February 29, 2012

የአሰቦት ገዳም ደን ለሁለተኛ ጊዜ እየተቃጠለ ነው


 • ማኅበረ መነኮሳቱ አስቸኳይ ርዳታ ጠይቀዋል
 • ከብት ዘራፊዎችና ከሰል አክሳዮች የቃጠሎ መንሥኤዎች ናቸው ተብሏል
 • ‹‹ውኃ የለንም፤ የሚረዳን ሰውም የለንም፤ እሳቱ ወደ ትልቁ ደንና ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እየተቃረበ በመሆኑ ከፍተኛ ርዳታ ያስፈልገናል›› /የገዳሙ መነኮስ/
 • ገዳሙ በግራኝ ወረራ የመጥፋት፣ በኢጣልያ ወረራ የመዘረፍ አደጋ ገጥሞት ነበር፤ ከ20 ዓመት በፊት ‹‹የኦሮሚያ ነጻነት እስላማዊ ግንባር/ጃራ/›› ገዳሙን ወርሮ በአካባቢው የሚኖሩ 16 ክርስቲያን አባ ወራዎችን አርዶ ነበር
(ደጀ ሰላም፣ የካቲት 21/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 29/2012/READ THIS NEWS IN PDF)፦ እንደ ጥድ፣ ዝግባ፣ ወይራ፣ ግራር፣ ብሳና፣ ቀረሮ በመሳሰሉት አገር በቀል እና ዕድሜ ጠገብ ዛፎች የተሞላውን በአጠቃላይ 13ሺሕ ሄ/ር መሬት ያህል ይሸፍን እንደነበር የሚነገረው የአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ እና አቡነ ሳሙኤል ገዳም በአራት ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በተቀሰቀሰ ሰደድ እሳት እየጋየ መኾኑ ተሰማ፡፡

ጌታቸው ዶኒ እንደገና ወደ ዜና ብቅ ሲል


·  ዳግመኛ በተሾመበት ደብር የተቀሰቀሰው የምእመናን ተቃውሞ ተጠናክሯል
·    የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እስርና ማስፈራሪያ እየተፈጸመባቸው ነው
(ደጀ ሰላም፣ የካቲት 21/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 29/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በግንቦት 2003 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ራሳቸውን “ወንጌላውያን” ብለው ከሚጠሩ የፕሮቴስንታት አብያተ እምነት ጋ ያለው የዓላማ ግንኙነት በማስረጃ የተረጋገጠበት፣ በሕገ ወጥ የማጥመቅ ሥርዐትና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ጉልሕ ሃይማኖታዊ ሕጸጽ የፈጸመው ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ቀደም ሲል በአበው ካህናት እና ምእመናን ከፍተኛ ተቃውሞ ወደተባረረበት የቃሊቲ ደብረ ገነት ቁስቋም ማርያም እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተመልሶ አጥቢያውን እንዲያስተዳደር ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያክ አቡነ ጳውሎስ መሾሙ ተሰምቷል፡፡

February 20, 2012

ብፁዕ አቡነ አብሳዲ አረፉ


 (ደጀ ሰላም፣ የካቲት 12/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 20/2012)፦ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ አብሳዲ አረፉ። ላለፉት 60 ዓመታት በኢየሩሳሌም ገዳማት የኖሩትና በእግራቸው ከኢትዮጵያ ወደ ቅድስት አገር የመጓን ጥንታዊ ትውፊት ከፈፀሙት አበው መካከል የነበሩት ብፁዕነታቸው በሕመም እና በእርግና ምክንያት ከዚህ ዓለም ድካም በሰላም እንዳረፉ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ዝርዝር ዜናውን እንደደረሰልን እናቀርባለን። የብፁዕ አባታችንን ነፍስ በገነት ያኑርልን።
አሜን።

February 19, 2012

በቅዱስ ሲኖዶስና በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል የተካሄደው የዕርቀ ሰላም ውይይት ተፈፀመ


 (ደጀ ሰላም፣ የካቲት 10/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 18/2012)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሰሜን አሜሪካ በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል በአሜሪካ - አሪዞና ግዛት ከየካቲት 4 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ሲያሄድ የሰነበተው ሁለተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ውይይት ተፈፀመ፡፡  መግለጫም አውጥቷል። የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንንይጫኑ።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

February 16, 2012

በጎንደር ከተማ ሁለት የአብነት ት/ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተቃጠሉ


 • አንዱ ቤተ ጉባኤ በኢትዮጵያ ብቸኛው የመጻሕፍተ መነኮሳት ትርጓሜ ማኼጃ ነበር ተብሏል:: (READ THIS ARTICLE IN PDF)

(ደጀ ሰላ የካቲት 8/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 16/2012)፦ በሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ጎንደር ከተማ በሳምንት ልዩነት በሁለት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በተነሡ የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች አንድ ጥንታዊ የመጻሕፍት ትርጓሜ ቤት ሌላ የቅኔ ቤተ ጉባኤ ሙሉ በሙሉ ወደሙ፡፡ በጎንደር ከተማ የሚገኘው የሐመረ ኖኅ ሠለስቱ ምእት መጻሕፍተ መነኮሳት ትርጓሜ ት/ቤት ሙሉ በሙሉ የወደመው ከትላንት በስቲያ፣ ከየካቲት 6 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ላይ መንሥኤው ባልታወቀ አኳኋን በተነሣ የእሳት ቃጠሎ መሆኑን ደቀ መዛሙርቱ ተናግረዋል፡፡ የትርጓሜ ት/ቤቱ በኢትዮጵያ ከአራቱ ጉባኤያት አንዱ የሆነውን መጻሕፍተ መነኮሳትን ብቻ የሚያሄድ ብቸኛ ቤተ ጉባኤ እንደነበር ተገልጧል፡፡

የዋልድባ ገዳማት ህልውናና ክብር የገጠመውን ፈተና በተመለከተ ገዳሙ ያቀረባቸው ደብዳቤዎች

(ደጀ ሰላም፣ የካቲት 8/2004 ዓ.ም፤ፌብሩዋሪ 16/2012/ READTHIS ARTICLE IN PDF)፦ ባለፈው የካቲት 2/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 10/2012 ስለ ዋልድባ ገዳም እና መንግሥት በአካባቢው እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ ዙሪያ የገዳሙን አቤቱታ እና ኡኡታ መዘገባችን ይታወሳል። ያንን ዜና በድጋሚ ለማስታወስ እያቀረብን፣ ገዳሙ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የጻፈው ደብዳቤ ሙ (ይህንን ይጫኑ) ማስቀመጣችንን በዚሁ አጋጣሚ እናስታውቃለን። ገዳሙ በገጠመው ችግር እንደ ሁላችሁም ሁሉ ጥልቅ ኃዘን የተሰማን መሆናችንን እየገለጽን አንዳንዶቻችሁ ባነሳችሁት መሠረት ለመንግሥት የሚቀርብ “አቤቱታ/ ፔቲሽን” በማጋጀት የኦርቶዶክሳውያንን ድምጽ ለማሰማት በኩላችንን እንሞክራለን። በእግዚአብሔር ቸርነት ዋልድባ ገዳማችን ዛሬም፣ ነገም ይከበራል።

በቅዱስ ሲኖዶስና በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል የዕርቀ ሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው


·        ከአገር ቤት ልካን አንዱ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ከጤና እክል ጋራ በተያያዘ በውይይቱ ላይ አይሳተፉም፤ ወደ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ገብተው ሕክምና እየተከታተሉ ነው
(ደጀ ሰላም፣ የካቲት 7/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 15/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና በሰሜን አሜሪካ በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል ሁለተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም ውይይት ዛሬ፣ የካቲት 7 ቀን 2004 ዓ.ም፣ ማምሻውን በአሜሪካ - አሪዞና ግዛት እየተካሄደ ነው፡፡ የዕርቀ ሰላም ውይይቱን በሚያስተባብረው የሰላም እና አንድነት ጉባኤ በወጣው መርሐ ግብር መሠረት ይኸው ሁለተኛ ዙር ንግግር ከየካቲት 4 - 9 ቀን 2004 ዓ.ም እንደሚቆይ ተገልጧል፡፡

