March 30, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ምጥን ዘገባ (ክፍል አንድ)


·         ስብሰባ የጎንደርን ካህናትና ምእመናን እንደማይወክል ተገለጸ
·         “ዋልድባ ቅዱስ ገዳማችን ነው፤ እንዲነካ አንፈልግም፤ እኛም እንደ ክልል እነ ኣባይ ፀሃዬ ጉዳዩን የት እንዳደረሱት እንከታተላለን፤ ሁላችሁም ሄዳችኹ አይታችኹ እውነታውን ማረጋገጥ ትችላላችኹ” (አቶ አያሌው ጎበዜ፤ የክልሉ ፕሬዚደንት)።
 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 20/2004 ዓ.ም፤ ማርች 29/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ “የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት” በዋልድባ ገዳም ህልውና እና ክብር ላይ የጋረጠውን አደጋ በተመለከተ “የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ካህናትና ምእመናን የሚያነሡትን ሐሳብ ለመስማት” የሚል ስብሰባ ትንት መጋቢት 19 ቀን 2004 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ዐምባ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

March 29, 2012

በዋልድባ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሕዝባዊ ውይይቶች ቀጥለዋል


·         ምእመናን ለቤተ ክርስቲያናቸው መቆም ያለባቸው ጊዜ ላይ መደረሱ ተወስቷል፡፡
·         ሰላማዊ ሰልፎች ማድረጉ ይቀጥላል።
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 20/2004 ዓ.ም፤ ማርች 29/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በዋልድባ እና በጠቅላላው የቤተ ክርስቲያን ህልውና ጉዳይ የተቀሰቀሰው ቁጣ በሕዝባዊ ውይይቶች ታጅቦ እየቀጠለ መሆኑን የሰሜን አሜሪካ ምንጮቻችን ገልጸዋል። በመላው የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በስልክ ኮንፈረንስ ሐሳባቸውን እንዲሰጡ እያደረገ ባለው በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ የምእመናን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ስለ ዋልድባ ይዞታ መደፈር ወይም ስለ ዝቋላ እና አሰቦት ገዳማት የእሳት አደጋ ብቻ ሳይሆን “በጠቅላላው ስለ ቤተ ክርስቲያን ህልውና ነው መነጋገር ያለብን” ወደሚለው ገዢ ሐሳብ በመምጣት ላይ ናቸው ተብሏል።

March 28, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ ስብሰባ ጠራ


አርእስተ ጉዳዮች፡-
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 19/2004 ዓ.ም፤ ማርች 28/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦
·         ከሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ ከዋልድባ ገዳም ተወክለዋል የተባሉ መነኰሳት፣ ከጎንደር ከተማ የተመረጡ ምእመናንና በማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል ሥራ አስፈጻሚ አባላት ነገ፣ መጋቢት 19 ቀን 2004 ዓ.ም፣ የመንግሥት ‹‹የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት›› በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ ስለ ደቀነው ስጋት፣ በተጨባጭም ስለታየው መጋፋት ውይይት እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ስብሰባውን የጠራውን ብአዴን/ኢሕአዴግ ሲሆን የሚካሄደውም በጎንደር ከተማ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

March 27, 2012

የዋልድባ ገዳም ይዞታ መደፈርን የተቃወመ ሰላማዊ ሰልፍ በዲሲ ተካሄደ


·         ኤምባሲው ለሙስሊም ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊ ወገኖቻችን ያሳየውን ከበሬታ ለክርስቲያኖቹ አለማሰየቱ ግርምት ፈጥሯል፤
·         “መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱን ይንቃታል፤ ክርስቲያኑንም ይንቃል” (ሕዝብ)

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 18/2004 ዓ.ም፤ ማርች 27/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የኢሕአዴግ መንግሥት በዋልድባ እና አካባቢው  በግድብ ሥራ፣ በፓርክ እና በስኳር ፋብሪካ ግንባታ ስም የሚያካሒደውን ገዳሙን ድንበር፣ ትውፊት እና መንፈሳዊ ይዞታ የመግፋት መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ በመቃወም ላይ ላሉ ገዳማውያን አበው እና እመው ያላቸውን አለኝታነት ለመግለጽ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ትናንት በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመሰለፍ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።

