July 31, 2011
“አዲስ አድማስ” ጋዜጣ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የዘገበውን ዜና ቀጥሎ ያንብቡ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
የእርስ በርስ ቀውስ
- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
- የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራር ከፓትርያሪኩ ጋራ ሳይወያዩ ቀሩ፤ ጉዳዩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ደርሷል።
July 29, 2011
የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴን አስመልክቶ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ከማኅበረ ቅዱሳን አመራር ጋር ውይይት አደረጉ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(EOTCMK):- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ከማኅበረ ቅድሳን ሥራ አመራርና አስፈጻሚ ጉባኤያት ተወካዮች ጋር ነሐሴ 15 ቀን 2003 ዓ.ም ስለ ማኅበሩ አገልግሎትና በተለይም የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ውይይት ማድረጋቸውን የማኅበሩ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
July 28, 2011
“ማኅበረ ቅዱሳን የውይይት እና የምክክር ባሕሉን ይቀጥል” (ደጀ ሰላም)
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2011/ READ IN PDF):- የዲ/ን ዳንኤል ክብረትን
ጽሑፍ ካስነበበንበት ወቅት ጀምሮ ብዙ ደጀ ሰላማውያን እጅግ በጣም ገንቢ ሐሳቦችን፣ ምክሮችን እና ቁም ነገሮችን ለግሳችሁናል።
ብዙዎቻችሁ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት “የዓይናችን ማረፊያ” ያላችሁትን የማኅበረ ቅዱሳንን “ገመና” እና መለያየቱን በአደባባይ
ማቅረባችን ትልቅ ሐዘን እንደፈጠረባችሁ ገልጻችሁልናል። አንዳንዶቻችሁም በሥራችን መከፋታችሁን፣
ከፍተኛ ቁጭት እና ሐዘን እንደተፈጠረባችሁ ደጀ ሰላም ተረድታለች።
July 27, 2011
July 22, 2011
"ስብሐት ፣ ከጳውሎስ እስከ ማኅበረ ቅዱሳን" (By Mesfin Negash)
Posted by
DejeS ZeTewahedo
![]() |
(አቦይ) ስብሐት ነጋ
|
"በምርጫ 97 ማግስት ድንጋጤ ያርበተበው ፓርቲ/መንግሥት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማሰርና በመፍታት ስራውን አላጠናቀቀም
ነበር። ይህን ተከትሎ እስከ ገጠር ቀበሌ ድረስ “ለምን ተሸነፍን? የጦስ ዶሮዎቹን አድኑ” የሚል አውጫጪኝ ተካሂዶ ነበር። ይህ በየክልኩ የደኅንነት አካሎችና በፓርቲው መዋቅር
(አንድም ሁለትም ናቸው) የተካሄደው “ጥናት” አስደናቂ ውጤቶችን አስገኝቷል። ከእነዚህ ውጤቶች አንዱ “በአማራ እና በደቡብ
ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች ኢሕአዴግ ለደረሰበት ሽንፈት፣ ተቃዋሚዎች ላገኙት ድጋፍ ሚና ከነበራቸው አካሎች አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን
ነው” የሚል ነበር።" (ከጽሑፉ
የተወሰደ)
“ዝነኛው” አቦይ ስብሐት የዛሬ ሦስት ሳምንት ገደማ በ“ፍትሕ” ጋዜጣ ለወጣባቸው ትችት የሰጡት መልስ አስተያየት የሚጋብዝ ነው። የ“ፍትሑ” አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝም አቦይ ስብሐት ሕዝብ በተሰበሰበበት የተናገሩትን ለንባብ ማቅረቡ የሚጠቅም ነው፤ “ሰውየው መዘባረቅ ልማዳቸው ነው” ብሎ አለመተዉን ለማድነቅ ነው። (ተጨማሪ ምልልሶችን በ “ፍትሕ” ጋዜጣ ድረ ገጽ ማግኘት ይቻላል።)
July 21, 2011
ማኅበረ ቅዱሳን በለንደን ታላቅ ዐውደ ርእይ አዘጋጀ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ፤