February 10, 2012

የዋልድባ ገዳማት ህልውና እና ክብር ለአደጋ ተጋልጧል

·     በገዳሙ ክልል እና ዙሪያ (በዓዲ አርቃይ ወረዳ በኩል) የፓርክ ይዞታ ለመከለል እና የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም በሚል በሚካሄደው የጥርጊያ መንገድ ሥራ (ከማይ ፀብሪ እስከ ዕጣኖ ማርያም) የቅዱሳን አበው ዐፅም እየፈለሰ መሬቱ እየታረሰ ነው
· የሦስቱ ገዳማት ማኅበረ መነኮሳት ዕቅዱ የገዳሙን ክብር የሚጋፋ ህልውናውንም የሚያጠፋ በመሆኑ እንዲቆምላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል

February 9, 2012

Monastic Life in Waldebba Monastery (ETV)

የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት የብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን እንቅስቃሴ አስመልክቶ መግለጫ አወጣ


·         የመግለጫውን ሙሉ ቃል ይዘናል። 
(ደጀ ሰላም፤ ጥር 30/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 8/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አስቸኳይ አጠቃላይ ጉባዔውን በኖርዝ ካሮላይና ሻርለት ባካሔደ ማግስት ሀ/ስብከቱ ባለበት አጠቃላይ ሁኔታ ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው እንደሚያትተው “የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ ይህንን መግለጫ ለመስጠት ያነሳሳው ዋና ምክንያት በቅርቡ ጥር 12 ቀን 2004 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካ ድምጽ የአማርኛ አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ሕዝበ ክርስቲያኑን የሚያንጽ በአባትነት ደረጃ አስተማሪ የሆነ ነገር መናገር ሲጠበቅባቸው ሕዝበ ክርስቲያኑን እና አብያተ ክርስቲያኑትን ያሳዘነ ሀሳብ ሰጥተዋል። በሰጡትም ቃለ መጠይቅ ላይ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት እንደሌለ፤ በሀገረ ስብከቱ መዋቅር ሥር  ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ቃለ ዐዋዲ ጠብቀው እንደማይንቀሳቀሱ በመናገር የቤተ ክርስቲያንን የበላይነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ እና  ሕዝበ ክርስቲያኑንም ወደ አልተፈለገ አለመግባባት የሚመራ ገለጻ መሆኑን በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ተገንዝበዋል” ብሏል።

February 8, 2012

ይድረስ ለአቡነ ፋኑኤል


(ብርሃኑ መላኩ/ READ THIS ARTICLE IN PDF.)
የብፁዕነትዎን ይቅርታ እየጠየቅሁ እንደ መንፈሳዊ ልጅነቴ በግሌ ላሳስብዎት የምሻውን ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ። እድሜ 30ዎቹ ሲሆን በውጭ ሃገር ተወልደው አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋ እምነትን በባለቤትነትና በኩራት የሚከተሉ ሁለት ልጆችን እግዚአብሔር ሰጥቶኛል። ድሜቸው በአስራ ሲሆን በእምነታቸው ግን በጣም በመብሰላቸው ለዘመኑ የኢ . . . ቤተ ክርስቲያን ንትርክ ሳይወዱ ተካፋይ ሆነዋል። ለዚህም የዳረጋቸው የየአብያተ ክርቲያናቱ ዶግማና ቀኖና ርዓት ነው። ዝርዝሩን እዚህ ላይ ባላሰፍረውም የሁሉም የእምነቱ ተከታይ የሆኑት ምእመናን ቤት ጠንቅቆ ያውቀዋል።

February 6, 2012

የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ


·         በስብሰባው ያልተገኙት አቡነ ፋኑኤል ከአካባቢው ለሰበሰቧቸው ካህናት አዲስ ሹመት ሰጥተዋል፤
(ደጀ ሰላ ጥር 28/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 6/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አስቸኳይ አጠቃላይ ጉባዔውን በኖርዝ ካሮላይና ሻርለት በማካሄድ እና መሠረታዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ እንደተጠናቀቀ ምንጮች ለደጀ ሰላም ገልጸዋል። ጥር 25 እና 26/ 2004 ዓ.ም በሀ/ስብከቱ ሥር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በተገኙበት በተደረገው የምክክር ጉባኤ ላይ “የሀ/ስብከቱን መኖር አላውቅም” ያሉት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አለመገኘታቸው ታውቋል።