March 26, 2012

Ethiopian Christians Protest in DC (የአሜሪካ ድምጽ ሪፖርታዥ)

የቦሌው ችሎት በመ/ር ዘመድኩን ላይ የገደብ ቅጣት ወሰነ


·        መ/ር ዘመድኩን ይግባኝ ይጠይቃል::
·        ማስረጃ ያልቀረበላቸው የዐቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃዎች ውድቅ ተደርገዋል::
·        መ/ር ዘመድኩን በመንፈሳዊ አገልግሎቱና በማኅበራዊ ተሳትፎው ያቀረባቸው የቅጣት ማቅለያዎች ተቀባይነት አግኝተዋል::
 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 17/2004 ዓ.ም፤ ማርች 26/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት መ/ር ዘመድኩን በቀለ በዐቃቤ ሕግ በቀረበበት የስም ማጥፋት ወንጀል በብር 3000 መቀጮ እና በስድስት ወራት እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡ የ3000 ብር የገንዘብ ቅጣቱ ተከፍሎ የስድስት ወራቱ እስራት ሳይፈጸም በሁለት ዓመት ገደብ እንዲታይ ውሳኔ የሰጠው ችሎቱ ተከሳሹ ቀደም ሲል በዋስ ያስያዘው ብር 5000 ስለ መልካም ጠባይ ዋስትና ታግዶ እንዲቆይ ትእዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡

March 23, 2012

“እሳት በመንደርም ይነሣል፤ በቤተ ክርስቲያን ሲሆን ለምን ይገናል?” (የጠ/ ቤተ ክህነቱ መግለጫ)


(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 14/2004 ዓ.ም፤ ማርች 23/2012. READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ሁሉም ሓላፊዎች በዋልድባ ገዳማት፣ በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአባ ሳሙኤል ገዳም እና በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከተፈጠረው ችግር ጋራ በተያያዘ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምላሽ ተመጣጣኝና ፈጣን እንዳልሆነ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ላይ የሚሰነዘረውን ወቀሳ በማጣጣል አስተባብለዋል፡፡

አቤቱ የሆነብንን አስብ

የመንበረ ፓትርያርኩ ጠ/ቤ/ክ መግለጫ ቤተ ክርስቲያን-ቤተ ክርስቲያን አይሸትም


 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 14/2004 ዓ.ም፤ ማርች 23/2012. READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በዋልድባ ገዳማት ክልልና ዙሪያ የሚካሄደው ‹‹የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት›› ስለተፈጠረው ውዝግብ፣ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳምና አካባቢ እንዲሁም በደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ሳሙኤል ገዳም ይዞታ በሆኑ ደኖች ስለደረሰው ቃጠሎ አደጋ የሰጠው መግለጫ ምንም ዓይነት የቤተ ክርስቲያንም ሆነ የቤተ ክህነት ጣዕም እና ቃና የሌለው ሆኖ ተገኝቷል፡፡

March 22, 2012

የመንበረ ፓትርያርኩ ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት በወቅታዊ የገዳማት ሁኔታ ላይ መግለጫ ይሰጣል

 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 13/2004 ዓ.ም፤ ማርች 22/2012 READ THIS IN PDF)፦ የመንበረ ፓትርያክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በዋልድባ ገዳማት ክልልና ዙሪያ የሚካሄደው ‹‹የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት›› ስለተፈጠረው ውዝግብ፣ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳምና አካባቢ እንዲሁም በደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ሳሙኤል ገዳም ይዞታ በሆኑ ደኖች ስለደረሰው ቃጠሎ አደጋ ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

Waldibba Monastery 3rd Reportage by VOA Radio

Ziquala Fire Report (2012) by VOA Radio

ስለ ዝቋላ እሳት ጉዳይ - ምስጋና እና ስጋት


(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 12/2004 ዓ.ም፤ ማርች 21/2012/ READ IN PDF)፦ ስጋቱ - ዛሬ አዳሩን ከምሽቱ 300 ገደማ የቅዱሳን ከተማ በሚባለው ስፍራ ሲጤሱ የዋሉ የገመኑ (የተቃጠሉ) ጉቶዎችና ግንዶች ምሽቱን እሳት መቀስቀሳቸው ተሰምቷል፡፡ የእሳቱ መጠን ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ለጊዜው ማወቅ ባይቻልም÷ በየአቅጣጫው ሁኔታውን በንቃት እየቃኙ በነበሩት መናንያን በተሰማው ደወል በገዳሙ አዳራሽ የነበረው ምእመን እንዲጠራ ተደርጎ፣ በተራራው ላይ የመከላከሉን ተግባር በከፍተኛ ደረጃ ሲያግዙ ከነበሩት የፌዴራል ፖሊስ እና የመከላከያ ኀይሎች ጋራ የተቀሰቀሰውን እሳት ለማጥፋት እየተረባረቡ መሆኑ ተገልጾልናል፡፡

