January 3, 2012

ሰበር ዜና - ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ


  • READ THIS ARTICLE IN PDF.
  • በየአህጉረ ስብከቱ ለሚፈጠሩት ችግሮች የአቡነ ጳውሎስ ግፊት እንዳለበት ቅዱስ ሲኖዶስ ገለጸ
  • አስቸኳይና ድንገተኛ ስብሰባ የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ፓትርያርኩ ያቀረቧቸው አጀንዳዎች “ለአስቸኳይ ስብሰባ የማይበቁ ናቸው” በሚል አጣጥሏቸዋል::
  • በፓትርያርኩ እልከኝነትና ተንኮል ላይ ያመረሩት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት “የቤቱ ችግር ተጣርቶ መወገዝ ያለበት ይወገዝ፤ ስለ ወንጌል አገልግሎት፣ መልካም አስተዳደር፣ ሰላም እና ልማት መነጋገር ሲገባን ቤተ ክርስቲያን በእርስዎ የተነሣ ስትበጠበጥ እና ስትናጥ መኖር የለባትም” በሚል አቡነ ጳውሎስን ሲገጹ እና ሲያስጠነቅቁ አርፍደዋል::
  • ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከሲዳማና ጌዲኦ ዞኖች አማሮና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት እንዲነሡ ‹በ15,000 ምእመናን ፊርማ› ቀርቧል የተባለው ‹አቤቱታ› ስድነት የተሞላበትና በአቡነ ጳውሎስ ግፊት የቀረበ የተሐድሶ መናፍቃን ሤራ መሆኑን ሲኖዶሱ ገልጧል፡፡ በሕገ ወጥ አድመኞች የቀረበውን ይህንኑ ስድ አቤቱታ በመቃወም 20,000 የሐዋሳ እና ዲላ ምእመና ያሰባሰቡት የተቃውሞ ፊርማ አቤቱታ ለሲኖዶሱ ጽ/ቤት ደርሷል::
  • አቡነ ጳውሎስ “ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም” የሚለውን ስመ ማዕርጋቸውን በመጠቀም በአኵስም ሀገረ ስብከት ላይ ሥልጣናቸውን የሚያጠናክር አጀንዳ አቅርበዋል፡፡ አጀንዳው አቡነ ጳውሎስ አስገነባዋለሁ ከሚሉት ሙዚዬም አገልግሎት ጋራ በተያያዘ አጠያያቂ ገጽታዎች እንዳሉበት ተነግሯል::
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 24/2004 ዓ.ም፤ January 3/2012)፦ አስቸኳይ ስብሰባ የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ታኅሣሥ 23 ቀን 2004 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡ የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች እንዳስታወቁት አስቸኳዩን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የጠሩት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ናቸው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ እና ድንገተኛ ስብሰባ ለመጥራት መንሥኤ የሆኑት አጀንዳዎች ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው “አቡነ ገብርኤል ከሲዳማና ጌዲኦ ዞኖች አማሮና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስነት እንዲነሡ 15,000 ያህል ምእመናን የተቃውሞ ፊርማ አቅርበዋል” መባሉ ነው፡፡
ሁለተኛው አጀንዳ ደግሞ በረጅሙ ስመ ማዕርጋቸው ውስጥ “ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም” የሚለውን ሥልጣናቸውን የሚያጠናክር እንደሆነ የተነገረለት ነው፡፡ ይኸውም በአሁኑ ወቅት የትግራይ ማእከላዊ ዞን አኵስም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብፁዕ አቡነ ሰላማን ከሀገረ ስብከቱ በማንሣት አልያም በገጠር ደረጃ በመወሰን እርሳቸው በሀገረ ስብከቱ ቀጥተኛ ቁጥጥር እንዲኖራቸው የሚጠይቅ ነው፡፡ በጸሎታቸውና ፍጹም መንፈሳዊነታቸው የሚታወቁት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሰላማ “እኔ ቆሞስ ልሆን ነው ወይስ ወዴት ልሄድ ነው?” በማለት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አጀንዳ ማዘናቸው ተገልጧል፤ አዘውትረው በሚለዩበት “ይግባኝ ለታቦተ ጽዮን” በተሰኘው የተግሣጽ እና የአረኅርኆ ቃላቸው ጉዳዩን አብልጠው ‹እንደሚያመለክቱበትም› ተገምቷል፡፡
በሌላ በኩል አጀንዳው አቡነ ጳውሎስ አስገነባዋለሁ ከሚሉት ሙዚዬም ጋራ በተያያዘ ከአንድ የውጭ ኤጀንሲና ከሕገ ቤተ ክርስቲያን በተፃራሪ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅና በአሜሪካ ካቋቋሙት የውጭ ግንኙነት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተጠሪ ጋራ በወል ለማሰባሰብ ላቀዱት የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ‹ሁኔታዎችን ለማስመቸት› እንደ ሆነ ተጠርጥሯል (ለዚህ ጥርጣሬ መነሻ የሆነውን መረጃ ዝርዝር እንደ ደረሰን እናቀርባለን)፡፡
በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 14 ንኡስ አንቀጽ 1 እንደተመለከተው ፓትርያርኩ ከተሾመበት ቀን ጀምሮ በመላዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚጠራበት የማዕርግ ስምና መንበር “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ እገሌ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት” የሚል ብቻ እንደሆነ ተደንግጓል፡፡ ያለ ኤጲስ ቆጶስ (ሊቀ ጳጳስ) የሚመራ ሀገረ ስብከት እንደማይኖር በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የተመለከተ ሲሆን ኤጲስ ቆጶስ (ሊቀ ጳጳስ) አንዴ ከተሾመበት ሀገረ ስብከት ሊዛወር እንደማይችል፣ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በዕድገት ወይም በሌላ ሥራ ምክንያት እንዲዛወር አስፈላጊ ከሆነ ወይም በተመደበበት ቦታ ለመቆየት አስቸጋሪ ሆኖ ከተገኘ በቅዱስ ሲኖዶስ ተጠንቶ በውሳኔ ሊዛወር እንደሚችል በአንቀጽ 22 ከንኡስ አንቀጽ 1 - 3 ላይ ተደንግጓል፡፡
ሁለቱም አጀንዳዎች ሲኖዶሱን ለድንገተኛ የስብሰባ ጥሪ የማያደርሱ መሆናቸውን የተቹት የአስቸኳዩ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተሳታፊዎች÷ “በአስቸኳይ መነጋገር ካለብን መነጋገር ያለብን እርስዎን በተመለከተ ነው፤ ያቀረቡት አጀንዳ ሆነ ተብሎ ግጭት ለመፍጠር የታሰበበት ነው፤ ይህንንም የሚያደርጉት እርስዎ ነዎት፤ ከጀርባውም የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ አለበት፤ ቤቱም ድጋፍ እየሰጠበት ነው፤ ስለ ወንጌል አገልግሎት፣ ገዳማት ልማት፣ ሰላም እና መልካም አስተዳደር መነጋገር ሲገባን ሁልጊዜ በዚህ መቸገር አለብን? ጥለን ወደ ገዳም እንሂድ እንዴ? ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜ መበጥበጥ ሁልጊዜ መናጥ አይገባትም፤ ነገሩ የሃይማኖትም ጉዳይ ስላለበት ከቤቱ ጀምሮ ተጣርቶ፣ ተለይቶ መወገዝ ያለበት ይወገዝ!!” በማለት በፓትርያርኩ የማያባራ እልክ እና ተንኮል መማረራቸውን በመግለጽ ቁርጥ ማሳሰቢያቸውን አስታውቀዋቸዋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶሱ ሁለቱንም አጀንዳዎች አጣርቶ እና አጥንቶ ለግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚያቀርብ፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የሚመራ የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና ሕግ ባለሞያዎች ኮሚቴ እንዲቋቋም በማዘዝ ለግማሽ ቀን ያካሄደውን አስቸኳይ ስብሰባ አጠናቆ ተነሥቷል፡፡ በተለይም የሲዳሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል እንዲነሡ ቀርቧል የተባለው የ15,000 ሕዝብ የፊርማ አቤቱታ ከጀርባው የተሐድሶ መናፍቃኑ ቅስቀሳና ሤራ እንዳለበት አስረግጦ የተናገረው ቅዱስ ሲኖዶስ÷ የሚቋቋመው ኮሚቴ ፈርመዋል የተባሉ ግለሰቦችን ሃይማኖታዊ ማንነት ጭምር በሚገባ እንዲያጣራ ነው ያዘዘው፡፡ በስብሰባው ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በበኩላቸው እርሳቸውም የሕገ ወጥ አድመኞቹን ሤራ የሚቃወም የ20,000 ምእመናን ፊርማ መያዛቸውን በማስታወቅ እንደተባለው ችግሩ ያለው በቤቱ [በዚያው በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ከፓትርያርኩ ዘንድ] በመሆኑ ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ችግሩ በቁርጥ እንዲለይለት በአጽንዖት ጠይቀዋል፡፡ ይኸው የ20,000 ምእመናን የተቃውሞ ፊርማ ከሐዋሳ እና ዲላ ከተሞች ምእመናን የተሰበሰበ ሲሆን ከአስቸኳዩ ስብሰባ ቀደም ብሎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ደርሶ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡
በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተከታታይ ዘገባዎቻችን እንዳስታወቅነው “አስቸኳይ እና ድንገተኛ ነው” የተባለው ይኸው አጀንዳ በርግጥም በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ወቅት ርእሰ መንበር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በተደጋጋሚ አቅርበውት በምልአተ ጉባኤው አባላት ውድቅ የተደረገባቸው ነው፡፡ አጀንዳው የተገፋበት መነሻ በጥቅምቱ ምልአተ ጉባኤ ዋዜማ በመናፍቁ አሰግድ ሣህሉና ሌሎች የሕገ ወጥ ቡድኑ አባላት አስተባባሪነት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተጠርቶ በነበረው የተቃውሞ ትዕይንት “ከሀገረ ስብከቱ የተለያዩ ከተሞች የመጡ ናቸው” በተባሉ ግለሰቦች እንደቀረበ የተነገረ ጥያቄ ነበር፡፡
