March 23, 2012

የመንበረ ፓትርያርኩ ጠ/ቤ/ክ መግለጫ ቤተ ክርስቲያን-ቤተ ክርስቲያን አይሸትም


 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 14/2004 ዓ.ም፤ ማርች 23/2012. READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በዋልድባ ገዳማት ክልልና ዙሪያ የሚካሄደው ‹‹የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት›› ስለተፈጠረው ውዝግብ፣ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳምና አካባቢ እንዲሁም በደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ሳሙኤል ገዳም ይዞታ በሆኑ ደኖች ስለደረሰው ቃጠሎ አደጋ የሰጠው መግለጫ ምንም ዓይነት የቤተ ክርስቲያንም ሆነ የቤተ ክህነት ጣዕም እና ቃና የሌለው ሆኖ ተገኝቷል፡፡


ስለ ጉዳዮቹ አጣራን ብለው መግለጫ የሰጡት የቤተ ክህነቱ ባለ ሥልጣናት በዋልድባ መንግሥት በአቶ ዓባይ ፀሐዬ በኩል የሰጠውን ፈርጠም ያለ መግለጫ የደገመ ሲሆን ስለ ገዳማቱ ላይ ስለተነሣው እሳትም ማንንም የማያረካ መልስ ሰጥተዋል። “ገዳሙን ለፖለቲካ መጠቂማነት” ለማዋል የሚፈልጉ መነኮሳት መኖራቸውን ለመግለጽ የሚሞክረውን የመንግሥት ክስ የቤተ ክህነቱ ልዑካንም ደግመውታል። በርግጥም ይህ መግለጫ የቤተ ክርስቲያናችን ሳይሆን የራሱ የመንግሥት ከመምሰሉም በላይ ምንም ዓይነት ሃይማኖታዊ ቃና የሌለው ሆኖ ተገኝቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በገዳማት ያለውን ችግር ክብደት “ዝቅ ለማድረግ” እሳቱ ሳይጠፋ ጠፍቷል በሚል የሚያቀርቡት ዘገባ ሕዝቡን ከማበሳጨቱም በላይ ወዳልተፈለገ ጥርጣሬ ውስጥ እየከተተው መሆኑን የጀርመንድምጽ ሬዲዮ ዶይቸ ቨለ ዘግቧል። እሳቱን በመከላከል ላይ ያሉት ወገኖች ከእሳቱ ጋር እየታገሉ ባሉበት ሁኔታ ወደ እሳቱ አካባቢ ሳይደርሱ “ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ውሏል” የሚል ዘገባ በማቅረብ ሕዝቡን ማደናገራቸውን እንዲያቆሙ እየተጠየቀ ነው።
የእሳቱ መነሣትና ሕዝቡ የሰጠው ትኩረት ያስጨነቃቸው የሚመስሉት ዘገባዎቹ ጉዳዩ ከሕዝብ መወያያነት እንዲወጣ እና የሕዝቡ መነሣት ውኃ እንዲቸለስበት መፈለገቻው አስገርሟል። በተቃራኒው ግን ምእመናን ከዕለት ወደ ዕለት ስለ ጉዳዩ ለማወቅ አላቸው ጉጉት እየጨመረ፣ ተግባራዊ ምላሽ መስጠታቸውም እየተጠናከረ የመጣ ሲሆን ከአገር ውስጥ እስከ ባሕር ማዶ ርብርቡ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡

8 comments:

Ewunet Tenagari said...

Sooner than later The Almighty God will say to both the people in the palace and in the Church leadership: 'MENE,MENE,TEKEL,UPHARSIN/PERES. Be ready to witness the miracle of God.

Anonymous said...

SEALILENE KDIST
Is that any poletical person can exist in WALDBA?
This is unblivable that given both by BETEKHNET and the government, they are already shown us themselves and their poprpose is try to kill our church so we must be weakup!!!!
GOD BLESS ETHIOPIA.

Anonymous said...

This is what we expect from 'Aba' Paulos and his 'buchiloch'. Did you expect something that benefit the church? From my side, never. I will never expect something good from 'Aba' Paulos.

A3a said...

What lessons can we learn from The muslimes movement in Awelia?

MAN YAZEWAL said...

