March 18, 2012

የዋልድባ ገዳም አበምኔት ቤት በፌዴራል ፖሊስ ፍተሻ ተካሄደበት


·         አበምኔቱ ያሉበት አልታወቀም
·         የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ልኡካን ጠንካራ ተቃውሞ እየገጠማቸው ነው
 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 8/2004 .ም፤ ማርች 17/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF) በዋልድባ ገዳማት ህልውና እና ክብር ላይ ከተፈጠረው ችግር ጋራ በተያያዘ ወደ ስፍራው ያመሩት ሁለት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች በዓዲ አርቃይ ስብሰባ ማድረጋቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ እና የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ ሓላፊው አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ በዓዲ አርቃይ ከገዳሙ ማኅበር ተወካዮች ጋራ ያደረጉት ውይይት የገዳሙን ተወካዮች በጫና ውስጥ በሚያስገባ አኳኋን በመንግሥት የተወጠነውን ዕቅድ አሳምኖ ‹ልማቱን በማስቀጠል› ላይ ብቻ ያተኰረ እንደ ነበር ተጠቁሟል፡፡

ይኹንና በውይይቱ “የታሰበው ሳይሳካ ቀርቷል” ያሉት ምንጮቹ ከስብሰባው በኋላ በውይይቱ ላይ ያልነበሩት የገዳሙ አበምኔት ቤት በፌዴራል ፖሊስ እና ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀዳሚ ውይይት ከተካሄደበት ማይ ፀብሪ በመጡ ባለሥልጣናት ፍተሻ እንደተካሄደበት ተዘግቧል፡፡ የመረጃው ምንጮች አበምኔቱ መምህር ገብረ ጊዮርጊስ ገብረ አረጋዊ ያሉበት ትክክለኛ ቦታ ለጊዜ እንደማይታወቅ ለደጀ ሰላም ገልጸዋል፡፡
ዋልድባ እንዲህ ባለ ችግር ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት ቅዱስ ሲኖዶስ እና ፓትርያርኩ ምን እያደረጉ ነው የሚለው ጥያቄ ከፍ ብሎ መሰማት ጀምሯል። አንዳንዶችም “አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያኒቱን እያጠፏት ነው” የሚለውን ወደማመኑ እየደረሱ ነው። ከ16 ዓመት በፊት የዋልድባ አብረንታንት ገዳምን የጎበኙት አቡነ ጳውሎስ “ሴቶችና ወንዶች በአንድነት የሚቆርቡበት ቤተ ክርስቲያን ይሠራ” በሚል የሰጡት መመሪያ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀስቅሶ ነበር፡፡ መመሪያው በገዳማውያኑ ጸሎት እና ለፓትርያሪኩ በቀጥታ በተጻፈላቸው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተፈጻሚነት አለማግኘቱ ቢገለጽም አሁን የሚታየው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዳተኝነት የዚህ ክትያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡
በወቅቱ (በ1989 ዓ.ም) አበምኔቱ በገዳሙ ክልል ውስጥ በሚካሄደው የከብት ስምሪት እና በየዓመቱ በሚያጋጥመው ሰደድ እሳት ሳቢያ ቅዱሳኑ እየተረበሹ፣ የዱር እንስሳቱም እየተሰደዱ የመሆኑን ችግር ለፓትርያኩ አመልክተው ነበር፡፡
በ1989 ዓ.ም በከፍተኛ የጥበቃ አጀብ በገዳሙ ተገኝተው የነበሩት አቡነ ጳውሎስ እንደ አንድ ድርጎኛ ተቆንነዋል፤ በአብያተ ምርፋቁ ቋርፍ ተመግበዋል፣ ጭልቃ ጠጥተዋል፤ ሕጽበተ እግር ተደርጎላቸው ማየ ዮርዳኖስን ቀምሰዋል፤ ከገዳሙ ሥምረት ገብተው መቁጠሪያ ተቀብለዋል፡፡ ለመናንያኑና አገልጋይ መነኰሳቱ የረዱት 50,000 ብር ግን “ኀምሳ ሺሕ ጣጣ ያመጣብናል” በሚል “ይቅርብን” አሰኝቶ ነበር፡፡

ስለ ዋልድባ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን እንደ ደረሰን እናቀርባለን፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡ 

11 comments:

ዘ ሐመረ ኖህ said...

ኧረ የሰው ያለህ ኧረ ምን እስክንሆን እየጠበቅን ነው ኧረ አባካቸሁ በመንችለው ሁሉ እንድረስላቸው አበምኔቱን አፍነው ወስደዋቸው መሆን አለበት ከመጀመሪያው ገዳሙ ይታረስና ይፈርስም ዘንድ የፓትሪያርኩ እጅ እንዳለበት የታወቀ መሆኑን ከገዳሙ አባቶች ተረድተናል ፓትርያርኩና መንገስት ተጋግዘው ተዋህዶን እያጠፉ ነው በማለት እቅጩን ተነግሮናል
ምንድነው የምነጠብቀው
መቼስ ነው የምንነቃው
ተፈጸመ ሲባል ነው
መልካሙን ገድል የሚጋደል ጠፋ ማለት ነው
ኧረ የሰው ያለህ

Anonymous said...

Betam yemiyaszin negere new, endih yale zemene meta, abatoche min eyseru new? Tebabari yimeselugnal kemengist gar. mejemeriyawunem wede siltan yemetut bemengist haile new. Eg/r libona sitachew.

Anonymous said...

አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያኒቱን እያጠፏት ነው

Anonymous said...

ገዳማት በእሳት እየጋዩ ነው:: አባ ጳውሎስ እሳቱን ትተው ገዳማቱን ለማጥፋት አጋጣሚውን እየተጠቀሙበት ነው:: ምንድነው የሚሻለው? ምን ነበር ያቺ አልቃሽ ያለችው?
አንድ እግር በርበሬ መንቀል አቅቷችሁ
እንደዚህ ለብልቦ አቃጥሎ ፈጃችሁ:: አይደለም? ልብ ያለው ልብ ይበል::

Gebre Z Cape said...

What is your main point when you mention this " ከገዳሙ ሥምረት ገብተው መቁጠሪያ ተቀብለዋል፡፡ ለመናንያኑና አገልጋይ መነኰሳቱ የረዱት 50,000 ብር ግን “ኀምሳ ሺሕ ጣጣ ያመጣብናል” በሚል “ይቅርብን” አሰኝቶ ነበር፡፡"

What kind of message are you trying to tell us??????????????

Anonymous said...

aba powelos nefes yemar!!

Anonymous said...

hulachenem woregna nen...lefilafi hula nen...aned weney yalew enkuwan yelem...melefilef bicha...deje selamem aned neger enkuwan mareg alichalkem wore eyelekeku sewen masichenek bicha..eski aned selamawi selef enkuwan beyifa teru...lewet lemefiter eninesa

Fenql said...

I have no words to say but it is pityfull!

Anonymous said...

yehenene qelede tetene sele waledeba petition bemazegajete mefetehea bifelege melekam yemeselegnal

sew yefelgal geta said...

sew bela ,awera ,dedebe, kehadi ,emayereba hulu ,worea bicha naw mene yametalu belaw ayedel enda endi yemeyadergat tarik yelesh hulla yega betekerstiyan gen endedoletulat sayehom ENDA AMELAKE FEKAD holem tenoralech!!!!!!!!!!!!!!

Anonymous said...

Elohe elohe...Ebakh Getaye Ethiopian bemhreth gobgnat...Yeweyane jele Agezaz ybeqanal....Melkam ena arqo asabi meri sten!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)