March 27, 2012

የዋልድባ ገዳም ይዞታ መደፈርን የተቃወመ ሰላማዊ ሰልፍ በዲሲ ተካሄደ


·         ኤምባሲው ለሙስሊም ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊ ወገኖቻችን ያሳየውን ከበሬታ ለክርስቲያኖቹ አለማሰየቱ ግርምት ፈጥሯል፤
·         “መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱን ይንቃታል፤ ክርስቲያኑንም ይንቃል” (ሕዝብ)

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 18/2004 ዓ.ም፤ ማርች 27/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የኢሕአዴግ መንግሥት በዋልድባ እና አካባቢው  በግድብ ሥራ፣ በፓርክ እና በስኳር ፋብሪካ ግንባታ ስም የሚያካሒደውን ገዳሙን ድንበር፣ ትውፊት እና መንፈሳዊ ይዞታ የመግፋት መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ በመቃወም ላይ ላሉ ገዳማውያን አበው እና እመው ያላቸውን አለኝታነት ለመግለጽ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ትናንት በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመሰለፍ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።


በምእመናን አስተባባሪነት በተጠራ በዚሁ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በዋሺንግተን ዙሪያ ካሉት ከቨርጂኒያ እና ከሜሪላንድ ግዛቶች በተጨማሪ ከነርዝ ካሮላይ እና ከኒውዮርክ የመጡ ክርስቲያኖችም በሰልፉ ተካፍለዋል። በቤተ ከርስቲያን መካከል ያለው አስተዳደር መከፋፈል ሳይገድባቸው ከሁሉም አቅጣጫዎች የተመሙት ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ኃይለቃሎችን ይዘው ድምጻቸውን በክርስቲያናዊ ጨዋነት አሰምተዋል።  

በዕለቱ ከተሰሙት ኃይለ ቃሎች እና መፈክሮች መካከል ለአብነት ያህል “በዋልድባ ጉዳይ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድነት እንቆማለን፣ ጳጳሳት ውሳኔያችሁ ይሰማ፣  የአባቶቻችን ርስት ተጠብቆ ለትውልድ ይተላለፍ፣ የገዳማት አባቶቻችን መብት ይጠበቅ፣ መንግሥት የመነኮሳቱ ድምጽ ይስማ፣ ዋልድባ የቅዱሳን እንጂ የኢንቨስተር አይደለችም፣ አባቶቻችን ያስቀመጡልን ገዳማት ሲፈርሱ ዝም አንልም፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዝምታችሁ ይብቃ፣ ገዳማትን የሚያፈርስ መንግሥት አንፈልግም፣  የልጣኔ ምንጭ የሆነች ቅድስ ቤተ ክርስቲያን መብቷ ይከበርላት፣ ገዳማት የጸሎት ቦታ እንጂ የመዝናኛ ቦታዎች አይደሉም፣ አድባራትንና ገዳማትን ማጥፋት ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው፣ የአባቶቻችን ተረፈ-አጽማቸው ይከበር፣ አጽማቸው ቆፍሮ ማውጣት ይቁም ልማት ገዳማትን በማፍረስ አይመጣም፣ ሃይማኖታችን የማንነታችን መገለጫ ነው፤ ሃይማኖት ከሌለ ሀገር አይኖርም፣ ገዳማት የሚያፈርስ መንግሥት ተቀባይነት የለውም፣ ዱስ ሲኖደስ የገዳማትን ይዞታ የማስከበ ግዴታ አለበት፣ ገዳማትን ማጥፋት በታሪክ ያስጠይቃል፣ ገዳማትን የሚያፈርሱ አይከበሩም፣ ዋልድባን ለማጥፋት የሚሞክሩ ይጠፋሉ፣ ገዳማቶቻችን ታሪካችን ናቸው፣ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ለሃይማኖታቸው ዝም አይሉም፣ መንግሥት ሃይማኖታችን ከማጥፋት ይቆጠብ፣ አጥፊዎች ለፍርድ ይቅረቡ” ወዘተ የሚሉት ይገኙባቸዋል።

