February 10, 2012

የዋልድባ ገዳማት ህልውና እና ክብር ለአደጋ ተጋልጧል

·     በገዳሙ ክልል እና ዙሪያ (በዓዲ አርቃይ ወረዳ በኩል) የፓርክ ይዞታ ለመከለል እና የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም በሚል በሚካሄደው የጥርጊያ መንገድ ሥራ (ከማይ ፀብሪ እስከ ዕጣኖ ማርያም) የቅዱሳን አበው ዐፅም እየፈለሰ መሬቱ እየታረሰ ነው
· የሦስቱ ገዳማት ማኅበረ መነኮሳት ዕቅዱ የገዳሙን ክብር የሚጋፋ ህልውናውንም የሚያጠፋ በመሆኑ እንዲቆምላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል

·   መንግሥት ካቀዳቸው 10 ግዙፍ የስኳር ፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክቶች አንዱ በዋልድባ ገዳም ክልል እና ዙሪያ (ወልቃይት - መዘጋ) የሚቋቋም ሲሆን በዛሬማ ወንዝ ላይ 3.8 ቢልዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ የመያዝ አቅም ያለውና 40,000 ሄ/ር የሸንኮራ ተክል የሚለማበት ግድብ ይቆምለታል፤ ግድቡ በሚሸፍነው ስፍራ (ማይ ዲማ) የሚገኙ አራት አብያተ ክርስቲያን የሚነሡ ሲሆን ለ10,000 የፕሮጀክቱ ጊዜያዊ እና ቋሚ ሠራተኞች የመኖሪያ ካምፕ ግንባታ እየተካሄደ ነው
·    በቅድስት ገዳማችን ዋልድባ ውስጥ ለሚደረገው አግባብ ያልሆነ እንቅስቃሴ አበው ቅዱሳን አባቶቻችን ልዩ ሥራ እንዳይሠራባት የውግዘት ቃል (እንበለ ፈላሲ ኢይባዕ ነጋሲ) ያሳለፉባት ቦታ በመሆኗ ማኅበረ መነኮሳቱ ባደረግነው ምልአተ ጉባኤ መሠረት ለሚሠራው ሥራ ፈጽሞ ፈቃዳችን አለመሆኑንና የአባቶቻችን ቅዱሳንን ፈለግ ሕግና ሥርዐት ተከትለን የምንሄድ መሆናችንን በጥብቅ እናሳውቃለን

(ደጀ ሰላ የካቲት 2/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 10/2012)፦ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ እና ታሪካዊ ገዳማት አንዱ ነው፤ ለግሑሳን(ፍጹማን) ባሕታውያን መሸሸጊያ፣ ለስውራን ቅዱሳን መናኸርያ፣ በብዙ ሺሕ ለሚቆጠሩ መነኮሳት፣ መነኮሳይያት እና መናንያን መጠጊያ፣ ለምእመናኑንም መማፀኛ እና ተስፋ ነው - የዋልድባ ገዳም፡፡
ቅዱሳን አበው እንደ ጽፍቀተ ሮማን የሰፈሩበት፣ እንደ ምንጭ የሚፈልቁበት ገዳሙ እመቤታችን ከልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ስደት ወቅት በኪደቱ እግር ከረገጧቸው መካናት አንዱ ነው፡፡ በወቅቱ ጌታችን የወይራ ተክል ተክሎና አለምልሞ አርኣያ ስቅለቱን ገልጾበታል፤ ለቅዱሳኑ “እንደ ኢየሩሳሌም ትኹንላችሁ፤” ብሎ ቃል ኪዳን በመስጠት እህል እንዳይዘራባት፣ ኀጢአት እንዳይሻገርባት፣ ከድንግል አፈሯ የተቀበረ እንዳይወቀስባት እንዳይከሰስባት አዝዟል፡፡ በሰሜን ተራራዎች ግርጌ ዙሪያዋን በሰሜን አንሴሞ፣ በምሥራቅ ተከዜ፣ በምዕራብ ዘወረግ እና በደቡብ ዜዋ በተባሉ አራት ወንዞች በተከበበችውና የኢትዮጵያ ገዳማት ሁሉ መመኪያ በተባለችው ገዳም ከሙዝ ተክል ከሚዘጋጀው ቋርፍ እና ቅጠላ ቅጠል በቀር እህል አይበላባትም፡፡
በዚያ ቅዱሳን አበው፣ መነኮሳት እና መነኮሳይያት ረቡንና ጥሙን ታግሠው፣ የአገርን ቅርስና ሀብት ጠብቀው ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም እያለቀሱና እየጸለዩ፣ ዲማ በተባለው ፍልፍል ዛፍ በኣታቸው እያለፉ ኖረዋል፤ ቦታው ከፍተኛ የድኅነትና ሃይማኖት ፍራ ነውና ዛሬም ለአገር ሰላም፣ ፍቅርና ዕድገት ያልተቋረጠ ጸሎት እየተካሄደበት የሚገኝበት ቢሆንም ለ2000 ዓመታት በነገሥታቱ ሳይቀር ተጠብቆ የኖረውን ክብሩንና ሞጎሱን የሚፈታተን፣ ገዳማዊ ሕጉንና ሥርዐቱን የሚጋፋ፣ ማኅበረ መነኮሳቱንም ለከባድ ኀዘንና ጭንቀት የሚዳርግ አደጋ ተጋርጦበታል፡፡
የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበር፣ የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም ማኅበር እና የዋልድባ ዳልሽሓ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ማኅበር ምልአተ ጉባኤ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ዜናዊ በጻፉት አምስት ገጽ ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው÷ በዓዲ አርቃይ ወረዳ በኩል የዋልድባን ገዳም ውስጡን በፓርክነት ለመከለል በቀለም የተቀለሙ ምልክቶች እየተተደረጉ ነው፡፡ በወልቃይት ወረዳ ልዩ ስሙ መዘጋ በተባለ የገዳሙ የእርሻ እና አዝመራ ቦታ ላይ መንግሥት የዛሬማን ወንዝ ገድቦ የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በገዳሙ ክልል ዘልቆ የሚያልፍ ጥርጊያ መንገድ ለመሥራት በግሬደር እና ሌሎችም ከባድ የሥራ መሣሪያዎች በሚካሄደው ቁፋሮ የቅዱሳን አባቶች ዐፅም እየታረሰና እየፈለሰ መሆኑ የገዳሙን መነኮሳትና መናንያን ከፍተኛ ሐዘንና ጭንቀት ላይ ጥሏቸዋል፡፡
የማኅበረ መነኮሳቱ ደብዳቤ ጨምሮ እንደሚያብራራው የዛሬማ ወንዝ ግድብ ሲቆም በውኃ ሙላቱ ሳቢያ ከሚጠፉት የገዳሙ ወሳኝ ይዞታዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
1)             ልዩ ስሙ አባ ነፃ የተባለ የብዙ ቅዱሳን ዐፅም በክብር የፈለሰበትና የረገፈበት፣ ብዙ መነኮሳት እና መናንያን የሚቀመጡበት (የሕርመት/ተዐቅቦ ቦታ) የጻድቁ አቡነ ተስፋ ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንና መቃብር እንዲሁም የሙዝ ቋርፍ በከፍተኛ ደረጃ የሚዘጋጅበት እጅግ ሰፊ የሆነ የአትክልት ፍራ፤
2)            መዘጋ የሚገኙት ሞፈር ቤቶች/በገዳሙ ውስጥ እህል ስለማይበላ የዓመት ቀለብ የሆነ ቋርፍ የሚዘጋጅበት የአትክልት ስፍራ/
3)            በመዘጋ የገዳሙ መነኮሳት እህል የሚቀምሱበት ቤት
4)            ጥንታውያን የሴቶች መነኮሳይያት መኖሪያ ገዳሞችና ታሪካዊ ቦታዎች፤

