February 6, 2012

የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ


·         በስብሰባው ያልተገኙት አቡነ ፋኑኤል ከአካባቢው ለሰበሰቧቸው ካህናት አዲስ ሹመት ሰጥተዋል፤
(ደጀ ሰላ ጥር 28/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 6/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አስቸኳይ አጠቃላይ ጉባዔውን በኖርዝ ካሮላይና ሻርለት በማካሄድ እና መሠረታዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ እንደተጠናቀቀ ምንጮች ለደጀ ሰላም ገልጸዋል። ጥር 25 እና 26/ 2004 ዓ.ም በሀ/ስብከቱ ሥር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በተገኙበት በተደረገው የምክክር ጉባኤ ላይ “የሀ/ስብከቱን መኖር አላውቅም” ያሉት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አለመገኘታቸው ታውቋል።

የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ የምእመናን ተወካዮች እና የሰንበት ት/ቤት ተጠሪዎች በተሰበሰቡበት በዚህ ጉባኤ ላይ ሀ/ስበከቱ አሁን ስላለበት ሁኔታ በሰፊው እንደተመከረበት የተገለፀ ሲሆን የሀ/ስብከቱን አገልግሎት የበለጠ አጠንክሮ ለመቀጠልም ከውሳኔ ላይ ተደርሷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሀ/ስብከቱን አላውቀውም በሚል ዕውቅና ነፍገው የራሳቸውን አዲስ መስመር የጀመሩት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በበኩላቸው፣ በሀ/ስብከቱ ውስጥ የሌሉ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናትን በመያዝ የጀመሩትን የራሳቸውን እንቅስቃሴ በመግፋት ሹመት መስጠታቸውን ከዚያው አካባቢ የተላከልን ደብዳቤ ያመለክታል።
በቀጥታ ለቅዱስ ፓትርያርኩ አድራሻ በተደረገው እና ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ግን በግልባጭ በተጠቀሰው ደብዳቤ ላይ “በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት” ሊቃነ ካህናት፣ ፀሐፊዎች እና ሒሳብ ሹሞች እንዲሁም የሰንበት ት/ቤት ኃላፊዎች መሾማቸውን አሳውቀዋል።
ሊቀ ካህናት ተደርገው የተሾሙት ካህናት የመጡባቸው አብያተ ክርስቲያናት ገሚሶቹ የቅዱስ ፓትርያርኩን ስም የሚጠሩ ገሚሶቹ ደግሞ ራሳቸውን ገለልተኛ ብለው ያሉ እና ከሀ/ስብከቱ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው የሚታወቁ ሲሆኑ የተቀሩት ካህናት ደግሞ ምንም አጥቢያ የሌላቸው፣ አቋቁመውት የነበረውም የፈረሰባቸው፣ አንዳንዶቹም አዲስ ለማቋቋም ደጅ በመጥናት ላይ የሚገኙ ናቸው።
እስካሁን ባለን መረጃ የእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት “ቦርዶች” የተስማሙበት ይሁን ወይም አይሁን የታወቀ ነገር የለም። የደብዳቤውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንን ይጫኑ

ቸር ወሬ ያሰማን

አሜን

17 comments:

Anonymous said...

ወይ ሹመት የማይጠቅም የማይሰራ ስም ብቻ
ሰጭውም ተቀባዩም ወፈፌዎች
አሁን አሁን ስለናተ መስማት ማየት ብቻ ነው ለውጥ ተግባር
ስለሌለው ችግር የለም በርቱ ቀልዱ በቅርብ ቀን ሌላ እንሰማለን

Anonymous said...

ere minden new yegna yethiopiawyan gud. I think hagere sibketina senbet tmhert bet leyten yawekin aymeslegnm. B/c with out archbishop how comes we cal dc hageresibket metting in n Carolina this is shame wake up guys

Anonymous said...