በተለይ ለደጀ ሰላም፤ ጁላይ 21/2011)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደም ሲል ለአገሪቱ ያደረገቻቸው ታሪካዊ አስተዋጽዎችን፣ በአሁኑም ወቅት እያደረገች ያለውን ልማታዊ እና ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም ወደፊት ምን ለማድረግ እንደታቀደ የሚያመላክት ታላቅ ዐውደ ርእይ በለንደን ከተማ ውስጥ ተካሄደ፡፡
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ታሪካዊ መግለጫ አወጡ፤ ተሐድሶን እና አባ ሰረቀን ተቃወሙ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- ከአዲስ አበባ ውጪ በየአህጉረ ስብከቱ ያሉትም ይደግፏቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፤
- በሰሜን አሜሪካ ያለው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አጋርነቱን ይገልጻል ተብሎ ይጠበቃል፤
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 20/2011/ READ IN PDF):- በፕሮቴስታንታዊ - ተሐድሶ - ኑፋቄ ላይ ውስጥ ውስጡን እየተቀጣጠለ የሚገኘው
የምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች ቁጣ ፈንድቶ አስከፊ ጉዳት ከመድረሱ በፊት አስፈላጊው የእርምት ርምጃ እንዲወሰድ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ጠየቁ።
ፌዴራል ፖሊስ በሰንበት ት/ቤቶቹ የቀረበው አቤቱታ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጠው የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊን አሳስቧል
ተብሏል:: “ለሰንበት ት/ቤቶች የሚጠቅም አንዳችም ተጠቃሽ ሥራ አላበረከቱም”
የተባሉት ዋና ሓላፊው አባ ሰረቀ ስለ ተሐድሶ መናፍቃን የሰጡት መግለጫ ሰንበት ት/ቤቶችን አይወክልም፤ መግለጫው በመምሪያ ሓላፊነታቸው
እንዳይታመኑ የሚያደርግና በብዙኀን መገናኛ ተገቢው ማስተካከያ ሊሰጥበት የሚገባ እንደሆነ ተመልክቷል።
July 19, 2011
አቡነ ፋኑኤል በአትላንታ ክህነት ሰጡ፤ የሀ/ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ አላስፈቀዱም
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 19/2011/ TO READ IN PDF):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ፋኑኤል በአትላንታ ጆርጂያ በሚገኘውና ራሱን “ገለልተኛ” ብሎ በሚጠራው በአትላንታ መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ወኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ክህነት መስጠታቸውን የቤተ
ክርስቲያኑ
አስተዳዳሪ ቀሲስ ኤፍሬም ከበደ ጁላይ 10 ቀን 2011 በአትላንታ አካባቢ በሚተላለፈው
AM 1100 የሬድዮ ጣቢያቸው በሰጡት የደስታ መግለጫ አስታውቀዋል።
July 17, 2011
እነበጋሻው “የምእመናንን ተቃውሞ የሚያበርድ” ያሉትን አዲስ ቪሲዲ እያዘጋጁ ነው
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- የቅጥር ማመልከቻቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ሠራተኞች አስቆጥቷል፤
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 17/2011/ TO READ IN PDF)፦ በጋሻው ደሳለኝን እና አጋሮቹ
ራሳቸውን “ፍፁም ኦርቶዶክሳዊ” መሆናቸውን ለማሳየት ያዘጋጁት ነው የተባለ
ቪሲዲ በቅርቡ ለመልቀቅ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ታውቋል። ቪሲዲው እነበጋሻው እንባቸውን እንደ ማየ ክረምቱ ሲያንዠቀዥቁ
የሚያሳዩበት እንደሆነም ተነግሮለታል። በካሜራ ፊት በደቦ የተደረገ የልቅሶ ትዕይንት የሆነው የዚህ ቪሲዲ ተዋንያን በጋሻው ደሳለኝ፣ ትዝታው ሳሙኤል፣ ያሬድ አደመ፣ ዕዝራ ኀይለ ሚካኤልና
ምርትነሽ ጥላሁን ሲሆኑ ልቅሶውን በመሪ ተዋናይነት በመምራት የሚያላቅሳቸው /አስለቃሹ/ ደግሞ በሪሁን ወንደወሰን ነው ተብሏል፡፡
July 14, 2011
እነሆ 19 ዓመት ሆነ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 12/2011/ READ IN PDF)፦ አምስተኛው ፓትርያርክ በመንበረ ፕትርክና ከተቀመጡ እነሆ ዛሬ 19 ዓመት ሆናቸው።