እነዚህም፡-
4.1)  ማየ ሕርገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከመነኮሳት፣ መነኮሳይያት፣  መናንያን፣ የገዳሙ ተማሪ ቤቶችና መኖሪያ ቤቶቻቸው፤
4.2)  ዕጣኖ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የመነኮሳት፣ መነኮሳይያት አጠቃላይ መናንያ የገዳሙ የቤተ ክህነት ትምህርት መማሪያ ቤቶች ከመምህሮቻቸውና ተማሪዎቻቸው ጋራ፤
4.3)  በተለይም በዋልድባ አብረንታንት ውስጥ ያሉ ባሕታውያን፣ መነኮሳትና መናንያን የሙዝ ቋርፍ የሚዘጋጅበት ገዳሙ በዋናነት የሚተዳደርበት እጅግ ሰፊ የአትክልት ቦታ፤
4.4)  ደላስ ቆቃህ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን የመነኮሳት፣ መነኮሳይያት፣ መናንያን መኖርያ ቤቶች፣ የገዳሙ ቤተ ክህነት ት/ቤቶች፣ መምህሮቻቸውና ተማሪዎቻቸው እስከ መኖርያ ቤቶቻቸው ናቸው፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት የገዳሙ ይዞታዎች ከጠፉ ገዳሙ ምንም ዐይነት የገቢ ምንጭና መተዳደር /በደላሳ ቆቃህ እንደ ማሽላ፣ ዳጉሳ በማምረት/ የማይኖረው በመሆኑ መነኮሳቱ፣ መነኮሳይያቱ፣ መናንያኑ፣ መምህራኑና ተማሪዎቻቸው ለረብ እና ስደት የሚዳረጉ በመሆኑ ማኅበሩ ሙሉ በሙሉ እንደሚያከትምለት ያስረዳው ደብዳቤው÷ መንግሥት ሐዘናቸውንና ጩኸታቸውን ሰምቶ የገዳማቸውን ሕግ እና ሥርዐት እንዲያስከብርላቸው ተማፅነዋል፡፡
ቀደም ሲል በተለይም ከ1997 ዓ.ም ወዲህ ማይ ሰርኪን ከተባለው ቦታ ወርቅ እናወጣለን በሚሉ ቆፋሪዎችና ዕጣን እንለቅማለን በሚሉ መቀርተኞች (ቁጥራቸው በዐሥር ሺሕዎች በሚገመት ሰፋሪዎች) ተጥለቅልቀው ሲታወኩና ሲረበሹ መቆየታቸውን የጠቀሰው የማኅበረ መነኮሳቱ ደብዳቤ አሁን ደግሞ ፓርክ ለመከለል፣ የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋምና ጥርጊያ መንገድ ለማውጣት የሚካሄደው እንቅስቃሴ ለገዳሙ ህልውና በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሆነበት አትቷል፡፡
በበጋ ወቅት መንሥኤው የማይታወቅ የሰደድ እሳት ከሚያወድመው ደን ባሻገር በወርቅ ጫሪዎቹ እና በዕጣን መቀርተኞቹ ሳቢያ አበው መነኮሳት ጭብጥ ቋርፍ ይዘው ሱባኤ የሚይዙባቸው/የሚሰወሩባቸው ዛፎች (ፍልፍል ዲማ)፣ መድኃኒትነት ያላቸው ዕፀዋትና የግሑሳኑ መሳፈርያ የሆኑት የዱር እንስሳት (አንበሳ፣ አጋዘን፣ ነምር) ከገዳሙ እየጠፉ መሆናቸውም ተመልክቷል፡፡
ከማኅበረ መነኮሳቱ ጋራ ባለፈው ዓመት የመዘጋ እና የወልቃይት ነዋሪዎች ማይ ገባ ንኡስ ወረዳ ላይ የተቃውሞ ድምፃቸውን በሰልፍ ማሰማታቸውንም ያወሱት የገዳማቱ ተወካዮች ልማትን የሚቃወሙ ባይሆንም ስለ ዕቅዱ ምንም የተገለጸላቸው ነገር ባለመኖሩ ቦታው የጸሎት፣ የተጋድሎና የቅድስና መሆኑ ቀርቶ የዓለማውያን መናኸርያ፣ የነጋድያንና የሕዝብ መስፈርያ፣ የመኪና መሽከርከርያ እንዲሆን ፈቃደኞች እንዳይደሉ የገዳሙ ማኅበር አባላት ገልጸዋል፤ በገዳሙ ልዩ ሥራ እንዳይሠራ “እንበለ ፈላሲ ኢይባዕ ነጋሲ” በማለት ቀደምት አባቶቻቸው ያስተላለፉትን የውግዘት ቃል በማስጠበቅ በቅዱሳኑ ፈለግ ሕግና ሥርዐት መጓዛቸውን እንደሚቀጥሉም በጥብቅ አስተውቀዋል፡፡
በአምስት ዓመቱ የመንግሥት ልማት እና ትራንፎርሜሽን ዕቅድ መሠረት በስኳር ምርት ራስን ለመቻል ከሚቋቋሙት ዐሥር ግዙፍ የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የ4.2 ቢልዮን ብር ዕቅድ የተያዘለት ይኸው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ነው፡፡ ፋብሪካው በ40,000 ሄ/ር ላይ የሚለማውን የሸንኮራ ተክል የሚጠቀም ሲሆን የውኃ ምንጩም በዛሬማ ወንዝ ላይ የሚሠራው ርዝመቱ 700 ሜትር፣ ከፍታው 138 ሜትር የሆነና 3.8 ቢልዮን ሜትር ኪቢዩክ ውኃ የመያዝ አቅም ያለው ግድብ ነው፡፡
ውኃው ያርፍበታል በተባለው ማይ ዲማ በተባለው ቦታ የሚገኙት የማር ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የማይ ገባ ቅዱስ ሚካኤል፣ የዕጣኖ ቅድስት ማርያም እና የደለሳ ቆቃህ አቡነ አረጋዊ አብያተ ክርስቲያን እንደሚነሡ ተነግሯል፡፡ ሥራውን ያካሂዳል የተባለው የፌዴራል ውኃ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ሲሆን በአሁኑ ወቅት ለ10,000 የፕሮጀክቱ ቋሚ እና ጊዜያዊ ሠራተኞች የካምፕ ግንባታ እየተከናወነ፣ ቦታውንም ምቹ የማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
በሰሜን ምዕራብ ትግራይ - ሽሬ እንዳሥላሴ እና በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ዓዲ አርቃይ ወረዳ ክልል በሚገኙት ሦስቱ የዋልድባ ገዳማት በአጠቃላይ ከ3000 ያላነሱ መነኮሳትና መነኮሳይያት የሚገኙ ሲሆኑ የሴቶች ገዳም በሆነው የዳልሽሓ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ከ1500 ያላነሱ ሴት መነኮሳይያት ይገኙበታል፡፡ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ምክሆን ለገዳማተ ኢትዮጵያ ማኅበር ዘቤተ ሚናስ ዋነኛው የሕርመት/ተዐቅቦ ቦታ ሲሆን ወንዶች መነኮሳት ብቻ ያሉበት፣ እስከ 50 ዓመት ድረስ በአርምሞ ከሰው ተነጋግረው የማያውቁ ቅዱሳን በዘመናችን ሳይቀር የሚገኙበት ነው፡፡
ገዳሙን በማደራጀት እና የተባሕትዎን ኑሮ በማጠናከር በ14ው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበሩትና ሰባቱ ከዋክብት ከሚባሉት የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደቀ መዛሙርት አንዱ ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል (ሳሙኤል ፀሐይ ዘዋሊ) ይጠቀሳሉ፤ ገዳሙን ያቀኑትም በዐምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት በ1319 ዓ.ም ነው፡፡ የገዳሙን ኑሮ መልክ የሰጡት ከደብረ ሊባኖስ በሄዱት እንደ አባ ሙሴ የመሳሰሉት አባቶች ሲሆኑ “በገዳም እንኖራለን፤ እህል አይገባንም” በማለት ከእርሳቸው ጊዜ ጀምሮ የመነኮሳቱ ምግብ ቋርፍ - ሙዝ በጨው ተቀቅሎ እንዲሆን ተወስኗል፡፡
የዋልድባ መነኮሳት ከነገሥታት ጉልት አይቀበሉም ነበር፤ ሲሰጥም አጥብቀው ይቃወሙ ነበር፡፡ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ /1426 - 1460 ዓ.ም/ ዘመነ መንግሥት የዋልድባ ገዳም በአራቱ ጅረቶች መካከል እንዲሆን ተከልሎ ገዢ እንዳይገባ፣ አራሽ እንዳይሠማራ ተከልክሏል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን

አሜን34 comments:

Anonymous said...

begna zemen yalenen neger hulu matat endet yamal.hodam hulu tesebsibo lezich ken enkuan mehon yakten?ere ebakachu yekidus sinados abalat abatoch leyetgnaw edmeyachu new yemtserut?ere bemeskel lay demun slafesesew amlak telemenu?ere slekidusanu blachu? benante mankelafat egna tamemn,betekrstian bikefel benante,krstian bichfechef bezimita,yalenen binkema bezimita,endet new yemtmerun?ere mechohn astemrun?ere abet belu?egnako kemenafikanum,ketehadisowm yenante akuam gira geban?bemekera wist yalutn ye copt kiristian abatochn tinikare temelketu?yekedemut abatoch tariks min yastemrenal?ere lemenekosatu diresulachew?ebakachu,sile azagnetu...........

Anonymous said...

tmenekosatunem hone gedamun yminka neger yelm limat dagmo lhulum asflagi new. dejeslamoch sewn batagchu!

Anonymous said...

ወገኖቼ ጉዳዩ በጣም የሚያሳዝን ነው ! የገዳሙ መነኮሳት ወደ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አቤት ከማለታቸው አስቀድሞ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ብቅ አላሉምን??? ከጠቅላይ ቤተ ክህነትስ ምን ምላሽ አገኙ??? ጉዳዩ በቤተክርስቲያናችን ቅዱሰ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤስ መታየት የለበትምን??? ውሳኔ ሰጪ የሆኑ መንግሰታዊ አካላትን በተጨባጭ ለማሳመን አቤቱታው በቅዱስ ፓትርያርኩ ቢሮ በኩል ለሚመለከተው አካል ቢቀርብ ውጤታማ ይሆናልና በቶሎ ቢታሰብበት መልካም ነው። የመናንያኑ ጸሎት ከ 80,000,000 የሚበልጠው የቅድስት ሀገር ሕዝብ በአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ረድኤትና በረከት ተጠብቆ እንዲኖር ያደረገ እና መንፈሳዊ ረድኤቱ ከሁላችን ሕይወት ጋር የተያያዘ ነውና በዚሁ ጉዳይ ሁላችን ጸሎት እንድናደርግ አሳስባለሁ። ለታቀደው ልማት ሀገሪቱ ብዙ አማራጭ ሥፍራዎች አላትና ይህ በጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ የተገደመ በስደቱ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ያረፈበትና የባረከው ታላቅ የበረከት ሥፍራ መንፈሳዊ ቅርስነቱ ለሀገሪቱ ክብር ነውና ውሳኔ ሰጪዎች ደጋገማችሁ አስቡበት ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ እንዳትገኙ ቅዱስ ዳዊት መዝ 7:11-12 ላይ የተናገረውንም በማሰተዋል አንብቡት እንዲህ ይላልና እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ ነው፥ ኃይለኛም ታጋሽም ነው፥ ሁልጊዜም አይቈጣም። ባትመለሱ ግን ሰይፉን ይስላል።’ መዝ 7:11-12

Haile Michael said...