March 21, 2012

ዝቋላ ገዳምና አካባቢው የተቀሰቀሰው ቃጠሎ Ziquala Monastery Fire

የዝቋላን ቃጠሎ ለመከላከል ዓለም አቀፍ ድጋፍ ተጀምሯል


·         በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን የገንዘብ አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው
·         ሌሊቱን የእሳቱ መዛመት መሻሻል ቢታይበትም የፍሕሙ መብዛትና የአየሩ ሁኔታ አሁንም ያሰጋል
 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 12/2004 ዓ.ም፤ ማርች 21/2012 PDF)፦ በዝቋላ ገዳምና አካባቢው የተቀሰቀሰው ቃጠሎ ዛሬ፣ መጋቢት 13 ቀን 2004 . አምስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል፡፡ ንት ሌሊቱንና ቀትር ላይ በአደገኛ ሁኔታ እንደ አዲስ ተቀስቅሶ የነበረው የቃጠሎው መዛመት ዛሬ ሌሊቱን መሻሻል እንደታየበት የገዳሙ መነኰሳት ገልጸዋል፡፡

March 20, 2012

በፖሊስ ጥይት የቆሰሉት ተማሪዎች ሦስት ደርሰዋል


·        ወደ ደብረ ዘይት ለሕክምና ተወስደዋል
·        አጋጣሚው ቃጠሎውን ከመከላከል ሊያዘናጋን አይገባም!!!
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 11/2004 ዓ.ም፤ ማርች 20/2012 READ IN PDF)፦ በዝቋላ ገዳም የተነሣውን ቃጠሎ ለመከላከል ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ስፍራው ከተነቃነቁት አዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል በፖሊስ ጥይት የቆሰሉት ተማሪዎች ሦስት መሆናቸው ተዘገበ፡፡ በተማሪዎቹ ላይ የደረሰው ጉዳት መንሥኤ በተማሪዎቹ እና በአንድ የኦሮሚያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ መካከል የተፈጠረ አለመግባባት መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል፡፡

(ሰበር ዜና) በዝቋላ ገዳም ፖሊስ አንድ ተማሪ አቆሰለ


·         ትኩረታችን ወደ መከላከሉ - መዘናጋት አይገባም!!
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 11/2004 ዓ.ም፤ ማርች 20/2012 READ IN PDF)፦ በዝቋላ ገዳም ቃጠሎውን ለማጥፋት በተሰበሰቡ ወጣቶች እና በኦሮሚያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ መካከል በተቀሰቀሰው አለመግባባት ከአዳማ ዩኒቨርስቲ ከተጓዙት መካከል አንድ ተማሪ ከፖሊስ በተተኰሰ ጥይት እግሩ ላይ ቆስሎ ወደ ሕክምና በመወሰድ ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡
የአለመግባባቱ መንሥኤ ወጣቶቹ ቃጠሎውን አስመልክቶ በቀጥታ ስርጭት ዘገባ ማስተላለፍ ሥራ ላይ የነበረውን ጋዜጠኛ መቃወማቸው ነው ተብሏል፡፡ የዐይን እማኞች እንደተናገሩት ጋዜጠኛው እሳቱ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የሚገልጽ ዘገባ በማስተላለፍ ላይ ነበር፡፡