ገና በጠዋቱ ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ መትመም የጀመረው ሰልፈኛው እርስ በእርሱ ትልቅ የመረዳዳት መንፈስ አሳይቷል። የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚገኝበት አካባቢ የሌሎች አገሮች ኤምባሲዎችም በብዛት ስለሚገኙበት እና ለመኪና ማቆሚያ ምቹ ባለመሆኑ ሕዝቡ የየግሉን መኪና እየነዳ ለመምጣት የሚገጥመውን ችግር ለመቅረፍ በግላቸው ሕዝቡን የሚያመላልሱ ታክሲ ነጂ ኢትዮጵያውያን የትራንስፖርት አገልግሎቱን በግሩም ሁኔታ አካሂደዋል። ትብብሩ የሚያስመሰገን ነበር።

ሰልፉ ሲጀመር በመዝሙር እና መልእክታቸውን ከፍ ባለ ድምጽ ማስተጋባት ጀመሩ። በቦታው የነበሩት ፖሊሶች ብዙም ሥራ አልበዛባቸውም። ሰላማዊ ተቃውሞ ነበር። የሰልፈኛው ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ ለመኪና ማሳለፊያ የሚሆን ቦታ ለመክፈት የፖሊስ አጥራቸውን ዘረጉ። መፈክሩም፣ ግጥሙም፣ መዝሙሩም ቀጠለ።

የሰልፈኛው ስብጥር በዕድሜም፣ በጾታም የተለያየ ነበር። ሕጻናት ልጆቻቸውን ይዘው ከመጡት ባለትዳሮች ጀምሮ፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን አባቶች እና እናቶች የተሳተፉ ሲሆን ከምእመኑ መካከል ብዙም የማይታዩት ካህናቱ ነበሩ። በብዙ የፖለቲካ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ “ካልባረክን፣ እኛ ነን ግንባር ቀደሞቹ” የሚሉት አሁን ግን በዋልድባ ጉዳይ ብዙም መታየት አልፈለጉም። ምናልባት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት በመሆኑ “የሰው ዓይን” እንዲያርፍባቸው አልፈለጉም ይሆናል።

ቀደም ብሎ ለኤምባሲው በተነገረው መሠረት ሰልፍ አስተባባሪዎቹ ያዘጋጁትን ደብዳቤ ለማድረስ እና የምእመናኑንም ስሜት በኤምባሲው አማካይነት ለአገራቸው መንግሥት ለማሰማት ያቀረቡት ጥያቄ እጅግ ንቀት በተሞላበት ሁኔታ ውድቅ ተደርጓል። አቶ ሰሎሞን በተባሉ የአሜባሲው አታሼ አማካይነት ለተወካዮቹ ይሰጥ የነበረው መልስ የተሰላፊውን ልብ የሚያሳምም ነበር።
በክርስቲያኑ ኅብረተሰብ የተዘጋጀውን ሰልፍ ተመርኩዘው የራሳቸውን ድምጽ ለማሰማት የመጡ “የኢሕአፓ ወጣት ክንድ” አባላት ነን ያሉ ኢትዮጵያውያን መፈክር ያስቆጣቸው የኤምባሲው አታሼ “ደርግ ካሸነፈው ከኢሕአፓ ጋር አንወያይም” ሲሉ ተደምጠዋል። ሕዝቡም “ከኢሕአፓ ጋር ተወያዩ” አላለም፣ ወይም “እኛ ኢሕአፓዎች ነን” አላለም። ኢሕአፓዎቹ “ሰላማዊ ሰልፍ ሰባሪዎች” (ሰርግ ሳይጠሩ በሰው ሰርግ የሚመጡ ሰዎች wedding crashers እንደሚባሉት) እንጂ የሰላማዊ ሰልፉ አካሎች አለመሆናቸውን አስተባባሪዎቹ በግልጽ ተናግረዋል። “ጥያቄያችን የሃይማኖት ጥያቄ እንጂ የፖለቲካ ጥያቄ አይደለም” ሲሉም ተደምጠዋል። ይሁን እንጂ ኤምባሲው ምንም ዓይነት ለውጥ ሳያሳይ ይልቁንም ፖሊሶቹ ተሰላፊውን ጠራርገው እንዲያባብሩላቸው ለማዘዝ ሞክረዋል። ፖሊስ ግን “መብታቸው ነው” በሚል ጥያቄያቸውን አልተቀበለውም።  

በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ ጊዜያት በዚሁ ሥፍራ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱ ሙስሊም ኢትዮጵያውን ጥያቄያቸውን ኤምባሲው በክብር ተቀብሎ፣ ተወካዮቻቸውንም ጊዜ ሰጥቶ ወደ ውስጥ በማስገባት እንዳነጋገረ የሚያውቁ ክርስቲያን ተሰላፊዎች መንግሥት ለሙስሊም ወገኖች ያሳየውን አክብሮት ለክርስቲያኖቹ ባለማሳየቱ ከልብ አዝነዋል። አንዳንዶቹም “መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱን ይንቃታል፤ ክርስቲያኑንም ይንቃል” ብለዋል። የክርስቲያኑ ክፍል አንድነት ማጣት እና ድምፁ ላለመሰማቱና ላለመከበሩ ምክንያት መሆኑን ተገንዝበዋል።

አቶ ሰሎሞን የተባሉ አታሼ ያሳዩት አቋም የኤምባሲው በሙሉ እንዲሁም የመንግሥትም አቋም ይሁን አይሁን ውሎ አድሮ የሚታይ ቢሆንም ከዚህ የተሻለ ሊያደርግ እንደሚገባው ግን እሙን ነው። የሕዝብ ተወካዮችን ማነጋገር ውርደት አይደለም። የተነሣውንም ተቃውሞ ሊያለዝብ የሚችል ተግባር ይሆን ነበር። “ዳያስፖራውን ለመያዝ” እየሞከረ መሆኑን የሚገልጸው መንግሥት ከኖርዝ ካሮላይና እስከ ቦስተን ማሳቹሴትስ ድረስ ካሉ ግዛቶች የመጡ ክርስቲያኖችን ለጥቂት ደቂቃዎች እንኳን ለማነጋገር አለመፍቀዱ “የሕዝብ ግንኙነት ሀሁ” ለሚያውቅ ለማንኛውም ባለሥልጣን ትልቅ ስሕተት ነው።

ኤምባሲ ማለት የ“ፐብሊክ ሪሌሽን” ማዕከል ነው። የዲሲው ኤምባሲ ግን የዚያ ተቃራኒ ተግባር ሲፈጽም ውሏል። የሚያሳዝንም የሚያሳፍርም ነው። ሰልፈኛው ጸያፍ ቃላት ከመናገር የተቆጠበ፣ ክርስቲያናዊ ግዴታውን ለመወጣት የመጣ መሆኑን ለመገንዘብ ብዙም አዳጋች አልነበረም። የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚዎቹ እንዴት ባለ ሁኔታ እንደሚያዋርዱት ብዙ ልምድ አለው። ከዚያ ዓይነቱ ሰልፍ ፍጹም በተለየ ሁኔታ መንፈሳዊነቱን ጠብቆ የመጣውን አቤቱታ አቅራቢ መግፋት ትልቅ ዕድል ማበላሸት ነው -  በፖለቲካ ሚዛንም ቢሆን። ሪፖርተር ጋዜጣ በርዕሰ አንቀጾቹ ብዙ ጊዜ እንደሚያስተጋባው “የዚህ መንግሥት ዋነኛ ጠላቱ - ራሱ መንግሥት ነው”።

ኤምባሲው እንደሠራው ስሕተት ሁሉ የኢሕአፓ ፓርቲም ቢሆን ሌሎች ክርስቲያኖች ባዘጋጁት ሰልፍ ላይ የፓርቲያቸውን አቋም ለማንጸባረቅ ያደረጉት ድንበር ተጋፊ ድርጊት ሰልፉ ላይ ጥቁር ጥላ ጥሎ አልፏል። ኤምባሲውም የሰልፉን ተወካዮች ላለማነጋገር ጥሩ ምክንያት ሆኖለታል። ክርስቲያኑ ሕዝብ ግን የኢሕአፓን ዓላማ ብሎ ሳይሆን ቤተ ክርሰቲያኑን ብሎ መውጣቱን ኢሕአፓም ራሱ ማክበር ይገባው ነበር። የራሳቸውን ሐሳብ በሌላው ላይ ለመጫን መሞከር አይገባቸው እንላለን። ልክ እንደ ኤምባሲው ሁሉ ኢሕአፓ-ዎቹም በሕዝቡ ዘንድ ያላቸውን አመለካከት ያበላሹ ካልሆነ በስተቀር የተጠቀሙ አይመስልም። ሌላ አካል ያዘጋጀውን “ዝግጅት” ለመጥለፍ መሞከርስ ምን ይባላል? በሌሎች ቦታዎች ሊዘጋጁ ለሚችሉ ሰልፎች ትልቅ ትምህርት ነው። የኢሕአፓ መሪዎችም ከዚህ ስሕተት ቢታረሙ መልካም ነው። በእርግጥ ኢሕአፓዎቹን ይመሩ የነበሩት አንዳንድ ሰዎች ሌላው ሰልፈኛ የሚለውን እና የሚያስተጋባውን ቃል ደግመው እንዲሉ ለፓርቲ አባሎቻቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይሁን እንጂ ለሃይማኖታዊው ሰልፍ ፖለቲካዊ ትርጉም ማሰጠታቸው ተገቢ አልነበረም። “በዋልድባ የመሸጉ የፖለቲካ ኃይሎች” ለሚለው የመንግሥት ሐሰተኛ ውንጀላም ምክንያት ሰጥተዋል፤ ገዳሙን ከመጥቀም ይልቅ ሊጎዳ የሚችልበትን ተግባር ፈጽመዋል።

