January 22, 2012

በደ/ብ/ብ/ክልል በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ጥምቀት በዓል የወጡ ክርስቲያኖች በአክራሪ ሙስሊሞች ጉዳት ደረሰባቸው


(ደጀ ሰላም፣ ጥር 13/2004 ዓ.ም፤ January 22/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ጥር 12/2004 ዓ.ም የቃና ዘገሊላን በዓል ለማክበር በወጣው ምዕመን ላይ የሙስሊም አክራሪ ቡድን የድንጋይ ነዳ በመውርወር ብዙ ክርስቲያኖች ላይ የማቁሰል አደጋ ማድረሳቸውን በአካባቢው የሚገኙ ደጀ ሰላማውያን ሲገልፁ በተመሳሳይ በአዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ የተቀሰቀሰ ተመሳሳይ ግጭት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን “አዲስ ነገር ኦንላይን” ዘግቧል።

ሕዝበ-ክርስቲያኑ በዓሉን በሰላም ለማክበር በማሰብ የቃል-ኪዳኑን ታቦት እያጀበ በታላቅ ምስጋናና ዝማሬ  ከማደርያው ቦታ ሲመልስ በከተማው መሐል ባለው መስጊድ አካባቢ (ኑር መስጊድ) ሲደርስ “በመስገጃ ሰዓታችን ረብሸውናል” በሚል ሰበብ አዳራቸውን የሰው ሐይላቸውን አጠናክረው በመዘጋጀት ድንጋይ፤ የስለት መሳርያዎችን በመጠቀም በመጠበቅ ታቦተ-ህጉ ላይ የድንጋይ ናዳ በመወርወር እንዲሁም ዝበ-ክርስቲያኑን በድንጋይና በጦር በመውርወር ሰፊ የሆነ ጉዳት አድርሰዋል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም የዝበ-ክርስቲያኑን ንብረት በመሰባበር እና በማቃጠል ፤ በየመንደሩ እየዞሩ ከክርስቲያን ወገኖች አንገት ላይ ማተብ የበጠሱ ሲሆን እንዲሁም የፖሊስ ጽ/ቤት ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ በወቅቱ የልዩ ወረዳው አስተዳደር ሁኔታውን ከማረጋጋት ይልቅ የጥፋቱ ተባባሪ በመሆን ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡ የዓይን ታዛቢዎች እንደገለጹት ባለስልጣናቱን ጨምሮ የሙስሊም ፖሊሶች ተባባሪ በመሆን ክርስቲያኑን ሲያስደበድቡና ሲደበድቡ ታይተዋል፡፡
 በከተማው ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ጉዳት ሲያደርስ የነበረው ይህ አክራሪ የሙስሊም ቡድን ያደረሰው ጉዳት አልበቃ ብሎት ሰላማዊና ከክርስቲያን ወገኖቹ ጋር በብረትና በፍቅር እየኖረ ያለውን የገጠሩን ማበረሰብ “ክርስቲያኖች በከተማው ውስጥ ያለንን መስጊዳችንን አፈረሱብን” በሚል የሰት ቅስቀሳ በማድረግ ተቻችሎ እየኖረ ያለውን ዝብ እርስ-በርሱ እንዲጋደል ከፍተኛ ሚና ቢጫወቱም ዝበ-ክርስቲያኑ አፀፌታ ከመመለስ ይልቅ ከአምላኩ የተማረውን ዕንባን ከፀሎት ጋር በማቅረብ  ከዚህ የባሰ ጉዳት እንዳይደርስ እግዚአብሔር ረድቶታል፡፡
መንግሰት የዜጎች የሃይማኖት ነፃነት እንዲከበር እንዲሁም ሁሉም ሃይማኖቶች በእኩልነት፣ በመቻቻልና በመከባበር እንዲኖሩ በሚያደረግበት ሰዓት የወረዳው አስተዳደር ጉዳዩ ወደ ከፍተኛ ዕልቂት እንዳይደርስ መከላከል ሲችል ከሕዝብ የተሰጠውን ታላቅ ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው  የቡድኑ አባላትን በማገዝ ህዝበ-ክርስቲያኑን ማስደብደባቸው መንግስት የሰጣቸውን የህዝብ አደራ አለመወጣታቸውን  የሚያረጋግጥ እና እንዲሁም በሕግ የሚያስጠይቅ ሲሆን ለሙስሊሙ አክራሪ ቡድን አባላት ሽፋን መስጠታቸውና በቀጥታ ተሳታፊ መሆናቸው ከተፈጠረው ጉዳት ጋር መጠየቅ እንዳለባቸው ህዝበ-ክርስቲያኑ በምሬትና በዕንባ ገልጸዋል ሲል ከአካባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡
በተያያዘ ዜና ዓመታዊውን የጥምቀት በዓል ለማክበርና ታቦት ለማስገባት መርካቶ ራጉኤል ቤተክርስቲያን አካባቢን ሲያጸዱ የነበሩ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ምእመናን እና የዓርብ (ጁምዓ) ጸሎትና ስግደት ለማድረግ አንዋር መስጊድ የተሰባሰቡ ሙስሊም ወጣቶች መጋጨታቸውን፣ በቦታው ይገኙ የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላትም ወዲያው  ኃይል ጨምረው ሁኔታውን ወደ ከፋ ግጭት ሳያመራ መቆጣጠራቸውን “አዲስ ነገር ኦንላይን” (የጋዜጣው የፌስቡክ ገጽ) ዘግቧል፡፡
በመርካቶ አካባቢ የሚገኙ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች በየዓመቱ ጥር 10 ቀን ተሲያት በኋላ የቅዱስ ራጉኤል ታቦትን አጅበው በአስፋ ወሰን ሆቴል በኩል በተለምዶ በአራተኛ ፖሊስ ጣቢያ አድርጎ በአቡቶቡስ ተራ እና በኳስ ሜዳ፣ በአበበ ቢቂላ ስታዲዮም ጎን በሚገኘው ጥምቀተ ባህር ሜዳ ያርፋል። ከአንድ ቀን በኋላ ጥር 11 ቀን ተመልሶ ወደ ቤተክርስቲያኑ ቅጥር ጊቢ የሚገባው በወጣበት በኩል ሳይሆን በንግድ ባንክ ቁጭራ ባንክ ቅርንጫፍ አድርጎ በራጉኤል ቤተክርስቲያንና በአንዋር መስጊድ አካፋይ መንገድ አቅራቢያ ባለው የቤተክርስቲያኑ በር በኩል ነው፡፡
እንደተለመደው ዓርብ ጥር 11 ቀደም ብለው ታቦት ለመቀበል የቤተክርስቲያኑንና የአካባቢውን ጽዳትና የአስፋልት እጥበት ሲያከናውኑ የነበሩየኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችማኅበረ ምእመናንከአንዋር መስጊድ አቅራቢያ የመጡ ሙስሊም ወጣቶች እኛ የዓርብ (የጁምዓ) ጸሎትና ስግደት ስለምናደርግበት አስፋልቱን አሁን አትጠቡት በሚል ክርክር ወደ ጸብ የገቡ ሲሆን የቃላት ልውውጡ ወደ ሁከት እንደተቀየረ በአካባቢው የነበሩት የአዲስ አበባ ፖሊሶች ሁኔታውን ለመቆጣጠር ሞክረው ከቁጥጥራቸው ውጪ መሆኑን ሲረዱ ከአራተኛ ፖሊስ ጣቢያ የፖሊስ ኃይል በማስጨመር ሁኔታውን ወደ ከፋ ግጭት ሳይቀየር ለመቆጣጠር መቻላቸው ተዘግቧል።
 ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጭራ ባንክ ቅርንጫፍ አካባቢ ሙስሊም ወጣቶች እንዲርቁና ወደ አንዋር መስጊድ እንዲያመሩ ያደረጉት የአዲስ አበባ ፖሊሶች ምዕመናንኑም አስፋልት ማጠቡንና አካባቢውን ማስዋብ ለጊዜው እንዲያቆሙና ከዓርብ የሙስሊሞች ስግደት በኋላ ማከናወን እንደሚችሉ በመንገርና በአካባቢው ላይ በፓትሮል መኪና በርካታ ፖሊሶችን ጭነው በመዘዋወርና በመቃኘት ሁኔታውን ለማለዘብ ሞክረዋል፡፡
 ፖሊሶቹ ከአንዋር መስጊድ ኢማሞች ጋር በመነጋገርም የሙስሊም ወጣቶች ከራጉኤልና ከቁጭራ ባንክ አካባቢው በቡድን እንዳይንቀሳቀሱ በማድረግ በምትካቸው አካባቢውን ከፖሊሶችና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አባቶች ጋር በመተባበር በሰላማዊ መንገድ ለዓርብ ስግደት የመጡ ሙስሊሞችን እንዲያስተናግዱየቁርዓንና የስፍ ኻዲሞችየሚል ጽሑፍ ያለበት ነጭ ቶብ እና የሙስሊም ቆብ ያደረጉ ጎልማሳ ሙስሊም አባቶችን እንዲሰማሩ አድርገዋል፡፡

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)