ተጨማሪ መረጃዎች:- የዝቋላ ገዳም አሁን ያለበት ደረጃ

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 11/2004 ዓ.ም፤ ማርች 20/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦
Picture: Courtesy of Nigusie Girma
የዝቋላን ገዳም ቃጠሎ ለመከላከል እየተደረገ ባለው ጥረት፡-
·     ቃጠሎውን ጨርሶ ለማጥፋት የአቢሲኒያ የበረራ አገልግሎት አውሮፕላን ለመስጠት ፈቃደኛ ነው፤ ሂሊኮፕተርም ከአየር ኀይል ለማግኘት ዕድሉ አለ፤ ይሁንና የመርጫ መሣሪያ ቴክኖሎጂ በአገሪቱ የለም፤ የኬሚካሉም መወደድ ችግር ሆኗል፡፡
·      አሁን ባለው የቴክኖሎጂ አቅም በዝቅተኛ ከፍታ እየበረሩ ወደ ጥልቁ ገደልና ጫካ ውኃ ብቻ ለመርጨት ቢሞከር አደጋ መጋበዝ ይሆናል፤ በከፍታ በረራ ቢረጭ ደግሞ ውኃው አየር ላይ ነው የሚቀረው፡፡ በመሆኑም ዘልቆ ሊወርድ የሚችለውን የማጥፊያ ኬሚካል በውድ ዋጋ ለማግኘት ቢቻል እንኳ የመርጫ መሣሪያው በእጅጉ አስፈላጊ ይሆናል፡፡
·     የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ያሰማራው ኀይለ ግብር የተዳፈነው እሳት አሁን ካለበት የባሰ እንዳይዛመት እሳተ ከላ(Fire Break) በግንድ፣ በቅጠሉ መሥራት እንደ ተሻለ አማራጭ ውስዶ እየተረባረበ ነው፡፡ ቃጠሎውን ለመከላከል የሚመጡ ምእመናንም የዝቋላን አቀበት ተቋቁመው ወጥተው በምንጣሮ፣ በቁፋሮ፣ በሸክም ለመራዳት የሚችሉ መሆን ይገባቸዋል፡፡

የዝቋላ ገዳም አሁን ያለበት ደረጃ

  • (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 11/2004 ዓ.ም፤ ማርች 20/2012/ PDF)፦  የዝቋላን ገዳም ቃጠሎ ለመከላከል እየተደረገ ባለው ጥረት፡- 
  • የዝቋላን ገዳም ቃጠሎ ለመከላከል የተሰማሩ ወጣቶች በጠቅላይ ቤተ ክህነት ናቸው - ተቃውሟቸውን ለመግለጽ፣ ጥያቄያቸውንም ለማቅረብ፡፡ 
  • ፖሊስ ወጣቶቹ እንዲበተኑ እያዘዘ ነው፡፡ 
  • ቃጠሎውን ጨርሶ ለማጥፋት የግል አውሮፕላን ከአቢሲኒያ የበረራ አገልግሎት በኪራይ ተገኝቷል ተብሏል፤ ውድ የሆነውና በመንግሥት ዘንድ ብቻ የሚገኘው ኬሚካል ግን ቸግሯል፡፡


  • በየቦታው የተከማቸው የቃጠሎ ፍሕም በጣም ብዙ ነው፤ በተደጋጋሚ ቃጠሎ የመቀስቀስ ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡
  • ለማጥፋት የሚቻለው በአውሮፕላን/ሄሊኮፕተር በሚረጭ ኬሚካል ብቻ ነው::