February 5, 2012

ግእዝ እና ንባበ-መለኮት፦ ለእስ-በስ ውይይት


ውድ ደጀ ሰላማውያን፤

እንደምን ሰነበታችሁ? ከዚህ በታች የምታገኙት ጽሑፍ ከ “ግእዝ በመስመር ላይ” የጡመራ-መድረክ አዘጋጅ የተላከልን ነው። እናመሰግናለን። አስቀድማ ደጀ ሰላም ኢትዮጵያ 9ኛውን የኦሪየንታል ኦርቶዶክስ እና የሮም ካቶሊክ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ታስተናግዳለች” በሚል ርዕስ የዘገበችውን መመልከት ጽሑፉን ለመረዳት ያግዛል።

ቸር ወሬ ያሰማን፣

አሜን

+++++

ግእዝ እና ንባበ-መለኮት፦ ለእስ-በስ ውይይት
(Geez and Theology: A Colloquy)

February 3, 2012

የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ የእነ በጋሻውን “የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር” አገደ

 • READ IN PDF & Read the Letter.
 •  በእግዱ ደብዳቤ ላይ “መምሪያው ከሚመድባቸው መምህራን ውጭ የሆኑ ግለሰቦች” የተባሉት እነበጋሻው በየጊዜው ፖስተር በመለጠፍ የሚያካሂዱት ቅስቀሳ ሕገ ወጥ መሆኑ ተመልክቷል
 •  የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የሕገ ወጥ ሰባክያንንና ዘማርያንን ስምሪት በመፍቀድ የቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያንና ውሳኔን እየጣሱ ነው
 • አብዛኞቹ የአህጉረ ስብከት ጽ/ቤቶችና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለመመሪያው ተፈጻሚነት እየሠሩ ሲሆን ተግባራዊ የማድረግ ድክመት የታየባቸውም አሉ
 • የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ፈቃድ የሌላቸውን ሕገ ወጥ ሰባክያንና ዘማርያን ነን ባዮች እንዲሁም ሕዝቡን የሚያደናግሩባቸውን የኅትመት ውጤቶቻቸውን ለመቆጣጠር የወጣውን የቅዱስ ሲኖዶስ መምሪያና ውሳኔ ለማስፈጸም የመንግሥትን እገዛ ጠይቋል
 • "ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዕውቅና እና ፈቃድ ውጪ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዐት እና መዋቅር በመጣስ በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ እና ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ እናሳስባለን”/የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጥያቄ ለአስተዳደሩ ፍትሕ ቢሮ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የጻፈው ደብዳቤ/

February 2, 2012

አቡነ ፋኑኤል ሀ/ስብከት በማፍረስ ጎዳና ላይ ይሆኑ?


(ደጀ ሰላም፣ ጥር 24/2004 ዓ.ም፤ February 2/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በብፁዕ አቡነ አብርሃም ምትክ የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሀ/ስብከቱን መኖር እንደማያውቁ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በተናገሩ ማግስት ለቅ/ፓትርያርኩ የላኩት ደብዳቤ ለድረ ገጻችን በአድራሻ ተልኮልናል፡፡ ደብዳቤውን ያደረሱንን ደጀ ሰላማዊ ከልብ እናመሰግናለን።
ሊቀ ጳጳሱ አስቀድሞ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ሀ/ስብከት መኖሩን አላውቅም” ማለታቸውን ሰምተናል። ያንን አስከትለው ደግሞ የለም ያሉትን ሀ/ስብከት “በሕግ ለመጠየቅ” ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ባልሸሸጉበት ሁኔታ በሀ/ስብከቱ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በብፁዕ አቡነ አብርሃም ሰብሳቢነት ባደረጉት ዓመታዊ ጉባኤ የተቋቋመውን የሀ/ስብከቱን ሥራ አስፈጻሚ “ሕገ ወጦች” እና “የግል ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለሰቦች” በሚል ጠርተዋል።

February 1, 2012

[Ethiopian] Christians Arrested at Private Prayer in Saudi Arabia


(Beirut/ www.hrw.org) – Thirty five Ethiopian Christians are awaiting deportation from Saudi Arabia for “illicit mingling,” after police arrested them when they raided a private prayer gathering in Jeddah in mid-December, 2011, Human Rights Watch said today. Of those arrested, 29 were women. They were subjected to arbitrary body cavity searches in custody, three of the Ethiopians told Human Rights Watch.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)