ራሳቸው አቡነ ጳውሎስ እንዳነሣሡትና ድጋፍም እንደሰጡበት የተነገረውን ይህንኑ የሕገ ወጦች ጥያቄ ለማቅረብ ወደ አዲስ አበባ መጥተው የታሰሩ አድመኞችን ጉዳይ ለመከታተልና ወደመጡበት ለመመለስ ፓትርያርኩ በልዩ ትእዛዝ ተቀብለው መስተንግዶ ባደረጉላቸው ወይዛዝርት በኩል ዐሥር ሺሕ ብር መስጠታቸው ተዘግቦ ነበር፡፡ በአንጻሩ በወቅቱ የጥቂት ሕገ ወጦችን የተቃውሞ ትዕይንት በፀረ ተቃውሞ ትዕይንት በመመከት 131 የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ምልአተ ጉባኤው በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ላይ ርምጃ እንዲወስድ ላቀረቡት ባለአምስት ነጥብ የአቋም መግለጫ ድጋፍ ለመስጠት በመገኘታቸው “ሁከት በማነሣሣት” በሚል ለእስር ለተዳረጉ ስምንት ወጣቶች አንዳችም ሐዘኔታ አላሳዩም፡፡
ይሁንና የዘንድሮው የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት 13 ቀን 2004 ዓ.ም በፕሮቴስንታንት ድርጅቶች እየተደገፉ ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን በመቀሰጥ እና ምእመኑን በመከፋፈል የጥፋት ተግባር ላይ የተሰማሩ ስምንት ማኅበራትና የሕገ ወጥ ቡድኑ አባላት የሆኑ ግለሰቦችም ኑፋቄ ተመርምሮ እንዲቀርብለት፣ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ዋና ሓላፊ የነበሩት አባ ሰረቀም ከሓላፊነታቸው ተነሥተው እምነታቸው እንዲመረር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ቀደም ሲል አቡነ ጳውሎስ ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገ ወጥ ሰባክያን ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ ለማስፈጸም የተጉትን የሲዳሞ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ዓለም እሸትን ያለ ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ስምምነት ከቦታቸው ለማስነሣት ከወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ጋራ በመመካከር ወደ አዲስ አበባ ለመጣው የጆቢራ ቡድን ብር 5000 ሰጥተው መሸኘታቸው ይታወሳል፡፡
በብፁዕ አቡነ ገብርኤል ላይ “የማይበርድ ቂም” እንዳላቸው በእነ ያሬድ አደመ የተነገረላቸው አቡነ ጳውሎስ በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ብፁዕነታቸውን ከሀገረ ስብከቱ ለማስነሣት በተደጋጋሚ አቅርበውት ውድቅ የተደረገባቸው አጀንዳ አሁንም መሣሪያ ያደረገው በእነ ያሬድ አደመ የተጭበረበረ ቅስቀሳ ተሰብስቧል የተባለውን የ ‹15,000 ምእመናን› የተቃውሞ አቤቱታ ፊርማ ነው፤ የተጭበረበው ፊርማው የተሰበሰበበት ርእሰ ጉዳይም ፈርመዋል የተባሉት ግለሰቦች ማንነትም ነው፡፡
የዜና ምንጮች ከሐዋሳ እንደ ተናገሩት፡- ሕገ ወጦቹ እነ ያሬድ አደመ የአቤቱታ ፊርማው ያሰባሰቡበት የሽፋን ርእሰ ጉዳይ “በሐዋሳ መስቀል አደባባይ ኮንፈረንስ ለማካሄድ ፈቃድ ለመጠየቅ” በሚል የተቀሰቀሰበት ነው፡፡ ቆይቶ ይኸው የአቤቱታ ፊርማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “በሀገረ ስብከታቸው የሉም፤ ከሀገረ ስብከቱ ይነሡልን” የሚል ሆኖ ቀርቧል፡፡ በግለሰብ ቅጽር ውስጥ በተከራዩት አዳራሽ ስብከት እንደሚያካሄዱ የተነገረላቸው ሕገ ወጦቹ እንደ ሰበብ የተጠቀሙበት ብፁዕነታቸው ጥቅምት 20 ቀን 2004 ወደ አሜሪካ ከሄዱ በኋላ ከሀገረ ስብከታቸው ውጭ ለአንድ ወር ያህል መቆየታቸውን ነው ተብሏል፡፡
በእምነት መካከል ያለው የአስተምህሮ ድንበር የማይገዳቸው እነ ያሬድ አደመ ዘረኝነትን በመጠቀም ወንጌልን መነገጃ በማድረግ እና በሌሎች መንገዶች እንዳሰባሰቡት በተነገረው በዚህ የተቃውሞ አቤቱታ ላይ ስማቸው እና ፊርማቸው የተመለከቱት ግለሰቦች በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ ሰበካ ጉባኤ እና ሰንበት ት/ቤት ማጣራት ቢደረግ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ ለመሆናቸው አጠራጣሪ እንደሆነም ነው የሚነገረው፡፡
በአሁኑ ወቅት በሀገረ ስብከቱ የሠርክ ዐውደ ምሕረት ጉባኤያት በምድብ እና ተጋባዥ መምህራን በተጠናከረበት፣ ሰንበት ት/ቤቶች የአገልግሎት መርሐ ግብሮቻቸውን ባጎለበቱበት ሁኔታ ይህ በአድማ የተሰበሰበው የሕገ ወጡ ቡድን ጥያቄ በርግጥም የቤተ ክርስቲያናችንን ውስጣዊ ሰላምና አንድነት የማይሹ የተሐድሶ መናፍቃኑ ሤራ እንዳለበት ግልጽ ያደርገዋል፡፡
መ/ር አእመረ አሸብር
