March 28, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ ስብሰባ ጠራ


አርእስተ ጉዳዮች፡-
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 19/2004 ዓ.ም፤ ማርች 28/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦
·         ከሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ ከዋልድባ ገዳም ተወክለዋል የተባሉ መነኰሳት፣ ከጎንደር ከተማ የተመረጡ ምእመናንና በማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል ሥራ አስፈጻሚ አባላት ነገ፣ መጋቢት 19 ቀን 2004 ዓ.ም፣ የመንግሥት ‹‹የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት›› በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ ስለ ደቀነው ስጋት፣ በተጨባጭም ስለታየው መጋፋት ውይይት እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ስብሰባውን የጠራውን ብአዴን/ኢሕአዴግ ሲሆን የሚካሄደውም በጎንደር ከተማ መሆኑ ተመልክቷል፡፡


በስብሰባው ላይ የፕሮጀክቱ ስፍራ ድረስ በመሄድ የግድቡን ግንባታ ከሚያካሂደው ተቋራጭ (ሱር ኮንስትራክሽን) ባለሞያና ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋራ የቀጥታ ውይይት አካሂደዋል የተባሉ ግለሰቦች በስብሰባው ላይ ሪፖርት ያቀርባሉ ተብሏል፡፡ እኒህ ግለሰቦች ከትላንት በስቲያ የኢትዮጵያ ቴሊቪዥን ዘገባ ላይ የግድቡ ግንባታ፣ የሸንኮራ ልማቱንና ስኳር ፋብሪካው ከገዳሙ ክልል ጋራ ግንኙነት እንደሌለው፣ ይልቁንም ልማቱ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በመሆኑ እንደሚደግፉት ሲገልጹ የተሰሙት ናቸው፡፡

የዜናው ምንጮች እንደሚገልጹት በኢ.ቴቪ ዜና ዘገባ ላይ ቀርበው እንዲህ ዐይነቱን አስተያየት የሰጡት ወገኖች ተጨማሪ ሹመት ሽልማት የሚፈልጉ፣ ሁሉንም የገዳሙን ማኅበር አባላት የማይወክሉ፣ ለድርጅቱ እንደ ካድሬ ሆነው የሚያገለግሉ በመሆኑ ሪፖርታቸው ተቀባይነት እንደማይኖረው ተነግሯል፡፡

በሌላ በኩል፡-
·         የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የገዳመ ዋልድባ ችግር ከተሰማበት ዕለት አንሥቶ ጸሎተ እንዲያዝ ዐውጀው እንደነበር ተሰምቷል፡፡ ይኹንና ‹‹እንዴት ጸሎት ያውጃሉ፤ ዐመፅ ለመቀስቀስ ነው ወይ?›› በሚል በአንድ የዞኑ ባለሥልጣን በተጠየቁበት ወቅት ‹‹ጸሎት እንዳላውጅ ማን ይከለክለኛል?›› ብለው መልሰዋል፡፡ የዞኑ ሓላፊም ማንኛውም ሰው ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ ሄዶ ግድቡ ለገዳሙ ጉዳት እንደሌለው ማረጋገጥ እንደሚችል በገለጸው መሠረት ሰዎች ተመርጠው ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ ለመሄድ ሲዘጋጁ ግን እንዳይሄዱ ተከልክለዋል፡፡


በምትኩ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ልኡካን በጎን ተልከው ባወጡት መግለጫ ምእመኑ ክፉኛ ማዘኑ ተመልክቷል፡፡ የግድቡ ውኃ የሚሸፍናቸው በገዳሙ ክልል የሚገኙ አራት አብያተ ክርስቲያን እንደሚፈርሱ ግልጽ ሆኖ እያለ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መግለጫና በኢ.ቴቪ ዘገባ የገዳሙ ድንበር እንዳልተደፈረ የተላለፈው ዘገባ ከእውነቱ የራቀ መሆኑም ተገልጧል፡፡ ይኸው ዘገባ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የገዳሙን ህልውና እና ክብር ለማስጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ቢያሳርፍም ‹‹የኢትዮጵያውያን ሁሉ ሀብት የሆነው ገዳመ ዋልድባ ዕድል በቀላጤ/ቅጥረኛ ሓላፊዎች መግለጫ ሊወሰን አይችልም፤›› ተብሏል፡፡


