January 19, 2012

አርዕስተ ዜና፦ የኩሪፍቱ ሪዞርት እና ስፓ የባቦ ጋያ መድኃኔዓለም ባሕረ ጥምቀት እና መስቀል ደመራ ቦታ “የይዞታ ባለመብት ነኝ” እያለ ነው

(ደጀ ሰላም፣ ጥር 10/2004 ዓ.ም፤ January 19/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF.
  • የኩሪፍቱ ሪዞርት እና ስፓ ሥራ አስኪያጅ የሆኑትና “ውል ተቀባይ ናቸው” የተባሉት አቶ ታዴዎስ ጌታቸው “የደብሩ የልማት ኮሚቴ ተጠሪ” ናቸው፤ ከባሕረ ጥምቀቱ እና መስቀል ደመራው አጠቃላይ 13,020 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ለሪዞርቱ ማስፋፊያ በሚል በሊዝ የወሰዱትን 11,000 ካሬ ሜትር መሬት በድርጅታቸው ስም ካርታ እና ፕላን በቢሾፍቱ ማዘጋጃ ቤት አሠርተውለታል፡፡ በምትኩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሓላፊነት ሥር ለሚቋቋም ሙዓለ ሕፃናት፣ ክሊኒክ፣ ዳቦ ቤት፣ ወፍጮ. . . መሥሪያ ወጪ በወሰዱት የማስፋፊያ ቦታ ላይ ግንባታ አጠናቀውና በይፋ ሥራ ጀምረው ጥቅም ማግኘት ከጀመሩበት ወር አንሥቶ በየወሩ ብር 20,000 “በግል ፈቃደኛነት እና በበጎ ፈቃድ ለመስጠት ተስማምተዋል”
  • የሪዞርቱ ባለቤት ቦታውን በሊዝ ወስዶ በይዞታ ባለቤትነት እንዲጠቀምበት ውል የተዋዋሉት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ የማነ ብርሃን ታደሰ፣ ምክትል ሊቀ መንበሩ አቶ መኰንን ግሩም፣ ጸሐፊው መዘምር ገብረ ሕይወት ዋለልኝ ናቸው፤ ውሉን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አጽድቀዋል፡፡ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ከተመረጠ ስምንት ዓመታት ያለፉ ሲሆን የኦዲት ይሁን ሌሎች የሥራ ሪፖርቶችን አቅርቦ አያውቅም፡፡ በምእመኑ በአዲስ መልክ የመረጣቸውን የሰበካ ጉባኤ አባላት ሀገረ ስብከቱ መካተት ይገባቸዋል በሚላቸው የቀድሞው ሰበካ ጉባኤ አንዳንድ አባላት ምክንያት አላጸድቅም ብሏል፡፡ የካህናቱ ደመወዝ በምእመኑ እና በጎ አድራጊዎች ርዳታ ነው የሚሸፈነው፡፡
  • በውል ሰጪው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ እና በውል ተቀባዩ የሪዞርት እና ስፓ ሥራ አስኪያጁ መካከል ተደረሰ የተባለውን ስምምነት ከይዞታው ቆርሶ ለቤተ ክርስቲያን መሥሪያ፣ ለመካነ መቃብር፣ ለባሕረ ጥምቀት እና መስቀል ደመራ በዓላት ማክበሪያ ከሰጠው ምእመን የተሰወረ ነው
  • ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ “እጃችሁን ተይዛችሁ እስር ቤት ትገባላችሁ” በሚል በካህናቱ እና ምእመናኑ በተቋቋመው የይዞታ አስመላሽ ኮሚቴ አባላት ላይ እየዛቱ ነው፤ ለሦስት ቀንም ያሳሰሯቸው የይዞታ አስመላሽ ኮሚቴ አባላትም አሉ፡፡ “ይዞታችንን አሳልፎ የሚሰጥ አባት የለንም” ያሉት ምእመናኑ በበኩላቸው የባሕረ ጥምቀት ይዞታቸው እንዲከበር፣ እስከዚያው ድረስ የዛሬውን በዓል የሚያከበሩበት ጊዜያዊ ቦታ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል
  • ውዝግቡ እልባት እስኪሰጠው ድረስ የደብሩ ካህናት እና ምእመናን የጥምቀት በዓልን የሚያከብሩበት እንዲመቻችላቸው ጥር 3 ቀን 2004 ዓ.ም “በስልክ ለሥራ አስኪያጁ በመደወል አሳስበዋል” ቢባልም የይዞታ አስመላሽ ኮሚቴ አባላቱ የቅዱስነታቸው አባታዊ መምሪያ እንዳልተከበረ አስታውቀዋል፤ አቡነ ጳውሎስ የኩሪፍቱ ሪዞርት እና ስፓ የክብር አባል(VIP) መሆናቸው የተዘገበ ሲሆን ከሥራ አስኪያጁ ጋራ ባደረጉት የስልክ ልውውጥ ይኸው ‹ወዳጅነታቸው› እንደ ቀጠለ መሆኑን የሚያሳብቁ ልውውጦችን አድርገዋል ተብሏል
  • በ6410 ሜትር ካሬ ስፋት ላይ የሰፈረው የኩሪፍቱ ሪዞርት እና ስፓ ከአዲስ አበባ 50 ኪ.ሜ ላይ የሚገኝ ሲሆን ዘመናዊ እና ውድ የመዝናኛ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በሪዞርቱ ለአንድ ቀን የመኝታ አዳር ብቻ እንደ የደረጃው በትንሹ ከ150 የአሜሪካን ዶላር ያላነሰ ይከፈልበታል፡፡ አባላት በየዓመቱ ከብር 3000 ያላነሱ የሚከፍሉ ሲሆኑ በመኝታ፣ ማሳጅ፣ ሳውና፣ ፀጉር ሥራ፣ ጃኩዚ እና ሌሎችም አገልግሎቶች ላይ የ25 በመቶ ቅናሽ ያገኛሉ፡፡