በጠቅላላው ሲታይ ግን ሰልፉ ክርስቲያኖች በእንዲህ ዓይነቱ ጉዳይ ለሃይማኖታቸው ሊጀምሯቸው ለሚችሉት ሌሎች ተግባራት ፈር ቀዳጅ ሆኖ አልፏል። ክርስቲያኖች ስለ መብታቸው፣ ንብረታቸው እና አጠቃላይ ይዞታቸው ጉዳይ ለብቻቸው ወጥተው የተናገሩበት ጊዜ የለም። ዋልድባ የዚህ የተዳፈነ ስሜት ቀስቃሽ ሆኗል። በዋሺንግተን ዲሲ የተጀመረው እንቅስቃሴ በሌሎች አገሮች በሚገኙ ክርስቲያኖች ዘንድ እንደሚደጋገም ይታወቃል። በሌሎች አካባበቢዎች የሚገኙ የመንግሥት ተወካዮች የዲሲ ኤምባሲ ኃላፊዎችን ዓይነት ስሕተት ይደግማሉ ብለን አንጠብቅም። ሕዝቡን አነጋግሩት!!!!!!    

ር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡

8 comments:

Anonymous said...

eskei european enenasa

Anonymous said...

Europian lemensat zegejet laye nen!
Europe gzew yegeletsal tezegaju!
Kes merhawi Memenu Lebete kerstyanu Metgnat yelebetem belewal!
Wegen Tenesaa!
Betekerstyan tefto anete atenorem betenorem aydelahem.
bedemu yemsertate nat mechem minm bidereg atetefam!
Dergem mewedkiaw endhu huneta nebrew!
Ayeee Ehadig mewdekiyah derse!
Medhanialem ejeun kanesa man yechelewal?

Anonymous said...

አባቶች ለሃይማኖታቸ ያላቸው እውነተኛነት ሲመች ወይም ሲደላ ብቻ መሆኑ በጣም ያሳዝናል ሁሉም የሚሮጠው ለስልጣን እንጂ እዉነት ለቤያንአስበው እዳልሆነ ከሰልፉ መረዳት ይቻላል በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገርግን አይዞአችሁ አለምን አሸንፌንፌአለሁና ተብለናል

Anonymous said...

mengist kristian hizibin ena betekristianin kenake eko koye. Egna feriwoch silihonin esey yiblene!!! Genam yebase yimetal!!! weri bich silehon ena mengistim yehin bahalachinin silemiyawik be betekristian lay yefelegewin kemadreg wede hola ayilm!!!

weri minim ayseram tegibar enji!!!

Anonymous said...

ከአቢዮቱ ጀምሮ ያሉ የኢትዮጵያ መንግስታት (ደርግና ኢሕአዴግ) እጅግ የበዛ ንቀትና ጥላቻ አላቸው፡፡ የደርግስ የለየለት ስለሆነ ብዙ አያነጋግርም፡፡ የአሁኑ ግን ይገርማል፡፡ በበረሃ በነበሩ ጊዜ ገዳማትን መጠለያ አድርገን ነበር እያሉ ሲያወሩ ሰምቸ አውቃለሁ፡፡ እነዴውም ከመካከላቸው አንዱ በገዳማውያኑ ሕይወት ተስበው እዚያው ዋልድባ መንኩሰው ከኖሩ በኋላ ቅርብ ጊዜ ማረፋቸውን ጋዜጣ ላይ አንብቤያለሁ፡፡ ሌሎቹ ግን (ምናልባትም ብዙዎቹ) በሦሻሊስታዊ አመለካከታቸው የተነሳ ለቤተክርስቲያን ከፍተኛ ንቀት አላቸው፡፡ ለምሳሌ ጠ/ሚኒስትሩ በእንድ ወቅት ሲናገሩ መጽሐፍ ቅዱስ እነደሚያነቡ ነገር ግን እነደማያምኑበት፤ እምነቱ ባይኖራቸውም በበረሃም በነበሩ ጊዜ ወደገዳማት ሲሄዱ እነደነበር ሲናገሩ እኔ ራሴ ሰምቻለሁ፡፡

