January 27, 2012

ጥምቀት በለንደን


(ተዋሕዶ ዘሎንዶን፤ ለደጀ ሰላም፣ ጥር 17/2004 ዓ.ም፤ January 26/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የ፳፻፬ ዓ.ም. የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በዩናይትድ ኪንግደም ርዕሰ ከተማ ለንደን በከፍተኛ መንፈሳዊ ስነ-ሥርዓት መከበሩን የሰ/ምዕ/አውሮፓ /ስብከት /ቤት አስታወቀ። ጌታ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ መጠመቁን ለማዘከር በቆየው የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት በለንደን የሚገኙት የኢ///አብያተ ክርስቲያናት በበዓሉ ዋዜማ ታቦቶቻቸውን ይዘው ከመቅደሶቻቸው ሲወጡና ለማደሪያ በተዘጋጀላቸው ሥፍራ ሲደርሱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናት፣ የሰንበት /ቤቶች ወጣት መዘምራን በያሬዳዊ ዜማና ዝማሬ፤ ምዕመናን በእልልታና ደማቅ የአምልኮት ስነ-ሥርዓት አሸኛኘትና አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከዋዜማው ጀምሮ ሌሊቱን ሙሉ እስከ በዓሉ ፍጻሜ ድረስ በሊቃውንቱ፣ ካህናቱና ወጣት መዘምራኑ በዓሉን የሚመለከት ያሬዳዊ ማኅሌትና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ዝማሬ ጥልቅ በሆነ መንፈሳዊ ስሜት ሲካሔድ ያደረ ሲሆን ንጋት ላይ በብፁዕ አቡነ እንጦንስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዓባልና የሰ/ምዕ/አውሮፓ /ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተመራው የቅዳሴ ስነ-ሥርዓት ተከናውኗል። ከዚያም ሥርዓተ ጥምቀቱ ተካሒዷል።
በበዓሉ ስነ-ሥርዓት ወቅት በዩናይትድ ኪንግደም የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንጌሎስ፣ የክርስትና ሃይማኖት መሪዎችና የካምደን ከተማ መስተዳደር ከንቲባ (ሜየር) በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን እንግዶቹ በየተራ ባደረጉት አጭር ንግግር ከሌላው ሁሉ ዓለም ልዩ ሆኖ ባገኙት የበዓሉ ስነ-ሥርዓትና የእምነቷ ተከታዮች መንፈሣዊ አገልግሎት በእጅግ መደነቃቸውን ገልፀዋል።


የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጋቤ አእላፍ ተወልደ ገብሩ በስነ-ሥርዓቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር ጥምቀት የክርስትና እምነት የተመሠረተበት፣ የእግዚአብሔር አንድነትና ሦስትነት የተገለፀበት ምስጢር ነው ካሉ በኋላ ኢትዮጵያ ከልደተ ክርስቶስ በፊት የብሉይ ኪዳን እምነትና ሥርዓት በመቀበል ከአምልኮ ባዕድ ርቃ የኖረችና በኋላም የክርስትናን እምነት ቀድመው ከተቀበሉት ጥቂት የዓለም አገሮች አንዷ፣ ከአፍሪካ ደግሞ የመጀመሪያዋ መሆኗን አስታውሰዋል። በዚያች አገር የተመሠረተችው የኢ///ቤተ ክርስቲያንም በአሁኑ ጊዜ ከ፵፭ ሚሊዮን በላይ ምዕመናን፣ ከ፶ በላይ ገዳማት፣ አድባራትና አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፣ ከ፬፻፶ በላይ አገልጋይ ካህናት እንዳሏትም ገልፀዋል።
ያለ /ስብከት አመራር የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በራሳቸው የተሟላ አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሎ እንደማይጠበቅ በንግግራቸው የጠቀሱት ሥራ አስኪያጁ ብፁዕነታቸው በሰጡት መመሪያ መሠረት በአሁኑ ጊዜ አስፈላጊ የሆኑ የአገልግሎት ክፍሎችን በማዋቀርና መንበረ ጵጵስናው በሚገኝበት ለንደን /ቤቱን በመክፈት እንቅስቃሴ መጀመሩን አክለው ገልፀዋል።
በሀ/ስብከቱ አስተባባሪነት እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ታቦቶቻቸውን ይዘው በአንድነት ሲያከብሩ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ከዚህ በኋላ በየዓመቱ የሚፈፀመው የጥምቀትና የመስቀል ስነ-ሥርዓት በዚህ መልኩ በአንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚደረግ መሆኑን /ቤቱ አስታውቋል።
በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ እንጦንስ ቃለ ቡራኬ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ የበዓሉ ስነ-ሥርዓት ተፈጽሟል።
በዚህ ታሪካዊ የጥምቀት በዓል ላይ ከለንደን እና ከሌሎች በአቅራቢያዋ ከሚገኙ ከተሞች የመጡ ከአንድ ሺህ በላይ ምእመናን ተገኝተው በልዩ መንፈሳዊና ብሔራዊ  ስሜት ያከበሩ ሲሆን በዓለ ጥምቀቱን በአንድነት ማክበርመቻላቸውም በእጅጉ ያስደሰታቸው መሆኑንንም ከብዙዎች አስተያየት መረዳት ተችሏል።
በሰ/ምዕ/አውሮፓ ሀ/ስብከት ሥር ዩናይትድ ኪንግደም፣ አየርላንድ ሪፐብሊክ፣ ጀርመን፣ ስዊድን፣ ዴንማርክ፣ ኖርዌይና ፊንላንድ የሚገኙ ሲሆን መንበረ ጵጵስናውም በለንደን ከተማ ነው

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)