February 24, 2012

"Kidane Mihret Emebete" By Zemarit Lemlem Kebede

10 comments:

Anonymous said...

Enwuan aderesachihu.You didn't get a hymne with out kebero???????? melkam beal!

Anonymous said...

አባቶቻችን ስለዚህ ጾም ምን አሉ ?
ይህ የ 318ቱ ሊቃውንት አባቶቻችን የጾም ስርዓት ነው፤ ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ፤ ጾም እንደምን ነው ብትል ጾምስ በታወቀው ዕለት በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው፤ በታወቀው ዕለት አለ ሰባቱን አጽዋማት ሲያነሳ ነው በታወቀው ሰዓት አለ ዓርብ ረብዕን እስከ 9 ሰዓት ጾመ ህርቃልን ጸሐይ እስክትጠልቅ እስከ 12 ሰዓት ይጹሙ ከቅድስት ሰኞ እስከ ኒቆዲሞስ ዓርብ እስከ 11 ሰዓት ይጹሙ ሰሙነ ሕማማትን ኮከብ እስኪወጣ እስከ 1 ሰዓት ይጹሙ፤ ጾመ ሕርቃል ይህ የያዝነው ሳምንት ነው፤ ቅድስት ሰኞ 2ኛው ሳምንትን ነው፤ ኒቆዲሞስ ዓርብ ከጸሎተ ሐሙስ ቀጥሎ ያለው ዓርብ ነው። ዳግመኛም ባስልዮስ በጻፈው መጽሐፍ አንቀጽ 70 ላይ በዓቢይ ጾም የቅዱሳንን በዓል በመብል በመጠጥ ልናከብር አይገባም፤ ይህን ያደረገ ካህን ከሹመቱ ይሻር ምዕመን ከሆነ ግን ቀኖና ይስጡት አለ። የቅዱሳን በዓል ሰኞ ወይንም ማክሰኞ ከዋለ ከፊት ያለውን ቅዳሜ ወይም እሁድ በአንዱ ያክብሩ፤ ሐሙስ ወይንም ዓርብ ከዋለ የሚመጣው ቅዳሜ ወይንም ዕሁድ በአንዱ ያክብሩበት፤ ረቡዕ ከዋለ ግን ወደፊት ወይንም ወደ ኃላ ካሉትን ሰንበታት በአንዱ ያክብሩበት አለ ። ዳግመኛ በሎዶቅያ የተሰበሰቡ ሊቃውንት በጻፉት መጽሐፍ አንቀጽ 51 ላይ በዓቢይ ጾም መጠጥ እንዳይጠጣ አዘዙ። በአቢይ ጾም መጠጥ የሚጠጣ ካህን ይሻር አሉ። በዓቢይ ጾም ተደላ ደስታ ካደረግንበት ትንሳኤውን ባየን ጊዜ ተድላ ደስታችን ወዴት አለ አዝኖ ደስታ ጾሞ ፋሲካ እንዲሉ።

Anonymous said...

