March 12, 2012

የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ለወረዳው መስተዳድር ደብዳቤ ጻፈ


READ THIS ARTICLE IN PDF
·       ገዳሙ በውሳኔው ጸንቷል፤ 
·   “በእኛ በኩል በዚህ ቦታ ላይ ልማት ይሰራ ብሎ መወሰን ፈጽሞ የማይታሰብና የማይታለም ነው። ቦታውም በቅዱሳን መካነ መቃብር የታጠረና የተከለለ ነው” (ገዳሙ)፤
·       በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው፤
(ደጀ ሰላ መጋቢት 3/2004 ዓ.ም፤ ማርች 12/2012)፦ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ እና ታሪካዊ ገዳማት አንዱ ነው፤ ለግሑሳን(ፍጹማን) ባሕታውያን መሸሸጊያ፣ ለስውራን ቅዱሳን መናኸርያ፣ በብዙ ሺሕ ለሚቆጠሩ መነኮሳት፣ መነኮሳይያት እና መናንያን መጠጊያ፣ ለምእመናኑንም መማፀኛ እና ተስፋ የሆነው የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ለፀለምት ወረዳ መስተዳድር በጻፈው ደብዳቤ ለስብሰባ ወክሎ እንዲልክ የተጠየቀውን መቶ መነኮሳት በጾሙ ምክንያት መላክ እንደማይችል አስታወቀ፡፡

በወልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ አበምኔት በመምህር ገ/ጊዮርጊስ ገብረ አረጋዊ ተጽፎ ማይ ፀብሪ ለሚገኘው መስተዳድር ጽ/ቤት የተላከው ደብዳቤ መስተዳድሩ “መንግሥት በቅድስት ዋልድባ ገዳም ላይ በጀመረው የስኳር ልማትና ግድብ …” በተመለከተ “መናንያን እና መነኮሳት ባደረግነው ምልዓተ ጉባዔ መሠረት በአሁኑ ወቅትና ሰዓት ወደ ማይጸብሪ ወጥተን በጉዳዩ ላይ ውይይትና የመፍትሔ ሐሣብ ለማግኘት ባቀረባችሁት ጥያቄ መሠረት … በዚህ ከባድ የሆነ የሱባዔ ሰዓት ላይ መቶ መነኮሳትን ወደ ማይፀብሪ ለመላክ በጣም አስቸጋሪና አዳጋች ሆኖብናል። ምክንያቱም አብዛኛዎቹ አባቶች እርጋታና በአርምሞ ላይ በመሆናቸው” ነው ብሏል።
ስለ ገዳሙ አቋምና ውሳኔም  ሲያትት “ከዚህ በፊት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስገባነው ደብዳቤ በሰፊው ተገልጿል” ሲል ያስረግጣል። “አሁንም ቢሆን ዚህ አንጋፋና ታሪካዊ ገዳም ህልውናውና ክብሩ ግርማውና ሞገሱ ተጠብቆ እንዲኖር መንግሥትም ሆነ መነኮሳቱ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረግ አለብን። እኛም የዚህ ገዳም ባለቤት የነገሥታት፣ የመኳንንት ወይም የመሣፍንት ሳይሆን እራሱ ባለቤቱ መድኃኔ ዓለም የገደመው ገዳም ነው” ካለ በኋላ ቦታው “የቅዱሳን መናኸሪያ፣ የዕውራንና የግሁሳን ባሕታውያን መስፈሪያ” በመሆኑ “በእኛ በኩል በዚህ ቦታ ላይ ልማት ይሰራ ብሎ መወሰን ፈጽሞ የማይታሰብና የማይታለም ነው። ቦታውም በቅዱሳን መካነ መቃብር የታጠረና የተከለለ ነው” ብሎታል። አክሎም “ቦታውን የሚያዝበት የቦታው አስተዳዳሪ እራሱ መድኃኔ ዓለም ነው። እኛም ብንሆን በዚህ ቅዱስ ቦታ ላይ ማንኛውንም የልማት ሥራ እንዲሠራ ፈጽሞ ፈቃደኞች አይደለንም” ብሏል።
ደብዳቤ ለወረዳው መስተዳድር በአድራሻ ከተመለከተ በኋላ “ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጸ/ቤት” እና “ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት” ግልባጭ ተደርጓል። ገዳሙ ለጠ/ሚኒስትሩ ያስገባውን ደብዳቤ በተለመለከተ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የተጠየቁት በመ/ፓትርያርክ የኮሚዩኒኬሽን ክፍል ኃላፊ አቶ ስታሊን ገ/ሥላሴ ደብዳቤው በቀጥታ ለቤተ ክህነቱ እንዳልተላከ በማውሳት “ጉዳዩ በቀጥታ አልተገለጸልንም” የሚል ሐሳብ ለማስተካለፍ መሞከራቸው ይታወሳል። ይኸው ገዳሙ ለመስተዳድሩ የላከውን ደብዳቤ ከዚህ ጽሑፍ መጨረሻ ማግኘት ይቻላል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ስለ ዋልድባ ገዳም ሁኔታ ደጀ ሰላም አብሪውን ዘገባ ካወጣች እና አሜሪካ ድምጽ እና ሌሎችም የመገናኛ ብዙኃን ተከትለው ስለ ጉዳዩ ከዘገቡ በኋላ ምዕመናን በከፍተኛ ሐዘን እና ቁጭት ላይ እንደሚገኙ ከሚደርሱን መልእክቶች የተረዳን ሲሆን በአሜሪካ አገር የሚገኙ ምዕመናን በበኩላቸው የተሰማቸውን ቅሬታ እና ተቃውሞ ለመግለጥ አሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸው ታውቋል። መጋቢት 26/2004 ዓ.ም (ማርች 26/2012) ከጠኋቱ 3 ሰዓት (9 ኤ.ኤም) ጀምሮ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ሰላማው ሰልፍ ላይ እንዲገኙ የሰልፉ አስተባባሪዎች በፌስቡክ ጥሪዎችን በማድረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን በዲሲና አካባቢው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ለአባሎቻቸው ጥሪውን ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በስልክ ቁጥሮች 571 224 2869 እና 703 956 0513 እንደሚገኙ ያስታወቁት የሰልፉ አስተባባሪዎች ሰልፉ የሚካሔድበት አድራሻ ኤምባሲው (3506 International Dr NW Washington, DC 20008) መሆኑን ጠቅሰው በባቡር ለሚመጡ UDC Metro Stop ሁለት ደቂቃ የእግር ጉዞ ብቻ መሆኑን አመልክተዋል። በትራንስፖርት አቅርቦት መራዳት የሚፈልጉ ምዕመናን ካሉም ርዳታቸውን በደስታ እንደሚቀበሉ ገልፀው ከቨርጂኒያ፣ ከሜሪላንድ ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ከዲሲ ርዕሰ አድባራት ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢዎች ትራንስፖርት ለሚፈልጉ ሰላማዊ ሰልፈኞች መኪናዎች የተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ቸር ወሬ ያሰማን