ጤና ይስጥልኝ የተዋህዶ ልጆች እንደምን ሰነበታችሁ
መቸም የቤተክርስቲያናችን ነገር ውሉ የጠፍብን ይመስል መፍትሄ ለማገኜት እንዲሁ ስንደክም እንሱ /ባለጊዜወቹ/ ማለቴ ነው ኑሮየ ብለው ምእመናንን እያምታቱና እያንገላቱ በሚሊዮኖች ብር እያወጡ ቪላወችንና ፎቆችን እየሰሩ የኛን ህይወት በከንቱ እያለፈች መሆኑን ማስተዋል ይጠበቅብናል:: መቸም እንደኔ ግምት ከነዚሀ ሰወች ጋር በምንፈጥረው ንትርክ ምንም አይነት በረከት እንደማይገኝ ላስታውሳችሁ እወዳለሁ :: እነዚህ ሰወች አጥፍቶ ጠፊወች ወይንም ጠፈተው ሌላውን ለማጥፋት የተዘጋጁ ስለሆኑ እግዚአብሄር አምላክ መፍትሄ እንዲሰጠን አጥብቀን በየአጥቢያችን ምህላ የሚያዝበትን ሁኔታ ብናመቻች መለካም ይመስለኛል ::
ቸር ወሬ ያሰማን

Anonymous said...

wey abun fanuel leyelachew malet new kkkkkkkkkkkk ye leje sira dergut eko ere wegn tome telot lesachew becha yasfelgal

Anonymous said...

Belew! yehe new chewata!!!!!!!!!!!!!

Anonymous said...

I think for all the good things that Abune Abraham did in the Archdiocese, he had one weakness. He did not put in place the structure and people who will administer the archdiocese.

I am a strong supporter of Abune Abraham but supporter or not, truth is truth.The so called "Sira Asfetsami" was elected at the last minute when Abune Abraham knew he was going to be replaced by Abune Fanuel.The fact that Abune Fanuel is doing this at the beginning of his term is positive.

The fact that most of these appointed people do not care about a unified EOTC in USA is the downfall of this archdiocese. It remains to be seen if Abune Fanuel would change their attitude by extending an olive branch to them without asking any chnage in position from them.

This is a big risk and it may either pay a good dividend or forever paint Abune Fanuel in black colors in the histroy of EOTC (coupled with his past deeds). I, for one, think this is a very very dangerous road and do not belive anything positive will come out of it.

I still believe the "sira Asfetsami" committee needs to start discussing this with Abune Fanuel and try to sort it out.

It is a pity both Abune Fanuel and the Sira Asfestami have dug in their positions and are not willing to come to a dialogue.

No wonder EOTC is messed up!

Ethiopia.lezelalem said...

Ahun Bekerbu Be Aba Fanuel sheber fetarinet Ke Egziabeher Yemitazze Leyu yehone Yedewe Mekseft yitazezebachewal bezum Aykoyum Lenseham Aybekum Meemenan bemehela betselotu kenba gar wede Egziabeher enamelket !

Anonymous said...

ጤና ይስጥልን ከተሰጠው ሹመት ዉስጥ ስለ ቴኔሲ መናገር እፈልጋለሁ አዲስ የተሾሙት ቀሲሱ ናሽቭልን ሲያምሱ ከከፋፈሉ በኃላ ምዕመኑ ቦርዱ ሳያውቅ የተሾሙ እንደሆኑ እንዲታውቅልን እንፈልጋለን. ክናሽቭል ቴኔሲ

Anonymous said...

belew!!! yihe new chewata!!!!!!

Anonymous said...

ኧረ አባታችን ምንዉ ተሿሚዎቹም ይታዘባሉ መ ለያየቱን በታም እያሰፉት ነዉ እንደ ሰንበት ትምህርት ቤት ጎረምሳ የሚመክሮት ተፋወይ? ሰዉ ከተፋ የተሸከሙት አስኬማ እና የያዙት መስቀል ትኩር ብለዉ ይዩቸዉ ከስጋዊ እልህ ወጥተዉ እንደ መንፈሳዊ አባት ያስቡ በደሙ በዋጀዉ ምአመንና ቤ/ክ ላይ የአዋቂም ቀልድ አይደለም እንዲህ የልጅ ወይም የእብድ ቀልድ አይቀለድም በታም የሚገርመዉ እርሶ ወዳጄ የሚሏቸዉ አንድምወዳጅ እንደሌሎት ነዉ ያሳያል የመጀመርያዉ የጵጵስናን ስራ የማያዉክ ጳጳስ አሳፋሪ አይሁኑ ተሸንፈዉ ያሸንፉ ሁሉንም ይቅርታ ይተይኩ ይህ ካደረጉ ነዉ ዳግም የክብርሹመት

Anonymous said...

ቸሩ መድኃኒዓለም እባክህ የዚህን ሰው ልቡና መልስለት!! የቤተ-ክርስቲያናችንን ሀዘን/ፈተና አቃልልን፡፡

Anonymous said...

kesis Derge aba fanuel megemeriya gezae temedibew semetu dc mekial lay shumetachewin yemanikebel mehonun lhizibu debdabe yanebebe aydel enidae? bezihim mikinyat kebetekirstyanu mebareru yitawkal. mechi tareku??? leba lelaba.... yemebalew eiwnet new!!!Abune Fanuel abedu!!!.seyasazinu!!!!!

Anonymous said...

http://www.youtube.com/watch?v=f_ZkRaFbg2M&feature=related
Tsionene Ke-be-buwate (1/4) የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት by Kesis Doctor Mesfin Tegegn

ከናስቪል ቲነሲ said...

ሰላም ለሁሉም
ለ አብነ ፋኑኤል ....በመጀመሪያ አቡነ ፋኑኤል ወደ dc ሲመደቡ የት ተብለው ተመደቡ የተ ሂዱ ተባሉ አባታችን ብፁ አብነ አብርሃም ኢትዮጵያ ያቀረብትን በ ቅዱስ ሲኖዶስ ሲቀርብ አይተናል ሰምተናል ሀገር ስብከት እንዳለ ለምን የሰው ስራ ማፈረስ ፈለጉ ቤተ ክርስቲያን ስረዓተ ትያዝ ሁሉ በስርዓቱ ይሁን ያለውን ለምን ማሳደድ ፈለጉ ይህስ እውነት የክርሲቲያን ምግባር ነው ወይ? ። ምነው አብነ ፋኑኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስቲያን ምን በደለች ምን አድገቸ አረ ለምን እንዲ መሆን አስፈለገ መቼነው እርሶ ለቤተ ክርሲቲያን አዘነውና ተቆርቁረው የምናየው ለምን እግዚሃብሄርን መፍራተ ተው, ለምን ቤተ ክርስቲያንን ማራቆት ፈለጉ ....... የ ሰሜን አሜርካ አንድነት ጉባኤ፣ ማህበረ ቅዱሳን፣ ማህበረ ባለወልድ ሁሉም በአንድ አላማ ቤተ ክርስቲያንን እየጠበቁ ያሉ ማህበራት ናቸው እርሶ ለምን ቤተ ክርስቲያንን ከሚጠብቅ ለቤተ ክርስቲያን ዕድገት ከሚሮጥ ጋር ማሳደድና ማጥላላት ለምን አስፈለገ ? እርሶስ አብነ ፋኑኤል መቼነው እርሶ ብር(dollar)የሚበቃኦት ስንት እንደ ሚፈለጉ ይንገሩንና ሰብሰበን እንስጦት ቤተ ክርስቲያንን ይልቀቆት አብነ ፋኑኤል ቸሩ ፈጣሪ የነብስም የስጋም እረፈት ይስጦት ለንሰሀ ያብቃኦት የስላም ያድርግሎት......አሜን

Anonymous said...

It is beter to come together instaed to acuse each ather this iS not a time to devide. Every siraAsfesamy members need to realize it gonabe mess. You can' t do any thing with out bishaP. Do some thing for togethernes . Thanks

Anonymous said...

ያባ መላኩ ጵጵስና ያለ ብቃት- ትምህርት እና መንፈሳዊነት በገንዘብ የተገዛ ጵጵስና ነው::

ገዥውንና ሻጩን እናውቃለን

የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8
1 በዚያን ቀንም በኢየሩሳሌም ባለች ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ሁሉም ከሐዋርያትም በቀር ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ አገሮች ተበተኑ።
2 በጸሎትም የተጉ ሰዎች እስጢፋኖስን ቀበሩት ታላቅ ልቅሶም አለቀሱለት።
3 ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ያፈርስ ነበር፤ ወደ ሁሉም ቤት እየገባ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወኅኒ አሳልፎ ይሰጥ ነበር።
4 የተበተኑትም ቃሉን እየሰበኩ ዞሩ።
5 ፊልጶስም ወደ ሰማርያ ከተማ ወርዶ ክርስቶስን ሰበከላቸው።
6 ሕዝቡም የፊልጶስን ቃል በሰሙ ጊዜ ያደርጋት የነበረውንም ምልክት ባዩ ጊዜ፥ የተናገረውን በአንድ ልብ አደመጡ።
7 ርኵሳን መናፍስት በታላቅ ድምፅ እየጮኹ ከብዙ ሰዎች ይወጡ ነበርና፤ ብዙም ሽባዎችና አንካሶች ተፈወሱ፤
8 በዚያችም ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ።
9 ሲሞን የሚሉት አንድ ሰው ግን። እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ፥ እየጠነቈለ የሰማርያንም ወገን እያስገረመ ቀድሞ በከተማ ነበረ።
10 ከታናናሾችም ጀምሮ እስከ ታላላቆቹ ድረስ። ታላቁ የእግዚአብሔር ኃይል ይህ ነው እያሉ ሁሉ ያደምጡት ነበር።
11 ከብዙ ዘመንም ጀምሮ በጥንቈላ ስላስገረማቸው ያደምጡት ነበር።
12 ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም እየሰበከላቸው ፊልጶስን ባመኑት ጊዜ፥ ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ።
13 ሲሞንም ደግሞ ራሱ አመነ፤ ተጠምቆም ከፊልጶስ ጋር ይተባበር ነበር፤ የሚደረገውንም ምልክትና ታላቅ ተአምራት ባየ ጊዜ ተገረመ።
14 በኢየሩሳሌምም የነበሩት ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንደተቀበሉ ሰምተው ጴጥሮስንና ዮሐንስን ሰደዱላቸው።
15 እነርሱም በወረዱ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ይቀበሉ ዘንድ ጸለዩላቸው፤
16 በጌታ በኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር እንጂ ከእነርሱ በአንዱ ላይ ስንኳ ገና አልወረደም ነበርና።
17 በዚያን ጊዜ እጃቸውን ጫኑባቸው መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ።
18 ሲሞንም በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጥ ባየ ጊዜ፥ ገንዘብ አመጣላቸውና።
19 እጄን የምጭንበት ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ይቀበል ዘንድ ለእኔ ደግሞ ይህን ሥልጣን ስጡኝ አለ።
20 ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው። የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ።
21 ልብህ በእግዚአብሔር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም።

22 እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንሰሐ ግባ፥ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ወደ እግዚአብሔር ለምን፤
23 በመራራ መርዝና በዓመፅ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና።
24 ሲሞንም መልሶ። ካላችሁት አንዳች እንዳይደርስብኝ እናንተው ወደ ጌታ ለምኑልኝ አላቸው።
25 እነርሱም ከመሰከሩና የጌታን ቃል ከተናገሩ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ በሳምራውያን በብዙ መንደሮችም ወንጌልን ሰበኩ።

እንግዲህ እንወቅ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እና ሃይል በገንዘብ አይገዛም

Anonymous said...

ይድረስ ለአቡነ ፋኑኤል ለቴኒሲ የሰጡት ሹመት ማለት ለመላከ ሕይወት ቀሲስ ታደሰ ዱጋ የሰጡትን ሹመት እሳቸው ከቤ/ክኑ ጋር ገለልተኛ መሆናቸውንና ሹመቱን እንዳልተቀበሉት በእለተ ሰንበት እሁድ ለህዝበ ምዕመናን አስታውቀው በፊርማቸው አረጋግጠዋል፤ ፤

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)