ለመሆኑ ይህን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ሰዎች እነማን እንደሆኑ ሊታወቅ ያ ስፈልጋል። ጎበዝ በቤተ ክህነት ታሪክ ውስጥ እንደዚህ
ዓይነት መግለጫ በእንደነዚህ ዓይነት ምናምንቴ ሰዎች ሲሰጥ የመጀመሪያው ነው። ብዙውን ጊዜ መግለጫ ሲሰጥ የምናየው በፓ ርያርኩ በኩል እንደሆነ የሚታወቅ ነው ።
መግለጫውን ያቀረቡ ሰዎች እነማን ናቸው ብለን ብንጠይቅ ቤቤተ ክህነታችን ውስጥ የመንግስትን ሥራ የሚሰሩ ካድሬዎች ናቸው። ሊቀ ማዕምራን በሚል ሽፋን ስም ወደቤተ ክህነት የገቡት ኃይለ ሥላሴ በአዲስ አበባ በድሬ ደዋና በፍቼ ሀገረ ስብከት ከመንግስተ የተሰጣቸው ተልዕኮ በማስፈጸም የሠሩ ዛሬም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ከሐይማኖታዊ ሥራ ይልቅ የፖለቲካው ን ሥራ በሰላይነት የሚሰሩ ናቸው። አቶ ተስፋዮ የተሻለ ሕሊና ያለው የፓርቲው አባል ሲሆን በትንሳኤ ዘጉባኤ ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ ለብዙ ጊዜ የሰራ ሰው ነው። እስክንድር ምንም ዓይነት የቤተ ክርስቲያንም ሆነ የዘመናዊ ዕውቀት የሌለው ካድሪ ነው። ቤተ ክህነቱን ከሚሰልሉትና አባቶች እንዲደበደቡ ያደረጉ የመንግስት ቅጥረኖች ናቸው። እንኩና ከነዚህ የመንግስት ቅጥረኖች ከአባት ተብየው ምንም በማንጠብቅበት በዚህ ፈታኝና አስቸጋሪ ወቅት ይህን መግለጫ ስሙ የቤተ ክህነት ተብሎ ቢወጣ የመንግስት መግለጫ ነው። የሚደንቀኝ ቤተ ክርስቲያኗ ገፍተኛ ገንዘብ እያወጣች የምታስተምራቸው የከፍተኛ መንፈሳዊ ምህርት ቤት ተማሪዎች እያሉ እንደነዚ ዓይነቱ በሁለት ቢላ የሚበሉ ሰዎችን በቤተ ክህነቱ ውስጥ መኖራቸውን ሳይ በቅርቡ ፍትህ የተባለ ጋዜጣ ሲኖዶሱና ሙጅሊሡ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ ያለው ለካስ እውነቱ ነው። በዚህ ሰዓት እናንተ ዝም ብትሉ እነዚህ ድንጋዮች ያመሰግናሉ እንዲል። ሃላፊነት ላይ ያሉ የእግዚአብሔርን ሥራ መሥራት አቅቶቸው በሚገኙበት ሰዓት እግዚአብሔር ከተናቁት ጋር ከወጣቱና ከምእመኑ ጋር እየሰራ መሆኑን ዓይናችን ያየው ዝቋላ ላይ ነው።

Anonymous said...

አይግረማችሁ ወገኖቼ አባ ጳውሎስ እያሉ ቤተ ክርስቲያን ሰላምና የተማረ ሰው አያገለግላትም እነ "አቶ እና ወዛዝርት ናቸው እየመሩአት ያሉት የቤተ ክርስቲያናችን ቀሳጮች እንዲህ ታሪኳን ጥንታዊነቷን ለማጥፋት ሲሯሯቱ ሐብቷን ንብረቷን ሲዘሩፉ ሲሸጡ ሲለውጡ አብረው ተባባሪዎች ናቸው መስሎአችው እንጂ እግዚአብሔር ቤቱን ይጠብቃል የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ሀገራችንና ሐይማሆታችንን ይጠብቅ

Anonymous said...

የሚገርም ነገር ነው ቤተ ክርስቲያናችን የሚመራት ስው አጣች? ከ50 በላይ የጳጳስ ክምችት አለ አይደል! ሠራቸውን ትተውታል እንዴ? እንደተዉትማ ያስታውቃል ባንድ በኩል ተቃሪኒ ሃይማኖቶች በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እንደፈለጉ አፋቸውን ሲያላቅቁ ገዳማቱ ሲቃጠሉ ጥንታዊው ንዋየ ቅድሳት ሲዘረፍ በየትም ዓለም ተደርጎ የማያውቅ ቤተ ክርስቲያን ፈርሶ ሸንኮራ አገዳ ሲዘራ ክርስቲያኖች ሲታረዱ.....አባቶች ግን ምን ቸገረኝ በእኔ እስካልመጣ ብለው መቀነጣቸው በእጅጉ አሳፋሪ ነው ከእግዚአብሔርን የተሰጣቸውን አደራ ለመወጣት ምነው ፈሩ? እንዲህ ነው እንዴ አደራ? እውነት ተናግረው እንደ ጥንቱ አቡነ ጰጥሮስ በሥጋቸው ቢሞቱ በነፍሳቸው ሕይወት አላቸው አረ ሰማይና ምድርን በዘረጋ በእግዚአብሔር ስለ ድንግል ማርያም እንደው በጨበጣችሁት የክርስቶስ ዙፋን በሆነው በመስቀሉ ብላችሁ ለምእመናን አለኝታነታችሁን ግለጡ!ቤተ ክርስቲያናችን ወደ አልተፈለገ መንገድ እየሄደች ነች በዓም የሚያስፈራ ወቅት ላይ ነኝ ትውልዱ ሲረግማችሁ እንዳይኖር ከእናተ በፊት ወደ እግዚአብሔር የተጠሩ ምንኛ የታደሉ ናቸው አባቶች አናተን ልንናገር አይገባንም እባካችሁ የመንፈስ ቅዱስን ዝናር ታጠቁና ከአላውያን ነገሥታት ጋር ተዋጉ... ይቀጥላል

wub said...

Bewunu enezih sewoch kebetekihinet woyis kebetemengist? Lemehonu silebetekrstian angebgabi guday meglecha lemestet papasatu yethiedu? Sirachewus minyihon? Yegedamatun chigr, te'amunim yekemesut kaltenagerut lene'Ato endiet yigeletilachewal? Abatochachin lebetemengist melkam mengedin siyasayna siyastekakilu koytewal, zarie gin ...
Amlak'hoyi bekabelen !

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)