March 19, 2012

ስለ ዝቋላ ገዳም አሁን የደረስንበት … የዝቋላ ገዳም ቃጠሎ ግራ አጋቢ (ተኣምራዊ?) ትዕይንት እየታየበት ነው


 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 10/2004 ዓ.ም፤ ማርች 19/2012/ PDF)፦  
·         እሳቱ በአንድ አካባቢ ኀይሉ ሲቀንስ/ሲገታ በሌላ ሥፍራ ድንገት እየተቀሰቀሰ የመከላከሉን ጥረት አድካሚና ግራ አጋቢ አድርጎታል፡፡
·         “በምዕራብ ስናጠፋው በምሥራቅ እየዞረ፣ በምሥራቅ ስናጠፋው በምዕራብ እየዞረ፣ በተለይም ዐርብ ረቡዕ በሚባለው የተራራው ገጽ በኩል፣ ጠበል ሜዳን (ጠበሉ የሚገኝበትን ጥቅጥቅ ያለ ጫካ) እየከበበ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከገዳሙ በማእከላዊ ግምት ከ300 - 400 ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡”
·         በእሳት አጥፊ አውሮፕላን ወይም ሄሊኮፕተር በሚረጭ ኬሚካል ካልሆነ በቀር ከሦስት ቀናት በፊት ጀምሮ ባፈር በቅጠሉ በሚደረገው የነፍስ ወከፍ መከላከል ጥረት ጨርሶ ሊጠፋ ወይም መጥፋቱ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡
·         እሳቱ ጠበሉ ወደሚገኝበት ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ከገባ ገዳሙ የነበር ታሪክ ይሆናል፡፡
·    የተወሰኑ የአየር ኀይል እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ምእመናኑና ገዳማውያኑ ከሚያደርጉት ውጭ የተለየ መከላከል ሊያደርጉ አልቻሉም፡፡
·         የውኃ እጥረት እና የተራራው አቀበትነት ትግሉን አስቸጋሪ አድርጎታል።
·         ዛሬ ቀን ላይ በሦስት መኪኖች ከአዲስ አበባ ተጉዘው ከስፍራው በመድረስ በተለይም እሳቱ አስቀድሞ በተነሣበት ምሥራቃዊ አቅጣጫ (አዱላላ) ጥረት ሲያደርጉ ያመሹት ቁጥራቸው እስከ 300 የሚገምቱ በበጎ ፈቃድ የተሰበሰቡ የሰንበት ት/ቤት፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እና በተለይም የአውቶቡስ ተራ አካባቢ ወጣቶች ማምሻውን ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ ናቸው፡፡ ወጣቶቹ፣ “ቃጠሎው በአንድ ቦታ ኀይሉ ሲቀንስ/ሲገታ ባልታሰበ ሌላ አቅጣጫ ድንገት የመቀስቀስ ግራ አጋቢ እና ተኣምራዊ ጠባይዕ ያለው ነው፤” ብለዋል፡፡
·         የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ለመንግሥት ደብዳቤ መጻፉ ተሰምቷል፡፡ ደብዳቤው ቃጠሎውን ለመከላከል መንግሥት እገዛ እንዲያደርግና መንሥኤው እንዲጠና የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡
·         ይህ በእንዲህ እንዳለ በጥንታውያን ገዳሞቻችን ህልውና እና ክብር ላይ እየተጋረጠ በሚገኘው አደጋ በቂ ወይም ምንም ጥረት እንዳላደረጉ እየተወቀሱ የሚገኙት ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ነገ፣ መጋቢት 11 ቀን 2004 ዓ.ም፣ በይፋ እንደሚፈጸም በሚጠበቀው የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን 117ኛ ፖፕ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሲኖዳ የቀብር ሥነ ሥርዐት ላይ ለመገኘት ዛሬ ማምሻውን ወደ ግብጽ እንደሚጓዙ ተዘግቧል፡፡ ከፓትርያኩ ጋራ አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሌሎች ሁለት የፓትርያኩ ፕሮቶኮል ሰዎች አብረዋቸው ይጓዛሉ፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን

አሜን


ዝቋላ ገዳም በቃጠሎ ዋዜማ ላይ ነው


·         ቦቴ መኪናዎች ቢኖሩ ለውጥ ያመጡ ነበር፤
·         መከላከያው በሄሌኮፕተር እንዲረዳ ሊጠየቅ ይገባው ነበር፤
·         የአዲስ አበባ ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ተሰባስበው ወደ ገዳሙ ሄደዋል፤
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 10/2004 ዓ.ም፤ ማርች 19/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦  በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊበን ዝቋላ ወረዳ አዱላላ ቀበሌ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ በሚገኘውና የመንግሥት ይዞታ በሆነው ደን ምሥራቃዊ ገጽ ቅዳሜ ቀትር ላይ የተነሣው እሣት በመስፋፋት ገዳሙ አፋፍ ላይ መድረሱን ምንጮች እየገለጹ ነው። ምእመናን የአቅማቸው በማድረግ ለማጥፋት ቢረባረቡም ሊቋቋሙት አልቻሉም።

March 18, 2012

በዝቋላ ገዳም በቁጥጥር ሥር ውሏል የተባለው ቃጠሎ ዳግመኛ አገርሽቷል

·         ቃጠሎው የገዳሙን ዙሪያ ገባ እያካለለው ነው
·         የቃጠሎው መንሥኤ “ከሰል አክሳዮች ናቸው” መባሉ አጠራጥሯል
·         “ትንት ምሽቱን ነው ዳግመኛ የተቀሰቀሰው፤ የተጠበቀው የአየር እገዛ አልተደረገልንም፤ እሳቱ ዙሪያውን ይዞታል፤ በእሳቱ እየተከበብን፣ በጭሱ እየታፈንን ቢሆንም ባፈር በቅጠሉ እየታገልን ነው፤ ወደ ጠበሉ ከገባ ግን አለን ለማለት አይቻልም፤ . . . ገብረ መንፈስ ቅዱስ መቶ ዓመት ለጸለዩባት፣ ለደከሙባት ቅድስት ቦታ ምላሹ ይህ ነውን? እንዲያው ወሬ ብቻ ነን!!” /የገዳሙ መነኰስ/
·         ዳሩ እሳት - መሀሉ እሳት!! በምሥራቅ እሳት - በመሀል እሳት - በሰሜን እሳት!! 

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 9/2004 ዓ.ም፤ ማርች 18/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦  በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊበን ዝቋላ ወረዳ አዱላላ ቀበሌ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ በሚገኘውና የመንግሥት ይዞታ በሆነው ደን ምሥራቃዊ ገጽ ትንት ቀትር ላይ ተነሥቶ ማምሻውን በቁጥጥር ሥር መዋሉ የተገለጸው ቃጠሎ ሌሊቱን አገርሽቶ ዙሪያ ገባውን ከፍተኛ ጥፋት እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ሰበር ዜና - የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የተነሣው የእሳት ቃጠሎ በቁጥጥር ሥር ዋለ


·   ሁለት ጋሻ መሬት ደን በእሳት ቃጠሎው ወድሟል (የገዳሙ መነኮስ)::
·    ቃጠሎውን ለማጥፋት ከደብረ ዘይት አየር ኀይል ርዳታ ተጠይቋል::
·   የቃጠሎው መንሥኤ ከከሰል ማክሰል ጋራ የተያያዘ ነው ተብሏል::

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 8/2004 ዓ.ም፤ ማርች 17/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊበን ዝቋላ ወረዳ አዱላላ ከተማ የሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በሚገኝበት ተራራ በስተምሥራቅ አቅጣጫ ዛሬ፣ መጋቢት 8 ቀን 2004 . ቀትር ላይ የተነሣው የእሳት ቃጠሎ ማምሻውን በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰማ፡፡ በቃጠሎው ሁለት ጋሻ መሬት የሚሸፍን ደን መውደሙ ተነግሯል፡፡

የዋልድባ ገዳም አበምኔት ቤት በፌዴራል ፖሊስ ፍተሻ ተካሄደበት


·         አበምኔቱ ያሉበት አልታወቀም
·         የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ልኡካን ጠንካራ ተቃውሞ እየገጠማቸው ነው
 (ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 8/2004 .ም፤ ማርች 17/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF) በዋልድባ ገዳማት ህልውና እና ክብር ላይ ከተፈጠረው ችግር ጋራ በተያያዘ ወደ ስፍራው ያመሩት ሁለት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች በዓዲ አርቃይ ስብሰባ ማድረጋቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ እና የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ ሓላፊው አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ በዓዲ አርቃይ ከገዳሙ ማኅበር ተወካዮች ጋራ ያደረጉት ውይይት የገዳሙን ተወካዮች በጫና ውስጥ በሚያስገባ አኳኋን በመንግሥት የተወጠነውን ዕቅድ አሳምኖ ‹ልማቱን በማስቀጠል› ላይ ብቻ ያተኰረ እንደ ነበር ተጠቁሟል፡፡

March 17, 2012

ሰበር ዜና - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ አረፉ

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 8/2004 .ም፤ ማርች 17/2012/ PDF) ተወዳጁ የቅብጥ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ ሺኖዳ ሣልሳዊ በተወለዱ 88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የአገሪቱን ሬዲዮ የጠቀሰው ቢቢሲ ዘግቧል። ለእረፍታቸው ምክንያት የሆነው ምን እንደሆነ ያልተገለጸ ቢሆንም በዕድሜ አረጋዊ የኾኑት ቅዱስነታቸው  ለረዥም ጊዜ ሲታመሙ መቆየታቸው ይታወቃል። 

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)