February 16, 2012

በቅዱስ ሲኖዶስና በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል የዕርቀ ሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው


·        ከአገር ቤት ልካን አንዱ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ከጤና እክል ጋራ በተያያዘ በውይይቱ ላይ አይሳተፉም፤ ወደ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ገብተው ሕክምና እየተከታተሉ ነው
(ደጀ ሰላም፣ የካቲት 7/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 15/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሰሜን አሜሪካ በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል ሁለተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ውይይት ዛሬ፣ የካቲት 7 ቀን 2004 ዓ.ም፣ ማምሻውን በአሜሪካ - አሪዞና ግዛት እየተካሄደ ነው፡፡ የዕርቀ ሰላም ውይይቱን በሚያስተባብረው የሰላም እና አንድነት ጉባኤ በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ይኸው ሁለተኛ ዙር ንግግር ከየካቲት 4 - 9 ቀን 2004 ዓ.ም እንደሚቆይ ተገልጧል፡፡

ከየካቲት አራት ቀን ጀምሮ በዕርቀ ሰላሙ የመነጋገሪያ ሐሳቦች ላይ በሁለቱ አካላት ልካን ተወካዮች መካከል ሲካሄድ በቆየው የቅድመ ውይይት ንግግር ሰባት አጀንዳዎች ተለይተው ነበር፡፡ ይሁንና ዛሬ በተጀመረው ውይይት ዋነኛ የመነጋገሪያ ጉዳይ የሚሆነው በአጀንዳ ተራ ቁጥር አንድ የተቀመጠው “ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን በተመለከተ” በሚል የተመለከተው ነጥብ ነው ተብሏል፡፡
በዚህ አጀንዳ÷ አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው እንዲነሡ በተደረገበት ሁኔታ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተጥሷል ወይስ አልተጣሰም? የቅዱስነታቸው ቀጣይ ሁኔታስ ምን መሆን ይገባዋል? የሚሉትና ተያያዥ ጉዳዮች ትኩረት እንደሚሰጣቸው ተዘግቧል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ባለው ሁኔታ ውይይቱ በመግባባት እየተካሄደ ስለመሆኑም የስብሰባው ምንጮች ለደጀ ሰላም ተናግረዋል፡፡ ከውዝግቡ በኋላ ስለተሾሙት ጳጳሳት፣ አንዱ በሌላው ላይ ስላስተላለፋቸው ውግዘቶች፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከሚደረጉ የመንግሥት ጣልቃ ገብነቶች ተቋማዊ ነጻነት ስለማግኘት፣ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ አሠራር እና የስምምነቶች አፈጻጸም እንዲሁም ስለ ብሔራዊ ዕርቅ የሚያወሱት ቀሪዎቹ ስድስት አጀንዳዎች በዚህ ዙር ውይይት ይነሣሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ቅዱስ ሲኖዶስን በመወከል የድሬዳዋ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት የውጭ ግንኙነት ላፊ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የልካን ቡድኑን በመምራት፣ የደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስአባልነትየአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ ድ ኤልያስ ብርሃ ደግሞ በካን ቡድኑ ሐፊነት በዕርቀ ሰላም ውይይቱ ላይ ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ያመሩት የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ.ም ነበር፡፡
በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ሦስተኛው የልካን ቡድኑ አባል የሆኑት የሰሜን ምዕራብ ሸዋ-ሰላሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ባጋጠማቸው የጤና እክል ሳቢያ አብረው አልተጓዙም፡፡ ብፁዕነታቸው ከየካቲት 2 ቀን ጀምረው በአዲስ አበባ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ገብተው ሕክምና በመከታተል ላይ ሲሆኑ ሕመማቸው የሳምባ ምች እና ስኳር መሆኑ ተመልክቷል፡፡ የሆስፒታል ምንጮች እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት ብፁዕነታቸው ከሳምባ ምች ሕመማቸው በማገገም ላይ እንደሆኑና ከፍተኛ የስኳር መጠናቸውም በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡ በሰሜን አሜሪካ በስደት ከሚገኙት አባቶች ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ እና ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ እና መልአከ ገነት ገዛኸኝ የዕርቀ ሰላም ንግግሩ ዋነኛ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

15 comments:

Desalew said...

tanks god!!! DESSS yilal. god bless ethiopia and ethiopian church!!!

tadewos said...

