- የደብሩ አስተዳዳሪ የአጥቢያውን ልማት የመምራት አቅም የላቸውም::
- ፖሊስ ሁለት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችንና አንድ ምእመን ይዞ አስሯል::
- ተዋንያኑ ፋንቱ ማንዶዬ እና ችሮታው ከልካይ በቁሉቢ ለአኵስም ጽዮን ሙዚዬም ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ያካሂዳሉ::
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ
18/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 28/2011. READ IN PDF)፦ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የሚገኙ የስምንት
አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች እናምእመናን በሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ
የተፈጸመው ሙስና ተጣርቶ በሙሰኞቹ ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ፣የደብሩን አስተዳደር በመምራት ረገድ የከፋ የአቅም ማነስታይቶባቸዋል፤በሰበካ
መንፈሳዊ ጉባኤው የተተለሙ የልማት ዕቅዶች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ ዕንቅፋት ፈጥረዋልየተባሉት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ኀይል ቆሞስ
አባ ገብረ እግዚአብሔር ቸኮል ከሓላፊነታቸው እንዲወገዱ በተቃውሞ ትዕይንት ጠየቁ፡፡