በላዔ ሰብ በአማርኛ ሰው በላ ማለት ነው፤ ትክክለኛ ስሙ ግን ስምዖን ይባላል ቅምር በሚባል አገር የሚኖር እጅግ ባለጸጋ ነበር፤ እንደ አብርሃም እንግዶችን እየተቀበለ ድሆችን እየመገበ የሚኖር ጻድቅ ነበር፤ ሰይጣን በዚህ ስራው ቀናበት ሊፈትነውም በሦስት አረጋዊ ሽማግሌዎች ስላሴ ነን ብሎ ተገለጠለት ልክ እንደ አብርሃም፤ ሐዋርያው ጳውሎስ ሰይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ ይመጣል እንዳለ፤ እርሱም ሥላሴ መስለውት ተቀበላቸው ተንከባከባቸውም፤ ምግብ አቀረበላቸው ምግብ አንበላም የምንጠይቅህን ግን ትፈጽምልን ዘንድ ቃል ግባልን አሉት ቃል ገባላቸው እንግዲያውስ የምትወደን ከሆነ አንድያ ልጅህን ሰዋልን አሉት፤ መጀመሪያ ደነገጠ ኃላ አብርሃም ልጁን ሊሰዋ አልነበረምን እኔንም ሊፈትኑኝ ይሆናል ብሎ ለማረድ ተዘጋጀ፤ተው የሚለው ድምጽ አልሰማም፤ አረደው አወራረደው ይዞላቸው ቀረበ፤ መጀመሪያ ቅመስልን አሉት ቀመሰው ወዲያው እነዚያ ሰዎች ተሰወሩበት እርሱም አህምሮውን ሳተ ተቅበዘበዘ ከዚያ በኃላ ምግብ አላሰኘውም የሰው ስጋ እንጂ መጀመሪያ ቤተሰቦቹን በላ ከዚያም ጓደኞቹን ጦርና የውኃ መንቀል ይዞ ከቤቱ ወጣ ያገኘውን ሰው እየገደለ ይበላል የበላቸው ሰው ቁጥር 78 ደረሰ፤ በመንገድ ተቀምጦ የሚለምን በደዌ የተመታ አንድ ደሃ አገኘ ሊበላው ወደ እርሱ ተጠጋ ግን ቁስሉን አይቶ ተጸየፈው፤ ደሃውም “ስለ እግዚያብሔር ከያዝከው ውኃ አጠጣኝ” አለው “ዝም በል ደሃ” ብሎት አለፈ፤ “ኸረ በውኃ ጥም ልሞት ነው ስለ ጻድቃን ስለ ቅዱሳን” አለው አሁንም ዝም ብሎት ሄደ ለሦስተኛ ጊዜ “ስለ አዛኝቷ ስለ እምዬ ማርያም” አለው፤ ሰውነቱን አንዳች ነገር ወረረው “አሁን የጠራከውን ስም እስኪ ድገመው ስለ ማን አልከኝ” አለው፤ ስለ አዛኝቷ ስለ እመቤቴ ማርያም አለው፤ ይህቺስ ደግ እንደሆነች በምልጃዋም ከሲኦል እንደምታወጣ ህጻን እያለው እናትና አባቴ ይነግሩኝ ነበር፤ በል እንካ አለው እጁን ዘረጋለት ጥርኝ ውኃ ጠብ አደረገለት ወደ ጉሮሮው አልወረደም የተሰነጠቀ እጁ ውስጥ ገባ እንጂ፤ በለዔ ሰብ ከዚያች ደቂቃ በኃላ አዕምሮው ተመለሰለት እንዲህም አለ “በአንድ ዋሻ ውስጥ ገብቼ ስለ ኃጢያቴ አለቅሳለሁ ስጋዬ ከአጥንቴ እስኪጣበቅ እጾማለሁ ወዮሊኝ ወዮታም አለቢኝ አለ፤ ወደ ዋሻ ገባ ምግብ ሳይበላ ውኃም ሳይጠጣ 21 ቀን ኖሮ በርሃብ ሞተ ይላል ተአምረ ማርያም። ጨለማ የለበሱ ሰይጣናት እያስፈራሩ እያስደነገጡ ነፍሱን ወደ ሲኦል ሊወስዷት መጡ፤ እመቤታችን ፈጥና በመካከላቸው ተገኘች፤ ልጄ ወዳጄ ይህችን ነፍስ ማርሊኝ አለችው እናቴ ሆይ 78 ነፍሳትን የበላ እንዴት ይማራል አላት፤ የካቲት 16 ቀን በጎለጎታ የገባህልኝ ቃል ኪዳን አስብ ስምሽን የጠራ መታሰቢያሽን ያደረገን እምርልሻለው ብለኸኝ የለምን አለችው፤ እርሱም እስኪ ይህቺን ነፍስ በሚዛን አስቀምጧት አለ ቢያስቀምጧት ጥርኝ ውኃው መዝኖ ተገኘ፤ ስላቺ ስል ምሬታለው ሰባት ቀን ሲኦልን አስጎብኝታችሁ ወደ ገነት አግቧት አላቸው። ቦታሽ እዚህ ነበር እያሉ ሲኦልን አስጎብኝተው ወደ ገነት አገቧት። ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን። ተአምረ ማርያም

Anonymous said...

please write valuable things you post this mezemur for advertisement write useful one only Gospel

Anonymous said...

May God bless your service!

መላኩ said...

እንኳን አደረሰን!

123... said...

+++

Selam Deje Selamoch,

Ebakachihu attach yaregachihutin ye KEBERO MEZMUR-KIDANE MIHRET YEMILEWIN TOLO ATFU. BE TSOM WEQT KEBERO MISALE YIHONAL. LELOCH LEMENKEFYA TAMECHACHALACHIHU. Sirate Betekrstyanm adelem BE TSOM.Please be NISHA KEYRUT TOLO.

bertu

melkam tsom

123... said...

ye kebero mezmur be tsomu. Tiliq chigir be blogu lay endemifetr asibu.Ebakachihu be Nisha keyrut.Sirate bete chrstyanm adelem. Ke ezih befit be tsom kebero yasmetut be DEJE SELAM sinte tenekfew wetewal? mn nekachihu? please ....please ....fitenu be Nisha mezmur keyiru. e-mailm likelachihu neber. Aklilachihu atyut.Blogun waga yasatawal.. please simu.

Anonymous said...

This is a kebre bebal in Ethiopia, tabot goes outside and then returns to its mebere. So on this holiday where their is a kidane meheret tabot kebro has been hit around the whole. So taking that into consideration, having a mezmur with kebro uploaded during tsome on this appropriate day is not any harm.

Anonymous said...

"This is a kebre bebal in Ethiopia, tabot goes outside and then returns to its mebere. So on this holiday where their is a kidane meheret tabot kebro has been hit around the whole. So taking that into consideration, having a mezmur with kebro uploaded during tsome on this appropriate day is not any harm."እግዚአብሔር ይስጥልን፤ ቢሆንም ግን መዝሙሩ ክብረ በአሉን የሚያሳይ መዝሙር ስላልሆነ ብሎጉ ምን ነካው ያስብላል ይቅር ይበለን፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)