February 20, 2012

ብፁዕ አቡነ አብሳዲ አረፉ


 (ደጀ ሰላም፣ የካቲት 12/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 20/2012)፦ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ አብሳዲ አረፉ። ላለፉት 60 ዓመታት በኢየሩሳሌም ገዳማት የኖሩትና በእግራቸው ከኢትዮጵያ ወደ ቅድስት አገር የመጓን ጥንታዊ ትውፊት ከፈፀሙት አበው መካከል የነበሩት ብፁዕነታቸው በሕመም እና በእርግና ምክንያት ከዚህ ዓለም ድካም በሰላም እንዳረፉ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ዝርዝር ዜናውን እንደደረሰልን እናቀርባለን። የብፁዕ አባታችንን ነፍስ በገነት ያኑርልን።
አሜን።

16 comments:

Anonymous said...

የሚገርመኝ እግዚአብሔር ቅዱሳኑን የሚሰበስበው ዐውደ ዓመትን ተከትሎ መሆኑ ነው!!!

Anonymous said...

Egzabher Amlak Nefisachewin Be Gent Mengiste Semaiat Yadirgilin!

Anonymous said...

ልዑል እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን! በረከታቸው ይደርብን!

Anonymous said...

Betam Yasasenal! Beqirb yemakatchew nebercu.Esatchew betam tiru, kidus sew neberu. Nefsatchew yemar!!!

nibret said...

Wude keduse abatachene teleyun!! Hazenachene Merire new!! Lenesuma betachewe hedu, legna degemo redietachewe, lemenachewe, reherahiachewe kerebene!! Balebetue ketsadekane gone yadergelene!!
WoldeGebriel

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

የአባታችንን፡ነፍስ፡ይማርልን፡ከአብርሃም፡ከያዕቆብ፡ ከይስሐቅ፡ጋራ፡ያስቀምጥልን፡መንግስተ፡ሰማያትን፡ ያውርስልን!!!

Anonymous said...

የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን ብቻ የሚለው ቢበቃን መልካም ይመስለኛል እኛ ስለርሳቸው ነፍስ የምንማልድ አይደለንም ከኢትዮጵያ እየሩሳሌም በእግሩ ለሄደ ቅዱስ አባት ነፍስ ይማርልን በማለት የምንናገረው ልማዳዊ አነጋገር ለሌሎች ያለንስሃ በድንገት ለተጠሩት ብናደርገው መልካም ነው እላለሁ ፡፡ የብፁዕነታቸው በረከት በሁላችን ይደርብን

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

Anonymous ነፍስ፡ይማር፡የሚባለው፡ዝም፡ብሎ፡ልምድ
አይመስለኝም፡፡አንድ፡ሰው፡በሰው፡ዘንድ፡ወይም፡በሰው፡ አስተያየት፡ፃድቅ፡መስሎ፡ታይቶ፡ፈጣሪና፡እሱ፡ብቻ፡ የሚያውቁት፡ሃጢአት፡ሊኖርበት፡ይችላል፡፡ስለዚህ፡ለኛ፡ ቸሩ፡አምላክ፡ካልገለጸልን፡ስለማናውቅና፡እርግጠኛ፡መሆን
ስለማንችል፡ለማንኛውም፡ሰው፡ነፍስ፡ይማር፡እንላለን፡፡ እንደዚህ፡ስል፡ግን፡የብፁዕ፡አባታችንን፡ቅድስናቸውን፡ ለመቃወም፡አይደለም፡፡

Anonymous said...

የብፁዕነታቸው በረከታቸው ይደርብንና!በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት መሰረት ለርሳቸው አይነት ለበቁ አባት ነፍስ ይማር አይባልም ::የቤተክርስቲያናችንን ስርአትና ትውፊት መጠበቅ አንዱ የተዋህዶ ልጂነት መለያ ነው::
የብፁዕነታቸው በረከት በሁላችን ይደርብን!!!
አሜን!!!

Anonymous said...

ስለ ብፁዕ አባታችን አቡነ አብሳዲ ዜና እረፍት ዝርዝር መረጃ እንደምታደርሱን ገልፃችሁ ነበር ይህን አስተያየት እስከላኩላችሁ ድረስ ግን ምንም ያወጣችሁት ዝርዝር ነገር የለም፡፡
ደጀ ሰላሞች እባካችሁ ብፁዕነታቸዉ ከሀገር ከወጡ ረጅም ጊዜ በመሆኑ ወይንም በሌላ ምክንያት ስለ እሳቸዉ ብዙም የማናዉቅ በርካቶች አለንና አጠቃላይ የህይወት ታሪካቸዉንና ሌሎች በህይወት ዘመናቸዉ ያከናወኗቸዉን ተግባራት በዝርዝር ብታደርሱን፡፡
እኔ በእዉነቱ ከሆነ በአጭር ዜና ስለ እርሳቸዉ ባወጣችሁት መረጃ ልቤ ተንጠልጥላለች ምክንያቱም እንደነዚህ አይነት አረጋዉያን ቅዱሳን አባቶች ለዛሬዉ ዘመን የቤተ ክርስትያን ችግር መጽናኛ ናቸዉና እባካችዉ ስል ብፁዕ አቡነ አብሳዲም ይሁን ስለ ሌሎች በገዳም ተወስነዉ ስለሚገኘዉ አረጋዉያን ጳጳሳት ህይወት አሳዉቁኝ

Ewnetu said...