12 comments:

Anonymous said...

ኩሪፍቱ የአቶ ታዲዮስ ሳይሆን የነ አቶ መለስና የነ አባ ጳውሌ ንብረት ነው :: ታዲዮስ ቅጥረኛ ጉዳይ አስፈጻሚ ኢንቨስተር መሳይ / ማስክ /ነው :: አባ ጳውሎስ ባለቤት እንጅ የክብር አባል አይደሉም ስለዚህ ታዲዮስ የታዘዘውን ነው የሚሰራው እንጅ እሱ በምንም አይነት ሁኔታ የቤተክርስቲያንን ይዞታ ለመውሰድ አይደፍርም የቤተክርስቲያኗን ንብረት እንደፈለጉ የሚያደርጉት ማን እንደሆኑ ይታወቃል::
አባ ጳውሎስ

Anonymous said...

ቤተክርስቲያኗ የባለሃብቱ ናት ወይስ ባለሃብቱ የቤተክርስቲያኗ ናቸው??????????????

Anonymous said...

አቶ ታዲዮስ
ከመዳህኒአለም ቤተክርስቲያን ጋር የተጀመረው አላገባብ የመበልፀግ ሙከራ መጨረሻው ሞት ነው መቸም ገንዘብን በቃኝ የሚል በጠፋበት ዘመን ያሉ ሰው ቢሆኑም ከወያኔ ጋር የጀመሩት አላገባብ የመበልፀግ ትግልና በኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት የመባለግ ህይወት ቢያስተውሉት የሚዘገንን ነው :: ያም አልበቃ ብሎወት በድፍረት የእግዚአብሄር የሚመለክበትና የክብሩ መግለጫ የሆነውን የባሕረ ጥምቀቱ እና መስቀል ደመራ ቦታውን 11,000 ካሬ ሜትር መሬት በስምዋ ካርታ እና ፕላን ማውጣት አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች አይነት ስለሆነ የእግዚአብሄርን ለእግዚአብሄር ይመልሱ ::
እባክወትን በመዳህኒአለም ይለመኑን እስቲ የያዙትን ይብሉት::

Anonymous said...

