March 26, 2012

የቦሌው ችሎት በመ/ር ዘመድኩን ላይ የገደብ ቅጣት ወሰነ


·        መ/ር ዘመድኩን ይግባኝ ይጠይቃል::
·        ማስረጃ ያልቀረበላቸው የዐቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃዎች ውድቅ ተደርገዋል::
·        መ/ር ዘመድኩን በመንፈሳዊ አገልግሎቱና በማኅበራዊ ተሳትፎው ያቀረባቸው የቅጣት ማቅለያዎች ተቀባይነት አግኝተዋል::
 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 17/2004 ዓ.ም፤ ማርች 26/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት መ/ር ዘመድኩን በቀለ በዐቃቤ ሕግ በቀረበበት የስም ማጥፋት ወንጀል በብር 3000 መቀጮ እና በስድስት ወራት እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡ የ3000 ብር የገንዘብ ቅጣቱ ተከፍሎ የስድስት ወራቱ እስራት ሳይፈጸም በሁለት ዓመት ገደብ እንዲታይ ውሳኔ የሰጠው ችሎቱ ተከሳሹ ቀደም ሲል በዋስ ያስያዘው ብር 5000 ስለ መልካም ጠባይ ዋስትና ታግዶ እንዲቆይ ትእዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡

ፍ/ቤቱ ዛሬ፣ መጋቢት 17 ቀን 2004 ዓ.ም በሰጠው የቅጣት ውሳኔ÷ የፍርድ ቤትን ውሳኔ ጨምሮ የሌሎችን ሐሳብ መተቸት ሕገ መንግሥታዊ መብት መሆኑን አጽንዖት ሰጥቶበታል፡፡ መ/ር ዘመድኩን በማራኪ መጽሔት የግል ተበዳይ በተባለው በጋሻው ደሳለኝ ላይ ትችት መስጠቱ ሊያስጠይቀው እንደማይችል፣ ይሁንና ደንቆሮ መሃይም ማለቱ ‹የተበዳይን› ተቀባይነትና ሰብእና ስለሚጎዳ ተገቢ አለመሆኑን ምክር ሰጥቶበታል፡፡
መ/ር ዘመድኩን በተለያዩ አብያተ ክርስቲያን የሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት እና በኦዲዮ ቪዥዋል አሳታሚዎችና ተዛማጅ መብቶች ጥበቃ ዙሪያ በሚሠራው ማኅበር ውስጥ በጸሐፊነት የቆመለትን የሕግ ማስከበር አገልግሎት በተመለከተ እንደ ቅጣት ማቅለያ የቀረቡ ማስረጃዎችን በመቀበል በስድስት ደረጃዎች ከተቀመጡት የቅጣት እርከኖች በሁለቱ ብቻ እንዲቀጣ መወሰኑን ፍ/ቤቱ በቅጣት ሐተታው ውስጥ አመልክቷል፡፡
በአንጻሩ ዐቃቤ ሕግ በተለያዩ ቀናት/መዝገቦች የተከፈቱ ተመሳሳይ ክሶችን በመከፋፈል ‹‹ተከሳሽ ወንጀል መፈጸምን ልማዱ/አመሉ አድርጎታል›› በሚል ያቀረበውን የቅጣት ማክበጃ ፍ/ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል - መ/ር ዘመድኩን ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ክስ ቀርቦበበት ከተቀጣ በኋላ ሌላ ወንጀል በድጋሚ ስለ መፈጸሙ ዐቓቤ ሕግ ያቀረበው ማስረጃ ይሁን የቅጣት ሬከርድ የለምና፡፡
ከተላለፈበት የቅጣት ውሳኔ ይልቅ በችሎቱ ፍትሐዊ መስተንግዶ ደስ መሰኘቱን ያልሸሸገው መ/ር ዘመድኩን በቅጣት ውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ታውቋል፡፡ በአርማጌዶን ቪሲዲ የተነሣ በአራዳው ምድብ ችሎት በተላለፈበት የአምስት ወራት እስራት ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ የሚጠይቀው ይግባኝ በሂደት ላይ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
በሌላ በኩል መ/ር ዘመድኩን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስቸጋሪ በሆነው ዞን ሁለት እየፈጸመ በሚገኘው ሐዋርያዊ አገልግሎት እርስ በርሳቸው ጠብ በማንሣት የሚደባደቡና የሚፈነካከቱ እስረኞች ከመጥፎ ድርጊታቸው መወገዳቸው ተገልጧል፡፡ ጥቂት የማይባሉት ከመጥፎ ሱሳቸው ለመላቀቅ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡
መ/ር ዘመድኩንን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ እስር ቤቱ የገቡ የሰንበት ተማሪዎች፣ ካህናትና መነኮሳት በትንሹ የጀመሯትን ቤተ ጸሎት በማስፋፋት ከነግህ እስከ ሠርክ በጸሎት፣ ምክክርና መንፈሳዊ ትምህርት በሚፈጽሙት አገልግሎት ከርኩስ መንፈስ የተላቀቁ፣ የበጠሱትን ማዕተብ መልሰው ያሰሩ ብዙዎች ናቸው፡፡
መጪውን የትንሣኤ በዓልም ከበጎ አድራጊ ምእመናን ጋራ በመነጋገር በከፍተኛ ችግር ላይ የሚገኙ ታራሚዎች በመሠረታዊ ፍላጎቶቻቸው በማሟላትና ሌሎች ደማቅ መንፈሳዊ መሰናዶዎች ለማክበር በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡

10 comments:

Anonymous said...

