March 18, 2012

ሰበር ዜና - የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የተነሣው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ሥር ዋለ


·   ሁለት ጋሻ መሬት ደን በእሳት ቃጠሎው ወድሟል (የገዳሙ መነኮስ)::
·    ቃጠሎውን ለማጥፋት ከደብረ ዘይት አየር ኀይል ርዳታ ተጠይቋል::
·   የቃጠሎው መንሥኤ ከከሰል ማክሰል ጋራ የተያያዘ ነው ተብሏል::

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 8/2004 ዓ.ም፤ ማርች 17/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊበን ዝቋላ ወረዳ አዱላላ ከተማ የሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በሚገኝበት ተራራ በስተምሥራቅ አቅጣጫ ዛሬ፣ መጋቢት 8 ቀን 2004 . ቀትር ላይ የተነሣው የእሳት ቃጠሎ ማምሻውን በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰማ፡፡ በቃጠሎው ሁለት ጋሻ መሬት የሚሸፍን ደን መውደሙ ተነግሯል፡፡

የገዳሙ መነኰሳት ከስፍራው በስልክ እንደገለጹት÷ ዛሬ ቀትር ላይ በገዳሙ ዙሪያ በሚገኘውና የመንግሥት ይዞታ በተደረገው ደን ውስጥ በተነሣው የእሳት ቃጠሎ ሁለት ጋሻ የሚሸፍን የደኑ ይዞታ እንደ ወደመ ተገምቷል፡፡ የገዳሙ ቤተ ክርስቲያን ከሚገኝበት ቦታ በግምት 3 - 4 . ርቆ የተነሣውን የእሳት ቃጠሎ ለማወቅ የተቻለው ይትጎለጎል የነበረውን ጭስና የእሳቱን ነበልባል ከተመለከቱ በኋላ መሆኑን መነኰሳቱ ለዜና ሰዎች ተናግረዋል፡፡
በሰዓቱ ስብሰባ ላይ ነበርን፤ ጩኸት ሰምተን ወጥተን ጢሱን በርቀት ስንመለከት ደወል (መጥቅዕ) ደወልን፤ በመንደርም ጥሩንባ ተለፈፈ፤ መናንያኑ፣ ደጅ ጠኚው፣ አፈር ጠባቂው፣ ጠበልተኛው፣ ደቀ መዛሙርቱ፣ የሰንበት ተማሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኛው ሆነን ተሯሩጠን ባፈር በቅጠሉ አጥፍተነዋል፤ ከቦታው ስንደርስ የማጥፋቱን ሥራ አስቸጋሪ ያደረገብን ደኑ እንደ ክትክታ፣ ወይራ ባሉት አገር በቀል ዛፎች መጠቅጠቁ ነው፤ የእሳቱ ነበልባልም እስከ መቶ ሜትር ያህል አያስቀርብም ነበር፤ ለጊዜው ቃጠሎው ወደ መንደሩና የገዳሙ ቤተ ክርስቲያን ሳይደርስ የጠፋ ቢሆንም ከወቅቱ ደረቅ የአየር ሁኔታና በከሰል አክሳዮቹ ምክንያት ዘላቂነቱ አስተማማኝ አይደለም” ብለዋል መነኰሳቱ፡፡
ነበልባሉ መጀመሪያ ላይ ከነበረው ኀይል እና ከአራት ዓመት በፊት (መጋቢት 10 ቀን 2001 . እስከ ገዳሙ ቤተ ክርስቲያን ተቃርቦ ከነበረው ቃጠሎ) አንጻር ለደብረ ዘይት አየር ይል የሄሊኮፕተር ርዳታ ጥያቄ ቀርቦ ነበር፡፡ አየር ኀይሉ ቃጠሎው ከአቅም በላይ ከሆነ የበኩሉን እገዛ ለመስጠት ዝግጁ እንደ ሆነ የተቋሙ ሓላፊዎች መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ ከአራት ዓመት በፊት ተነሥቶ በነበረው ቃጠሎ እንደ አርዘ ሊባኖስ፣ የሐበሻ ጥድ ያሉት ዕድሜ ጠገብ አገር በቀል ዛፎች በከፍተኛ ደረጃ መውደማቸው ይታወሳል፡፡
እንደ መነኰሳቱ ገለጻ ከቀትር አንሥቶ እስከ 1130 በቆየውና ከአራት ሰዓታት የጋራ ርብርብ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋለውን የዛሬውን ቃጠሎ አስገራሚ የሚያደርገው እንደ ዘንድሮው ሁሉ 2001 . መጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ በሳምንት ልዩነት ተነሥቶ ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰው የአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ሳሙኤል ገዳም ደን መቃጠል ጋራ መከታተሉ ነው - በገዳሞቻችን (ለዚያውም በጥንታውያኑ) አጠቃላይ ህልውና ዙሪያ የተጋረጠው ሰው ሠራሽ ይኹን ተፈጥሯዊ አደጋ እውነትም ያጠያይቃል፤ ያነጋግራል፤ የድንገትም አይመስልም፡፡
በጥንታዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ደጅ ጠኚውን፣አፈር ጠባቂውንእና የአብነት ትምህርት የሚከታተሉ ደቀ መዛሙርትን ሳይጨምር እስከ 350 መነኰሳት እና መነኰሳዪያት እንደሚገኙበት ተዘግቧል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን

አሜን

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)