March 22, 2012

የመንበረ ፓትርያርኩ ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት በወቅታዊ የገዳማት ሁኔታ ላይ መግለጫ ይሰጣል

 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 13/2004 ዓ.ም፤ ማርች 22/2012 READ THIS IN PDF)፦ የመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በዋልድባ ገዳማት ክልልና ዙሪያ የሚካሄደው ‹‹የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት›› ስለተፈጠረው ውዝግብ፣ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳምና አካባቢ እንዲሁም በደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ሳሙኤል ገዳም ይዞታ በሆኑ ደኖች ስለደረሰው ቃጠሎ አደጋ ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች - ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ፣ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ዋና ሓላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ - በዋልድባ ገዳማት ጉዳይ ወደ ስፍራው አምርተው ከመንግሥት፣ ከአህጉረ ስብከት እና ከገዳሙ ተወካዮች ጋራ መነጋገራቸው በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ እና በደጀ ሰላምም መዘገቡ ይታወሳል፡፡
የሕዝብ ግንኙነቱ መመሪያው ምክትል ሓላፊው ሊቀ ኅሩያን ዳዊት ታደሰ እንዲሁም የካህናት አስተዳደር መምሪያ ሓላፊው (መጋቤ ካህናቱ) ሊቀ ማእምራን ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም ከምዕራብ ሐረርጌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ጋራ በደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ሳሙኤል ገዳም ተጉዘው እንደ ነበር ተሰምቷል፡፡
በሰሞኑ የዝቋላ ገዳምና አካባቢው ቃጠሎ ደግሞ እሳቱ ከተነሣ ሦስት ቀናት በኋላ በገዳማት አስተዳደር መምሪያው ሓላፊ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም ያሉበት ኮሚቴ ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ውሎ እና አዳራቸውን በዚያው አድርገው ወደ መንበረ ጵጵስናቸው የተመለሱት ትንት ረፋድ ላይ ነበር፡፡
ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የተሰማሩትን የሦስቱንም ቡድን ልኡካን ጉዞ ንቅናቄዎች አንድ የሚያደርጋቸው፡- ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ መንግሥት ዕቅዱን ለማሳመን የሚጥረውን ያህል ቤተ ክህነታችን እንደ ባለቤት አጀንዳውን የራስ በማድረግ ፈጣን ምላሽ አለመስጠቱ፣ አደጋውን ከሐቁ ለማሳነስ አንዳንዴም ጨርሶ ለማስተባበል የተሞከረበት መሆኑ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ መብትና ጥቅም ላይ አገርንም ቤተ ክርስቲያኒቱንም ሊጠቅም የሚችል አቋም ከመያዝ ይልቅ የመደራደር ዝንባሌ መታየቱ፤ ከዚህም አልፎ በቤተ ክርስቲያኒቷ ችግር የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የችግር አፈታትና የሕዝብ ግንኙነት አቅም ተፈትኖ ደካማ ሆኖ መገኘቱ ናቸው፡፡
እግዚኦ በሚያሰኝ ሁኔታ ችግሩን ለመፍታት ከሄዱበት ህልውናው በአደጋ ውስጥ ከሚገኝ ገዳም አበል ጠይቀውና ተቀብለው የመጡ አሳፋሪ ልኡካንም እንዳሉ ጥቆማው ደርሶናል፡፡
ለማንኛውም ‹ጨርሶ ከመቅረቱ መዘግየቱ ይመረጣል›ና የተባለውን ወቅታዊ መግለጫ እንጠብቃለን፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡

9 comments:

Balemlay L. said...

bzuwoch ke Egziabher yilik mengistin yemiferu,, kehaymanotachew yilik lehodachew yaderu hunew sale endet tikit yemaybalu abatoche besint mekera yakoyuatin yichin talak betekristian endimeruat memeretachew new hulem ygermegnal:: Egziabherim mihiretun arakebin endet binaskeyimew ena binasazinew yhon???!!!

kidist said...

I totally disagree what they are trying to do. We know
Betekehnet means betemengest , so there is no hope,Anyway Mafereya woch nachew hulume , cher Yaseman

Thank you DS

asbet dngl said...