የፓትርያርኩ የሃይማኖት አባትነት ለመቼ ነው? የሃይማኖት አባትነትስ እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? አቦ አቦ የሚሉለትን መንግሥት በዚህ ጉዳይ አነጋግረው መፍትሔ ማበጀት የማይችሉ ከሆነ ለምን ይሆን ኢሕአዴግን የሚደሰኩሩልን ?
ወይስ እንደሚባለው የወያኔን ጉዳይ ለማስፈጸም ቤተክህነት የገቡ ሰው ናቸው?

Anonymous said...

are Egzio yemiyasegn neger new. Tekilay ministiru be'andi wekt egna tarik linatefa sayihon tarik linitebik new yetageln new bilew neber. Tadiya ahun ageritwa hizbuwa egziabher bemihret enditebikat 24 se'at bemitseleyibet gedam wust arat betekiristiyan yifersalu eyetebale new. Be'ewunet yih neger ewunet kehone ena betekiristiyanu keferese tekilay ministiru andim ken besiltan endemayikoyu mawek yigebachewal ye'egaziabher na yehizbu kuta belayiwo lay tifetsemalechina degmew degmew biyasibubet melkam new. Ye Ethiopia hizb behaymanotu kemetubet wedehala endemayil tenkikew yawkalu. Angetachin leseyf enisetalen enji yih neger fetsimo lihon ayichilim. Lelimat yemihone me'at bota eyale tarik, kirsi eyatefu limat yemibalew fetsimo tekebayinet yelewum. Tarikachin kemitefa berehab binimot yishalenal. Egziabher amlak tarikachin enditebikulin lib yistilin lebalesiltanatu. Abatochachin menokosatim Egziabher yitebikilin yatsinalin

Anonymous said...

ውድ ምዕመናን እኔ ያልገባኝ ነገር ማንን ነው የምንጠብቀው? ማንን ነው የምንፈራው? በቤተክርስቲያን ላይ ለሚመጣው ቁጣ ለመከላከል ቆርጠን ካልተነሳን እራሳችን ካልተሰዋን ምኑ ነው ክርስትና?
አባ ጳውሎስ ያመጡት ጣጣ አይደል እንዴ_?
በእርግጥ ብዙ አባቶች አሉ ግን ከተናገሩ ስለሚደበደቡ ዝምታን መርጠዋል።
አቡነ መልከጼዴቅ ታጋይ ስለነበሩ ደብድበው ለሞት አብቅተዋቸዋል። አቡነ ቄርሎስም አሁን በጸና ታመዋል።
አቡነ አብርሃምም በአሜሪካ ምድር ይህ የማይባል ስራ ሰለ ሰሩ ወዴት እንደተመደቡ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።
አሁንም አቡነ ጳውሎስ ከሆነ ከግራኝ ባሱ እንጂ አልተሻሉም።
ምክንያቱም ግራኝ ከውች ስለነበር አልተክፋፈልንም በጋራ ተዋጋነው እኚህ ግን ውስጥ ገብተው እውነተኛ አባቶችን በጠብመንጃና በተለያየ ነገር እያጠፉብን ነው።
ለምን ይሆን የፈጣሪስ ዝምታ?እኛስ ለምን መተኛት መረጥን?መቼ ነው ልክ እንደ ክርስቲያን ጠንክረን የምንቆመው?
እስቲ ሁላችንም እንጠይቅ
የገብስን አረም የሚነቅል ባለቤቱ ነው። የቤተክርስቲያናችንም ጸላዒ የሆኑትን የሚነቅለው እርግጥ መድኃኒዓለም ክርስቶስ ነው።
ግን እሱ ከእኛ ጋር ሊነጋገርበት ነው ቃል ገብቶ የሰጠን እኛ ካለተናገርን እርሱ ወርዶ እንዲያነጋግረን ነው ይምንፈልገው?
እግዚአብሔርስ በቅድስና ተውስነው ነው ቅዱሳኑ የሚያነጋግሩት ።
ሟች የሆንን እኛ እንኳን ሰው ካላናገረን መች እናወራለን?
ፈጣሪ ግን በተቃራኒ ሁሌም ያናግረናል። መስማት ተስኖን ነው እንጂ። እኔ ግን እንነሳ ነው የምለው።

Anonymous said...

To whom it may concern

This is what has been happening to all rural churches and monastries of Ethiopia. Now they are almost done with the rest and now they came to the main monastry on which the social and spritual welbeing of the country is based. This is the strategy of striping the church of its spritual power. And secularizing the country. The humans are the tools and devil is deriving them. " The fight is not with blood and flesh" it is with evil sprit. The solution is ' our love to one another, our peace, our kindness, our prayer... bearing spritual fruits. What can you think about the church with out its monastries, its traditional church schools?.

The world has been shouting about the project of Gilgel gibe three. As to me that project is so sound and constructive. With this project I do not know if social feasibility study has been conducted. If it were conducted I do not know how it can be seen as socially feasible! The Monastry life it self is a heritage. And Waldiba is special in its kind world over.In adition, the biodiversity ( the fauna and the flora, the Ethenobotany associated with it is a heritage for the world. Above all this is a delicate powehouse of the church that has over 50 million fellowers. The issue is not only the issue of the monks and nuns there ! It must be the question of the 50 million Ethiopians and ofcourse all national and international groups concerned with Biodiversity ! Hence, we the elites of the church have to organise ourselves and undertake the following:

1) Some may identify as "anti development when we say why ! but this will be because awareness and lack of knowledge. Hence, Public awareness creation on what is going on there has to be intensified.

2) Organise workshops on the value of the monastry for the spritual welbeing of the church and the country.

3)Publicise the value of the monastry for the ethenobotany, biodiversity conservation etc

4) Back stop the demand of the monks and the nuns in formal and civilsed way.

Ofcourse, the monastry communities must pray towards GOD.PRAYER PRAYER. Application alone does not have power !!!! And every christian has to pray for this.

All the political CADRES who identify your self as ORTHODOX you have to say NO ! this time!. This is red line ! You can not keep quite while identifying your self as member of the church.

The so called ' preachers" you can not also keep quite while thiese things are happening to the church.Preach about it ! It is not right ! it is not constitutional ! and Any project of this kind will not be sustainable.Brotherly

selam said...

since when church has to be destroyed to do 'LIMAT' this absurd,የቅዱሳን አምላከ ሌት ተቀን ወደ እሱ የሚጮሁትን ልጆቹን ይጠብቅ፣ ቸር ወሬ ያስማን

Anonymous said...

krstianoch ahun new lebete krstianachin menesat yalebin Amlak yirdan

Anonymous said...

