January 30, 2012

የመ/ር ዘመድኩን የመከላከያ ምስክሮች ተሰሙ


  ·    የተከሳሽ ጠበቃ እና ዐቃቤ ሕግ የክርክር ማቆሚያ ንግግር አድርገዋል::
  ·     ውሳኔው ለየካቲት 27 ቀን 2004 ዓ.ም ተቀጥሯል::
  ·   የአርማጌዶን ቪሲዲ እውነትን መሠረት አድርጎ ከፍ ላለ ሞራላዊ ዓላማ የተሠራ ዝግጅት እንጂ የስም ማጥፋት ተግባር አይደለም፤ አዘጋጁም ሥራውን የመሥራት ችሎታ እና ሥልጣን አላቸው፡፡ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች የግል ተበዳይ [ከሳሽ በጋሻው ደሳለኝ] አጉራ ዘለል መሆኑን በበቂ አላስተባበሉም፤ የማስተማር ችሎታ እና ሥልጣን እንዳለው ያቀረቡት አሳማኝ ማስረጃ የለም” (የተከሳሽ ጠበቃ)::
(ደጀ ሰላም፣ ጥር 20/2004 ዓ.ም፤ January 29/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ አርማጌዶን ቪሲዲ የተነሣ የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የቀረበበት መ/ር ዘመድኩን በቀለ የመከላከያ ምስክሮቹን ለፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት አቅርቦ አሰምቷል፡፡ ተከሳሹ ከቆጠራቸው አምስት የመከላከያ ምስክሮች መካከል በችሎቱ የተሰማው የሦስቱ የምስክርነት ቃል ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ ምስክሮች ከሦስቱ የተለየ የማያስረዱ በመሆኑ ከምስጋና ጋራ ተሰናብተዋል፡፡ የግራ ቀኙ ክርክር የተጠቃለለ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ እና የተከሳሽ ጠበቃ የክርክር ማቆሚያ ንግግራቸውን ለችሎቱ አቅርበዋል፡፡ መዝገቡን መርምሮ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለየካቲት 27 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በኋላ በ8፡00 ሰዓት ቀጠሮ ተይዟል፡፡

January 27, 2012

ጥምቀት በለንደን


(ተዋሕዶ ዘሎንዶን፤ ለደጀ ሰላም፣ ጥር 17/2004 ዓ.ም፤ January 26/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የ፳፻፬ ዓ.ም. የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በዩናይትድ ኪንግደም ርዕሰ ከተማ ለንደን በከፍተኛ መንፈሳዊ ስነ-ሥርዓት መከበሩን የሰ/ምዕ/አውሮፓ /ስብከት /ቤት አስታወቀ። ጌታ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ መጠመቁን ለማዘከር በቆየው የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ትውፊት መሠረት በለንደን የሚገኙት የኢ///አብያተ ክርስቲያናት በበዓሉ ዋዜማ ታቦቶቻቸውን ይዘው ከመቅደሶቻቸው ሲወጡና ለማደሪያ በተዘጋጀላቸው ሥፍራ ሲደርሱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናት፣ የሰንበት /ቤቶች ወጣት መዘምራን በያሬዳዊ ዜማና ዝማሬ፤ ምዕመናን በእልልታና ደማቅ የአምልኮት ስነ-ሥርዓት አሸኛኘትና አቀባበል አድርገውላቸዋል።

January 24, 2012

የዘርዐ ያዕቆብ አደባባይ የአደባባይነት ቅርስነቱ አበቃ?

 • አቡነ ጳውሎስ በተገኙበት በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ አደባባይ የነፈሰው ማዕበል መሰል ውቅንብል ነፋስ የባሕረ ጥምቀቱን ሥነ ሥርዐት ለሩብ ሰዓት አስተጓጐለ::
 • ማዕበል መሰሉ ነፋስ “መልአከ እግዚአብሔር ወርዶ እየባረከ ነው” የሚል ትርጉም ቢሰጠውም በምእመኑ ዘንድ ግን የአስከፊ ድርጊት ንግር ተደርጎ ተወስዷል::
 • የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በዘርዐ ያዕቆብ አደባባይ ላይ አገልግሎት ሰጪ ሕንፃ ሊያስገነባ ነው፤ ታሪካዊው አደባባይ የደብረ ብርሃን ከተማ አብያተ ክርስቲያን ባሕረ ጥምቀት እና መስቀል ደመራ የሚያከብሩበት ነው::
(ደጀ ሰላም፣ ጥር 15/2004 ዓ.ም፤ January 24/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ምድር መሠረት፣ የሰማይ ዐምድ የሆነው ረቂቁ ነፋስ በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደሚነሣ፣ እንደ ዐውሎ (ጥቅል) ሆኖ ሲነፍስም ድንገቴ ነውና የእግዚአብሔር ፍርድ ምሳሌ እንደሆነ ይታመናል (መዝ.106(107)÷25፤ ምሳ. 10÷25፤ ኢሳ. 17÷13፤ ናሆም 1÷3)፡፡ ጥር 13 ቀን 2004 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ከተማ በታሪካዊው ዘርዐ ያዕቆብ አደባባይ እና አካባቢው የታየው ይህንኑ የሚያጠይቅ ነው ተብሏል፡፡

