February 16, 2012

በቅዱስ ሲኖዶስና በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል የዕርቀ ሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው


·        ከአገር ቤት ልካን አንዱ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ከጤና እክል ጋራ በተያያዘ በውይይቱ ላይ አይሳተፉም፤ ወደ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ገብተው ሕክምና እየተከታተሉ ነው
(ደጀ ሰላም፣ የካቲት 7/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 15/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሰሜን አሜሪካ በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል ሁለተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ውይይት ዛሬ፣ የካቲት 7 ቀን 2004 ዓ.ም፣ ማምሻውን በአሜሪካ - አሪዞና ግዛት እየተካሄደ ነው፡፡ የዕርቀ ሰላም ውይይቱን በሚያስተባብረው የሰላም እና አንድነት ጉባኤ በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ይኸው ሁለተኛ ዙር ንግግር ከየካቲት 4 - 9 ቀን 2004 ዓ.ም እንደሚቆይ ተገልጧል፡፡

ከየካቲት አራት ቀን ጀምሮ በዕርቀ ሰላሙ የመነጋገሪያ ሐሳቦች ላይ በሁለቱ አካላት ልካን ተወካዮች መካከል ሲካሄድ በቆየው የቅድመ ውይይት ንግግር ሰባት አጀንዳዎች ተለይተው ነበር፡፡ ይሁንና ዛሬ በተጀመረው ውይይት ዋነኛ የመነጋገሪያ ጉዳይ የሚሆነው በአጀንዳ ተራ ቁጥር አንድ የተቀመጠው “ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን በተመለከተ” በሚል የተመለከተው ነጥብ ነው ተብሏል፡፡
በዚህ አጀንዳ÷ አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው እንዲነሡ በተደረገበት ሁኔታ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተጥሷል ወይስ አልተጣሰም? የቅዱስነታቸው ቀጣይ ሁኔታስ ምን መሆን ይገባዋል? የሚሉትና ተያያዥ ጉዳዮች ትኩረት እንደሚሰጣቸው ተዘግቧል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ባለው ሁኔታ ውይይቱ በመግባባት እየተካሄደ ስለመሆኑም የስብሰባው ምንጮች ለደጀ ሰላም ተናግረዋል፡፡ ከውዝግቡ በኋላ ስለተሾሙት ጳጳሳት፣ አንዱ በሌላው ላይ ስላስተላለፋቸው ውግዘቶች፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከሚደረጉ የመንግሥት ጣልቃ ገብነቶች ተቋማዊ ነጻነት ስለማግኘት፣ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ አሠራር እና የስምምነቶች አፈጻጸም እንዲሁም ስለ ብሔራዊ ዕርቅ የሚያወሱት ቀሪዎቹ ስድስት አጀንዳዎች በዚህ ዙር ውይይት ይነሣሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ቅዱስ ሲኖዶስን በመወከል የድሬዳዋ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት የውጭ ግንኙነት ላፊ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የልካን ቡድኑን በመምራት፣ የደቡብ ወሎ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስአባልነትየአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ ድ ኤልያስ ብርሃ ደግሞ በካን ቡድኑ ሐፊነት በዕርቀ ሰላም ውይይቱ ላይ ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ያመሩት የካቲት 2 ቀን 2004 ዓ.ም ነበር፡፡
በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ሦስተኛው የልካን ቡድኑ አባል የሆኑት የሰሜን ምዕራብ ሸዋ-ሰላሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ባጋጠማቸው የጤና እክል ሳቢያ አብረው አልተጓዙም፡፡ ብፁዕነታቸው ከየካቲት 2 ቀን ጀምረው በአዲስ አበባ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ገብተው ሕክምና በመከታተል ላይ ሲሆኑ ሕመማቸው የሳምባ ምች እና ስኳር መሆኑ ተመልክቷል፡፡ የሆስፒታል ምንጮች እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት ብፁዕነታቸው ከሳምባ ምች ሕመማቸው በማገገም ላይ እንደሆኑና ከፍተኛ የስኳር መጠናቸውም በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡ በሰሜን አሜሪካ በስደት ከሚገኙት አባቶች ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ እና ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ እና መልአከ ገነት ገዛኸኝ የዕርቀ ሰላም ንግግሩ ዋነኛ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)