እርሳቸው ወደዚህ ሥልጣን ሲመጡ ቤተ ክህነቱ የተለያዩ ችግሮች ነበሩበት። ከ19 ዓመታት በኋላ ስንመለከተው እነዚህ ችግሮች አድገውና
ሰፍተው፣ ዓይነታቸውም ተበራክቶ፣ ይልቁንም ይህንን ችግር ይቀርፋሉ የተባሉ ርዕሰ ቤተ ክርስቲያን የችግሩ ፊት-አውራሪ ሆነዋል።
19 ዓመት የአንድ ወጣት ዕድሜ ነው። ለተሳሳተ ሰውም ለመመለስ 19 ዓመት ረዥም ጊዜ ነበር። ከጥፋት ከመመለስ ይልቅ በበደል ላይ
በደል መጨመርን ተካኑበት እንጂ። ከዚህ በታች ያለውና (ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 5/2009) ያወጣችው ጽሑፍ ምን ማለታችን እንደሆነ የበለጠ ይገልጸው ይሆናል።
July 13, 2011
አባ ሰረቀ ፍ/ቤት ቀረቡ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- ፍ/ቤቱ አባ ሰረቀ የብር 4000 ዋስትና አስይዘው ሰኞ ሐምሌ 11 ቀን እንዲቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል::
- የኢ.ቢኤስ ቴሌቪዥን የአዲስ አበባ ቢሮ እነበጋሻው ደሳለኝ ለስድስት ተከታታይ ሳምንታት ባስተላለፉት ፕሮግራማቸው ማኅበረ ቅዱሳንን በስም ጠርተው የተናገሩት ውንጀላ እንዳይደገም ማሳሰቢያ ሰጠ፤ ትዝታው ሳሙኤል “የተሐድሶ ምንጩና መፍለቂያው ማኅበረ ቅዱሳን ነው” ሲል የተናገረው ስላቅ ከሕግ ዐይን አኳያ እየተጤነ ነው::
July 11, 2011
(ታሪክ በዚህ ሳምንት) - “መስለህ አስተምር በሚለው የመናፍቃን የማስተማር ዘይቤ” የሃይማኖት ሕጸጽ ባሰራጩ ሰባክያን ላይ ቅ/ሲኖዶስ የወሰደው ርምጃ ሲታወስ
ማውጫ፦
ሐተታ
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- “ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያናችን ዙሪያ የሚታየውን ችግር የማስወገድ አቅሙን እያጎለበተ በመምጣቱ ቤተ ክርስቲያኒቱን ከመናፍቃን ወራሪ ነጻ በማውጣት የሚካሄደው የሥራ እንቅስቃሴ በአጀንዳ ከቀረቡለት የወቅቱ ጥያቄ አንዱና ዋነኛው ሆኖ ተመዝግቧል” (የቅዱስ ሲኖዶስ የ1990 ዓ.ም ውሳኔ መግቢያ)
- ሕገ ወጥ ሰባክያኑ (አሰግድ ሣህሉ፣ በጋሻው ደሳለኝ) በጠቅላይ ቤተ ክህነት የተለያዩ መምሪያዎች ውስጥ ለመቀጠር ማመልከታቸው እየተነገረ ነው፤
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 11/2011/ TO READ IN PDF CLICK HERE)፦ 13 ዓመት ወደ ኋላ፤ ወርኀ ግንቦት
1990 ዓ.ም - በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ የከተተው የአዲስ አበባ ከተማ ምእመን ዐይኖች በአዳራሹ
ውስጥና ዙሪያ በተደረደሩ ከ20 ያላነሱ ቴሌቪዥኖች ተከብቧል፡፡ ምእመናኑ የጽርሐ ጽዮን አንድነት ማኅበር ቤተሰብ በሆነው እንደ መ/ር ታዬ አብርሃም ባሉ ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን መምህራን
አስተባባሪነት ቀደም ሲል በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን የተሰበሰቡ ሰባክያነ ወንጌል በወሰኑት መሠረት በተመሳሳይ
ቀንና በአንድ ላይ በዐውደ ምሕረትና በተለያዩ መንገዶች ባደረጉት ቅስቀሳ ጥሪ የተላለፈላቸው ነበሩ፡፡
July 6, 2011
የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ሕገ ወጥ ሰባክያንን አገደ
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአጥቢያውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በተመለከተ ‹‹በበላይነት መምራትና ማስተዳደር አልቻለም›› ባለው የደብሩ አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስጠንቅቆ ነበር
- ሰንበት ት/ቤቱ በሕገ ወጥ ሰባክያኑና የእነርሱ ተባባሪ በሆኑት የአጥቢያው ስ/ወንጌል ሓላፊዎች የሚመራው የስብከተ ወንጌል አካሄድ ‹‹ወዳልተፈለገ ግጭት›› እንደሚያደርስ በመጥቀስ ለሀ/ስብከቱ አቤቱታ አቅርቦ ነበር
- በሙሰኛነቱና ባለበት የሥነ ምግባር ችግር ተቃውሞ የተነሣበት ናሁ ሠናይ ነጋ የተባለው የአጥቢያው ስብከተወንጌል ሓላፊ የእገዳውን ምክንያትና ፋይዳ ለማስተባበል እየተፍጨረጨረ ነው።