እኔን የሚገርመኝ፦

በእንዲህ ያለ አገራዊ እና ሃይማኖታዊ ጕዳይ ለጠቅላይ ሚንስትር... ለፓትርያርክ... የሚባለው ነገር። ባካችኹ እነዚህን ኹለት ሰዎች አትጨቅጭቋቸው። ስማቸውን ካነሣችኹም በሚገባው መንገድ አንሡ። ለምሳሌ በዚህ ጕዳይ ላይ የነሱ ሲም ሊነሣ የሚችለው ወሬው ስለ"ሼር" (share) ከኾነ ብቻ ነው። የጠቅላይ ሚንስትሩ "ሼር" ስንት ነው? የፓትርያርኩስ? ለማለት ብቻ።

ያለዚያ ግን፦

ስላገር፣ ስለሃይማኖት እነሱን ማንሣት? ይባስ ብሎ ለነሱ ማመልከቻ መጻፍ? እንዴት ኾኖ? የማያገባቸውን?

"አልሰሜን ግባ በሉት" አሉ። (እኛን ማለቴ እንጂ መነኮሳቱ "አልሰሜ" ቢኾኑ የሚጠበቅ ነው።)

ለመኾኑ መቸ ነው ዕርማችንን የምናወጣው? ረ ወዲያ! አገሪቱ በዐላዊ ንጉሥ፣ ቤተክሲያኗም በመናፍቅ ጳጳስ እየተገዙ መኾናቸውን ለማየት ያልቻለ ዐይን ካለ፤ ቢጠፋ ይሻለዋል።

የህንን ሐቅ ካልተቀበልን፤ የመፍትሔ አግጣጫዎቻችን ኹሉ ምንም መድረሻ የሌላቸው የድካም ጎዳኖች ኾነው ይቀራሉ።

ኢታርእየና ሙስናሃ said...

ደጀ ሰላሞች?
ለምንድነው ጽሑፍዬን ያላወጣችሁት? ስለዚህኛው ጉዳይ፣ ማቆች ክፍፍል ከመፍጠር ይልቅ ከፓትርያርኩ እስከ ዓጻዌ ሖህቱ ያለን አንቀሳቅሱን ማለት ነውር ነው ብላችሁ ተርጉማችሁት ነው ? ወይስ እናንተም ጸረ ገዳሙ በመሆናችሁ!

Anonymous said...

ወገኖቼ ይህ ጉዳይ ሁላችንም ልንሳተፍበት የሚገባ ሃገራዊ ጉዳይ ነው ። ሀገርን ማልማት ማለት ያለንን እያጠፋን አዲስ ነገር መገንባት አይደለም። በማንኛውም ሃገር አዲስ ፕሮጀከት ሲጠና ከሚታዩት ዓበይት ጉዳዮች አንዱ የሚሠራው ፕሮጀክት የሚኖረው ማሕበራዊና አከባቢያዊ ተጽእኖ ነው። ማንኛውም ሰለ ምሕንድስና ወይም ማህበራዊ ጉዳዮች ጥናት አነስተኛ ግንዛቤ ያለው ሰው ይህንን በሚገባ ይረዳዋል:፡ በመሆኑም ፕሮጀክቱ ሲጠና የሚነሳ/የተነሳ ጉዳይ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ- ፐሮጀክቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው ቢሮአቸው ተቀምጠው ካልጻፉት በቀር። የእኔ ግምት ጥናቱ ቢቀርብም የፕሮጀክቱ ቀጣይነት የሚወሰነው በፖለቲካ ውሳኔ ነው፤ ስለሆነም ጉዳዮ ለፖለቲከኞቹ ቀርቦ ያሚኖረው ተጽእኖ ቢገለጽላቸውም “ቄሶቹ ምንም አያመጡም ወይም ምንም አይጠቅሙም- ፕሮጀክቱ ይቀጥል” ተብሏል የሚል ግምት አለኝ።


ይህ ከሆነ በእርግጥም የቤተክርስቲያኒቷ ልጆች በመንግሥት ላይ ያለን ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን የተረዱት አይመስልም። ስለሆነም ይህንን ጥያቄ ማንሳት ተገቢና ወቅታዊ ነው። በማንኛውም መመዘኛ ቢለካ ይህ ጥያቄ ትንሹ የመብት ጥያቄ ነው። በዓለም ላይ ከሚገኙት የተቀደሱና የተጠበቁ ሥፍራዎች አንዱ በዚህ ሁኔታ ሲጠፋ ዝም ማለት እንኳንስ ለክርስቲያኖቸ ለማንኛውም የሰው ልጅ ከወንጀለኝነት ያስቆጥራል። ከሃይማኖት ማዕከልነትና የቅድስና ምንጭ ከመሆኑም በላይ ለዘመናት ተጠብቆ የኖረና በምንም ምክንያት ሊነካካ የማይገባው የዓለም ሁሉ ሀብት ነውና።

ስለሆነም አስቀድሞ ባለው የቤተክርስቲያኒቷ መዋዕቅር በኩል ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል እንዲቀርብ መደረጉ አግባብ ቢሆንም የእያንዳንዳችንን ቁርጠኛ ተሳትፎ ይጠይቃልና ሁላችንም ጉዳዮን በአጽንኦት ልንከታተል ይገባል።

ፕሮጀክቱን በቅርበት የሚያውቁ የቤተክርስቲያን ልጆችም ጉዳዩ በተመለከት መረጃዎችን ከመስጠት ጀምሮ የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የአባቶቻችን አምላክ ተስፋ የምናደርጋተውን የቅዱሳንን በኣት ከመጥፋት ይሰውርልን!

ዘ ሐመረ ኖህ said...

ለሰማእትነት መነሳት ከነበረብን ጊዜ በጣም ብንዘገይም አሁንም ጊዜ አለን ተነሱ እንነሳ አውነት ለልማት ቦታ ጠፍቶ ነው አይደለም ጠቅላይ መኒስትሩና ፓትርያርኩ ተባብረው ቤተክረስቲያኗን ማጥፋት ከጀመሩ ሰንብተዋል በቃ ምን ቀረ ሰማዕት የሚሆን ሰው ሲጠፋ እንደ ሞሮኮና ቱኒዝያ ሙሉ ለሙሉ ጠፍተን ለአስማኤላውያን መልቀቅ ነው የእስማኤላውያን እጅ ከበስተጀርባ እንዳለበት ግልጽ ነው እነ አላሙዲን ዋናው ስራቸው ይሄ ነው በዝምታችን መቀጠሉን አቁመን እንነሳ

ዘ ሐመረ ኖህ said...