·         አባ ነፃ በተባለው የብዙ ቅዱሳን ዐፅም በክብር የፈለሰበትና፣ የሙዝ ቋርፍ የሚዘጋጅበት የገዳሙ የአትክልት ቦታ የታረሰ በመሆኑ ‹‹ለቋርፍ ተለዋጭ መሬትና በጠፋውም የቋርፍ ተክል ምትክ በስድስት ወር የሚደርስ የሙዝ ዘር እንሰጣችኋለን፤›› ቢባልም ማኅበረ መነኰሳቱ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተዘግቧል፡፡ የሙታን ዐፅም ከተቀበረበት መፍለሱን ያመኑት የመንግሥት ባለሥልጣናቱ ‹‹የፈለሰው ግን የቅዱሳን ዐፅም አይደለም›› ለማለት መሞከራቸው ባልተጣቸው ሥልጣን መግባታቸውን ያሳያል፡፡
·         ከአራቱ የገዳሙ አብያተ ክርስቲያን መነሣት ውጭ የቀሪዎቹ 14 የገጠር አብያተ ክርስቲያን መነሣት በተመለከተ ከጥቂት ጊዜያት በፊት በጎንደር ከተማ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጋራ በተፈጠረ አለመግባባት ሙስሊሞቹ ከቦታው ሲነሡ መስጊዱ ግን እስከ አሁን ተጠብቆ የቆየበት ሁኔታ በምሳሌነት ቀርቧል፡፡ ከዚህ አኳያ ሕዝቡ ሲነሣ ማኅበራዊ ተቋሞቹ አብረው ይነሣሉ በሚል 14 አብያተ ክርስቲያን እንደሚፈርሱ መገለጹ ፍትሐዊ ባለመሆኑ ተቀባይነት አላገኘም፡፡
ይህ በዝምታ ከታለፈ ነገ በከተማ ያሉ አብያተ ክርስቲያን ሳይቀሩ በስመ ልማት ይፍረሱ የሚባሉበት ጊዜ ሩቅ ባለመሆኑ መንግሥት የክርስቲያኑን ጩኸትና አቤቱታ አድምጦ ተገቢ ምላሽ እንዲሰጥ ጸንቶ መታገል እንደሚያስፈልግ የዜናው ምንጮች ተናግረዋል፡፡


ቀደም ሲል በዓዲ አርቃይ፣ በማይ ፀብሪ እና በሽሬ ተመሳሳይ ውይይት ስለመካሄዱ በመንግሥት ባለሥልጣናትና ብዙኀን መገናኛዎች መገለጹ ይታወሳል፡፡
 አሜን፡፡

30 comments:

Anonymous said...

"'እዴት ፀሎት ያውጃሉ አመጽ ለመቀስቀስ ነው እዴ" ዞንተብዬ ፃምን ቢፃሙ ቢፀልዪ ይልቅ በረከትን ያገኛሉ ስልጣንዎም ከርስዎ ጋር ይቆያል.

Ewunet Tenagari said...

ዋናው ጉዳይ አሁን ድንበር መጋፋቱ ብቻ ሳይሆን ከአስርና ሃያ አመት በኋላ ዋልድባ ገዳም መሆኑ ቀርቶ ዋልድባ የሚባል አዲስ ከተማ ሊሆን እንደሚቺል ነው አጽንዖት ሊሰጠው የሚገናው።
ወንጂና መታህራ የሚባሉ ከተሞች የተመሰረቱት በስኳር ፋብሪካ ምክንያት ነው። ካልጠፋ ቦታ ኢትየጵያ ሰፊ ሀገር ሆና ሳለ ለምን ዋልድባ? ሁሉም ነገር ለኛ ብቻ ከሚል ስግብግብነት አልያም ቤተክርስቲያንን ከማጥፋት እቅድ ካልሆነ በስተቀር።

Haile Michael zemerahe berhanat said...

መነግሥት በየውይይት መድረኩ ባለፉት ሥርዓቶች ተጠቃሚ የነበረ ሃይማኖት ነው እያለ ኦርቶዶክሳውያንን አንገት ለማስደፋት በማያገባውና በማያውቀው ስዘባርቅ ከነበረው ይሀንንም አቶ ተፈራ ዋልዋ በ1997 ዓ/ም ቤተክርሰቲያንን በይፋ ከተሳደቡበት ፡ከወያኔ መሥራች አንዱ የሆኑት አረጋዊ በርሔ የወያኔን ታሪክ በጻፉበት ወያኔ ትግራይን ለመገንጠል የኢትዮጵያን ሕዝብ በብዙ ነገር አስተሳስራ ያለችውንና ብሔራዊ መንፈስን የሚታስተምረውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በቅድሚያ ማዳከም እንዳለበት አቅዋም ይዞ መነሳቱን (A Political History of the Tigray People’s Liberation Front ፡ Neutralizing the Church and Mobilizing Muslims፡“A combination of factors made relations between TPLF and the EOTC church difficult …the church taught its followers to respect their allegiance to the Ethiopian state and was, in effect , a school for national consciousness, using national symbols such as the flag in all religious and social events. No church ever conducted major ceremonies without hoisting the Ethiopian flag – an act also regularly observed …’ page 244

“The pragmatic TPLF understood the church’s role in village social life and its support for the unity of the country .It also understood a possible alliance between the Church with its forces that stood against socialism and nationalization of the land as well as separatism .The church was viewed as a force standing in the way of TPLF. …there was no doubt that it wanted to subordinate the church to its cause” page 245) እና በተለያዩ አካላት በቤተክርስቲያን የሚፈጸመውን ተጽእኖ ስናይ ይህ ሁሉ የሚፈጸመው በመንግሥት ይሁንታ እነደሆነ እናረጋግጣለን፡፡

በዝህም ብቻም አያበቃም የወያኔ ሤራ ፡፡ቤተክርስቲያንን ለማዳከም ይህን አጀነዳ እነደያዙ በቤተክርስቲያን መዋቅር በቀጥታ መሳተፍም ጀምረዋል፡፡

በቅርቡ የአድዋ ድል የትግራይ ሕዝብ ብቻ እንደ ነበረ ጽፈው በትግራይ ክልል ወጣቱ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ያለው አመለካከት እንድለወጥ(To Brainwash) ያሰራጩትንና ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቁትን ገብረ ኪዳን ደስታን መጥቀስ ይቻላል::

እነደ ጩሉሌ ነጣቂ አስመሳይ መነኮሳት መብዛታቸው ከተሐዲሶ መናፍቃን ባሻገር የዚህ ሤራ አካል ሳይሆን አይቀርም::ሰሞኑን ዋልዲባ ገዳምን አስመልክቶ የተሰጠው የቤተክህነቱና የቤተመንግሥቱ መግለጫ “የዐይጥ ምስክር ድንቢጥ” ዓይነትና ከእውነት የራቀ የሆነው አንዱ የዚህ ሤራ ይመስለኛል::

እስኪ አቡነ ጳውሎስና ጋሻ ጀግሬዎቻቸው እስካሁን ከቤተክርስቲያን የዘረፉትን ገንዘብ ገምቱ: የት እየሄደ ነው ?

Haile Michael zemerahe berhanat said...

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ኦርቶዶከሳዉያን:-በቤተክርስቲያናችን ላይ የሚደርሰው ተጽእኖ በዓይነቱ ከኅቡእነት ወደ ግልጽነትና ንቀት ወደ ተሞላበት :መንግሥት እስካሁን ሰድቦ ለሰዳቢ ስሰጥ ከነበረበትና በሃይማኖታችን ላይ በተለያዩ አካላትና በባለሥልጣናቱ ለሚደርሰው ተጽእኖ ጆሮ ዳባ ልበስ እያለ ከሚያፍንበት ራሱ በግልጽ ገዳማቱንና አብያተክርስቲያናቱን ወደ ማፍረስ በተሸጋገረበት በብዛት ደግሞ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት የተቀናጀ ኃይል ተልእኮውን በግልጽ እየፈጸመ ባለበት የቤተክርስቲያንን ሕልውና ለማስቀጠል "ምን እናድርግ ? "ማለት ግድ ይሆናል::በግፍ የተገደለን አንድ ሕጻን መረጃ ለማጥፋት አስከሬን ሳይመረመር “ቅበሩት!” ማለት ምን ማለት ነው?(http://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=906:2012-03-21-14-41-35&catid=1:-&Itemid=18)ወዴት እየሔድን እንደሆነ እስኪ አስቡት:: ይህ ሁሉ ግፍስ በአጋጣሚ ብቻ የሚከሰት ይመስላችሁዋል ወይስ የሚሳበበው የውጭ አክራሪ እስልምና ብቻ ይማስላችሁዋል?

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አፍሪካን ወክለው ስለ ካርቦን ልቀት እንዳልደሰኮሩ ችግኝ ተከላ እየተባለ እንዳልተለፈፈ የዝቁዋላ ገዳም ደን ሰቃጠል መንግሥት እሳቱን ለማጥፋት እንደ መተባበር ለቅድስት ቤተክርስቲያን ካለው ጥላቻና ንቀት ብዛት የሚቀጠለው ደን መሆኑ እንኩዋ ጠፍቶት የማጥፋት ሥራውን እሳቱ ሳይጠፋ ጠፍል በማለትና ለማጥፋት የሚሄዱትንም በማስተጉዋጎል ለደኑ መቃጠል አስተዋጽኦ እንዳደረገ ያስተውሉዋል:: በቤቱዋ ቀጋ በውጭ አልጋ እነዲሉ:: “ኢትዮጵያ የ100 ዓመታት ታሪክ ነው ያላት የ3000 ዓመታት ታሪክ አላት የሚባለው ውሸት ነው”ያሉትን እነደ ዝቁዋላ ያሉ ሕያው አሻራዎችን በማጥፋት ለመጭው ትውልድ እውነት አስመስሎ ለማስተላለፍ ይሆን እንዴ ሤራው?

በቅርቡ በስልጢ ዞን ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ “እስከ ላይ ተነጋግረን ጨርሰናል አፍርሱ” ተብለው በትእዛዝ አይደል ያፈረሱብን?