አሜን


9 comments:

Anonymous said...

አዎን በገዳም አድባራቶቻችን ፈጽሞ አንደራደርም!!!! የሚመለከታቸው ሆዳሞች ቢያንቀላፉም እኛ በያለንበት ዝም አንልም!!! አምላክ የቅዱሳኑን ጸሎት ተቀብሎ እንደሚረዳን እናምናለን!ለ usa ምእመናን የአባቶቻችን አምላክ ጽናት ይሁናችሁ!!!


ስለጽዮን ዝም አልልም!!!!!

Bike said...

Hi!Deje selamawian!the America Ethiopian do that!what we do practically? except give an information&post comments? Plc a huge war broke out over EOTC from d/t diraction;in Waldba through the governmental project,in Asebot from Issa Somali tribe through the means of cattle teft;from the Patriarch through means of silet,etc.Asawn lematfat Asawn atmdo bemyaz endaltechale sireda Sytan wuhawn madrek yemil strategy be abyt Gedamat lay yekefete mehonun awken mnchu syderk mfthe enflg by prying,..

Anonymous said...

ተመስገን ጌታይ!!!
ደጀ ሰላሞች ከወሬ ወደ ተግባር ስለመራችሁን እግዚአብሄር አምላክ አገልግሎታችሁን ይባርክ!!!!
እኛንም ለቤተክርስቲያናችን ቀናኢ ያድርገን!!!
እነ አቶ በጋሻው የዘመናችን አገልጋ ነኝ ባዮች ለሆዳቸውና ለስማቸው ፍርድ ቤት እየሄዱ የቤተክርስቲያንን ለጆች በጉቦ ያሳስራሉ ሆዳም ነጋዴዎች ደግሞ ትናንት የኩሩፍቱ መዳህኒያለምን የታቦቱን ቦታ በስማቸው ካርታ አሰሩ ዛሬ ደግሞ ወደ ዋልድባ ገዳም ገቡ እኛስ ምንድን ነው የምናደርገው?
ከሰልፍ በኌላ በቀጣይ ማድረግ ያለብንን ካሁኑ ሁላችንም ለናስብበት ይገባል ለማንኛውም ዲሲ ስንገናኝ ሰብሰብ ብለን እንመካከራለን::
ቸር ወሬ ያሰማን

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

የሚመለከታቸው ሆዳሞች ቢያንቀላፉም እኛ በያለንበት ዝም አንልም!!Anonymous ትክክል፡ብለሃል፡እስከ፡መቼ፡ቤተ፡ክህነት፡የሞቀ፡ወንበር፡ላይ፡ቁጭ፡ብለው፡የላመ፡የጣመ፡እየበሉ፡ቤተ፡ክርስትያን፡ላይ፡ይቀልዳሉ፡፡ይህን፡ጉዳይ፡ተከታትለው፡ከመንግስት፡ጋራ፡መከራከር፡ሲገባቸው....ልቡና፡ይስጣቸው፡፡

Kolo temari said...

