(ብርሃኑ መላኩ/ READ THIS ARTICLE IN PDF.)
የብፁዕነትዎን ይቅርታ እየጠየቅሁ እንደ መንፈሳዊ ልጅነቴ በግሌ ላሳስብዎት የምሻውን ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ። እድሜዬ በ30ዎቹ ሲሆን በውጭ ሃገር ተወልደው አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነትን በባለቤትነትና በኩራት የሚከተሉ ሁለት ልጆችን እግዚአብሔር ሰጥቶኛል። ዕድሜያቸው በአስራዎቹ ሲሆን በእምነታቸው ግን በጣም በመብሰላቸው ለዘመኑ የኢ .
ኦ . ተ .
ቤተ ክርስቲያን ንትርክ ሳይወዱ ተካፋይ ሆነዋል። ለዚህም የዳረጋቸው የየአብያተ ክርቲያናቱ ዶግማና ቀኖና ሥርዓት ነው። ዝርዝሩን እዚህ ላይ ባላሰፍረውም የሁሉም የእምነቱ ተከታይ የሆኑት ምእመናን ቤት ጠንቅቆ ያውቀዋል።
ወደ ዋና ሃሳቤ ልመለስና፤ እንደዚህ ዓይነት የማን አለብኝነት መንፈሳዊ ሥራ ከማድረግዎ በፊት ማሰብና ማድረግ የሚገባዎ ብዙ ነገሮች ነበሩ። የተደረገው ድርጊት ትክክል እንዳልሆን የሚያብራሩ ሐሳቦቸን ከዚህ በታች አቀርባለሁ።
1.
ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ አሜሪካ ሲልክዎ ለየትኛው ወገን እንደሆነ አውቀው ተግባራዊ አለማድረግዎ (ለአቡነ አብርሃም ወይስ “ለገለልተኛው” ወይስ “ለተገንጣዩ አቡነ መርቆርዮስ”)፤
2.
አሜሪካ እንደደረሱ ቅዱስ ሲኖዶስ ለላከዎት ወገን ቀርበው የሥራ አቋምዎን አለመግለጽዎ፤
3.
እንደ መንፈሳዊ አባት ዛሬ እየከሰሱዋቸው ያሉትን ቀደም ብለው የተዋቀሩትን የሃገረ ስብከቱ አስተዳደር ክፍል ለማነጋገር አልሞክርም ብለው አገረ ስብከት እንደሌለ በቪኦኤ መግለጫ መስጠትዎ፤
4.
ሕጋዊ ያልሆነ እያሉ የሚወነጅሉትን ክፍል ሕጋዊነቱን ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ እስከ አሜሪካ ክፍለ ሃገር ያስተዳደራዊ መብቱን ያስጠበቀ መሆኑን ለመገንዘብ አለመቻልዎ፤
5.
እንደ ክርቲያናዊ አባትነትዎ እርቅን ከመሻት ይልቅ የበላይነትንና በቀልን ምርጫ ማድረግዎ፤
6.
የቅዱስ ሲኖዶስ ሙሉ አካል ሆነው ያገለገሉትን ያቡነ አብርሃምን ሥራ ጅምር ተከታትሎ ከማስፈጸም ይልቅ አብያተ ክርቲያናትን የሚበታትንና የእርስዎን ተቀባይነት የሚያሳጣ ተግባር መፈጸምዎ፤
7.
የሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያን ሳያነጋግሩ ማኅበሩን የሚመራ አባል ምርጫ እንዲደረግ ማድረግዎ፤
8.
እንደ ክርቲያናዊ አባት መምከርና ማወያየት ሲገባዎ ለልጅዎ (ልጆችዎ) የማስፈራሪያና ዛቻ የተሞላበት ደብዳቤ መጻፍዎ፤ ለዚያውም የግል መብቱን በመንካት። ለመሆኑ በአሜሪካ ሕግ የአንድ በመንፈሳዊ ድርጅት ሥራ ውስጥ እየሠራ ያለ ሰው የግል መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እያወቁ ይሆን ይህንን ደብዳቤ የጻፉት።
9.
ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔና ትዕዛዝ ሳይሰጠዎ በራስዎ ሥልጣን ይህንን ሹመትና ክስ ማቀናበርዎ፤
10.
እንደ አቡነ ዘካርያስ ያሉ አባት በቅርብ ዕያሉ ከእርሳቸው ጋር መመካከርና ሁሉንም ክፍል እንዲያነጋግሩና በመንፈሳዊ ሥራ እንዲረዱዎት ማድረግ ሲገባዎ ለዚህ ሁሉ በጥባጭ ለሆነ ድርጊት ክንውን መምረጥዎ፤
እነዚህና ሌሎችም ቀደም በለው የተደረጉት ምንኛ እርስዎን ሊጎዱዎት እንደሚችሉ አስቀድመው ማወቅ ይጠበቅበዎት ነበር።
ለምእመናን የሚሆን መልእክት።
ለምእመናን የሚሆን መልእክት።
ሀ. አቡነ ፋኑኤል የተላኩት በቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑን ሁላችንም እንስማማለን።
ለ. ቅዱስ ሲኖዶስም የላካቸው አቡነ አብርሃምን ለመተካት ነው። በዚህም እንስማማለን።
ሐ. ቅዱስ ሲኖዶስ ደግሞ በአቡነ አብርሃም አባታዊ መሪነት የተመሠረተ አገረ ስብከት እንዳለ ጠንቅቆ ያውቃል።
መ. ታዲያ ብፁዕነታቸው አቡነ ፋኑኤል ጽ/ቤቱን እንደመጡ መረከብ የለባቸውምን?
ሰ. ለምንድንስ አቡነ አብርሃምን በአካል ተገናኝተው ከአገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ድረስ በመሄድ አላነጋገሩም?
ረ. እነዚህ አባቶች ሁለቱም የቅዱስ ሲኖዶስ አካል ሲሆኑ ለምን አንዱን አስተዳደር አንዱ ይበትናል።
እንደኔ አስተያት ችግሩን እያባባሰው ያለ ምዕመናኑ ነው። ስለዚህ እባክዎትን ይንቁ፤ ችግሩ ከእርስዎ የበላይ እንደሆነ ይረዱ፤ በማስተዋልና በጸና እምነት ሆነው አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነትን ይጠብቁ፤ በጎችንም በጥሩ መስክ ያሰማሩ። በሌላ በኩል ደግሞ አንባቢው የአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች አባል ከሆኑ፤ ነቃ ይበሉ በከፍተኛ ማስተዋል በእምነትዎ ይጽኑና አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነትን ይጠብቁ። ጠላታችን የጥቅም ጥያቄ ነው (ውስጣዊ ተሃድሶ) እንጂ እነ ግራኝ መሃመድ ተመልሰው አልወረሩንም። እድሳት የማትሻ አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነትን እንጠብቅ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር