February 2, 2012

አቡነ ፋኑኤል ሀ/ስብከት በማፍረስ ጎዳና ላይ ይሆኑ?


(ደጀ ሰላም፣ ጥር 24/2004 ዓ.ም፤ February 2/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በብፁዕ አቡነ አብርሃም ምትክ የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሀ/ስብከቱን መኖር እንደማያውቁ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በተናገሩ ማግስት ለቅ/ፓትርያርኩ የላኩት ደብዳቤ ለድረ ገጻችን በአድራሻ ተልኮልናል፡፡ ደብዳቤውን ያደረሱንን ደጀ ሰላማዊ ከልብ እናመሰግናለን።
ሊቀ ጳጳሱ አስቀድሞ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ሀ/ስብከት መኖሩን አላውቅም” ማለታቸውን ሰምተናል። ያንን አስከትለው ደግሞ የለም ያሉትን ሀ/ስብከት “በሕግ ለመጠየቅ” ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ባልሸሸጉበት ሁኔታ በሀ/ስብከቱ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በብፁዕ አቡነ አብርሃም ሰብሳቢነት ባደረጉት ዓመታዊ ጉባኤ የተቋቋመውን የሀ/ስብከቱን ሥራ አስፈጻሚ “ሕገ ወጦች” እና “የግል ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለሰቦች” በሚል ጠርተዋል።
ከዚያም አልፎ “ማኅተም በሕገ ወጥ መንገድ በማሳተም” እንደሚሠራም በግልጽ ተናግረዋል። ብፁዕነታቸው ሀ/ስብከቱን ዕውቅና ካለመስጠት ጀምሮ በሕግ ወደመጠየቅ ለመሔድ ከማስፋራራታቸው ባሻገር ቅ/ሲኖዶስ ያፈረሰውን “በሰሜን አሜሪካ የውጪ ግንኙነት ጽ/ቤት” ከሞት በመቀስቀስ ነፍስ ሊዘሩበት ሞክረዋል። እንግዲህ ሕገ ወጡ ማነው? የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ ያስተሃቀረውስ ማነው?በቪኦኤ ሲናገሩ እንደሰማነው ሀ/ስብከቱ መኖሩን አላውቅም ያሉት “አውሮፕላን ማረፊያ መጥቶ” ስላልተቀበላቸው መሆኑን አብራርተዋል። አውሮፕላን ማረፊያ አልተቀበለኝም ያሉት በወቅቱ በአካባቢው የነበሩትን ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ይሁን የሀ/ስበከቱን ሥራ አስፈጻሚ በግልጽ አላስቀመጡም። አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ካልተደረገላቸው ተቋሙ አይኖርም ማለት ነው። ታዲያ ሹመቱን ሲቀበሉ የየትኛው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ እሆናለሁ ብለው ነበር? ዘይገርም ነው።
ብፁዕነታቸው የዲሲና አካባቢውን ሀ/ስብከት ለማፈራረስ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጎን ለጎን ወጣቶች የተሰባሰቡባቸውን የማኅበረ ወልድ እና የሰሜን አሜሪካ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትንም እንደማያውቁ ሰሞኑን በጠሩት የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። በስብሰባው ላይ ሲነገር እንደተሰማው “ማኅበራቱ የተቋቋሙት ለአቡነ አብርሃም” ነው። የሚገርመው ግን ማኅበራቱ የተቋቋሙት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በሀ/ስብከቱ ሳይቀመጡ መሆኑ ነው።
ብፁዕነታቸው ደብዳቤያቸው ላይ ገለፁት ሌላው ዐቢይ ነጥብ “ተከፋፍለው የነበሩ ካህናትን፣ ምዕመናንና ምዕመናትን …” አንድ ለማድረግ በመጣር ላይ መሆናቸው ነው። ከሆነ መቸም አንድነትን የሚጠላ ማንም የለም ነበር። ነገር ግን አንድነት ያሉት ሳራቸውም በተቀመጡበት አጥቢያ የማያከብሩት እና ሌሎቹም “ባያከብሩት ችግር የለውም” የሚሉትን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ከሆነ አንድነቱ አንድነት ሳይሆን መላ ቅጡ የጠፋ ውጥንቅጥ ነው ማለት ነው። እርሳቸው ሰሞኑን በቆሙባቸው መድረኮች ሁሉ ሲያንቆለጳጵሷቸው የሚውሉትን ቅዱስ ፓትርያርኩን ስም በቅዳሴ ሳይጠሩ፣ ራሳቸው በቃለ ዐዋዲ ሳይመሩ፣ ራሳቸው የተሰጣቸውን የዲሲ እና አካባቢውን ሀ/ስብከት ጥለው ሌላ “ተለጣፊ” ሀ/ስብከት ለማቋቋም ደፋ ቀና እያሉ፣ የወጣቶች ማኅበራትን ለመዝጋት፣ ሌሎችንም ለመክሰስ እያስፈራሩ አንድነት አመጣለሁ ማለታቸው በእጅጉ የሚያስገርም ሆኗል።
እንግዲህ ማንን እንስማ የሚለውን ጥያቄ የምንጠይቅበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። በተለይም በአሜሪካ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት እና ምእመናን ቅ/ሲኖዶስን ወይ አቡነ ፋኑኤል ይስሙ? ቅ/ሲኖዶስ ዘጋውን እርሳቸው ከከፈቱ፣ ሕገ ቤተ ክርስቲንን ለራሳቸው በሚመች መልኩ ቅምጥል ጥብቆ ገው ለመስፋት ከታተሩ፣ በሐዋሳ ያሳዩትን አዋኪነት በአሜሪካም ከገፉበት፣ "This is America" እያሉ አሜሪካዊ ዜጋ መሆናቸውን እንዲሁም በእጅ አዙር የሚያስተዳድሩትና ለቤተ ክህነቱ የማይገዛ አጥቢያ ለቸው መሆናቸውን ከተመኩበት የሚያዋጣቸውን እርሳቸው ያውቃሉ።
ደጀ ሰላምም በዚህ ጉዳይ ላይ በሰፊው እንደምትመለስበት ቃል እየገባች፣ ተያያዥ ማስረጃዎችን እና የዲሲ ሀ/ስብከት የሔደባቸውን መስመሮች በሰፊው እንደምታቀርብ ታስታውቃለች።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
           