ነገሩ አጋጣሚ ወይም የተወሰኑ ሰዎች ችግር ብሆንማ ቤተክርስቲያኑን ለማፍረስ የመንግሥትን ሥልጣን ተገን ያደረጉት ከ3 ባላነሱ ወንጀሎች ተከሰው ፍርድ ቤት ቆመው ባየን ነበረ 1)ሥልጣንን ያለ አግባብ በመጠቀም 2)ወንጀል በመሥራት 3) ሕዝብን በሕዝብ ላይ በማነሳሳት 4) የሃይማኖት ነጻነት በመጋፋት::

ዳሩ ግን ወደ አዲስ አበባ ተዛወሩ እነጂ ለእርሳቸው ሕግ ሚሠራ አይደለም::

እሰኪ የአራዳው ምድብ ችሎት በመምህር ዘመድኩን ላይ ያስተላለፈውን ብያኔ ተመልከቱ ::ነገ አንድ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ወይም አስመሳይ በቤተክርስቲያን መድረክ እንግዳ የሆነ ትምህርት ቢያስተምር ብንቃወም ጳጳስ ካልሆንን ዘብጢያ እንወርዳለን ማለት ነው::በጋሻው የሃይማኖት ችግር ከሌለበት እዉነተኝነቱን መረጋገጥ የሃይማኖት ጉዳይ ነው ፡፡ከዚያ ባለፈ የሃይማኖት ነጻነትን ተጋፍታሃል የሚለው የአራዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ ሌላ ጉዳይ ነው ::(ልብ በሉልኝ የቦሌ ምድብ ችሎት ዳኛን እያልኩ አይደለሁም )፡፡

Haile Michael zemerahe berhanat said...

እንደ እኔ እምነት በተለያየ ሚዲያ አውርተን ወዲያው ዝም ማለታችንና ተገቢውን ጥያቄ በተገቢ መልክ ለመጠየቅ አለመንቀሳቀሳችን ለመንግ ሥትና ለአጽራረ ቤተክርስቲያን የልብ ልብ እንድሰማቸው ያደረገ ይመስለኛል:: እንዲህ አውርተን ፈሪዎች መሆናችንን ከሚናስመሰክር ዝም ብንል ይሻላል ::ምክንያቱም ዝም ብንል ቢያንስ ከሰሙ ………….. እየተባለ እንዲህ በንቀትና በግልጽ በድፍረትም በቤተክርስቲያን አይዘበትም ነበረ::ከተነጋገርን ከሰማን ካየን ወደ መፍትሔ እንሂድ ወይ አናውራ ዝም እንበል::አሁን የቤቱ ግድግዳው ተበልቶ አልቆአል ::የቀረው እያንዳንዳችንን ማተብ በጥስ ሃይማኖት ለውጥ የሚል አዋጅ የጣሪያው መቃጠል ነው፡፡በ

ስለዚህ ብንዘገይም የባሰ ሳይመጣ አሁን ወደ መፍትሔ እንሂድ:-

1) አባቶቻችን ካህናት ይህን ሁሉ ጥፋት ላያዉቁ ይችላሉ፡ ቢያዉቁም አቡነ ጳውሎስና መንግሥት እጅና ጉዋንት ስለሆኑ (ለመንግሥት ህልውና ቅድሚያ ስለሚሰጡ) ካህናቱም በብዛት ቤተሰብአቸውን የሚመሩት ከቤተክርሰቲያን ከሚያገኙት ገቢ ስለሆነ ከፊት መሆን ልከብዳቸው ይችላል::

2) ስለዚህ በሰበካ ጉባኤ በሰንበት ትምህርት ቤት በአባልነት ያለን በተላይም ዲያቆናት እንቀሳቀስ ::

3) እስካሁን ያዩትና የሰሙት ከበቂ በላይ ቢሆንም መረጃ ለመእመናን በማዳረስ ረገድ በርትተን እንሥራ: ይህንንም መረጃ በቀላሉ ልዳረስ በሚችልባቸው አከባቢዎች በተለይም በዩኒቨርሲቲዎች በኮልጆች በቴክኒክና ሙያ ተቁዋማት እናተኩር ::

ነገሩ ወደ ውጤት ከመምጣቱ በፊት ለማስፈራራት እንዳይጠቀሙት ጥያቄያችንን በአንድነት እስከምናቀርብበት ቀን ድረስ በጥንቃቄ እንሥራ ይህንንም እስካሁን በቤተክርስቲያን ላይ በመንግሥት በአጽራረ ቤተክርስቲያን የደረሱ ግፎችን በመረጃ በማጠናከርና በመላክ የሰሙትም እንዲሰሙና የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጅነት ግድታቸውን እንድወጡ በማሳሰብ በfacebook እናስታውቅ በemail እንላክ::