"በቤተ ክርስቲያን ላይ ከሚደረጉ የመንግሥት ጣልቃ ገብነቶች ተቋማዊ ነጻነት ስለማግኘት፣.... "

ለዚህ ውይይት ወጤታማነትም የመንግሥት ጠልቃ አለመግባትና የአቡነ ፓውሎስ ከቤተክርስቲያን ይልቅ ለወያኔ ቅድሚያ አለመስጠት የማዕዘን ድንጋይ ነው::
ካልሆነ ውኃ ወቀጣ ነው::
አቡነ ፓውሎስን ማመን አይቻልም::
ልዑካኑን የላኩት ለይምሰል እንዳልሆነና ልዑካኑ እዚያው እያሉ በስልክም ተጽእኖ እንደማያደርጉባቸው ማረጋገጥ አይቻልም::
እኛ ግን በእንተ ዝንቱ ነገር ጸሎት አይለየን::

Anonymous said...

ቸር ወሬ ያሰማን!!!

Anonymous said...

Abatochachin ebakachihu Amlak bemiwodat kidist Haymanotachin yeminamin lijochachihun yeandinetin, yemefakerin , yemekebaberin menged astemrun. Amlak beandinet yatsnan. Amen

Anonymous said...

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና በስደት ላይ ባለው ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የዕርቀ ሰላም ውይይት አቶ ታምራት ላይኔ የቀድሞው ጠቅላይ ሚ/ር ተጠርቶ በሰላም እና አንድነት ጉባኤ በኩል ስለ አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው እንዲነሡ በተደረገበት ሁኔታ ላይ በህይወት እያለ ቃሉን ቢሰጥ ለትክክለኛ ፍርድ አሰጣጥ መልካም ነው እላለሁ ::
ቸር ወሬ ያሰማን

lele said...

abato AMELAKACHEN macharashawen yasamerelen.telatoche yefaro egame ande laye honane bamesegana endenezamer.ABATE HOYE talamanane..

Tewahedo said...

Thanks DEJESELAM for your wise and substantiated reporting. I presume that you have learnt from your previous naive and hasty reporting mistakes.

Let us hope that our Gracious Lord Jesus Christ will unite our Mother Church and we will glorify His Holy Name in unison.

Tewahedo Ze-Toronto

Anonymous said...

Is the conflict between the Holy Synod and Fathers in exile or between the Fathers?

Anonymous said...

እግዚአብሄር መንፈስ ቀዱስ ይምራቸው። የመቻቻል፣ የመከባበር፤ አንደበታቸውን የሚገዙበትና ለሕዝበ ክርስቲያኑም አራያ ያድርግልን።

Anonymous said...

yhun est

Anonymous said...

slam------------ amlak ycemerbet abun merkoryosn gn meteqemiy eyaderegeacew ymeslal mknyatum menafqanu hulu eyetetaegu yalut beesacaw sr new yhem ytasebbet

Anonymous said...

Geta Amlak bekachu yebelen! Satan Yefer

Anonymous said...

As Christians, we need to rely on the will of God and His miracles Hands. However, My hope is so down as I get to know and see more and more about Abune Poulose and his dangerous mission on our holy church. I have also a big disappointment on the other side after I saw the ESAT interview with Abune Melketsedik. Especially, his concluding remarks and hope for reconciliation. According to him, all the Ethiopian in Diaspora need to go home (Ethiopia) (http://www.ethiomedia.com/broad/3446.html) for the reconciliation process to be successful (as a condition). I wish Abune Merkoriwos himself be on the negotiation table instead of Abune Melketsedik. Any ways, Let “HIS(GOD’S) WILL SHALL BE DONE”

Anonymous said...

የአባቶቻችን የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብ አምላክ
መልካሙን ሁሉ እንድታገርጉ ይርዳችሁ።

“እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ ደቀ መዛሙርቴ
እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።”
ዮሐ. 13:35

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አይለያችሁ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ድሉ said...

ክርስቶስ ሠምራ ሞክራው ነበረ የሚባለው አይነት እርቅ ይመስላል። ክርስቶስ ሠምራ ማንና ማንን ነበር ለማስታረቅ ሞክራ ሳይሳካለት የቀረው ? እርቁንስ ማን ነበር እብይ ያለው ?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)