18 comments:

Anonymous said...

Dear Deje Selamawiyan,

These days I am doubting your sincerity. You are posting news that only support your cases.

How come you have not posted the turmoil that is going on around Atlanta Debre Bisrat St. Gabriel EOTC where a Monk(the former tsebate Yemanebirhan Asrat) who has been having sexual activities with several women has been fighting with the congregation after the case came to light and the congregation threw him out of the church.

It is to be recalled that you decided not to post news about this "Monk" when he decided to have the entire Kidase without closing the curtain as required by our cannon. (Even if the news was sent to you)

As a church blog, if your aim is to preserve our beloved church, you need to report all that is happening. You should not hide those news that puts a monk/priest that you identify with.

Regarding the so called Sira Asfetsami of the DC archdiocese, have you inquired what they have done to bring stability to the archdiocese?

I have read the letter they wrote to the Holy Synod when they heard Abune Fanuel was appointed and I think that was right.

But once he came here, have they really tried to talk to Abune Fanuel? Remember, whatever his sins are, he is still legally appointed by the Holy Synod. They should have discussed their issues first and laid out their concerns before continuing their objections to him.

He did not do anything worse than Abune Paulos. if they do not recognize Abune Fanuel, logic says, they don't recognize Abune Paulos too. Anyways we all should not runt to take some one to court before sitting down with each other and try to see if we can work out our differences. And the sira asfetsami should have taken the initiative to talk to him rather than ask Abune Fanuel to talk to them. They have to remember he is still a father and they are children.

For the record, I do not support what Abune Fanuel is doing, but neither do I support what the sira Asfetsami is doing. And it is within his right to gather those churches who will work with him and choose a new sira asfetsami even if that will not advance our church's cause.

May God deliver us from this type of divisions.

Anonymous said...

Beka yibelen degimo jemerachihu semonun yesew neger mesmat kertobin nebere Abune Fanueil Ahun tikikil mehonachewn awkenal Hagere Sibket Malet Papas Yalebet new enante eneman nachihu ?yeman tsebeka nachihu ? yebete kirsityan-ye Abune Abirham -ye Abune Pawlos-ye sunday shoole-ye Mahibere Kidusan? Ahun Degimo takasesuna fetena amitsu were amitsu Sira Asifetsam yetebalachihu wendimoche hulunim neger asbubetna Abune Fanueiln lemanegager mokiru yerasachew tsikim yekerebachew yalut neger sihitetnew beterefe gin Abune Fanueil yetesasatut neger yelem Wondimoch temekakeru
Kesis Birhanu Gobena -Kesis Ergete kal-Kesis Teshome Yohanis-D Efirem Eshete-Dr Mesifin -Aba Gebre wold -tengager mastewlun tibebun yistsachuhu Abune Fanueil yetemdebut Be sinodos new Dalas Tx beneberew sibseba lay hulum neger tegeltso taytal besbisebaw lay leke kahinat Hayile Silase -lke Maemiran Leyikun -rese Debir Moges-kesis Tadese kesis Mesifin -kesis Samueil ke 30 Yalanesu Abatoch neberu hulum amnewbet tesmamtew new yehedu beteley Leke Maemiran Leyikun Leke Kahinat Hayile silase Abune Fanueil sinodosu yelakachew silehone abiren mesrat alebn bilew yesetsut hasab le betekirsityan yemitsekmatin neger askemtsewal hulachihum tenegageru bemekerareb yemayifeta chigir yelem ahun yalew neger merarakin yametsal Abune Fanueil negeru beztobachew lekew bihedum selam aimetsam selam yemimetsaw tenegagiro mefithe sifelg bicha new hulachininm egzeabher yilemenen
Masasebiya ahun yememetut astarak abatoch astarkewachu yihdu elaleh

Anonymous said...

እርሱ[ዲያብሎስ]ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።

ብዕሩ ዘ-አትላንታ said...

በቅድሚያ ደጀ ሰላማዉያን ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ያለንን ግንዛቤ በወቅቱ እንድንከታተል ስላደረጋችሁን ።
አቡነ ፋኑኤል በዚህ ሀገር እዉቅና ያለዉንና የተመዘገበዉን የቤተ ክርስቲያን መዋቅር የለም ካሉ ደጋግመዉ ራሳቸዉን በጸሎት እንዲጠየቁ ከመምከር በቀር ሌላ አማራጭ ያለ አይመስለኝም። ልክ በየሰዉ ላይ የተለያየ አላርጂ(allergy ) የበሽታ አይነት እንዳለ ሁሉ እርሳቸዉን የተጠናወታቸዉ በሽታ ለቤተ ክርስቲያን የሚተጉ ሰዎችን በተለይ ወጣቶች በህብረት ሆነዉ ሲያገለግሎ ማየት የሚያስጠላቸዉ አይነት አላርጂ ነዉ። ምክንያቱም የጠራ ሥራን ማደፍረስ፣የተረጋጋን ማወክ፣አንድነትን መበታተን ፣ያለዉን ማጠናከር ሲገባ መናድ ወይም ከጎን ሌላ ማቋቋም ከሆነ ለአምባጓሮና ለንትርክ ለጸብ ቀጠሮ መያዝ ነዉ። ለጸብ ቀጠሮ የሚይዝ ሰዉ ደግሞ በሕይወቱ ምን ያህል የቆሸሸ ህሊና እንዳለዉ ለእርሳቸዉ መናገር ለቀባሪዉ ማርዳት እንዳይሆንብኝ እተወዋለሁ።
በአንድ ወቅት አንድ ኮሜዲ “ ወዮልሽ ኮሜዲ፣ወዮልሽ ኮሜዲ በሕዝቤ ላይ እንደተሳለቅሽ ኮሜዲኖ ዉስጥ ከትቼ ቁልፍ ነዉ የማደርግብሽ “ እንዳለዉ የእርሳቸዉም በምእመኑ ላይ ያሳዩት የተሳልቆ አንደበት በእግዚአብሔር ፍርድ የሚገታበት ጊዜ አለ። ለመንጋዉ የማይራሩ ፣የቤተ ክርስቲያን ነገር ግድ የማይለቸዉ እንደሆኑ ንግግራቸዉ ይመሰክራል። አባቶቼ እባካችሁ ነገር ማሳመር ስለማያስከብር በሕይወት ኑሩ። እዉነትን ለመመስከር የያዛችሁትን መስቀል አስቡ። ትዕቢትና መታጀር የአንድ አባት ግብር አይደለም። በተለይ ደግሞ በዓላማ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገልና ለቤተ ክርስቲያን ለመስራት የሚታትርን ትዉልድ መዉጋት ከኃጢያትም ኃጢያት ከሞትም ሞት ነዉ።
ወደ አስተያየቴ ልመለስና አባ ፋኑኤል እየሰሩትና እየሄዱበት ያለዉ መንገድ ቤተ ክርስቲያንን ፈጽሞ ለመበታተን የሚደረግ ሴራ ስለሆነ መእመናን እንዲጠነቀቁ በግልጽ ማሳወቅ ሲሆን ሌላዉ ለዚህ ተልዕኮ የሚያበረታታቸዉ ከጀርባቸዉ ሌላ ኃይልም እንዳለ የመላክታል። ይህ ባይሆን አፍ ሞልተዉ መዝለፍና ንቀት ከእርሳቸዉ አንደበት ባልወጣ ነበር።
ደጀ ሰላማዉያን በርቱ !!! ብዕሩ ዘ-አትላንታ

Anonymous said...

2 joro -2 ayin-hulet egir-yesetsen amilak ahun degimo hulet neger yasnebibenal Deje Selam sinager Aba Selama yafersal Aba Selama Sinager Deje Selam yafersal enkan hulet honachihu Ahun yemimekrachihu tesmamu -tareku teweyayu huletachihum ye godachihut bete kirsityann new yesew neger degimo akumu sew hulu teleyachihu -tselachihu -rakachihu- ferachihu- sheshachihu- mikinyatum enanten yaldegefe hulu menafik- kehadi-dedeb tebale yedegefe degimo awak -mihur tebale Like Maemiran Leyikun hulunim neger yawkalu yetekeber sew nachew Memerat yalebin sinodos bewesenew new enj Mahiber bewesenew ayidelem yalut tikikil new Ahunim Abune Fanueil & mahibere Kidusan Yitareku

Anonymous said...

"ቸር ወሬ ያሰማን" ይቀየርልን
የተከበራችሁ ደጀ ሰላሞች እንዴት ነው በየቀኑ ነገር ብቻ እያፈነፈናችሁ በመጨረሻ ቸር ወሬ ያሰማን የምትሉት መፈክር ነው ወይንስ ????በተቃራኒው ይሞከርና እስቲ እንየው "ቸር ወሬ ያሰማን" ይቀየርልን::

Anonymous said...

Dear deje selamawiam thank you for posting But I am confuse Because of this information. I know there is a problem in side of the dc archdiosis because of steate betekrestian. Some of want to accept any of the holy sinod Wsane no matter who comes as archbishop some of have a personal issue. That is whay Dc archdiocese stat divided t in to many picess I remember Va Ledeta church, St georgis church been a member of Dc diociss now they not. Va st teklehaymanot too on half way to saparet and work with Abune fanuel becaus the comette of dc diocese not standing for the eotc unity I guess they take a good action to me and my fellow we have to see our church icon kale awadi work with no matter who assigned from bete kehinet.

Anonymous said...

Dear deje selamawiam thank you for posting But I am confuse Because of this information. I know there is a problem in side of the dc archdiosis because of steate betekrestian. Some of want to accept any of the holy sinod Wsane no matter who comes as archbishop some of have a personal issue. That is whay Dc archdiocese stat divided t in to many picess I remember Va Ledeta church, St georgis church been a member of Dc diociss now they not. Va st teklehaymanot too on half way to saparet and work with Abune fanuel becaus the comette of dc diocese not standing for the eotc unity I guess they take a good action to me and my fellow we have to see our church icon kale awadi work with no matter who assigned from bete kehinet.

Anonymous said...

ደጀብርሃንFeb 2, 2012 03:55 AM

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መንግሥት በሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ዓይኑን ተክሏል። የሚያግለበልበው ትኩሳት ስላለ ያንን ለማብረድ ሲፈልግ በፍርድ ቤት፤ ሲሻም በደህንነቱ መስሪያ ቤት፣ ሲፈልግ ደግሞ በተቃዋሚው ጎራ ትንሽ በትንሹ የሚከረክመውን ጎፈሬ ከነመቀሱ ይታየናል። ከዚህ አንጻር ማኅበረ ቅዱሳን በሚያደርገው ስልታዊ ጉዞውና በማድፈጥ ባህሪው የተነሳ ከመንግሥት ጎፈሬን የመከርከም መቀስ በመትረፍ ሕይወቱን ሊያሰነብት ችሏል። ያ ማለት ግን መንግሥት ሰዶ ከማሳደድ ይልቅ ጊዜና ቦታ እየጠበቀለት ይሆን እንደሆን እንጂ የዘነጋው ሆኖ አይደለም። ማቅም እንደድመት ጸጉሩን አለስልሶ እንቅልፍ የያዘው መምሰሉ ጊዜና ቦታ እየጠበቀ እንደሆን እንጂ ለአብዮታዊ ዲሞክራሲ መርህ እጁን የሚሰጥ ሆኖ እንዳልሆነ ይታወቃል። ሁለቱም እስከሚበላሉ ቀንን የሚጠብቁ ናቸው። ይህ መሆኑ ማቅ ለመኖር እድሜን አግኝቷል። በሌላ መልኩ ለማቅ እድሜ ማግኘትና እንዳንሰራራ መቆየት ዋናው ምክንያት የኢትዮጵያ መንግሥት ትእግስት ወይም የማቅ ስውር ሴራ አለመታወቁ ሳይሆን መንግስት በጥቅሉ እንደሚለው (ቄሶቹ፣ ሲኖዶሱ ማለት ነው)ይህን ማኅበር እራሳቸው እንዳቋቋሙት እራሳቸው ያፍርሱት ወይም ከአቅማችን በላይ ሆኗል ብለው አቤቱታ ያቅርቡልኝ እንጂ ራሳቸው በጣዱት እሳት ሲቃጠሉ እኔ ጣልቃ ገብቼ ለማብረድ ስል ለምን ወደሰዶ ማሳደድ እገባለሁ ከሚል እሳቤ የተነሳ ሊሆን ይችላል። የቄሶቹ ጉባዔ(ሲኖዶስ)ደግሞ ገሚሱ በፍትፍት አፉ የተዘጋና፣ ገሚሱ ደግሞ በገመና ድራማ ታሪክ የተመዘገበ ስለሆነ በማኅበሩ ላይ ይህንን ያህል አስጊ ነገር ያመጣበታል ተብሎ አይታሰብም። ትልቁ ቄስ ብቻቸውን ቢዘሉ በውስጥ በማቅ የቄሶቹ ብድን ተቃውሞ ሲወርድባቸው በውጭ ደግሞ በሃይማኖት የለሽነት ዘመቻው የሚዲያውን አየር ይበክላል። ጥቂት ሰራተኞች ካሉ ደግሞ እነሱ ላይ በመዝመት «መጽሐፉም ዝም፣ቄሱም ዝም» እንዲሉ ለማድረግ በቤተክህነቱ አካባቢ እነአባ ሠረቀብርሃንን በመሳሰሉ፣ በመድረኩ ላይ እነበጋሻውን በመሰሉ፣ በውጪው እነ አባ ፋኑኤልን በመሰሉ ሁለገብ መንገድ ዝም ጭጭ በማድረግ የተቀናቃኝ ጎራውን ረምርሞ «ወጣ ገባነው መንገዱ፣ ወደግሸን ሲሄዱ» በሚል ዜማ በነበረት ለመቀጠል ሁሉን ዐቀፍ እርምጃውን እያሳየ ይገኛል። በጥቅሉ ለዚህ ማኅበር እስትንፋስ ተጠያቂው ሁለት ወገን ያለው ነው። 1ኛ/ በዚህ ማኅበር መንፈስ የሰከረ ደጋፊ ቡድንና 2/ ለዚህ ማኅበር መንፈስ ዘብ የቆመው የቄሶቹ(ሲኖዶስ)ቡድን ነው። በዚህ መሀከል ቤተክርስቲያን ወዲያና ወዲህ እየተናጠች ትገኛለች።
ከዚያ በተረፈ የማቅን ስልታዊ ማፈግፈግ ሁሉ መንግስት በስልት እንደሚጠብቀው ጥርጥር የለንም። የስልቱ የአጥፊና ጠፊ ፍጻሜው መቼ ይሆን?ለሚለው ጥያቄያችን ጊዜ ይፍታው ስንል ለቄሶቹ ብድን(ሲኖዶስ) ግን አንድ ጥያቄ ለማቅረብ እንወዳለን። እውን ይህ ማኅበር «እስኪይዝ ያነክስ ከሚለው የጅቡ ምሳሌ በዘለለ የእናንተን መረማመጃነት ይፈልግ ይሆን?»ብለን እንጠይቃቸዋለን።

Anonymous said...

‹‹እኔን ለምን ትወቅሱኛላችሁ››
ጥቅምት 21/2004 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤው ባካሄደው ዐሥረኛ ቀን ስብሰባው አቡነ ፋኑኤል በሌላው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገብተው ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በፈጸሙት ተግባር በግልጽ ገሥጧቸዋል፡፡ በተለይም ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ ‹‹ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን በሚባሉት ተገኝተው የሚባርኩት፣ ሥልጣነ ክህነት የሚሰጡት ማን ፈቅዶሎት ነው? በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የሾሟቸው ‹ካህናት› ክህነት ወድቅ እንደሚደረግ አያውቁም? እርስዎ ባቋቋሙት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስነታቸው ስም ይጠራበታል? የሚጠራበት የእርስዎ ስም ነው፤ ይህ ሕገ ወጥነት ነው፤ ተገቢም አይደለም!!›› በማለት በከፍተኛ ኀይለ ቃል ገሥጸዋቸዋል፡፡ አቡነ ፋኑኤልም ‹‹እኔን ለምን ትወቅሱኛላችሁ፤ አቡነ አብርሃም ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን ሄደው አይባርኩም፤ ሄደህ አገልግል ብለው ፓትርያርኩ ስላዘዙኝ ነው፤›› በማለት ችግሩ ከወደላይ መሆኑን አጋልጠዋል፡፡ አቡነ ፋኑኤል ይህን ጉድ ሲገልጡት ርእሰ መንበር ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አንገታቸው ዘልሰው አንዳችም ቃል አለመናገራቸው ምልአተ ጉባኤውን ማስገረሙን ያዩ ተናግረዋል፡፡

አወዛጋቢው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤል በፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ትእዛዝ በመፈጸሙት ኢ-ቀኖናዊ ተግባር የሹመት ሽልማቱን በዚህ መልክ ያግኙ እንጂ በአህጉረ ስብከቱ ግን ጠንካራ ተቃውሞና ተቀባይነት ማጣት እንደሚጠብቃቸው ግልጽ ነበር ፡፡ የምልአተ ጉባኤውን ውሳኔ አቡነ ፋኑኤል በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከፈጸሙት ኢ-ቀኖናዊ ድርጊት በተቃራኒ እዚያው እንዲሾሙና ምፀታዊ በሆነ መልኩ አቤቱታ አቅራቢዎቹ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲነሡ መወሰኑ ተከታዩን ችግር አርቆ አለማየትን.ያመለክታል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ለወሰነው ውሳኔ ተገዥዎች ነን። ሆኖም ግን በሰሜን አሜሪካ ያለን ምእመናን ለመናፍቃን አሳልፎ የሚሰጠን ሳይሆን ከጠላት የሚታደገን ኖላዌ ትጉህ ያስፈልገናልና ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔውን ደግሞ እንዲመረምር ማድረግ ይጠበቅበታል ምክንያቱም የችግሩን ስፋት ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይ ሊያውቀው የሚችል የለምና።

ለመሆኑ አቡነ ፋኑኤል ለየትኛው አገረ ስብከት እንደተላኩ ያውቃሉን?
የሚከሱትስ ለየትኛው አገረ ስብከት ነው? ሴኖዶስን ነው ወይስ እራሳቸው?
“ከሳሽ የተክሳሽን ልብ ቢያውቅ ኖሮ ከቤቱም ባልወጣ ነበር” እነደሚባለው ብጹነታቸው እየከሰሱ ያሉ እራሳቸውን ነው።

Anonymous said...

Why are you calling him "ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤል"

He should never be a bishop. He is not qualified.

He doesn't exhibit the Spirit of the Lord.

Anonymous said...

awssa setama lene belhe sema yhlual ahun new
abune fanuel is one of ejegayu's group whom desterb our mother church a year a go i was invited his home at kalite and a saw what makes shemin his home he have bar it seem like grocery.he is guided by kisses solomon mulugeta and begashaw.
he conseder that fighting aginest MK is helping His group but he strongly scaterd church.
Church conon mantiond about bishop that to be Fathers to all and fight aginest Psudo teaching.his grace what i tell you that it is better work to the church than yoursrlf and Abba pawlos.
lastly what i recomend that the Holy Synod should give foucos to Church in diaspora befor the church loss Her autosophalesity up on her congrgation and must be appoint additional3 bishop to north American main probelem is that lack of knowldge about church Hstory and admin....this gap open achnc to renewals(tehadeswoch).
pleas we have to strugel to mother church but not personal or group centerd interst.
from seattel

Miskin said...

ስላም ደጀ ስላም
በጣም የሚገርመው አባ ሰላማ የተባለው ድህረ ገጽ ቅዱሳንን የሚሳደብ የቤተ ክርስቲያንን ስረዓት የሚንቅ ታድያ ሰለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምን ይመለከተዋል ይህ ድህረ ገጽ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰራ የሚንቅ የሚሳደብ ምንም መነፈሳዊነት የሌለበት ከ እውነይ ይልቅ 100፥ ውሽት የሚላቀ comments እነኮን የማልቀበል አነባቢውም ኮሜንት ሰጭውም እራሱ ድህረ ገጽ መሆኑ ለምን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርሲቲያን ይጨነቃሉ ቤተ ክርስቲያን እንደዘሀ አይነት ምእመን የላትም ደጀሰላም በረቱ

Anonymous said...

+++
ተወዛግባችሁ ምዕመናንን የምታወዛግቡ ከንቱ ውዝግባን ሁሉ፤ ወዮልሽ! በኃጢአታችን ብዛት የመጣውን ፈተና በጸሎትና በጾም ለመወጣት የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረቱን አይተውምና፡፡
አቡኑ… ዘመናዊ ቪላ ቤት ከ9 መታጠቢያ ገንዳ፣ ጃኩዚ፣ መዋኛ ገንዳው…ማስገንባትዎ ለርስዎ ከንቱ መሆኑን ነጋሪ የሚፈልጉ አይመስለኝም፡፡ ስንቱ ገዳማትና አድባራትን ለመጠገን/ለመርዳት ይሯሯጣል የርስዎና መሰሎችዎ አባት ነን ባዮች ግራ ናችሁ፡፡ አንድ አባት አንድ አባትን ሲያመነኩሱ ያሉት ነገር ባሰብኩት ቁጥር የነ ነጋዴ ነገር ይመጣብኛል፡፡ እኔም የሚገባኝን ሳልሰራ፤ የናንተን ኮተት ሳረበርብ በናንተ ጎራ የተሰለፍኩ ያክል ተሰማኝ፡፡ እባካችሁ ወደ ልቡናችን እንመለስ!

yemelaku bariya said...

ለአባ ፋኑኤል ክስ ቀላል መስሏቸዋል:: የጠራ የክስ ፋይል ይዘው ካልቀረቡና ከተወከሉበት ኃላፊነት ውጭ የጥቅም መጋጨት ካለ በሚመጻደቁበት አገራቸው እንዳይቀድሱ ሁሉ እንደሚችሉ አብረው ቢያስቡበት መልካም ነው:: ምናልባት በትውልድ አገራቸው አለቃቸው አቡነ ጳውሎስ በስልክ ፍርድ ቤቱን እያዘዙ ክስ ሲሰረዝ፣ ውሳኔ ሲገለበጥ አይተዋልና ይህ ሊሆን የቻለው ቅዱስነታቸው ተሰሚነታቸው ሃያል ስለሆነና ትእዛዛቸውም ዓለምአቀፋዊ መስሏቸው ለዲሲ ድስትሪክት ፍርድ ቤት እንደአዲስአባው የሚደውሉላቸው መስሏቸው ከሆነ ዋ እኔ የለሁም:: ፍትህ ከቤተ ክህነቱ እንደሁ ጠፍቷል ምናልባት ከአሜሪካ ፍርድ ቤቶች እናገኝ ይሆ ናል ያውም በራሳቸው አመልካችነት::

Anonymous said...

The diversity of nature always surpises me. The wisdom of God ! it is nice to have people like " Deje Birhan". Who lives in 21st century and thinks like stone-age.
He thinks the government or EPRDF officials are not capable of doing what they do. He thinks that they are like him. You and EPRDF are different you think nothing more than " Yebele'am Ahiya". EPRDF knows well what it does. And Mahibere qidusan is not " Yemesheta bet mahiber" to which you belong. It is tested like GOLD and has proven its truthfullness to the church fathers (to whom you reffered as qesochu) and the government. So try another strategy. This one has expired like you.

Biniam Nashville said...

ኣረ በቃ ፣ ክርስትናው ጠፋብን እኮ
ምን አይነት ጊዜ
ይቅር ባይ ልብ፣ ቅኑነት ጠፋ እኮ
የወደድኩዋችሁን ያህል አዘንኩባችሁ ደጀሰላሞች ፣ምነው ሰላሙን ብታወርዱ ጤነኛ ዓይናችሁን ምን ነካብን
ስርዓት ይከበር ከሆነ ምነው ብንቀበላቸው ያለፈውን ትተን እድል ብንሰጥ ፣ መቼም የተለያየ ሰው አንድ አይነት ያሰራር ስልት የለው
በቃ በቃ
Biniam Nashville

Anonymous said...

Please about the turmoil that former tsebate Yemanebirhan Asrat has started around Atlanta. He has recently announced that he has opened a new church...smh

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)