መምህር ዘመድኩን አምላክ አገልግሎትህን ይባርክ! እግዚአብሄር አላማ አለው ፣ ማን ያውቃል በዚህ ምክንያት በእስር ሆነው የጠፉትን በጎች ሊሰበስብ ቢሆንስ? አይዞህ እግዚአብሄር ያበርታህ! እማምላክ ከክፉ ሁሉ ትሰውርህ!

Anonymous said...

"ለእግዚአብሔር፡የምስጋና፡መስዋዕት፡ሰው፥
ለልዑልም፡ሰለትህን፡ስጥ፤
በመከራ፡ቀን፡ጥራኝ፥
አድንህማለሁ፡አንተም ታከብረኛለህ።"
መዝ. ዘዳዊት ምዕ.49 ከቁ. 14-15
ዲያቆን፡ዘመድኩን፡በርታ!የአባቶችህ፡የአቡነ፡ተ
ክለ፡ሃይማኖትና፡የአቡነ፡ገብረ፡መንፈስ፡ቅዱስ፡አ
ምላክ፡ካንተ፡ጋር፡ነው።እግዚአብሔር፡አምላክ፡ተ
ጋድሎህን፡በታላቅ፡
ደስታ፡እንደሚቀበለው፡ተዋሕዶ፤ኢትዮጵያ፡በሙ
ሉ፡የምናምንበት፡ነው።አብረንህም፡ቆመናል!ወዮ
ላቸው፡ለወንጀሉህና፡ላስፈረዱብህ!በታላቁ፡የፍር
ድ፡ቀን፡ሁሉም፡እንደየሥራው፡የፈረድለታል፣ወይ
ም፡የፈረድበታል።እግዚእትነ፡ማርያም፡ልጆችህን
ና፡ባለቤትህን፡ትባርክ።አብረንህ፡ቆመናል!!

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Hirut Ayano said...

Le memihir Zemedikun tsinatin eyetemegnehulet le tosm mefichaw lemideregew neger kebereketu tequwadash ehon zend bego adragiwochun yemagegnibet adrasha post bitadergulign des yilegnal ameseginalehu
Hirut Ayano
South Dakota

wub said...

Neger hulu lebego newu ... !

Anonymous said...

''Bemot tila mekakel enkuan bihed ante kene gar nehena kifun alferam.''Mezmur 22.
Wey wendim zemdkun betam edelegna nehe eshi Egziabher betleyaye menged eytetkmbeh new yalew ayehe ye anten esir bet megbat Egziabher yefelgew beza west yaluten lijochun selmifelgachew new be ante lay adero kalun endiyastemirachew malet new berta tsenatun bertatun yadelh yeyaznew samint '' GEBREHER ''aydel mekilithen eyatrefk new tamagne bariya huneh .Any way le wedajocheim lene begashaw Amilake kidusan Aba paulosin chemiro libona ,kena amelekaket seteto wede aymiroachew yemelisachew .Yemiyasadiduachun meriku meriku enji atrgemuachew selemil ye Amlakachin kal.

Kekirstos fiker yemileyegne
manew?
Mekera chegir sekay weys merakot new 2?

Miskin girl said...

መ/ር ሁሉም ነገር ለበጎ ነው የታስርከውም ለበጎ ነው በርታ

asbet dngl said...

የድንግል ማርያም ልጅ እንዲህ አይነቱን መንፈሳዊ ሞራል ያላቸውን ያበርክትልን :: በርቱ

Anonymous said...

ዘመድኩል መንፈሰ ጠንካራ የሆነ ሰው መሆኑን ባያቀኝም በሁኔታው ኢፍትሀዊነት ተነሳስተን ከጟደኛዬጋ በጎበኘሁት ጊዜ አረጋግጫለሁ በሀገራችን በሁኑ ጊዜ ሀሰተኛ ናዘራፊ የሚወደስበትና የሚሾም ጊዜ ነው እንዲሁም ፍትህ የሚዛባበት ዳኝነቱም እንደከሳሹና ተከሳሹ ግለሰብ ሁኔታ ውሳኔውም ተለዋዋጭ እውነት የመነመነችበት ስርአት ነው ያለው በኛልብ ውስጥ የዘመድኩን ተግባር የሚያሸልመውና የምንጋራው ነው ደጀሰላሞች ስራችሁን እግዚአብሔር ይባርክላቹሁ

Anonymous said...

you are lucky zemedkun.

Anonymous said...

selam deje selam jweane negr hjasasenal wldba waldba wa wa

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)