January 22, 2012

በደ/ብ/ብ/ክልል በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ጥምቀት በዓል የወጡ ክርስቲያኖች በአክራሪ ሙስሊሞች ጉዳት ደረሰባቸው


(ደጀ ሰላም፣ ጥር 13/2004 ዓ.ም፤ January 22/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ጥር 12/2004 ዓ.ም የቃና ዘገሊላን በዓል ለማክበር በወጣው ምዕመን ላይ የሙስሊም አክራሪ ቡድን የድንጋይ ነዳ በመውርወር ብዙ ክርስቲያኖች ላይ የማቁሰል አደጋ ማድረሳቸውን በአካባቢው የሚገኙ ደጀ ሰላማውያን ሲገልፁ በተመሳሳይ በአዲስ አበባ መርካቶ አካባቢ የተቀሰቀሰ ተመሳሳይ ግጭት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን “አዲስ ነገር ኦንላይን” ዘግቧል።

January 19, 2012

አርዕስተ ዜና፦ የኩሪፍቱ ሪዞርት እና ስፓ የባቦ ጋያ መድኃኔዓለም ባሕረ ጥምቀት እና መስቀል ደመራ ቦታ “የይዞታ ባለመብት ነኝ” እያለ ነው

(ደጀ ሰላም፣ ጥር 10/2004 ዓ.ም፤ January 19/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF.
 • የኩሪፍቱ ሪዞርት እና ስፓ ሥራ አስኪያጅ የሆኑትና “ውል ተቀባይ ናቸው” የተባሉት አቶ ታዴዎስ ጌታቸው “የደብሩ የልማት ኮሚቴ ተጠሪ” ናቸው፤ ከባሕረ ጥምቀቱ እና መስቀል ደመራው አጠቃላይ 13,020 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ ለሪዞርቱ ማስፋፊያ በሚል በሊዝ የወሰዱትን 11,000 ካሬ ሜትር መሬት በድርጅታቸው ስም ካርታ እና ፕላን በቢሾፍቱ ማዘጋጃ ቤት አሠርተውለታል፡፡ በምትኩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሓላፊነት ሥር ለሚቋቋም ሙዓለ ሕፃናት፣ ክሊኒክ፣ ዳቦ ቤት፣ ወፍጮ. . . መሥሪያ ወጪ በወሰዱት የማስፋፊያ ቦታ ላይ ግንባታ አጠናቀውና በይፋ ሥራ ጀምረው ጥቅም ማግኘት ከጀመሩበት ወር አንሥቶ በየወሩ ብር 20,000 “በግል ፈቃደኛነት እና በበጎ ፈቃድ ለመስጠት ተስማምተዋል”

የጥምቀት ልጆች ለበዓሉ ድምቀት በሥራ ላይ ናቸው:: Timket Preparation 2004 EC


 . ለአየካባቢያቸው ጸጥታ ሓላፊነት እንዲወስዱ ተደርገዋል::
. ጥምቀት - አንቀጸ ሃይማኖት(የድኅነት መግቢያ በር)::
(ደጀ ሰላም፣ ጥር 9/2004 ዓ.ም፤ January 18/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF.)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልደት እና ጥምቀት በየዓመቱ በፍጹም መንፈሳዊ አስተሳሰብና በደማቅ ሥነ ሥርዐት ከሚከበሩት የጌታችን ዐበይት በዓላት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡

የጥምቀት ልጆች ለበዓሉ ድምቀት በሥራ ላይ ናቸው


. ለአየካባቢያቸው ጸጥታ ሓላፊነት እንዲወስዱ ተደርገዋል::
. ጥምቀት - አንቀጸ ሃይማኖት(የድኅነት መግቢያ በር)::
(ደጀ ሰላም፣ ጥር 9/2004 ዓ.ም፤ January 18/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF.)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልደት እና ጥምቀት በየዓመቱ በፍጹም መንፈሳዊ አስተሳሰብና በደማቅ ሥነ ሥርዐት ከሚከበሩት የጌታችን ዐበይት በዓላት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡ የበዓላቱ አከባበር በሚታይና በሚዳሰስ ዝግጅት፣ በመብልና በመጠጥ፣ በልብስና በጌጣጌጥ ላይ ብቻ የሚያተኩርና በዚሁ ግርግር የሚታለፍ አይደለም፡፡ ይቅርታው እና ቸርነቱ ብዙ የሆነው የዓለም ፈጣሪ በስሕተት ጎዳና የተጓዘውን ዓለም(ሰውን) ለመፈለግ፣ ወደ እውነትና የሕይወት መሥመር ለመመለስና በኃጢአት በር ወደ ዓለም የገባውን ሞት በሞቱ ደምስሶ የሰውን ዘር ሁሉ ነጻ ለማድረግ ሰው የሆነበትና ሥጋን የተዋሐደበት ምሥጢር በልብ ይታሰባል፤ በትምህርት ይገለጣል፤ በተግባራዊ እንቅስቃሴ መንፈሳዊ ሥዕሉ በጉልሕ ይታያል፡፡ የሥነ በዓላቱ ጥልቀት እና ድምቀት የሚመሠረተው በዚህ ላይ ነው፡፡

Reminder, Tsome Gehad


January 18, 2012

መ/ር ዘመድኩን የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍ/ቤት አቀረበ


·    የመከላከያ ምስክሮች ተሟልተው አልቀረቡም::
·     የችሎቱ ሂደት የሚዲያዎችን ቀልብ ስቧል::
(ደጀ ሰላም፣ ጥር 8/2004 ዓ.ም፤ January 17/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ አርማጌዶን ቪሲዲ የስም ማጥፋት ወንጀል የተከሰሰሰው መ/ር ዘመድኩን በቀለ 20 ገጽ የሰነድ ማስረጃዎችን ለፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት አቀረበ፤ ተከሳሹ ለዛሬ፣ ጥር 8 ቀን 2004 ዓ.ም ቀርበው እንዲሰሙ ከቆጠራቸው አራት ምስክሮች መካከል ሦስቱ በተለያየ ምክንያት ባለመገኘታቸው ለጥር 18 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በኋላ በ8፡00 ሰዓት በተከሳሽ በኩል በሚደርሳቸው መጥሪያ አማካይነት ይህም ካልሆነ በሕግ አስገዳጅነት ታስረው እንዲቀርቡ ሲል ፍ/ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

January 16, 2012

በሐዲያ ዞን ምንነቱ ያልታወቀ የሰማይ እሳት ቤቶችን እየለየ በማቃጠል ላይ ነው


 • READ THE ARTICLE IN PDF.
 • እሳቱ እሳታዊነት በጩኸት ይበረታል፤ በእልልታ ይከስማል
 • እሳቱ ቤቶቹን የሚያቃጥለው “ምልክትና ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ” ነው
 • “የእግዚአብሔር ቁጣ ነው፤ በአካባቢያችን ኑፋቄ፣ ውሸት፣ ክፉ ቅንዐት እና ንብረት መቀማማት በርክቶ ይታያል”/የአካባቢው ነዋሪ/

(ደጀ ሰላም፣ ጥር 6/2004 ዓ.ም፤ January 15/2012)፦ በቅዱስ መጽሐፍ የተወደደ መሥዋዕት/ቍርባን ለሚያቀርቡ አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔር በእሳት ይመልስላቸው ማለትም እሳት ከሰማይ እየወረደ መሥዋዕታቸውን ይበላ እንደ ነበር ተጽፏል፤ እግዚአብሔርም ብዙ ጊዜ ራሱን በእሳት ነበር የሚገልጠው፡፡ ይኸውም እሳት የእግዚአብሔርን ክብር፣ ሕዝበ እስራኤልንም የመጠበቁን ሁኔታ ማመልከቻ ነበር፡፡ እሳት የእግዚአብሔርን ቅድስና፣ ጽድቅ እና ቁጣ እንደሚያሳይ ተገልጧል፡፡ ሰሞኑን በደቡብ የአገራችን ክፍል የተከሠተውና ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ያልጠው እሳት ክሥተት/ባሕርይ በመጽሐፍ ቅዱስ እሳት የፍትሐ እግዚአብሔር ምሳሌ እንደሆነ የተገለጸውን እንደሚያረጋግጥ አስተያየት እየተሰጠበት ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ 9ኛውን የኦሪየንታል ኦርቶዶክስ እና የሮም ካቶሊክ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ታስተናግዳለች


 • Read the article in PDF
 •  በቤተ ክርስቲያን ፍጹም አንድነት እና ግንኙነት(the full communion and communication) ላይ የሚያተኩረው ስብሰባ ከነገ በስቲያ ይጀመራል::
 • የስብሰባው ተሳታፊዎች በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ይገኛሉ፤ በሥርዐተ ቅዳሴ ይሳተፋሉ
 • ስብሰባው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከውጭ አብያተ ክርስቲያናት ጋራ ያላትን ግንኙነት ለማስፋፋት እና ለማጠናከር ሓላፊነት በተጣለበት ቅዱስ ሲኖዶስ ዘንድ አይታወቅም፤ ስለ ስብሰባው ልኡካን/ተልእኮ ቅዱስ ሲኖዶስ ይሁን ቋሚ ሲኖዶስ ያስተላለፈው ውሳኔ የለም::
 •  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የቅርስ ጥበቃና የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር እንዲሁም የቱሪዝም መምሪያ ሓላፊ እና በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር የሆኑት ሊቀ ዲያቆን ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ናቸው፡፡ በቀደሙት ጉባኤያት ቤተ ክርስቲያንን በመወከል ሲሳተፉ የቆዩት መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ (ከሊቃውንት ጉባኤ) እና ሊቀ ኅሩያን ጌታቸው ጓዴ (ከውጭ ግንኙነት) ነበሩ::

በዲታ ወረዳ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን የቃጠሎ አደጋ ደረሰበት


(www.eotcmk.org):- በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት፣ በዲታ ወረዳ፣ ጋና ደሬ ቀበሌ፣ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 29 ቀን 2004 .. ከሌሊቱ በስድስት ሰዓት አካባቢ በእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰበት፡፡ የቦታው አቀማመጥና አደጋው የደረሰበት ሰዓት ሌሊት በመሆኑ በቦታው ምንም ዓይነት ነዋያተ ቅድሳት ማትረፍ እንዳልተቻለ በቦታው የሚገኙት የደብሩ አገልጋይ ገልጸዋል፡፡ የአደጋውን መከሰት ሰምተው የመጡት የአካባቢው ምዕመናን ከሌሊት ጀምሮ ጥልቅ ሀዘናቸውን በለቅሶ ሲገልጹ እንደነበር በቦታው የተገኙት የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ዘግበዋል፡፡

January 14, 2012

ምዕመናኑ 300ሺህ ብር የት እንደገባ ጠየቁ


 • በዝግ ሂሳብ ባንክ ገብቷል - ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኢጲፋንዮስ
(Addis Admas):- በምዕራብ ሸዋ ሐገረ ስብከት (ዞን) የሚገኙ ምዕመናን ለገጠር አብያተክርስትያናት ተብሎ የተዋጣ 300 ብር በላይ የት እንደገባ እንደማያውቁና ሳይመዘበር እንዳልቀረ ሰሞኑን ተናገሩ፡፡ ገንዘቡ የተዋጣበት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በዞኑ ዋና ከተማ በአምቦ አለመከናወኑ ጥርጣሬ አሳድሮብናል ብለዋል - ምዕመናኑ፡፡ በምዕራብ ሸዋ ሐገረ ስብከት (ዞን) የአስተዳደር ችግር እንዳለ የጠቆሙት ምዕመናኑ፤ ሥራቸውን በአግባቡ ሲወጡ የነበሩት ከሃላፊነት ተነስተው መሾም የማይገባቸው ተሹመዋል እንዲሁም አምቦ አካባቢ የሚገኘው የአዋሮ ቅዱስ ሚካኤል መሬት ተሸንሽኖ ለግለሰቦች እየተሸጠ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡

January 6, 2012

የአራዳው ፍ/ቤት መ/ር ዘመድኩን እንዲከላከል አዘዘ


 • READ THIS ARTICLE IN PDF.
 • በእናቱ ሞት በደረሰበት ኀዘን እና በቁሉቢ ጉዞ በአራዳው ምድብ ችሎት በቀጠሮ ያልተገኘው መ/ር ዘመድኩን “የመደመጥ መብቴ ተነፍጓል፤ ከውሳኔ አስቀድሞ አቋም ተይዞብኛል” በማለት በዳኛው ላይ ምሬቱን ገልጧል::
 • “እናቱ ለመሞታቸው የሕክምና ማስረጃው ተተርጉሞ ይቅረብ፤ ከገብርኤል እና ከፍ/ቤት ማን ይበልጣል?” (ዳኛው)::
 • “ሊጠፋብን ስለሚችል ማረፊያ ቤት እንዲቆይ ይታዘዝልን”(ዐቃቤ ሕግ)::
 • በቦሌው ምድብ ችሎት መ/ር ዘመድኩን የመከላከያ ምስክሮቹን አሰምቷል፤ ሊቀ ጠበብት ዘሪሁን መከላከያ ምስክር ሆነው ቀርበዋል::
 • ማይምን” “መጋቤ ሐዲስ” የሚሉት ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል::
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 26/2004 ዓ.ም፤ January 5/2012)፦ በአርማጌዶን ቪሲዲ የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የተመሠረተበት መ/ር ዘመድኩን በቀለ ክሱን እንዲከላከል የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት አዘዘ፡፡

January 4, 2012

የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ሥራ አስፈጻሚ የብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን እንቅስቃሴ እየተቃወመ ነው


(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 24/2004 ዓ.ም፤ January 3/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ለዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ተመድበው ቢላኩም ሀ/ስብከቱን ማስተዳደር ያልጀመሩት አቡነ ፋኑኤልን በተመለከተ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ቀጥሎ ሀ/ስብከቱን እንዲያስተዳድር የተመረጠው ሥራ አስፈጻሚ “ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን” 1ኛ ቆሮ 14፡40 በሚል ርእስ ኅዳር 29 ቀን 2004 ዓ. ም ባወጣው መግለጫ በሀ/ስብከቱ ያለው ዋነኛ ችግር “የውስጥ የቤተ ክርስቲያን ፈተናና እና ችግር  የሆነው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት በማክበርና ባለማክበር፤ እውነታን በመናገርና ባለመናገር፤ የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም በማስጠበቅና የግል ጥቅምን ከቤተ ክርስቲያን በማስቀደም፤ መዋቅርን በመጠበቅና ባለመጠበቅ፤ ጽኑ መንፈሳዊ አቋም በመያዝና ባለመያዝ መካከል” መሆኑን ጠቅሷል።

January 3, 2012

ሰበር ዜና - ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ


 • READ THIS ARTICLE IN PDF.
 • በየአህጉረ ስብከቱ ለሚፈጠሩት ችግሮች የአቡነ ጳውሎስ ግፊት እንዳለበት ቅዱስ ሲኖዶስ ገለጸ
 • አስቸኳይና ድንገተኛ ስብሰባ የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ፓትርያርኩ ያቀረቧቸው አጀንዳዎች “ለአስቸኳይ ስብሰባ የማይበቁ ናቸው” በሚል አጣጥሏቸዋል::
 • በፓትርያርኩ እልከኝነትና ተንኮል ላይ ያመረሩት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት “የቤቱ ችግር ተጣርቶ መወገዝ ያለበት ይወገዝ፤ ስለ ወንጌል አገልግሎት፣ መልካም አስተዳደር፣ ሰላም እና ልማት መነጋገር ሲገባን ቤተ ክርስቲያን በእርስዎ የተነሣ ስትበጠበጥ እና ስትናጥ መኖር የለባትም” በሚል አቡነ ጳውሎስን ሲገጹ እና ሲያስጠነቅቁ አርፍደዋል::
 • ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከሲዳማና ጌዲኦ ዞኖች አማሮና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት እንዲነሡ ‹በ15,000 ምእመናን ፊርማ› ቀርቧል የተባለው ‹አቤቱታ› ስድነት የተሞላበትና በአቡነ ጳውሎስ ግፊት የቀረበ የተሐድሶ መናፍቃን ሤራ መሆኑን ሲኖዶሱ ገልጧል፡፡ በሕገ ወጥ አድመኞች የቀረበውን ይህንኑ ስድ አቤቱታ በመቃወም 20,000 የሐዋሳ እና ዲላ ምእመና ያሰባሰቡት የተቃውሞ ፊርማ አቤቱታ ለሲኖዶሱ ጽ/ቤት ደርሷል::

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)