ይህ እነግዲህ የሚያመለክተው ሲፈልጉ ቤተክርስቲያንን መጠቀሚያ ለማድረግ እነደሚጠጉ፣ መብቷን ለማስከበር ግን ምንም ደንታ እንደሌላቸው ያመላክታል፡፡ ለዚህም ትልቁ ማስረጃ አቡነ ጳውሎስን ወደመንበር ለማምጣት የኢሕአዴግ እጅ ያለቦታው ገብቶ ሲያቦካ እንደነበር መጥቀሱ ተጨማሪ ማስረጃ ነው፡፡

ከክርስቲያኑ ይልቅ ለሙስሊሙ ስለምን ልዩ ትኩረት ተሰጠው? እኔ እንደሚመስለኝ ክርስቲያኑ አጥፍቶ-የማጥፋት እርምጃ ስለማይወስድ ይሆናል፡፡

Let's SAVE WALDBA! together said...

ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፣
ደጀሰላም ስለዘገባው ከልብ እናመሰግናለን አዎ አሁንም ዝም አንልም በጸሎትም፣ በልመናም፣ በሰልፍም፣ ወይም በማንኛውም መንገድ በመጀመሪያ ወደ እግዚአብሔር እናመለክታለን በመቀጠል ደግሞ ወደ ምድራውያኑ ደግመን ደጋግመን ይሄ ነገር እስከሚቆም ድረስ፥ ቤተክርስቲያኒቱ ህልውናዋ እስኪከበር ድረስ እንቀጥላለን፤ ልመናችንን ጸሎታችንን እንዲሁም ትግላችንን ሰምቶ ዝም የማይል አምላክ እንዳለን በፍጹም እናምናለን።
"የቤተክርስቲያን ደጆቿ ይከበሩ!"
"መሪዎቿም በቅንንነት ከዘር ፖለቲካ ወጥተው ምዕመኑን ይምሩ"
"በዓለም ዙሪያ ያለች ቤተክርስቲያን አንዲት ናት"
በቀጣይነት ብዙ ሥራዎችን ለመሥራት ታስቧል እና ማንኛውንም መረጃ ወይም ድጋፍ ጸሎት ለምታደርጉልን ወገኖቻችን በሚከተለው ኢሜል አድራሻ ላሉልን

savewaldba@gmail.com
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያን እና ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን አሜን

የድር-ትዝብት said...

በአርግጥ የሰልፉ መንፈስ የተጠነሰሰው ሃይማኖታዊ ጥያቂን ኣንግቦ ቢሆንም ባልታሰበ ሁኔታ ግን የኣንድ የፖለቲካ ፕርቲ ከንፍ ነን በሚሉ ጋጠ ወጦች የሰልፉ ማንነት መልኩን ሊቀይር ችሏል። ይህ ደግሞ ለኤንባሲው ባለስልጣናት ኣሉታዊ መልስ ምክንያት ፈጥሮላቸዋል። ነገር ግን ምን አንደተፈጠረ ኣያውቁም ማለት ኣይደለም።ለማንኛውም ግን ወጣ ገባ አያሉ በክፉ ኣይናችው ሰልፈኛውን ሲገላምጡት የዋሉት የኤምበሲው ዘበኛ ይሁኑ ተላላኪ ማንነታችውን በውል ለማወቅ ኣልቻልኩም፤ ፖሊሶቹንም ለማዘዝ ሲቃቱ ታዝቤኣለሁ።ለሃገሩ አንግዳ አንዳይሆኑ ብየም ሰግቸ ነበር። ለማንኛውም ግን ወደፊት ለምናቅዳቸው ሰልፎች አነዚህን ተስፈኞች መዋጋት አንዳለብን ማወቅ ኣለብን።

Solomon birhanu said...

Yehe mengist gena bezu yiseral gen betekrestianen matfat aychelem tegten enkawemalen dengle kegonachen natna.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)