ሰሞኑን በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሃይማኖታቸው ርቱዕነት ላይ ጥያቄ ያነሣባቸው የሊቃውንት ጉባኤ ምክትል ሰብሳቢ መ/ር አእመረ አሸብር (ፎቶውን ይመልከቱ) ወደ ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሓላፊነት መዛወራቸው፣ በሐረር እና ድሬዳዋ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጆችና አቀንቃኞች በአካባቢው የሰነበቱትን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን እንደ ልብ ለማግኘት የቻሉበትን ባለሟልነት፣ በአንጻሩ በሁለቱም አህጉረ ስብከት ሙስናንና ኑፋቄን የሚዋጉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ዐይናችሁ ለአፈር የተባሉበትን መገፋት ስንመለከት አቡነ ጳውሎስን አዘውትረን ከምንገልጽበት የቅንነት ማነስ፣ እልከኛነትና ተንኮል በላይ ጉዳዩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከፋፍሎ የማዳከም ልዩ ተልእኮ እንደ ሆነ በውስጣችን የምናጉላላውን ስጋት በግልጽ እንድንናገረው ያደርገናል፡፡
ከታኅሣሥ 20 - 22 ቀን 2004 ዓ.ም በአሰበ ተፈሪ የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት የተቆጣጠሩት በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዞ የተለየው የ‹ሃይማኖተ አበው› ርዝራዦች የሆኑ ማኅበራት ከፓትርያርኩ ባገኙት ቀጥተኛ ፈቃድ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ ፈቃድ ውጭ የሰበካ ጉባኤያቱን ልዕልና እየተጋፉ በሊቃውንት ጉባኤ ሃይማኖታቸው እየተመረመረ ያሉ ሕገ ወጥ ሰባክያን መድረክ እንዲያገኙና እንዲፋንኑ ማድረጋቸው፤ በሐረር የተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኞች ቀድሞ ይነሡልን ያሏቸውን ብፁዕ አቡነ ያሬድን በማመስገን እንዲቆዩላቸው ለመጠየቅ፣ በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተመደቡትን ብፁዕ አቡነ አብርሃምን በመቃወም እንዳይመጡ ለመከላከል በቅርቡ ለማካሄድ ባቀዱት ጉባኤ ላይ ፓትርያርኩ እንዲገኙላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ አቡነ ጳውሎስን የፀረ ፕሮቴስታንታዊ  ተሐድሶ ተጋድሎ ዋነኛ ዒላማ አድርገን በይፋ እንድንታገላቸው ለማድረግ ከበቂ በላይ የሆኑ ማሳያዎች ናቸው፡፡
ለዚህም ባለፈው ሳምንት እሑድ በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት መካነ ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ አቡነ ያሬድን ለመሸኘት፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ለመቀበል በተከናወነው ደማቅ መርሐ ግብር ላይ ከሁለቱም ብፁዓን አባቶች የተላለፉት መልእክቶች ተስፋ የሚሰጡ ናቸው፤ ምእመኑ በሽኝት-አቀባበሉ መርሐ ግብር ላይ የነበረው ስሜትና ተሳትፎም የሚያበረታታ ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ያሬድ “እኔ ብሄድም ሌላ አባት ቢመጣም ሕግ አይለዋወጥም፤ አባቶቻችን እንዳደረጉት ነው የምናደርገው” በማለት ሐረር የተሐድሶ መናፍቃን የሚደራጁበት መደብር/ቅልዝ መሬት እንዳይሆን የወሰዱት አቋም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስበዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በበኩላቸው፣ “እኔ ውሸት አልፈልግም፤ መርሔ አሳምነኝ ወይ ላሳምነህ የሚል ነው፡፡ መጪው ጊዜ ስለ ሃይማኖታችን አብረን የምንሠራበት፣ የምንነጋገርበት፣ የምንጠብቅበት፣ የምናስጠብቅበት ይሆናል” በማለት የተሐድሶ መናፍቃንንና በአስተዳደራዊ መዋቅሩ የተሰገሰጉ አቀንቃኞቻቸውን ግንባር ለግንባር ለመፋለም መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል፡፡
በአንጻሩ በምዕራብ ሐረርጌ/አሰበ ተፈሪ የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ከኢትዮጵያ ውጭ በመሆናቸውና እስከ አሁን በሀገረ ስብከቱ ባለመገኘታቸው፣ የቀድሞው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ወደተዛወሩበት ወላይታ ሶዶ በመሄዳቸው ሀገረ ስብከቱን በማተራመስ ረጅም ታሪክ ያላቸው የቀድሞዎቹ መናፍቃን ክትያዎች የሆኑ የተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኝ ማኅበራት ከጥቂት ግለሰቦች ጋራ በመተባበር ለሕገ ወጥ ሰባክያን መድረክ እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ ጉዳዩ ከሕገ ወጦቹ ጋራ የዓላማ እና ጥቅም ተጋሪ የሆኑ የአቡነ ጳውሎስ ባለሟሎችና የራሳቸው የፓትርያርኩ መልካም ፈቃድ እንዳለበት ምንጮች ያረጋገጡ ቢሆንም ሀገረ ስብከቱ ያለተከላካይ አባት መቆየቱ አሉታዊ አስተዋፅኦ እንዳደረገም የሚካድ አይደለም፡፡ (የዚህን ዜና ዝርዝር በቆይታ እንመለስበታለን)

22 comments:

Anonymous said...

Ewunet newu Kezih Behala Aba Pawulosin Yeminitagesibet mikiniyat yale ayimesilim. Chigiru Kemeseretu Kaltenekele min tikim yinorewal. Ye Betekiristian Lijoch Hulachin Eniberita. Amilak Hoy Hyilihin Lak Enbelim.

ታዴዎስ said...

"ውሻ ከሔደ ጅብ ጮሀ" እንደሚባለው የአቡነ ፓውሎስ ቤተክርስቲያንን የማዳከም ዓላማ ግብ ከመታ በሁዋላ ለማልቀስ ካልሆነ በቀር ሰውዬው እስካሁን የሠሩት ክፋት ከበቂ በላይ ነበረ::
በተላይም ከተሐዲሶ ጋር በተያያዘ የፓትርያርኩ ጸረ ቤተክርስቲያን መሆናቸው ለምእመናን ሁሉ ግልጽ የሆነበት አጋጣሚ ብሆንም ወደ መፍትሔ መግባት አልተቻለም::
ስለ መፍትሔው ኃላፊነት ያለብን ሰዎች አንድ ባለማለታችን ከተጠያቅነት የሚናመልጥ አይመስለኝም::
እስኪ ተመልከቱ አያምጠውና: ይህችን ቤተክርስቲያን ተሐዲሶዎቹ እንኩዋን ለ2 መክፈል ይቅርና ትንሽ ብቆነጥሩዋት majority የሚሆኑት አሕዛብ ናቸው
አሕዛብ majority ከሆኑ ደግሞ ምን እንደሚከተል የአደባባይ ምሥጢር ስለሆነ ልተወውና
እንግድህ ይህን ከእሳት ጋር መጨወት የመሰለ ነገር ይዘን ነው በየጊዜው የፓትርያርኩን የየዕለት ውሎ እየዘገብን ግን አንዳች መፍትሔ ሳናመጣ እርሳችውና ቡድናቸው ሥራቸውን ሠርተው ከጨረሱ በሁዋላ የማይጠቅም ለቅሶ እንዳናልቅስ እሰጋለሁ::
የተሐዲሶዎቹን በየጊዜው ቤተክርስቲያንን ለመቆጣጠር ያደረጉትን የስልት ለውጥ ስናስብ አሁን ደግሞ በምን ዓይነት አዲስ ስልት እየሠሩ እንደሆነ ምንም የሚናውቀው ነገር የለም::
ካሁኑ ስህተታቸው ተምረው ነገ ዝም ብለው ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ መስለው ከተዘጋጁ በሁላ ጉዳዩን የአስተዳደር ብቻ አስመስለው ቤተክርስቲያን ብከፍሉስ ?
የሕዝቡ ንቃተ ኅሊና ምን ያክል ነው?

"ኢታርእየነ ሙስናሃ ለኢየሩሳሌም" እንዳለ
"ኢታርእየነ ሙስናሃ ለቤተክርስቲያን" የሚንልበት
በተግባርና በጾም በጸሎት መንቀሳቀስ ያለብን ጊዜ ነው::
ወላዲተ አምላክ ከክፉ ትሰውረን::

Anonymous said...

enkuan des alachuh, enkuanim aderegu, yihinie lela tera sew bihon noro yetebalewunim yalitebalewunim sitizebariku tigegnu neber, pawulos sihonu gin tset rechi alachuh sinit mereja endelelew sew, le ewunet yemitiseru bihonima noro yihe hulu gud balimetabin neber, bicha le enanitem gizie ale, endih endehonachuh atikerum, sira kehone sira new, silitan yalewun eyeferu ye ene bitiewun mediresha masatat tiru yimesilachuhal, fithawi sira siru, pawulose mebarer alebachew, yalewun mereja zekizikut, yabetew yifenda ena keriw hizib beselam yinur

ዘ ሐመረ ኖህ said...

ኧረ እባካችሁ አቡነ ፓውሎስ ተዋህዶን በተሃድሶ ለመቀየር በአዋጅ እስኪያስነግሩ ድረስ ዝም ብለን መመልከት የለብንም ለሃይማኖቱ ሟች የሆነው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሰው ሁሉ የት ገባ ምን ዋጠው ምን እስክንደረግ እየጠበቅን ነው እግዚአብሔርን ይዘን ሆ ብለን አስከመጨረሻው መነሳት አለበን

Anonymous said...

መንፈሳዊነት ከቤተክርስቲያናችንና ከሃይማኖት አባቶቻችን ሸሸ ወይስ መንፈሳዊነት ትርጉሙ ተዛባብኝ? ምን የሚያስጨንቅ ዘመን ላይ ደረስን !
እግዚኦ!

Anonymous said...

memhir aemereko ezih south africa metito sile tehadiso astemiron neber. endet new ahun esu litereter yechalew. ene algebagnim.

Kassahun said...

If there will be any uprising in this country, the cause will Abune Paulos. Ethiopia's Government effort for Ethiopia made Ethiopia one of the fastest growing economies in the world. This is a fact proven by international economic institutions such as World Bank and International Monetary Fund. Abune Paulos is contributing towards the deconstruction of this effort. Gobez - sayekatel Beketel.

Anonymous said...

አባ ጳውሎስ ያልተከፈለ እዳ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ከገጠማት አስከፊ ጊዚያቶች አንዱና ዋነኛው ጊዜ አሁን ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም። አባ ጳውሎስ ደግሞ ለፈተናዎቿ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ። እንደ አንድ የቤተ የቤተ ኬሬስቲያን አማኝ ጉዳዩን በመቆርቆርና በጥልቀት ስንመለከተው ፓትርያሪኩ የቤተ ክርስቲያኗን ሁለንተናዊ ክብር ለሃያ አመታት ያህል ማዋረድ ብቻ ሳይሆን እንደጥላትም ተዋግተዋታል ብል ጥላቻ የውለደው ብሂል ሳይሆን እውንት ምሆኑኑን ማሳያ ምክንያቶቼ ይምስክሩልኛል።

1 ምሳሌንታቸው ቅድስና የራቀው አገልጋይ በቤተ ክርስቲያን እንዲበዛ አድርጓል ሊቃንት እንደሚስማሙብት አይደለም ህይውት /ምሳሌነት / ንግግር እንኳን ከመሪ ይወረሳል ይላሉ። ሃዋርያውም እኔ ክርስቶስን እንደመሰልኩ እናተም እኔን ምሰሉ ሲል የሚምራት ቤተክርስቲያን ከንግግሩ ብቻ ሳይሆን ከህይወቱ እንዲማሩ ይመክራቸው ነበር ። በቅዱስ ጳውሎስ ስልጣን የተሰየሙት ፓትርያሪክ ጳውሎስ ግን በእውነቱ በተቀቡት ላይ መፍርዴ ሳይሆን ህይወታቸው ለደቂቃ የሚያስተምር አይደለም ። በቤተ ክርስቲያኗ እየተስፋፋ ያለው የነውር ውጤቶች ሁሉ በህይውቱ የሚያስተምር መንፈሳው መሪ በማጣቱ ነው። የራሱን ቤት እንደሚሰርቅ ክፉ ባለትዳር ሰው የተሾሙባት ቤተኬርስቲያንን ንብረት እንደጠላት ገንዘብ በድቦ የሚዘርፉ ጆቢራዎች የበዙት እርሳቸውና ቤተሰባቸው ክህነትን በገንዘብ ከመሸጥ አንስቶ የቤተ ክርስቲያኗን ገንዘብ ከሌቦች ጋር በመመሳጠር መዝረፋቸው በምታይቱ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በርኩሰት ስራ የተሞሉ አገልጋይ ሳይሆኑ መስለው የሚታዩ አደገኛ ቦዘኔዎች ቤተ ቤተክርስቲያኗን የሞሉት ለቅድስና የማይጨነቁ አለማዊነት ክብራቸው ይሆነ ነውረኞ መብዛታቸው ምስጢሩ ሌላ ሳይሆን አባ እንደ ቄሳሮች ሀውልት እያሰሩ አምልኮት ሁሉ ውዳሴና ቅኔም ክብርና ዝማሬም ለእኔ ብቻ ይሁን በለው በቅድስናው ስፍራ በርኩሰት በመሰየማቸው ነው።

2 ፓትርያሪክ ጳውሎስ የአቃቤ እምነት ተግባር ከማከናወን ይልቅ ለመናፍቃን መፈልፈል ምክንያት ከምሆናቸው በላይ መጠለያ ሆነዋል።
አባ የፕትርክና ሹመቱን በገኙበት እለት በመሃላ ያጸኑትን/ያሰሙትን /ቃል ችላ ብልው ቤተ ክርስቲያኒቱ በአረማውያን በመናፍቃንና በፖለቲከኞች እየደረሱባት ባሉት መከራዎች ሁሉ ለአንድም ቅን ተቆርቁረው ህዝባቸውን ሲያጽናኑ ታይተው አይታውቁም ። ከቤተ ክርስቲያኗ በተገኝው ገንዘብ በሚሊየን ብር በተገዛ መኪና እየንተፈላሰሱ ካህናቷ በመቅደስ ሲታረዱ መናፍቃኑ በጉያዋ ተስግስገው መርዝ ሲረጩ አይተው እንዳላዩ ዝም ይላሉ ከባሰም በዚ አኩሪ ተግባር ላይ የተንቀሳቀሱትን አካላ አካያሳድዳሉ ።

3 አባ ጳውሎስ ጸረ ሊቃውንት አፍቃሬ ቦዘኔ ናቸው። መቼም ከቅድሞ ጀምሮ አባ የማን ውዳጅ ነቡ ተብሎ ሲታወስ ሰውየው በእርግጥም ከሊቃውንት ይልቅ ቦዘኔዎችን ውዳጅ የሚያደርጉ ናቸው። እስቲ ልብ በሉ ከአለቃ አያሌው ይልቅ የድራፍት ቡድን የነበሩትን ዮሐንስ ዋለ በለጠ ይረፉ ተሾመ ገብረ መስቀል ወዳጆቻቸው ነበሩ። ዛሬም ከሊቃውንቱ ይልቅ ምንም ፍሬ የሌላቸውን ባዶ ደመናዎችን እነ ኤልዛቤል ጌታቸው ዶኒን እስንድር ገብረ ክርስቶስ ጸጋዬ ግደይ ሰሎሞን በቀለ እና መሰሎቻቸው ወዳጅ ሆነው ያማክራሉ ያሾማሉ ያሽራሉ ያሳድጋሉ ያዋርዳሉ ያቅብላሉ ይቀበላሉ በስማቸው ምለው ያስፈራራሉ ። እነ ሊቀ ካህናት ክንፈገብርኤል እያሉ የቄስ ኮሊና የኑፋቄ ማህደር የሆነውና በተደጋጋሚ በኑፋቄው ቤተ ክርስቲያንን ያገማውን አዕመረ እሸብርን የሊቃውንት ጉባኤ መሪ አሉ ። ይቀጥላል

Anonymous said...

አይ ....


የኝህ ሰውየ ሞት እንደናፈቀኝ 10 አመት ተቆጠረ :: በውነት የምንገናኝበት ነገር ቢኖር ይችው ቤተክርስትያን ነች (በሃይማኖትማ አንገናኝም እኔ በክርስቶስ ደም በታነጸችው በአንድነት እና በሶስትነት በቆመችው በተዋህዶ,በ እማምላክ አማላጅነት በጻድቃን ሰማእታት ተራዳኢነት የማምን ክርስትያን ነኝ : የሳቸውን አላውቅም ከኔ ጋር ግን እንደማይደመሩ እርግጠና ነኝ ) እና .... ምን አለ የአማኝን ልብ ማሳዘን ያምላካቸውን ልብ ማሳዘን አይደልምን ? አንቱ ሰውየ ወደነዎት ፈልገነዎት መሰለዎት አናት ላይ የተቀመጡት ... ጥሎብን ነው ... ምን ያደርጋል ? አንደ ሰማአት ጠፋ ግንባረዎትን ብሎ የሚገላግልልኝ ... አንድ ቀን እመብርሃን አሽመድምዳ ትጥልልኛለች ... መቸም አሁንም ቢሆን ይሄን ሁሉ በደል ቤተክርስትያን ላይ እያደረሱ እንቅልፍ ተኝተው አያድሩ ....

Anonymous said...

Dejeselam lemin melkam neger lemetsaf atimokirum . This is the time Ethiopia orthodox church need a person who is speaking and listening MELKAM NEGER (bible) deje Selam, EOTC have enough protester (menafikan and others) we want you be different than anti orthodox. Menafikan betekrstianen yesadebalu you did same thing, patriarch ena siltane kihnetun yesadebalu you did same thing Pleas chose your category Anti orthodox or real dejeselam

Anonymous said...

መ/ር አእመረ አሸብር taught me in Mekelle Kesate Birhan, frankly speaking he is knowledgeable, but I was at times not comfortable with what he taught me.

Anonymous said...

Welde Giorgis Eme Amlak HOY!!! yelibachin hazen meche new yemiwegedew? Kiristian mihiret neber yemileminew, ene gin yesewuyewun mot... Amlak hoy melkam eregna siten!

Anonymous said...

@January 3, 2012 12:48 PM
ውድ አንባቢ: @January 3, 2012 12:48 PM ላይ የጻፍከው አስትያየት የቁጭት ይመስላል:: እናም ክርስትና በአርዕያ ስላሤ ለተፈጠረ ሰው ሞትን እንድመኝ ሳይሆን እንድጸልይልት ነው ያስትማረችን:: ምንም እንኳን ጊዜው በጣም በቤተ ክርስቲያን ላይ ፈተና የበዛበት መሆኑ ግልጽ ነው:: አንቱ ጸሐፊም ሲጽፉ ይህን የቤተክርስቲያንን ወቅታዊ ችግር: ፈተና ተመልክትው ሊሆን ይችላል:: ነገር ግን ክርስቲያን እንደሆኑም ገልጸው, ለሰው ሞትን ያውም ሰማዕትነት ሰውን በመግድል ይመጣ ይመስል ሲመኙ ሲሳሉ የክርስትናዎ ትርጉም አልጠፋም? ጠፋ:: የእኛ አባት የድንግል ልጅ ያስተማረን ለሚያሳድዱን እንድጸልይላቸው እንጅ ሞትን እንድንሳልላቸው አይደለም:: እዚህ ላይ ዝም ብለን እንቀምጥ እያልኩ እንዳልሆን እንዲረዱልኝ እወዳልሁ::

ለሁላችንም ስለቤተ ክርስቲያን ዘብ የምንቆምበትን ልብና አእምሮ ይስጠን:: ለእርሳቸውም ለቤተክርስቲያን የሚያስቡበትን ልብ ይስጣቸው:: እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ከተኩላዎች ይታደግልን::

Anonymous said...

አገሬ ሃይማኖቴ እንደዚህ በባእዳን አስተሳሰብ ስትታመስ ማየት ምንኛ ያስከፋል!!! ይህ ትውልድ የተረገመ ነውን? ቤተክርስትያናችንን ለመጠበቅ ወጣቶቻችን እንደዚህ ሲደክሙ አባቶች ከመደገፍና በርቱ ከማለት ፈንታ የችግሩ ጸንሳሽና ደጋፊ መሆናቸው በጣሙን: በጣሙን ያሳዝናል:: ፓትርያርኩ በአባትነታቸው በጣም አክብራቸው ነበር: አሁን አሁን ግን ዲያብሎስን ይመስሉኝ ጀምራል:: እግዚአብሔር አገራችንና ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅልን: እኛ ምን አቅም አለን ባለጊዜዎቹ እነሱ ናቸው::

ዮሐንስ said...

አይ አባት አባት በብልሃት አባት በፍቅር አባት በማተዋል አባት በወንጌል ጥበብ አባት እራሱን የማይገልጥ ተሸንፎ የሚያሸንፍ አንድን የቤተክርስቲያን መዋቅር ቀኖና ትውፊት የማቀይር ማነው ? አንተ ሐረር /ተናገር እና ልወቅህ ማነህ መኑ እዴከ/ የሚለውን መርህ ይዞ ጀግናው የወንጌል ገበሬ እኔ ከምሰራበት አየር ማረፊያ ተነስቶ መታልህ እራስህን ድፋና ተሀድሶነት በሐረር አካባቢ ቅረብ ተነጋገር ለብጽህ አቡነ አብረሀም ሙሉ ጤንነት እግዚአብሔር እንዲያድልልን ቅዱስ ፍቃዱ ይሁን ዮሐንስ

Anonymous said...

EOTC egzihabeher meche endemigobegat alawkem meche sele abatoch melekam seru ymibalewn neger mesmat newu yenafekeg eski GBTAWIYANOCHN temeleketu sele haymanotachew semahet sihonu enji yabatochachewn gude siyanebu aytayem lenegeru yemehmenu dekama lehaymanotu leamlaku yalewu fekere ye ewshet selehone bayehone yehe hulu ateyafi neger balseman Egzihabere bechernetuna bemeheretu dekamachenen yaswegdelen

Anonymous said...