በቤተከርስቲያን ላይ እስካሁን የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን የጥፋት ሤራ በመረጃና በዝርዝረ በማስቀመጥ መፍትሔ በፍጥነት እንድሰጥባቸው ቢያንስ ፈርማ ለማሰባሰብ እንቀሳቀስ፡፡ይሀንንም በሰበካ ጉባኤ በሰንበት ትምህርት ቤት እንጀምር፡፡ ምክንያቱም የሰበካ ጉባኤ አባል ያልሆነ ቤተሰብ የለምና፡፡ የሰበካ ጉባኤ አመራር አባላትም ከምእመናን ከሰንበት ትምህርት ቤት ከካህናት የተወጣጡ ናቸውና ፡፡

ይህን ስንል ፖለቲካ የሚመስላቸው ልኖሩ ይችላሉ: በእርግጥ በፖለቲካው ዐይን ካዩ ፖለቲካ ልሆንባቸውም ይችላል::

እሱማ ዐራት ኪሎ ጠቅላይ ቤተክህነት ለተለያየ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ትንሽ ብዛት ያለው ሰው ከተገኘ ሁሉ ለመንግሥት ፖለቲካ መምሰል ከጀመረ ቆይቶአል::“.....

ታስታ

ውቅ ከደረቱዋ ትታጠቅ’” እንዲሉ :: እዉነት ፍትሕ ካለ ይህን ያህል ምን አስፈረው: መንግሥትን!?

መንግሥት መጣብን እነጂ እኛ አልሄድንበት::

ከጸሎት ባሻገር ሰማዕትነትን

እነደ አግባቡ መክፈል ተገቢ ባይሆን ኖሮማ የዋልድባ መነኮሳት”…….. የሚትሠሩት በእኛ መቃብር ላይ ነው::” በማለት ስብሰባ ረግጠው ባልወጡም ነበር ::መቼም ከመነኮሳቱ በላይ መንፈሳዉያን ነን እንደማንል እርግጠኛ ነኝ::

እኛ በፋሽስት ጣሊያን ጊዜ የነበርን ቢሆን “አይ እግዚአብሔር ከሰማይ መቅሰፍት አውርዶ እስኪያጠፋቸወ ዝም እንበል” ሳንል አንቀርም ::“ እግዚኦ እግዚእነ ኢታርዕየነ ሙስናሃ ለቤተክርስቲያን”

Anonymous said...

ተቀበሉ ለማለት እና እነዚህም ተሰብሳቢዎች ሀገረ ስብከቱና ማኅበሩን ጨምሮ የአቶ አባይ ጸሀዬን ቃል እንዲያስተጋቡ ተፈልጎ ከሆነ የሚሳካ አይመስለኝም። ሙስሊሞች አንድ ሼክ የሰገደበት ቦታ ስለሆነ ይከበርልን ብለው እያስከበሩ ባሉበት ሀገር የአብያተ ክርስቲያናትን መፍረስ ተስማምቶ የሚወጣ ክርስቲያን ሊል ነኝ አይችልም። በእውነት እምነታችን የሚፈተንበት ወቅት ላይ ነን። የቤተክህነት ተወካይ ነን ባሉት እጅግ አዝነናል። አሁን የቀሩን ሀገረ ስብከቱና ማኅበሩ ናቸው። የማኅበሩ አቋም በተግባር የሚፈተንበት ወቅት ነው። በብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ኮርተናል። ተዋህዶ የምትፈልገው እንዲህ ያለውን አባት እንጂ ህሊናውን ለፍርፋሪ እና ስልጣን የሸጠ አይደለም።

ልማትን ከማንም በላይ እንደግፋለን በአብያተ ክርስቲይናት መፍረስ እና በገዳሞቻችን መደፈር ግን አንደራደርም!!!

Anonymous said...

Kgonchu nen bertu!!!

Anonymous said...

እነዚህ ደም ጠጪዎች አቡነ መለኬ ጼዴቅንና ሌሎች አባቶችን እንደ ገደሉ አባታችን አቡነ ኤልሳዕንና ሌሎችንም አባቶች በስውር እንዳይገድሉብን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል

Anonymous said...

waldeba is in kilil one why kilil three talks about it.TPLF decides whatever in the country not beaden amara

lele said...

YAKEDOSANE AMELAKE YERADANALE

lele said...

EREDANE AMELAKA KEDOSANE

Anonymous said...

የዋልድባን እና ባጠቃላይ የገዳማቱንና የአብያተ ክርስቲያናቱን ሁኔታ አብሮ ለመስራት አለም አቀፍ የሆነ ግኑኝነት መፍጠር ያስፈልጋል ለዚህም ስራ አንድ የምታደርገንን ድህረ ገጽ ደጀ ሰላምን መጠቀም የምንችል ይመስለኛል :: በመላው አለም ያለን የተዋህዶ ልጆች አንድ በመሆን በሀገራችንና በቤተክርስቲያናችን ላይ የሚመጣውን ፈተና ልንመክት ይገባል::

Anonymous said...

Dear Dejeselam,

You said, the Pop requested a prayer. Please post the prayer. And let us all pray togther for one week. I think, this is morethan anything. Talking the problem alone doesn't bring a solution

Anonymous said...

