ከውይይቶቹ የተረዳሁትቤተ-ክርስቲያን እጅግ ድንቅ ልጆች ያሏት መሆኑን ነው፡፡ እኔ ብዙ ጊዜ ውስጤ ሲበሳጭ ሁለት ነገሮችን አስባለሁ፡፡ አነዱ ሐሳቤ ፓትርያርኩን ከነጋሻ ጃግሬያቸው፤ እንዲሁም ቤተ,ክርስቲያን እንድትፈርስ ስልታዊ ሴራ የሚሸርቡትን ፖለቲከኞች (በተለይ ኢሕአዴግን) ማውደም የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የመጀመሪያው ሐሳቤ ኃጢያት መሆኑን በማሰብ የአምላኬን ይቅርታ እየጠየኩ የተሻለው ሁሉንም ነገር ላንተ መተው ነው እልና እነደአቅሚቲ የምችለውን አስተዋጽዖ እየሞካከርኩ ዝምታን እመርጣለሁ፡፡
ዞሮ ዞሮ ግን የቤተ-ክህነቱና የፖለቲካው ሴራ ግን ሰላሜን አሳጥቶኛል፡፡ የሚያሳዝነው በተቃዋሚ ጎራ ያሉ ፖለቲከኞችም ቤተ-ክርስቲያንን ለማዳከም/ወይንም መጠቀሚያ ለማድረግ/ የሚጎነጉኑት ሴራ የዋዛ አይደለም፡፡ እንግዲህ እንደእኔ በሐሳብ እየተላጉ ከመዛል ይልቅ በአሜሪካን ያሉ ወገኖቻችን በውይይታቸው እንዳቀረቡት ዓይነት ጊዜ ተሸጋሪ ስልት መንደፍ ሳይሻል አይቀርም፡፡

lamelame europe said...

ESKE YAMENAWERA BECHA SAYEHONE YAMENESARAME YAREGANE

Anonymous said...

አወ!!!
ቸር ወሬ ያሰማን!!!
በአለም ዙሪያ ያለን የተዋህዶ ልጆች በያለንበት ቤተክርስቲያናችን ምህላ እንዲደረግ ለሰበካ ጉባኤ/ለደብሩ አሥተዳዳሪ/ በማሳሰብ ሁላቸንም በአንድ ልብ ሆነን ወደ እግዚአብሄር እግዚኦ ማለት አለብን:: የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ውስጣቸው በፖለቲካ ታሠረ ከሆኑና ለዚህ ፀለተ ምህላ ምክኒያት የሚያበዙ ከሆነ ለእንደነዚህ አይነቱ ካህት ጊዜውም ትእግስቱም እንደለለን አቋም ልንወስድ የግድ ይላል:: የምንሰጣቸው ፍቅርና አክብሮት ስለ ለስልጣነ ክህነትና ስለቤተክርስቲያናችን ክብር ስለሆነ የቤተ ክርስቲያን ነገር የማይገዳቸው ከሆኑ እነሱን የምንሸከምበት ትከሻ እንደሌለን በቀጥታ ልንነግራቸው በክርስቶስ ግዴታ አለብን:: የምናመልከው አምላክ አይን እያለው የማያይ ጆሮ እያለው የማይሰማ ጣኦት አይደለም ::እንፀለያለን ::
ይህን ለማለት ያነሳሳኝ ባለፈው ዋሺንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደረገው አቤቱታ ላይ ከቦስተን ከኒዮርክ በዋሺንግተን ዙሪያ ካሉት ከቨርጂኒያ ከሜሪላንድ እና ከነርዝ ካሮሎና የመጡ ክርስቲያኖች በሰልፉ ሲካፈሉ ታዋቂ ሰባኪያንና ካህናት ዲያቆናት አልተገኙም ይህም የሚያሳየን ቤተክርስቲያንን ለገንዘብ እና ለተለያዩ አላማወች እየተጠቀሙባት መሆኑ ብቻ ነው:: ስለዚህ በቀጣይ ህብረት የማይፈጥሩ ከሆነ ማንን ማን ይሰብካል? የሚል ጥያቄ ሊያስነሳባቸው ይችላል ብየ አስባለሁ:: ሰባክያን ይህ መንግስት በሀገራችን ገዳማትና በአብያተ ክርስቲያናት ህልውና ላይ ያነሳውን የክተት አዋጅ በእግዚአብሄር ቃል መቃወም ይጠበቅባቸዋል:: ካህናትም ምህላ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል::
የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የገዳመ ዋልድባ ችግር ከተሰማበት ጸሎተ እንዲያዝ ዐውጀዋል::
የመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የመላዕክታን ተራዳኢነት እና የፃድቃንና የሠማዕታት ፀሎትና በረከት አይለየን!!!
አምላከ እስራኤል ይርዳን!!!