ምእመናን ስታነቡት አይገርማችሁም:: እባካችሁ በጾሎት እንበርታ:: የድንግል ልጅ ሁሉን በጊዜው ያስተካክለዋል:: ዋናው ተስፋ ያለመቁረጥና እጃችን ወደላይ በመዘርጋት እንጸልይ:: የምድር አባቶችስ አልፈው ተርፈው ፈተና ነው የሆኑብን::ጌታ ልቦናውን ይስጣቸው::

Anonymous said...

ታዲያ እኛ በቤተክርስቲያን ላይ የቤተክህነቱ አንዳንድ ሰዎች ለሚ ፈጽሙት በደል ዝም በማለታችን ተጠያቂዎች ነን ማለት ነው? ዕድሜ ብቻ የሚገታው የቅዱስ ፓትርያርክ ስልጣንስ ቢሆን ለቤተክርስቲያኒቱ እየጠቀመ ካልሆነ የኛ ድርሻ ዝም ብቻ ነው? ደግሞ ሁሌ ያለ አበል ያለ ገንዘብ ቤቱን ሲመሩና ሲያገለግሉ ከነበሩ አባቶቻችን በተቃራኒ ፈጣሪ መኖሩን እንኳን የሚጠራጠሩ እስከ ሚመስል ድረስ ለገንዘብ እና ለሥልጣን ብቻ ያደሩ የፖለቲካ ሰዎች መናሃሪያ የሆነው ቤት የሚጸዳዉ እንዴት ነዉ :: የ እኛ ድርሻ ምን ይሁን ?
እንዴ ሌላው ሥራውን ጥሎ በባዶ አንጀቱ ከእሳት ጋር የታገለው እኮ ለእምነቱ ነው:: ከዚያ አበል መጠየቅ በጣም በጣም ልብ ይነካል::ያሳዝናል::መንግሥት ለስልጣኑ ብቻ ነው የሚያስበው ስለዚህ ዋልድባ አይነካም ምናምን እያለ የመናንያኑን ጥያቄ ሲያስተባብል::የቤተክህነቱ ሰዎች ያንን ማስተጋባት የወከሏትን ቤተክርስቲያን ማፍረስ አይሆንባቸውም::በጣም በጣም ያሳዝናል::እ/ር ይቅር ይበለን ::እኔ ግን ምን ልሥራ ?

Anonymous said...

SELAME Deje selame ened enesu yemelut kewnet yerake meslo new yetayeg meknyatu VOA interewe yeEthiopianem Tv houletun eske adamet abatoche ezawe kegedamu yemenor abatoche interevew tedergolachewal end lemen sewn lemastebabel yefelgalo lehoulom ega akem yelenem hayel yeEGEZYABHER NEWE ega tor yelenem mewageya mesaryachen AMELAK NEWE betelot entega cher wera yaseman

Anonymous said...

"Wuha biank bemin yaworardutal, Milachis biabit bemin yibetutal ..." Bitsuan abatochachin Abune Gorgorios ze'ziway & Abune Shinoda ze'gibts endalmotu Bitsue abatochin Abune Gorgorios ze'zequala besemonu sirachew ayitenal. -libonayisten!-
.wub.

Anonymous said...

What do u expect from these gangs? do u think they speak the truth. Not at all. never expect.

It is shame that they collect perdiem from those monastries.

I have one statement to the government. If it does not deliver its reposibility in safagurding the welbeing of the nation and if the people start to take their cause in their hand it will lead to anarchism. And I am afraid that we are on the verge of that, failing state.

As reports indicate government institutions are loosing credibility by the people ( recent reports ). This is one aspect of failing state.

We care about our spritual well being. Go hell with your sugar and cane. We lived for thousands of yours with out your sugar. If you care about it, take it to the right place. You can not simply ignore social consequences of the project. Diginified death than humilated life.

Anonymous said...

bete kerstiyanitun yemayewekelu wero beloch nachew.
eskender ye weyane temrach neber 1997 Dawit tadess ye oromon ezeb yeshete temerach neber h/selase zemaryam esk 1980ders yetewaga weyane new tesefayem behun bebetekhuntu yemengest teweqay new tadiya man new hewentun yemingern?

Tenaye said...

Abele kegedanu???!!

Enezin ye ken giboch birr ena megib eyasayou megeref neber!!!tadiya endet yemaren! le hodachen enji le betekerstiyan alekomen! Egezio meharene kirstos!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)