If we talk let us do something concrete. If we are not doing something concrete, let us stop talking. In my view, this is the right time to stand together for the dignity of our beloved church. So, let us discuss what we should do at home and abroad. Let us redeem the church or die! This is the choice we have. At least the coming generation might shine the coming peace in the church but that peace never comes unless we die today!!! Come on with concrete steps! Mewagat kalebinm enwaga le betekrstian!!! Patriarch Paulos kewist EPRDF kewich fejun:: Kes bekes kemigelun semaetinet enkebel!!!Ye betkrstian tewagiwoch eneho gizew!!!

Anonymous said...

የኢሕአዴግ አቋም የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች “ቦምብ በማፈንዳት ካልበጠበጡ አንተዋቸውም፤ እናሳድዳቸዋለን” የሚል ይመስላል፡፡ እንግዲህ የኢሕአዴግ ፍላጎት ይህ ከሆነ ምን አማራጭ አለን?

MelkameKene said...

Dear s the real son of Tewahido, this is the right time to save our churches from ruin. Do we have the history of ruining churches legally with the name of state government? For me this is the first bad historical era of Ethiopians (not only Christian but also our Muslim brothers). Look ስኳር ፋብሪካ is deliberately fabricated attachment case to the church for getting relief from their political stress. Have you hear in German radio one official of the government said during the interview “ራተ ቤተክርስቲያን”. Wherever, the place for us every church has the same status. We are not evaluated our church on the building status instead, all they are the absolute home of The Holy Communion. Please let start something tangible. We should have to be practical Christian like our elders not websites heroes. We should have to start to say no and we don't have gut to negotiate on our religion. Otherwise in a near future we will the impact on every corners of the country. Don’t forget principles of Christianity are allowed to a holy and heroic pass for our religion and believe. What will wait more than "'እዴት ፀሎት ያውጃሉ አመጽ ለመቀስቀስ ነው እዴ" this? I prefer to die than hearing this. Sorry to say this but it is beyond my control, these Guerrilla Satan-fare are the real son of Satan who fully devoted to perform his mission.

lele said...

batame yasazenal lebe yesetachawe kamane gare eyatagafo mahonone yawakote alemasalanem

Anonymous said...

በቅድሚያ ሁሉም የሚችል አምላክ እግዚአብሄር ገዳማችን ከጠላት ይታደግልን በአሁን ሰአት ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሚሆነው ጸሎት ነው እንደ ብጹአባታችን በመላው አሜሪካ ባሉት በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያንም ጸሎተ ምህላ መታዎጅ አለበት:: ሃይል ወዳለው መጮህ

Anonymous said...

enedate nabare sebesabawe???????????????????????????????????I WAIT

Anonymous said...

i wait

lamelame europe said...

enedate nabare sebesabawe???????????????????????????????????

Anonymous said...

abatoche tsaleyolen

Anonymous said...

የተከበራችሁ ደጀሠላማውያን [የኢሕአዴግ አቋም የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች “ቦምብ በማፈንዳት ካልበጠበጡ አንተዋቸውም፤ እናሳድዳቸዋለን” የሚል ይመስላል፡፡ እንግዲህ የኢሕአዴግ ፍላጎት ይህ ከሆነ ምን አማራጭ አለን?] የሚለውን አስተያየት ከሰጠሁ በኋላ እራሴ ላደርገው እችላለሁ? ብዬ ጠየኩ፡፡ በእውነት አላደርገውም፡፡ ምክንያቱም እራሴን እወዳለሁ፡፡ ለዚህም የቤተሰብ ኃላፊ መሆኔን እነደ አንድ ምክንያት አሰቀምጣለሁ፡፡ ምክንያት ባይኖረኝ ግን ቢያንስ አንድ ጸረ-ቤተክርስቲያን የማጠፋ ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ በእኔ አስተያዬት እንዳትገፋፉ ይቅርታ ጠይቄያለሁ፡፡

Anonymous said...

dear haile michael, melkam qen, asteyayet sechiwoch, egziabher amlak yibarkachihu! ahun betechirstian yemtfelgew endih yale tiwled new.tarikachinn zerfew chersewal ahun yalechin metsinagnachin qidest betecirstian nat! ersuan keqemun min qomin bilen enaweralen? ebakachihu zede fetren kewere yezelele sira mesrat enjemir.ye egna zimta lelawnm sayasatan ahun eninesa egizabher ke egna gar new please lets do it instead of talking...

Anonymous said...

menawe selasebesabawe zeme alachohe?ARA ATASECHANEKONE

Anonymous said...

Anonymous Haile Michael zemerahe berhanat said...

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ኦርቶዶከሳዉያን:-


“ እግዚኦ እግዚእነ ኢታርዕየነ ሙስናሃ ለቤተክርስቲያን”

March 28, 2012 3:05 AM
Anonymous Anonymous said...

ተቀበሉ ለማለት እና እነዚህም ተሰብሳቢዎች ሀገረ ስብከቱና ማኅበሩን ጨምሮ የአቶ አባይ ጸሀዬን ቃል እንዲያስተጋቡ ተፈልጎ ከሆነ የሚሳካ አይመስለኝም። ሙስሊሞች አንድ ሼክ የሰገደበት ቦታ ስለሆነ ይከበርልን ብለው እያስከበሩ ባሉበት ሀገር የአብያተ ክርስቲያናትን መፍረስ ተስማምቶ የሚወጣ ክርስቲያን ሊል ነኝ አይችልም። በእውነት እምነታችን የሚፈተንበት ወቅት ላይ ነን። የቤተክህነት ተወካይ ነን ባሉት እጅግ አዝነናል። አሁን የቀሩን ሀገረ ስብከቱና ማኅበሩ ናቸው። የማኅበሩ አቋም በተግባር የሚፈተንበት ወቅት ነው። በብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ኮርተናል። ተዋህዶ የምትፈልገው እንዲህ ያለውን አባት እንጂ ህሊናውን ለፍርፋሪ እና ስልጣን የሸጠ አይደለም።

ልማትን ከማንም በላይ እንደግፋለን በአብያተ ክርስቲይናት መፍረስ እና በገዳሞቻችን መደፈር ግን አንደራደርም!!!

March 28, 2012 3:55 AM
Anonymous Anonymous said...

Kgonchu nen bertu!!!

March 28, 2012 8:46 AM
Anonymous Anonymous said...

እነዚህ ደም ጠጪዎች አቡነ መለኬ ጼዴቅንና ሌሎች አባቶችን እንደ ገደሉ አባታችን አቡነ ኤልሳዕንና ሌሎችንም አባቶች በስውር እንዳይገድሉብን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል

March 28, 2012 9:49 AM
Anonymous Anonymous said...

waldeba is in kilil one why kilil three talks about it.TPLF decides whatever in the country not beaden amara

March 28, 2012 11:19 AM
Anonymous lele said...

YAKEDOSANE AMELAKE YERADANALE

March 28, 2012 11:21 AM
Anonymous lele said...

EREDANE AMELAKA KEDOSANE

March 28, 2012 11:25 AM
Anonymous Anonymous said...

የዋልድባን እና ባጠቃላይ የገዳማቱንና የአብያተ ክርስቲያናቱን ሁኔታ አብሮ ለመስራት አለም አቀፍ የሆነ ግኑኝነት መፍጠር ያስፈልጋል ለዚህም ስራ አንድ የምታደርገንን ድህረ ገጽ ደጀ ሰላምን መጠቀም የምንችል ይመስለኛል :: በመላው አለም ያለን የተዋህዶ ልጆች አንድ በመሆን በሀገራችንና በቤተክርስቲያናችን ላይ የሚመጣውን ፈተና ልንመክት ይገባል::

March 28, 2012 12:51 PM
Anonymous Anonymous said...

Dear Dejeselam,

You said, the Pop requested a prayer. Please post the prayer. And let us all pray togther for one week. I think, this is morethan anything. Talking the problem alone doesn't bring a solution

March 28, 2012 1:08 PM
Anonymous Anonymous said...

If we talk let us do something concrete. If we are not doing something concrete, let us stop talking. In my view, this is the right time to stand together for the dignity of our beloved church. So, let us discuss what we should do at home and abroad. Let us redeem the church or die! This is the choice we have. At least the coming generation might shine the coming peace in the church but that peace never comes unless we die today!!! Come on with concrete steps! Mewagat kalebinm enwaga le betekrstian!!! Patriarch Paulos kewist EPRDF kewich fejun:: Kes bekes kemigelun semaetinet enkebel!!!Ye betkrstian tewagiwoch eneho gizew!!!

asbet dngl said...

ይህ ከዚህ በታች የተሰመረበት አባባል ወገን በትኩረት ልናየው ይገባል:: ወልቃይት የሚባል ሰም እንጅ᎓ወልቃይት ተወላጅ በሙሉ በዚህ 20 ዓመት ውስጥ እንደፈለሰ የቅርብ ግዚ ትዝታ ነው:: ዋልድባ ገዳምም ይኌው እድል እየጠበቃት ነው::
ዋናው ጉዳይ አሁን ድንበር መጋፋቱ ብቻ ሳይሆን ከአስርና ሃያ አመት በኋላ ዋልድባ ገዳም መሆኑ ቀርቶ ዋልድባ የሚባል አዲስ ከተማ ሊሆን እንደሚቺል ነው አጽንዖት ሊሰጠው የሚገባው።
ወንጂና መታህራ የሚባሉ ከተሞች የተመሰረቱት በስኳር ፋብሪካ ምክንያት ነው። ካልጠፋ ቦታ ኢትየጵያ ሰፊ ሀገር ሆና ሳለ ለምን ዋልድባ? ሁሉም ነገር ለኛ ብቻ ከሚል ስግብግብነት አልያም ቤተክርስቲያንን ከማጥፋት እቅድ ካልሆነ በስተቀር።
አባት ሆይ እባክህ᎓እባክህ ሰው አዘጋጅ::አሜን

Anonymous said...

