- የግብረ ሰዶማውያኑ ስብሰባ የ(ICASA)ን ኮንፈረንስ አሉታዊ ትርጉም እንዳያሰጠው ተሰግቷል፤
- “Claim, Scale-up and Sustain”(የራስ ማድረግ፣ ማሳደግ እና ቀጣይነት) የግብረ ሰዶማውያኑ ውይይት መሪ ቃል ሲሆን አዲስ አበባ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ መዲና መሆኗን በመጠቀም በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር ዕቅድ ተይዟል፤
- እስከ አሁን ደቡብ አፍሪካ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ሕጋዊ ያደረገች ሲሆን በተቃራኒው የናይጄሪያ ፓርላማ ግብረ ሰዶማዊነትን ሕገ ወጥ ያደረገ ሲሆን በኬንያ እና በዑጋንዳ የግብረ ሰዶማውያን መብት በሚል ለፓርላማዎቻቸው ጥያቄ ቢቀርብም ውድቅ አድርገውታል።
- ዝምባቡዌ ግብረ ሰዶማውያን “ውሾች ናቸው” በሚል ከሀገር ታባርራለች፤
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 19/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 29/2011 PDF):- የውጭ አገር ዜጎች፣ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ወደ ውጭ አገር ለንግድ አብዝተው የሚመላለሱ
ኢትዮጵያውያን ግብረ ሰዶማዊነትን እንደ ዘመናዊነት/ሥልጣኔ ቆጥሮ በማስፋፋት ረገድ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን በአብዛኛው የሚጠራሩበት
ስም “ዜጋ” የሚል ነው፤ አንዳንዴ ይኸው ስያሜ “ኦፔራ፣ ወገን፣ ጅራሬ፣ ብርታሉ (ቁምጬ)፣ ጀሲካ ሞናሊዛ፣ ቆሚታ፣ መክተብ” በሚባሉ ስያሜዎች እንደሚተካ ተገልጧል፡፡



