January 18, 2012

መ/ር ዘመድኩን የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍ/ቤት አቀረበ


·    የመከላከያ ምስክሮች ተሟልተው አልቀረቡም::
·     የችሎቱ ሂደት የሚዲያዎችን ቀልብ ስቧል::
(ደጀ ሰላም፣ ጥር 8/2004 ዓ.ም፤ January 17/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ አርማጌዶን ቪሲዲ የስም ማጥፋት ወንጀል የተከሰሰሰው መ/ር ዘመድኩን በቀለ 20 ገጽ የሰነድ ማስረጃዎችን ለፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት አቀረበ፤ ተከሳሹ ለዛሬ፣ ጥር 8 ቀን 2004 ዓ.ም ቀርበው እንዲሰሙ ከቆጠራቸው አራት ምስክሮች መካከል ሦስቱ በተለያየ ምክንያት ባለመገኘታቸው ለጥር 18 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በኋላ በ8፡00 ሰዓት በተከሳሽ በኩል በሚደርሳቸው መጥሪያ አማካይነት ይህም ካልሆነ በሕግ አስገዳጅነት ታስረው እንዲቀርቡ ሲል ፍ/ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

ዛሬ ከቀትር በኋላ በ8፡00 ከጠበቃው ጋራ የቀረበው ተከሳሽ መ/ር ዘመድኩን ታኅሣሥ 19 ቀን በነበረው ችሎት ያልተገኘው በወላጅ እናቱ ሞት በደረሰበት ኀዘን ምክንያት ስለመሆኑ የሚያሳዩ ማስረጃዎችን እንዲያቀርብ በቀደመው ችሎት በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት÷ ወላጅ እናቱ ለሕክምና የገቡበት ደደር ሆስፒታል እንዲሁም ቀብራቸው የተፈጸመበት የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ቆሬ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ጽ/ቤት የተጻፉትን ደብዳቤዎች እንዲሁም እንደ ዙር ዐምባ ካሉ ታላላቅ ገዳማት የተላኩለትን የማጽናኛ መልእክቶች ለችሎቱ አቅርቧል፡፡ የቀረቡት ማስረጃዎች ከበቂ በላይ መሆናቸውን ያስረዱት ዳኛው ተከሳሹ መ/ር ዘመድኩን ለዋስትና ያስያዙት ገንዘብ እንደሚጠበቅላቸው አስታውቀዋል፡፡
በተከሳሽ ጠበቃ ለችሎት ከቀረቡት 20 ገጽ የሰነድ ማስረጃዎች መካከል ‹‹በአርማጌዶን ቪሲዲ መልካም ስሜ ጠፍቷል፤ ከሕዝቡ ልብ እንድወጣ ተደርጓል›› በሚል ክስ ያቀረበው በጋሻው ደሳለኝ እና ለምስክርነት የቆጠራቸው ታሪኩ አበራ፣ ናትናኤል ታምራት እና መናፍቁ አሰግድ ሣህሉ ከሕገ ወጥ ሰባክያን እና የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች መካከል እንደሚገኙበት የሚያስረዱ፣ ከዚህም የተነሣ የቅዱስ ሲኖዶስ መምሪያ የደረሳቸው አህጉረ ስብከት እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን መመሪያውን በአፈጻጸም ለማስከበር ስም እየጠቀሱ በተናጠል እና በቡድን ያወጧቸውን የእግድ እና ትእዛዝ ደብዳቤዎች፣ ለመንግሥት አካላት ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ይገ ኙበታል፡፡
መ/ር ዘመድኩን ከቆጠራቸው አራት ምስክሮች ከአንዱ በቀር ሦስቱ በዛሬው የችሎቱ ውሎ አልተገኙም፤ ለዚህም በተከሳሽ በኩል በቃል እንጂ በጽሑፍ የደረሳቸው የፍ/ቤት መጥሪያ ባለመኖሩ እንደ ምክንያት የተጠቀሰ ቢሆንም ችሎቱ ከተጀመረበት(8፡00 ጀምሮ) ዳኛው ሌሎች መዝገቦችን በጣልቃ እየተመለከቱ ምስክሮቹ በሰዓቱ ደርሰው የመከላከያ ምስክርነታቸውን ይሰጡ ዘንድ በተከሳሽ እና በጠበቃቸው አማካይነት ጥረት እንዲደረግ ሰፊ ዕድል መስጠታቸውን ታዝበ ናል፡፡ በዚህም መሠረት መ/ር ዘመድኩንና ጠበቃቸው ከችሎቱ ውጭ ለምስክሮቻቸው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደርጉም የአንዳቸውም ስልክ ጥሪውን የሚመልስ ባለመሆኑ ምስክሮቹ በቀጠሮው በአካል ቀርበው አልተሰሙም፡፡
በምስክሮቹ አለመቅረብ ምክንያት በመጀመሪያ ላይ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩ ሆነ ተብሎ ጉዳዩን ለማጓተት የሚደረግ ሙከራ በመሆኑ ችሎቱ እስከ ዛሬ በተመለከተው መጠን ውሳኔ እንዲሰጥ የጠየቀ ሲሆን በተፈጠረው አጋጣሚ ብስጭት የገባቸው መ/ር ዘመድኩንና ጠበቃው ችሎቱን ይቅርታ በመጠየቅ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው አመልክተዋል፡፡ ሁኔታው ልባቸውን ያራራቸው የሚመስሉት ዐቃቤ ሕጉ ከቆይታ በኋላ በሰጡት አስተያየት የተከሳሽ የመከላከል መብት ጠቦ እንዳይወሰን ዕድል መስጠት እንደሚገባ በመናገራቸው ዳኛው በነገው ዕለት ተከሳሽ ለመከላከያ ምስክሮቹ የፍ/ቤት መጥሪያ እንዲያደርሳቸው፣ ለጥር 18 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በኋላ በ8፡00 እንዲቀርቡም ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡
የመከላከያ ምስክሮቹ በጊዜ ቀጠሮው አለመገኘት ቀጥተኛ ባለጉዳዮቹን ብቻ ሳይሆን በችሎት የተገኙትን ተከታታዮች እና የችሎት ሠራተኞች ሲያስጨንቅ የታየ ሲሆን የሚዲያ ዘጋቢዎችን ቀልብም ስቧል፤ ለመ/ር ዘመድኩን ምክር እና ማበረታቻ የሚሰጡም ነበሩበት፡፡ 

4 comments:

Bekalu hawassa said...

Dingel maryam atleyih

Anonymous said...

ewenet kante gara nech netsa tewetaleh ayzohe. menafikan ena aba pawelos ende endehonu aykerem egziabher yet hedo! Cher were yaseman .Amen!!

Anonymous said...

Most of us believe Zemedkun deserves fair justice. However it is hard to trust the justice system in Ethiopis right now. I mean who knows! money talks.

One thing is for sure. Amlak yiferdal!!!!

lele said...

Egezeabehare YATSENAHE,YAKORETE KANE LEJE

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)