ወይ ጉድድድድድ ከዚህ ቀደም የተቋቋሙት 1ሺህ የሚሆኑ ችግር ፈቺ ኮሚቴዎች ምን ላይ እንደደረሱ ሳይታወቅ ሌላ ኮሚቴ ደግሞ አቋቋሙ? የእስከዛሬዎቹ ኮሚቴዎች እኮ ምን እየሰሩ እንደሆነ እንኳን አናውቅም; የግድ እኔ ልስማ ማለቴ ሳይሆን ውሳኔ ተወስኖባቸው ቢሆን ስራ ላይ ይውሉ ነበር ብዬ ስለማስብ ነው:: አሁንስ በጣም ከማናደድ አልፎ ጨዋታ እየመሰለ ስለሄደ ያስቀኝ ጀምሯል:: እርሱ መድሐኔዓለም አንድ ይበለን እንጂ ምን ይባላል ትዕግስቱን ይስጠና እንግዲህ::

Ameha said...

ይቅርታ፡ይደረግልኝና፡አበው፡አንድ፡አባባል፡አላቸው። "አባት፡ሁሉ፡አባት፡አይደለም፤ አንዳንዱ፡አባት፡እበት፡ነው።" አባ፡ጳውሎስን፡ከዚህ፡ለይቼ፡አላያቸውም።

“ለእግዚአብሔር፡የምስጋናን፡መሥዋዕት፡ሰዋ፤ ለልዑልም፡ስእለትህን፡ስጥ፤ በመከራ፡ቀን፡ጥራኝ፤ አድንህማለሁ፤ አንተም፡ታከብረኛለህ። ኃጢአተኛውን፡ግን፡እግዚአብሔር፡አለው፤ ለምን፡አንተ፡ሕጌን፡ትናገራለህ? ኪዳኔንም፡በአፍህ፡ለምን፡ትወስዳለህ? አንተስ፡ተግሣጼን፡ጠላህ፤ ቃሎቼንም፡ወደ፡ኋላህ፡ጣልክ። ሌባውን፡ባየህ፡ጊዜ፡ከእርሱ፡ጋር፡ትሮጥ፡ነበር፤ እድል፡ፈንታህንም፡ከአመንዝሮች፡ጋር፡አደረግህ። አፍህ፡ክፋትን፡አበዛ፤ አንደበትህም፡ሽንገላን፡ተበተበ። ተቀምጠህ፡ወንድምህን፡አማኸው፤ ለእናትህም፡ልጅ፡ዕንቅፋት፡አኖርህ። ይህን፡አድርገህ፡ዝም፡አልሁህ፤ እኔ፡እንደ፡አንተ፡እሆን፡ዘንድ፡ጠረጠርህ፤ እዘልፍሃለሁ፡በፊትህም፡እቆማለሁ። እግዚአብሔርን፡የምትረሱ፡እናንተ፡ይህንን፡አስተውሉ፤ አለዚያ፡ግን፡ይነጥቃል፤ የሚያድንም፡የለም።” መዝ. 49፡14-22

mary m said...

እባክዎትን ሰላም ይፍጠሩ ስለ ንጹህ ህዝብ ብለው ከመንፈሳዊ አባት ከሚባል ሰው ይህ አይጠበቅም ለነገሩ ማንነትዎ ገና አልታወቀም እግዚአብሄር ፍርድ ይስጥ።

Anonymous said...

Anonymous of Jan3/2012 12:48pm:

Thank you very much.I admire your courage to put it AS IT IS. It is very very clear that our problem will never be solved as far as this evil is sitting there. It will even get worse. He makes sure our church and believe is totaly and completely gone. This is his number one commitment to himself.

So if we are truely devoted to our church we need to make sure he is gone. I mean as you put it he is realy realy GONE. I believe he is going to hell!!

What I don't understand is why people are afraid to tell the truth AS IT IS like that of yours? We can't live for ever. I mean we are going to die anyway. So why not die while elliminating the evil? I think there are so many people who share/like your idea but are not brave enough to put it even in writing let alone to take action. That is why I appreciate your idea. God Bless you

Anonymous said...

Egziabher twagi new semume EGZIZBHER NEW eresu sel betkrstyan Ywagale!! Egna bteslot mtegat Ytebkebenal. menafikan btinat new yminkesakesut selzihe Egna mastwal ytebekebenal ahun yewstna ywuchi telat bzetwal men maderge enedalebene hulum btihitena, btsome, bteslot memaled mebertate keza melsun enagnewalen. EGZIABHER BIZGYEM MANIM AYKEDEMWUM. ORTODOKS TWAHIDO LIJOCHI HULU BZIHICH SAT BSIGDET, BMIHILA BERTU EBAKACHIHU adera elalhu mchem bawji SUBE yminegeren yelemena ende Nenewe hizbe wd EGZIABHIR ENCHUHE.

Fikertmariam A.A cment F

Anonymous said...

EGZIABHER SIL BETEKRSTIYAN YWAGAL WE BSELOT WD EGZIABHER MCHOHE NEW. EGZIABHER BIZEGYIM YMIKEDEMEW YELEM ENA. WE wd EGZIABHER limenachinen tesemeto mlisun enagenewalen bandi Libe honen btihitina mteslye albin.

Tibebe silase A.A

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)