አቶ ታዲዮስ
ከመዳህኒአለም ቤተክርስቲያን ጋር የተጀመረው አላገባብ የመበልፀግ ሙከራ መጨረሻው ሞት ነው መቸም ገንዘብን በቃኝ የሚል በጠፋበት ዘመን ያሉ ሰው ቢሆኑም ከወያኔ ጋር የጀመሩት አላገባብ የመበልፀግ ትግልና በኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት የመባለግ ህይወት ቢያስተውሉት የሚዘገንን ነው :: ያም አልበቃ ብሎወት በድፍረት የእግዚአብሄር የሚመለክበትና የክብሩ መግለጫ የሆነውን የባሕረ ጥምቀቱ እና መስቀል ደመራ ቦታውን 11,000 ካሬ ሜትር መሬት በስምዋ ካርታ እና ፕላን ማውጣት አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች አይነት ስለሆነ የእግዚአብሄርን ለእግዚአብሄር ይመልሱ ::
እባክወትን በመዳህኒአለም ይለመኑን እስቲ የያዙትን ይብሉት::

Anonymous said...

ቤተክርስቲያኗ የባለሃብቱ ናት ወይስ ባለሃብቱ የቤተክርስቲያኗ ናቸው??????????????

Anonymous said...

ቤተክርስቲያኗ የባለሃብቱ ናት ወይስ ባለሃብቱ የቤተክርስቲያኗ ናቸው??????????????

Anonymous said...

ቤተክርስቲያኗ የባለሃብቱ ናት ወይስ ባለሃብቱ የቤተክርስቲያኗ ናቸው??????????????

Anonymous said...

ቤተክርስቲያኗ የባለሃብቱ ናት ወይስ ባለሃብቱ የቤተክርስቲያኗ ናቸው??????????????

Anonymous said...

Why we Ethiopian kept silent when this woyanne lead patriarch ruining our church, look at the Muslim, they are fighting, we should not keep silent when they are fighting for their right. this issue is also ours. It is woyanne backed Paulos who are ruining our church. Please let us wake up and say no to paulos and woyanne!!!!!

Anonymous said...

ቤተ ክርስቲያናችን ጥቃት በዛባት::
አክራሪ እስላሞች ቅድስት ቤተክርስቲያንን አፈረሱ አቃጠሉ ክርስቲያኖችንም አርደው ገደሉ ማንም የጠየቃቸው የለም በቁማችንም ማተባችሁንን ካልበጠስን እያሉ ብዙ መከራን አበዙብን እንግዲህ ምን እናድርግ ክርስቲያኖቸ ወንድሞቸና እህቶቸ ያሁኑ ይባስ ቤተ ክርስቲያናችን በእስላሞች የምትጠቃው አንሶ በራሳችን ሰወች ስትደፈር ምንድን ነው ማደረግ ያለብን? ቁጭ ብለን በረጋ መንፈስ መነጋገር ያለብን ይመስለኛል:: ለባለጊዜ ነጋዴዎች ለሞስሊሞቹም ሆነ ለለምድ ለባሺ ተኩላወች የማያወላዳ መልስ የምንሰጥበት ጊዜው ዛሬ ነው::
በጣም በዛ የቤተክርስቲያንን ንውያተ ቅድሳት እየዘረፉ የሚነገዱት አንሶ ራሷን ቤተክርስቲያኗን ሲወርሱን ምንድነው የምንጠብቀው በእውነቱ ይህን ጉዳይ የምናልፈው አይሆንም በሰከነ መንፈስ ተነጋግረን መቋጫ እንሰራለታለን ደፋር ነጋዴ ከሀዲያንና አላውላን ነገስታት ሁሉም መስመራቸውን ይይዛል:: ቤተ ክርስቲያናችንም አበው እንዳስረከቡን ተከብራ ትኖራለች :: የምናመልከውም ጣአት ሳይሆን ህያው ሀያል አምላክ መሆኑን ያያሉ::
እግዚአብሄር አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን አገራችንንና ቤተክርስቲያናችንን በችርቻሮ ከመሸጥ ይጠብቅልን::
አሜን!!!!

Anonymous said...

we should do something time is up!!!!!!!!!!!

lele said...

AMELAKA KEDOSANE LABATOCHCHEN LEBE SETELENE,

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)