አሁን ማን ይሙት የሙስሊሞች መስጊድ ያለበት ቦታ ቢሆን እውነት እንዲህ ያፈርሱታል አማኞች በሌሉበትና በማይገለገሉበት ቦታ ሁሉ በመቶ የሚቆጠር መስጊድ ይታነጻል መነኮሳትና ተማሪዎች ያሉበት ገዳምና ቤተክርስቲያን ቅርስና ታሪክ ግን ይፈርሳል መንግስት ከፓትርያርኩ ጋር ሆነው ቤተክርስቲያኗ ላይ ከዘመቱ ቆዩ እኔ በበኩሌ በቃ እንነሳ በቁም ከመሞት በክበር መሞት አይሻልም ወይ ምን እስከምንሆን ነው የምንጠብቀው

Anonymous said...

ስለ እግዚአብሄር ብላችሁ የመፍትሄ ሀሳብ ያላችሁ በሀገር ውስጥ የምንኖር ምን ብናደርግ ይሻላል በውጭስ የሚኖሩ በምን መልኩ የመፍትሄው አካል ሊሆኑ ይችላሉ ባለፈው የኩሩፍቱ ሪዞርት ስራ አስኪያጅ አቶ ታዲዮስ የኩሩፍቱ መዳህኒአለም ይዞታን በስሙ ካርታ አስወጥቶ የራሱ ሲያደርገው አውርተን ዝም አልን የዛን ሁኔታ ሳይቌጭ አሁን ደግሞ የዋልድባ ነገር ተከሰተ ምን እናድርግ ? በኔ በኩል በውጭ ያሉ ቤተ ክርስቲያኖች እና ማህበራት ሰንበት ት/ቤቶች ሁሉም ምእመኑንና አባላቱን በማስተባበር በያሉበት የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ተቃውሞ በጽሁፍ ማስገባት በሀገር ውስጥ የምንኖር የሚሆነውን ሁሉ ዶክመንት መያዝ ምክንያቱም ይሄ ሁሉ ጥፋት ካለው መንግስት ጋር አብሮ ይጠፋል ::

ኢታርእየና ሙስናሃ said...

አስተያየት የሰጣችሁ ወንድሞች በጣም ግሩም ነው። በተለይ ከኔ በታች ያለህ አኖኒሙስ በቂ ግንዛቤ ያለህ ትመስላለህ። የኔም ቢሆን አንተ ከሰጠኸው ሐሳብ ተመሳሳይ ሰጥቼ ነበር አላወጡቱም እንጂ። ይኸውም ከጻፍኩት መለስ በሸንጋላ ምላሱ ካሳ ፣ምናምንቴ እሰጣችሀለሁ ብሎ ማመልከቻ ያስገቡትን መነኮሳት ሊያታልላቸው ስለሚችል የህግ ባለሙያ የሆኑትን የቤተ ክርስቲያን ሙሁራን ጠበቃ እንዲቆምላቸው ማስደረግና ጎን ለጎን ደግሞ ከፓትርያሪኩ እስከ ዓጻዌ ሆህቱ ያለን የእምነቱ ተከታዮች አቤቱታችንን ለማሰማት ማህበረ ቅዱሳን የተባላችሁ ሞብላይዝ አድርጉን ብዬ ነበርና ወያኔዎች አላወጡትም።

lele said...

lebe yesetachohe

Anonymous said...

እንደጥምቀት ያለ አንድ በዓል ካከበርን እና ስናከብርም ጆሮቿችን በትክክል የሚሠሩ ከነበረ፤ የሚከተለውን የወጣቶች የሆታ መሥመር ሳንሰማ ልናልፍ አይችልም፦

"እንቢ በል!"

እንዲያውም ስንኳን ወንዶች ሴቶችም ይኸንን ሳይጨፍሩ ዐድገዋል ማለት ይቸግራል። ምንጩን ግን እናውቀዋለን? ምናልባት እንዲያው የሥጋዊ ጥጋብ ውጤት፣ ከንቱ የ"ትምክህተኞች" ጩኸት፣ ይመስለን ይኾን?

የለም፤ በጭራሽ ልንሞኝ አይገባም። "እንቢታ" እኮ ጥርት ያለ መንፈሳዊ መሠረት አለው። በኔ ግምት ምንጩ፦

"ኦሆ በልዎ ለእግዚአብሔር ወእንብየ በልዎ ለጋኔን" የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ነው። "እግዜርን እሺ በሉ፤ ሰይጣንን እንቢ በሉ" ማለት ነው።

ታዲያ እነዚህን አገር እና ሃይማኖት ሊያጠፉ ቆርጠው የተነሡ የሰይጣን መልእክተኞች (አቶ መለስን እና አባ ጰውሎስን) "እንቢ" የምንለው መቸ ነው? አንድ ባንድ ሸጠው ከጨረሱን በዃላ? ያን ጊዜማ እግር ተወርች ታስረን ስንነዳ የነርሱ ጥርስ ቀለብ መኾን እንጂ ምንም ልናመጣ አንችልም።

ረ ባካችን እንንቃ፣ እንነሣ እና እንቋቋማቸው! ረ ባካችን፤ ረ ባካችን!!!

ደቂቀ ጸሃፍት said...