Anonymous said...

I am so happy today when I read the
foundation for unity at an INTERNATIONAL level of Ethiopian orthodox church.

1. It is a big mission-Big organizations are formed from big problems like we have.God makes everything for good. Our monasteries are burned as a sacrifice to our unity I can say. We could not listen to the preaching from heart . See what is happening, since our monasteries are built and kept by very spiritual fathers , when they move their bodies they are working by uniting all orthodox and making our hearts awake. Yeabatochachin tselot ahunim ayileyen.

2. Observe what is going on, all the so called"church fathers" are keeping silence and even are supporting the destroying of our church, our people and all the books,spiritual systems and all what we have, the churches people are struggling to keep the church , God bless you all and make your life prosper .If we need his kingdom and sacrifice our life, money, time,knowledge God will pay us back. God bless and help them those who are against the church to confess and help them to revive.

3. We have to support for the formation of international organization to tackle all the problems of the church and make our church internationally accepted so there will be many expertise who will help by giving their knowledge and strengthen the church by struggling against corruption, and make the church a democratic place where we could see the Work of God clearly. They can not hide in our church-those who are opponents including many of the church leaders.

4. We have to organize our effort to build the application of the church's law without doing by relationship, register our properties internationally(patent right) , develop system for the laws of the church will be respected and be transparent and much more, each of you may raise your ideas for sure more valuable than mine.

5.Get rid of false leaders and substitute by those who truly serve God at least in the eyes of miemen
we need to vote freely to choose our leaders with out no interference by non -church members
in all our awdemihret. we do not need to gather to approve already assigned non-church members-most of them.


6. Say No to oppression at least those who are living out of Ethiopia until we are free and let not go back to oppression all over the world ,we have to ask our church's freedom.

asbet dngl said...

በረዥም ጊዜም ዓለም አቀፍ የሆነ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ፋውንዴሽን መቋቋም እንዳለበት የቀረበው ሐሳብ በዓላማነት ተቀምጧል::ይህ ሐሳብ ወቅታዊና አስፈላጊም ነው ብየ አምናለሁ:: "ድር ቢያብር" ይባል የል::

Aresema said...

ምስጋና ለደጀሰላማዊያን በጣም ደስሜል ዜና ነው" ነካክተው ነካክተው የተኛውን በሬ አደረጉት አውሬ"አንድ ትልቅ አባት የሉት ትዝአለኝ አይቤተክህነት ካሁን በሓላ ይህዝብ እንደማይመለስላቸው ይግባቸው አክብሮትእንጂ ፍርሀት አይደለም ምንአይነት ህሊና እንዳለቸው ሳስብ ይርመኛል፤ ቸር ያሰማን ደጀሰላሞች ይህቃል ሁሌ ስትሉት ከምር ቸር ነገር እጠባበቃሉሁ ቃላቱ ያጽናናል.ተባረኩ የበ/ክ/ቲ አምላክ ይርዳን

bante views said...

“ሁላችሁንም በእግዚአብሔር ስም አንድ ነገር እለምናችኋለሁ። ከዘረኝነት ራሳችንን እናጽዳ። ዘር ለዱባና ለድንች እንጂ ሁላችን ከአንድ ከክርስቶስ ከማይጠፋው ዘር የተወለድን ነን”

Anonymous said...

+++

ሰዎቹ እንዴት ነው ከቅዱሳን ህይዎት ይልቅ ስኳሩ ጣማቸው?

እግዚአብሔር ይርዳን

Anonymous said...

Beseme Ab weweld wemenfes kidus Ahadu amlak Amen.
This message is for all Ethiopian Orthodox Tewahedo christians.This is not a time to sleep.Please wake up to protect our church from distruction.I hate..hate politics but when it comes to my church it is not a joke.I dont know how to put it.But I have never seen a government claiming to be democratic and destructing churches agians the will of the people.I know God is there to protect our beloved church,our idenmtity,our culture and our counrty.I support the development endeavours the government has put forth.Ethiopia need to go out of povery.Please make development plans by the will of the people protecting the country's heritage and culture which is our church.
May God bless Ethiopia and the people.May God protect our church.Let us all pray.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)