The 'Selamawi-self" should not be limited only in USA; rather it must extend all over the world including in Ethiopia.

I have been doing movement where arround me. Lets all do our share either physically, financially, orally, intellectually etc.

We never and ever negotiate by our religion!!!

asbet dngl said...

ደጀ ሰላም እግዝአብሔር ውለታችሁን ይክፈላችሁ:: ለመንግሥትም ይህን የአባቶች ገዳም ችግር የሚያስተውልበት ልቦና ይስጠው :: እድገት በማነኛውም መልኩ ለሀገር ጥሩ ነው ነገር ግን ታሪክናሃይማኖት :እየሸረሸሩ ከሆነ ግን ጽያፍ ይሆናል:: ለማነኛውም የገዳማቶቹ ጾለት ይርዳን::

Anonymous said...

ሰላም የተህዶ ልጆች
ወደ ኢትዮጵያ ኢምባሲ እና ለሚመለከታቸው ሁሉ በጽሁፍ በምናስገባው አቤቱታ/ይኖራል በሚል ነው/ የኩሩፍቱ መዳህኒያለምን የመሬት ይዞታ ጉዳይ ፡ አክራሪ እስላሞች በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየፈጸሙ ያሉትን የቅድስት አርሴማንና እና የሌሎችንም የገዳማት ችግሮች ጉዳይ ቢካተት መልካም ይመስለኛል::
ይህ የአጋንንት ውጊያ ጅምር በሰላማዊ ሰልፍ አይነት ይሁን እንጅ ለበአል ከምናደርገው ጉዞ የበለጠ በረከት የሚያሰጥ የሰማዕታት ጸዋ ለመጎንጨት የሚያዘጋጅ እስከ መጨረሻው ለጸና የሰማእታትን አክሊል የሚያቀዳጅ የመንፈሳውያን ውጊያ ስለሆን ሁላችንም ካህናት ዲያቆናት መዘምራን እና ምእመናን መሳተፍ ይጠበቅብናል በየ እስቴቱ ያላችሁ የሰበካ ጉባኤ /የቦርድ / አመራሮች እና በዋናበት የደብር አስተዳዳሪዎች ለዚህ ጉዞ ተቀዳሚ አዘጋጆች ትሆኑ ዘንድ ስለ ዋልድባ እማጸናችኋለሁ
ለበረከቱ ያብቃን
በዚችው ድህረ-ገጻ በጋራ እንንቀሳቀስ::

መላኩ said...

በባለሥልጣናት መታመንን ማቆም አለብን። ይህን መሰሉ ጉዳይ የያንዳንዳችን ኃላፊነት ሆኖ ሊወሰድ ይገባል። በልማት ስም ወደ ገዳሙ ጠጋ ጠጋ የሚሉትን የዲያብሎስ መልዕተኞች በጸሎትም ልንቋቋማቸው እግሮቻቸውን ልነሰብር ይገባል፡ ሰይጣን በገዳሞች ላይ ጦርነት አውጇል፡ ደኖቹም እየተቃጠሉ ነው፡ ብሉይ ኪዳናችንን ይዘን፣ ዳዊታችንን እየደገፍን ዘራፍ ማለት አሁን ነው።

ለመሆኑ "ስታሊን ገ/ሥላሴ" ስማቸው ከየት የተገኘ ነው?

haile michael said...

የሚመለከታቸው ሆዳሞች ቢያንቀላፉም እኛ በያለንበት ዝም አንልም!!Anonymous ትክክል፡ብለሃል፡እስከ፡መቼ፡ቤተ፡ክህነት፡የሞቀ፡ወንበር፡ላይ፡ቁጭ፡ብለው፡የላመ፡የጣመ፡እየበሉ፡ቤተ፡ክርስትያን፡ላይ፡ይቀልዳሉ፡፡ይህን፡ጉዳይ፡ተከታትለው፡ከመንግስት፡ጋራ፡መከራከር፡ሲገባቸው....ልቡና፡ይስጣቸው፡፡
lelijochachin sileminaweresew neger enitenkek .
be'egna zemen bezu neger tebelashe eko !

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)