ጎበዝ አሁን ለሃይማኖት ሲባል ፖለቲከኛ መሆን ካስፈለገ መሆን የሚገባብን ሰአቱ አሁን ሳይሆን አይቀርም። ይህቺን ቤተክርስትያን ሊገለብጣት የወደደ ይህ መንግስት እንደማስበው መገልበጫው ደርሷል። ከጸሎት እስከ መንፈሳዊም ይሁን ስጋዊው ትግል መደረግ ያለበትን ማድረግ ብቻ ነው ከእኛ የሚጠበቀው። መቼስ በእኛ ዘመን ይህች ቤተክርስያን ምን ያልሆነችው አለ? ሀገርንና መንግስትን እንደሀገር ስታስተዳድር የቆየች ታሪካዊት ሙዚየም እንዲህ ትገለባበጥ? ታሪክ የለሽ ለማድረግ ነው? ለልማት ነው? እውን ከመንግስት በስተጀርባ ሌላ ተልእኮ ያለው የለምን? ብቻ ነገሩን ሳናቀለው በጥልቀት እንየውና ወገኖቼ አስቸኳይ መፍትሄ እንፈልግ። ልጆቿ ሀገሪቱን ሲያስተዳድሩበት በነበረ ጊዜ የነበረውን ሁኔታ እናስታውስ። ዛሬ እኮ ቤተ ክህነትና ቤተመንግስት በመለየቱ የቤተክርስትያኗ ልጆች በሃገር ማስተዳደር ላይ ሚና ስለሌለን በፓርላማም ውስጥ ስለዚች ቤተክርስትያን የሚያዘክር ተወካይ ልጅ ስለሌላት ከፖለቲካው አለምም ነጻ ስለሆነች በዚያ ክፍተት ምክንያት ነው እየተጎዳች ያለው። ያደጉትን ሀገራት የእድገት ተሞክሮ ስንመለከት ታሪክ እያበላሹ አልነበረም ታሪክ ሲሰሩ የነበረው። ለምሳሌ የአሜሪካ ህገ መንግስት አመሰራረት ይዞታው ሃይማኖታዊ ነበር የሀገሪቱም አቀናን በሃይማኖተኞች ስለነበር ይሄው አሁንም ለዚህም ነው በሰለጠኑበት በዚህ ዘመን የመገበያያ ገንዘባቸው ላይ በፈጣሪ እንደሚያምኑ የሚገልጹት። ሁሉ ህዝብ በፈጣሪ የሚያምን ሆኖ አይደልም ያን ማለትና መዘከር ያስፈለጋቸው። ለታሪክ ሲሉ ግን ብለውታል። ገና ለእኛ ላለደግነው ሀገሮችማ በፈጣሪ ማመንም መታመንም ብሎም በመንግስት መስራችነቷና በሀገር አስተዳዳሪነቷ የምትታወቀው የኢትዮጵያ ቤተክርስትያንማ ሁሌ ታሪኳ ሲዘክር መኖር ነበረበት። የታሪክ አሻራን ለማጥፈት መጣር ትክክለኛ የልማት አካሄድ አይመስለኝም። የዚች የቤተክርስትያን ቅርስ የሀገሪቱም ጭምር መሆኑ መዘንጋት አልነበረበትም። ታሪክ በማበላሸት ታሪክ መስራት በታሪክ ያስወቅሳል። በዚህ በአሜሪካ የመቶ አመት እድሜ ያለው ዛፍ በክብር ተሰነዳድቶ በቱሪስት መስህብነት እንደሚታይ የሚያውቁ መሪዎች አሉን ይሆን? ታዲያ ምነው ለታሪካችን እና ቁሳዊም መንፈሳዊም ቅረሶቻችን ዋጋ አሳጡብን? የማንነት መገለጫዎችን ማጣት የማንነትን ቀውስ ያመጣል። ማንነትን አለማወቅ ደግሞ ከፍተኛ የስነልቦና ቀውስ ያመጣልና እባካችሁ የማንነታችንን አሻራዎች ለማስጠበቅ በአንድነት ከጸሎት ጋር እንነሳ! በሚደረገው ዘመቻ ከጎን አለሁ። በቸርነቱ አይለየን።

Minas said...

Wode Deje Selamoch:
This is a life or death story. I thank Deje selam for telling us this story. I am deeply saddned.And I asked myself a life or death question.My church is my life and my mother. Life without her is meaningless. I asked myself what should I do?
First, I have to repent from my heart all my sins and ask our Father for the wellbeing of our Mother.

Second, Please Deje selamoch as you are the one who broke this news you should be the one or any organized body to lead us to stop this action. Either you can let us write a petition, let us write letter to the prime minster, or the Ethiopian Embassy. or may be UNESCO, as this is a heritage that should be preserved, I mean in their eyes.
Or, write to World council of churchs, or to Pope shenouda -as he is now in good relations to Abune Paulos. or something.

Please, May the Lord pay you for voicing the problems of the church to us. But, Please don't be limited to this only. We need a leader to organize for this. As one of the commenttors said this is the time of Martyrdom. Please show us and lead us to be organized and bear a fruit.

Thank you and May the Lord be with you.

asbet dngl said...

ይህ ሲወራው ከኖረ የበለጠ ዘግናኝ ዜና ነው:: በእውነትም እጅግ የሜያሳዝንና መፍትሄ በአስቸኳይ የሚሻም ነው:: ወገን በአገራችን ሕግ የሚባል ካለ መዋጮው ይፋጠንና ሕጋዊ ጠበቃ እናቁም ያ ካልሰራ ግን ለመስቀል ያልሆነ አንገት ይበጣጠስ ተብሎ የል:: ይህ ገዳም ከመንፈሳዊነቱ ባሻገር ቅርሳችንም ነው:: እንዲት ነው ጉበዝ ትንሽ ቀና እንበል በጣም ሆዳሞች ሆን::

መላኩ said...

ደህና ዋላችሁ!

እረ ምን እዳ ነው! ብቻ በቂ አይደለም። እያንዳንዱ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ይህን መሰሉን ጉዳይ የራሴ ጉዳይ የራሴ ኃላፊነት ነው ብሎ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል። በመሪነት ቦታ በተቀመጡት ባለሥልጣናት ላይ እያተኮርን ጊዜና ጉልበት ስናጠፋ፣ በምጣኔ ኃብት እድገት ሰበብ ታች የተቀመጡት ባለሥልጣናት ጸረ ክርስትያን አጀንዳቸውን እያራመዱ ነው። ይህን መሰሉን ፋብሪካ ታሪካዊ የክርስትና ቅርሶች አካባቢ ለመሥራት ማን ሃሳብ እንዳቀረበ፣ ሃሳቡ በማን በኩል እንዳለፈ እና ማን እንዳጸደቀ በውስጥ ሰላዮች መጣራት ይኖርበታል፣ ግለሰቦቹ ከታወቁ እግራቸውን መስበር ያስፈልጋል። ጦርነት ላይ እንደሆንን እወቁት።

Anonymous said...

dejeselam yewdedkushn yahl litelash new,mikniatum yemeftihe hasab yeleshim.dejeselam manbeb kejemerku jemro yebetecrstian chigrochwan mawek kemigebagn belay aweku.neger gin meftihe mamtat alchalkum.bebtekrstian tetelilew yemiademuat abatoch,yesebeka gubay abalat,wegentegna miemenat batekalay hulun temeleketku.kene jemro yesew fit ayten yeminsera bicha nen.sile haymanote bilen yeminsera sintoch nen?lalefut 3 ametat bezih blog bizu bizu chigroch seman,neger gin le tinish kenat simetachinen kemantsebarek wuchi minm aladeregnm.ahun gin menesat yalebn yimeslegnal.sile haymanot semaetnet,semaetnet,semaetnet,,,,,
islam letifat yimotal,what about us,,,,,ende nabute yabatochen erist alsetim malet ygebal..ene zigju negn!!