Dear Brothers and sisters, the problem of waldiba and other monastries is not the begining. Let me tell you what is happening in the rural churchs of the country specially in Amhara region. The church is no more a palce of worship. It is a meeting place for political cadres to meet the people. It is a palce where development agents make discussion with people. It is a place where health extension workers preach about family planing etc. And if preachers are sent to preach in the rural churches, the cadres do not allow them even when they have permission to do so.While they say state and religion are different they are abusing the church. They are violating the teritory of the church. The worest thing with EPRDF is, it does not make public consultaion before formulation of law or implementaion of development project. They start to talk about public consultaion after the law is enacted by the parilament and implementaion of projects is already started. And afterwards they call meeting to let people accept their ill planned laws or projects. That is what we are all witnessing. They talk a single word from the priminster to the local ignorant cadres to convince people. And this is what they are planning on the meeting to be held with Gonder christians. I am a meber of EPRDF but I feel ashamed about this. I share the idea of Haile Michael that says " Waldiba shal be like wonji and metahara after few years"
I believe EPRDF has to revise this project. If not it will pay the price. No need to beg them what they fear is not GOD or The people...and 50 million christains can do alot of things. We do not oppose any development initiative in any corner of the country, but when the development violates the historic and constitutional right of the church, we do not accept it at all. All christians, including most of us, EPRDF mebers, do not support this project at this place. And our christian brothers and sisters you are not alone !!!

Anonymous said...

Interesting

samson mehari said...

ውድ ደጀሰላማውያን እንደምን አላችሁ...
በአሳለፍነው እሁድ አፕሪል 01-2012 በካናዳ ኤድመንተን ከተማ ውስጥ ብዛት ያላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ..የአባቶቼን ገዳም እረዳለሁ..በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን እና የገዳማት ቸግር ላይ በመወያየት በአሜሪካ የተካሄደውን አፋጣኝ ምላሽ በገንዘብ : በሞራል : በጸሎት እና አስፈላጊ በሆነው ሁሉ ለማገዝ በአንድ ድምጽ ተስማምተዋል::
በዚሁ ጉባኤ ላይ በአድመንተን ከተማ የሚገኙ የመድሃኒዓለም እና የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ምዕመናን እና አገልጋዮች መካከል እንዲሁም ከሁለቱም ወገን አይደለንም እኛ ሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት ጋር የምንሄድ ነን ሲሉ የተደመጡ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን: ሁሉም ልዩነታቸውን አስወግደው በወቅታዊ የገዳማት ችግሮች ላይ ግልጽ እና ጠንካራ ገንቢ ሃሳቦችን አንሸራሽረዋል::
በገዛ ፈቃደኝነት ተነሳስተው ይህንን ቅስቀሳ በማድረግ ጉባኤውን ያዘጋጁት ምዕመናን እና አገልጋዮች ያዘጋጁትን በፕሮጀክተር የታገዘ ገለጻ እና በራሪ ወረቀቶችን ለህዝቡ ካቀረቡ ቡሃላ: ከተሳታፊዎች የውይይት ሃሳቦች እና ጥያቄዎች ቀርበዋል: በአብዛኛው በዝቁዋላ እና በአሰቦት ገዳማት ላይ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ እና የአክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት ላይ አተኩሮ የነበረው የመደረኩ ገለጻ የዋልደባ ጉዳይ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ባለማቅረቡ ጥያቄ የቀረበ ሲሆን : ለዚሁም በቂ መረጃ ያላሰባሰብን በመሆኑ ከተሳታፊዎች መነሳቱ እንደማይቀርም በጋራ እንደምንወያይበትም እርግጠኞች ነበረን ተብላል:: በመጨረሻም ይህ ጉባኤ በቀጣይነት እንዲካሄድ እና ለመላው የኤድመንተን ምዕመናን ጥሪ ተደርጎ በማናቸውም ገዳማት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል የድርሻችንን ለመወጣት እንዲያስችል አስተባባሪ ኮሚቴ በመምረጥ እንዲሁም በአሜሪካ የማኅበረ ቅዱሳን ; ሰ/ት/ቤቶች አንድነት እና በዓለ ወልድ ማኅበር በእሳት ቃጠሎ ለተጎዱ ገዳማት በአዘጋጁት የባንክ አካውንት ገቢ የሚሆን ገንዘብ በማዋጣት ጉባኤው ተጠናቁዋል:: በኤድመንተን የሚገኘው የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በመፍቀድ ላደረገው አስተዋጻኦ ጉባኣኤው አመስግኖታል
ሳምሶን መሃሪ
ኤድመንተን : ካናዳ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)