"የብፁዕነታቸው በረከታቸው ይደርብንና!በቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት መሰረት ለርሳቸው አይነት ለበቁ አባት ነፍስ ይማር አይባልም "

እኛ ከቤተ ክርስቲያን ቀድመን "የበቁ" ማለት የምንችል አይመስለኝም:: ቤተክርስቲያን ጻድቅ/የበቁ እስትላቸው ድረስ ብንታገሥ:: የቡጽህነታቸውን ነፍስ በገነት ያኑርልን::

Anonymous said...

ማህበረ ክርስቲያን የቤተክርስቲያንን ትውፊት ጠብቀው የራሳቸውን ሃጢያትና በደል እያሰቡ የሚያዝኑበት ጊዜ በመሆኑ እኛንም የበረከቱ ተሳታፊዎች ለመሆን የበቃን ያድርገን፡፡

Anonymous said...

dear deje selamaweyan ye Bitsu abatachin sereate kebir gena altefetsemem ena zerzerun deje selamoch endedersachew ymiyasawekun yemselegnal ye Abatachin berket yedersen.

Anonymous said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!
ከአበው መነኮሳት ገዳማውያን ውስጥ ለጳጳስነት ሲታጩ በመጀመሪያ የመንፈሳዊ ህይወታቸው ብቃታቸው በቤተክርስቲያን የተመሰከረላቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ይሾማሉ:: እመቤታችን ብፁዕት እንደምትባል እነሱም ብፁዕ ይባላሉ /ብፁዕ አቡነ እገሌ ...ሲባሉ ከብፁአን ጳጳሳት ውስጥ አንዱ ፓትሪያሪክ ሲሾም ደግሞ ቅዱስ ይባላሉ /ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ እገሌ ... ::
እኛም የእግራቸውን ትቢያ እየሳምን በበረከት ስንኖር እንሱም ለአገልግሎታቸው ዋጋ /አክሊላቸውን / ከጌታችን ይቀበላሉ :: ከእረፍተ ስጋ በኋላም እንደ ብቃታቸው መጠን በቅዱስ ሲኖዶስ በስማቸው ታቦት/ሌላም መታሰቢያ ይሰራላቸዋል ::
በርግጥ በአሁኑ ወቅት የምናየው የቤተክርስቲያናችን ፈተናወች የብፁአን ጳጳሳትን የቅድስና ብቃት ጥያቄ ውስጥ ቢያስገባው አይደንቀኝም:: በዘመናችን በገንዘብ በጎሳ ለተለያዩ አላማ ማሳኪያ እንዲሁም እንደ አንድ የስራ ዘርፍ ክፍት የስራ ቦታ በመፍጠር የሚታደል ስለሆነ እነሱም ከቅድስና ስራ ይልቅ ለራሳቸው ቪላና ሀውልት ሲያሰሩ ገንዘብ ሲያተራምሱ ይታያሉ ስለዚህ ወንድሞች ብፁአበውንና ነጋዴው ተምታታባቸው ለማንኛውም በረከታቸው ይደርብን ማለት በረከታቸውን እንጅ ሌላ ርራቸውን ማለት አይደለም በረከት የማይፈለግ ግዴታ የለበትም ::ማቴ 10: 40
ቅድስና ብቃታቸው

Anonymous said...

አባታችንን፡ከአብርሃም፡ከያዕቆብ፡ ከይስሐቅ፡ጋራ፡ያስቀምጥልን፡መንግስተ፡ሰማያትን፡ ያውርስልን!!!

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

anonymousበእልከኝነት፡ባንናገር፡ጥሩ፡ነው፡፡አንተ፡ በጣም፡እንደምትወዳቸው፡አፃፃፍህ፡ይገልፃል፡፡እኔም፡እወዳቸዋለሁ፡ለሁላችንም፡አባት፡ናቸው፡፡አሁንም፡በረከታቸው፡ከሁላችን፡ጋራ፡ይሁን፡፡ወንድሜ፡Ewnetu፡ እንደገለጸው፡ቤተ፡ክርስትያን፡ቅዱስ፡እስክትላቸው፡እንታገስ፡፡ሰማዕቱ፡አባታችን፡አቡነ፡ጴጥሮስም፡አሁን፡ በቅርብ፡ነው፡ቅዱስ፡የተባሉት፡በአቡነ፡ጳውሎስ፡ዘመነ፡ፕትርክና፡፡እንግዲህ፡አቡነ፡አብሳዲን፡ቅዱስ፡ብላ፡ቤተ፡ክርስትያን፡እስክትጠራቸው፡እኛ፡ልንላቸው፡አይገባምይህ፡ማለት፡ግን፡እሳቸውን፡ከክብራቸው፡ማሳነስ፡አይምሰለን፡፡ብፁዕነታቸውን፡ቅድስናቸውን፡ንፅህናቸውን፡ማንም፡አይቀማቸውም፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)