123... said...

123...

Anebebkut...degemkut...azenku...bzu gize azgnalehu...ahun gn lbe dema.
Gudayu yemimeleketew Mengstn new.Ethiopia dimocratic mengst yasfelgatal. Gedamaten biyakebrlign des yilegn neber.Kalakeberelgn enem endet endemalakebrew masayet alebgn.Lela Egzyabher fit malqesen alaqomm.

Anonymous said...

Betsom tselot meftehewen kelay magegnet yeshalenalena besu enebereta! Dingel tselot lemenachenen kedem menberu le'egziene tadereselen. Amen

Samson said...

ውድ ኢትዮጵያውያን፤ ዕባከችሁ ጸልዩ፤ ቢዘገይም ክርስቶስ መልስ ይሰጠናል፡፡ በጠ/ቤ/ት በኩልም አቤት ይባል፡፡ከዚህና ከጸሎት ባሻገርም የሚያስፈልግ ነገር ከለ በአዋጅ አስተላልፉልን፡፡ የሕልውና ጉዳይ ስለሆነ የኢትዮጵያ ኦ.ተ.ቤ.አማኝ በአጠቃላይ ይሳተፋል፡፡ ይህ ግን የመጨረሻ 11ኛው ሰዓት ላይ ይሁን፡፡

ከህናት ባከችሁ ጸልዩ

አግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

Anonymous said...

አሁን ማን ይሙት የሙስሊሞች መስጊድ ያለበት ቦታ ቢሆን እውነት እንዲህ ያፈርሱታል አማኞች በሌሉበትና በማይገለገሉበት ቦታ ሁሉ በመቶ የሚቆጠር መስጊድ ይታነጻል መነኮሳትና ተማሪዎች ያሉበት ገዳምና ቤተክርስቲያን ቅርስና ታሪክ ግን ይፈርሳል መንግስት ከፓትርያርኩ ጋር ሆነው ቤተክርስቲያኗ ላይ ከዘመቱ ቆዩ እኔ በበኩሌ በቃ እንነሳ በቁም ከመሞት በክበር መሞት አይሻልም ወይ ምን እስከምንሆን ነው የምንጠብቀው?

Anonymous said...

What a very shoking news! This is completely absurd, and should not be accepted. What a government? The socio-economic contribution of the Monastery is totally neglected by the State. We all are ready to work hand and glove to realize the transformation and diversification of the production structure. But this should not be at the expense of the Holy Church of God, its history and traditon, its Monasteries, its followers, its cultural heritages and so on. This is intolerable. A big mistake, that should be corrected. The Monastery of Waldiba belongs to the Church of God, not to any of the regional states mandate,... where is the Holy Synod? where is the Patriarch? Where are the preiests and their floks? Are we in this planet? ... This is one way of denouncing the history of the country, dishonoring the power of the Church, dishonoring the Saints and thier commandment, disobeying God....Antichrist!... Nabute, Nabute, Nabute....

Anonymous said...

Church burning in gamogofa by radical muslims.


http://www.youtube.com/watch?v=5vNS_sEq8T4&list=UUaktN8bZfmwqjSFwdh5Kyvg&index=1&feature=plcp

መሲ said...

ገዳማውያን ለተልእኮ ወደአለም እንደሚገቡ ሁሉ አለማውያንም ለንሰሃ ወደገዳም የሚገቡበትን ዘመን ያምጣልን ፤ እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ!!!

Anonymous said...

Deje selamoch!!!!!!
you should be the one to lead us to stop this action. Either you can let us write a petition or tel us what to do.

Anonymous said...

እጅግ በጣም አሳዛኝ እና ዘግናኝ ነው::አባቶች ለጸሎት ይነሱ ምዕመናን ሀገር ውስጥም ሆነ ውጭ ያላችሁ በአንድነት ድምጻችንን እናሰማ!በእውኑ ነገ ጥለነው የምንሄደው መኖርያ ቤታችን እንዲነሳ (እንዲፈርስ)ቢወሰን ምን ይሰማን ይሆን? የእለት ስራችንን ትተን መፍትሄ ለማግኘት መሯሯጣችን መቼምአይቀርም::ታዲያ ይህ ታላቅ የቤተክርስቲያናችን እና ሀገራችን ቅርስ ለአደጋ ሲጋለጥ ዝምታችን እስከ መቼ ነው??????? አባቶች በጸሎት ወደ እግዚአብሄር ጩሁ:: ምእመናን ለምን በሰላማዊ ሰልፍ ድምጻችንን አናሰማም?

cher worea yaseman. said...

yihen guday mengist endetera hasab limleketewu aygebam ...yih teyakea minalebatem abzeuhanu ethiopiyawi newu.mahibere kiduan sefi sera mserat yitbekebetal.
cher worea yaseman.
yedngil Mariyam amalaginet ayleyen.amen.

Anonymous said...

. . . ኢትዮጵያዊት ቅርስ ጎጆ የምእመናን ኩራዝ ሻማ
የእምነቷ ድርብ ጥበብ የእግሮቿ አልቦ ጫማ
ዕፀ ሕይወት፥ ዕፀ ገነት፥ ዕፀ ድንግል ቡሩክ ተክሏ
የምስጋና መዝሙር ድምጿ የቅላጼ መድበሏ
ዋልድባ።
በተፈጥሮ ተጎናጽፋ ተዋሕዶን መከተሏ
በቅንነት ሳታሰልስ ፈጣሪዋን ማገልገሏ
ቤተ እምነት መቅደስ ሆና በምህላ መሸምገሏ
ሰማያዊ ተክሊል ደፍታ ለአርአያነት መታደሏ
ዋልድባ።
ተአምር ስንቋ
ገነት ቅርቧ
ቃለ እግዚአብሔር ክንብክቧ
ምስጢራዊት ዝምተኛ እምነት በልብ ረቂቋ
በምን ብዕር ላወድስሽ ያንቺን ገድል በምን ቋንቋ?
ዋልድባ።

ቴዎድሮስ አበበ
መጋቢት ፲፱፻፹፯ ዓ.ም. (March 1995)
(ከ ፈተና፤ «የዕንባ ጉዞዎች» እና ሌሎች ግጥሞች ፥ ገጽ 76 በከፊል የተወሰደ)

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)