- “ሥላሴ አትበሉ ብያለሁ፤ ሥላሴን አትመኑ ግን አላልሁም” (በጋሻው ደሳለኝ- በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን)
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 6/2011, Read in PDF.)፦ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጽ/ቤት በቅዱስ ሲኖዶስ፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና በሀገረ ስብከት ያልተፈቀደላቸው ሰባክያን ከሰኔ 24 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በአጥቢያው እንዳይሰብኩ መታገዳቸውን አስታወቀ፤ ጽ/ቤቱ ይህን ያስታወቀው የእገዳውን ውሳኔ ተቀብለው ተግባራዊ እንዲያደርጉ የደብሩ ስብከተ ወንጌል ሓላፊዎች ለሆኑት መ/ር ናሁ ሠናይ ነጋ እና መ/ር ታሪኩ አበራ በቁጥር 6020/03 በቀን 28/10/03 በጻፈው ደብዳቤ ነው፡፡
July 5, 2011
July 3, 2011
“ጳጳሶቹ አይረቡም … (ቤተ ክህነቱ) ወደ ሞት አፋፍ እየሄደ ነው” (አቦይ ስብሐት ነጋ)
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 1/2011, To Read in PDF, click HERE)፦ የሕወሐት/ኢሕአዴግ የፖለቲካ መሐንዲስ መሆናቸው የሚነገርላቸው አረጋዊው አቶ ስብሐት ነጋ ስለ ቤተ ክህነት በሰጡት ግልጽ አስተያየት ላይ “ጳጳሶቹ አይረቡም”፣ ቤተ ክህነቱም “ወደሞት አፋፍ እየሄደ ነው” ሲሉ ተናገሩ። ዛሬ አርብ ሰኔ 24/2003 ዓ.ም በወጣው “ፍትሕ” ጋዜጣ ላይ ረዥም ጽሑፍ ያስነበቡት አቶ ስብሐት ነጋ (በተለምዶ አቦይ ስብሐት ይባላሉ) ስለ ቤተ ክህነቱ በከፋ አስተዳደራዊ ብልሽት ውስጥ መውደቅ ምክንያቱ “ራሱ ቤተ ክህነቱ” እንጂ መንግሥት አለመሆኑን አብራርተዋል።
July 2, 2011
ሁለት ሊነበቡ የሚገባቸው ቃለ ምልልሶች
ማውጫ፦
From Contributors
Posted by
DejeS ZeTewahedo
በ“ሰባት ወይራ ሆቴል” አስተዳደር ጉዳይ የቅዱስ ላሊበላ ደብር እና ጠቅላይ ቤተ ክህነት እየተወዛገቡ ነው
ማውጫ፦
ዜና
Posted by
DejeS ZeTewahedo
- አስተዳዳሪውን ያባረሩት የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ማኅበር በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሽምግልና አስተዳዳሪው “ለተወሰነ ጊዜ ወደ ገዳሙ ማረፊያቸው ገብተው በክብር እንዲወጡ” በሚል ተስማምተዋል፤ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ በበኩላቸው “ሳልበታትነው” በሚል በገዳሙ ማኅበር አንድነት ላይ መዛታቸው ተሰምቷል፤
Subscribe to:
Posts (Atom)
Blog Archive
-
▼
2011
(227)
-
▼
July
(19)
- ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በፖሮቴስታንታዊ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ዙሪያ እና በወቅታዊ ...
- “አዲስ አድማስ” ጋዜጣ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የዘገበውን ዜና ቀጥሎ ያንብቡ
- የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴን አስመልክቶ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ከማኅበረ ቅዱሳን አ...
- የሰሜን አሜሪካ ሰንበት ት/ቤቶች ታሪካዊ መግለጫ አወጡ፤ ተሐድሶን ተቃወሙ
- “ማኅበረ ቅዱሳን የውይይት እና የምክክር ባሕሉን ይቀጥል” (ደጀ ሰላም)
- ፍ/ቤቱ አባ ሰረቀ የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ወሰነ
- "ስብሐት ፣ ከጳውሎስ እስከ ማኅበረ ቅዱሳን" (By Mesfin Negash)
- ማኅበረ ቅዱሳን በለንደን ታላቅ ዐውደ ርእይ አዘጋጀ
- የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ታሪካዊ መግለጫ አወጡ፤ ተሐድሶን እና አባ ሰረ...
- አቡነ ፋኑኤል በአትላንታ ክህነት ሰጡ፤ የሀ/ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ አላስፈቀዱም
- እነበጋሻው “የምእመናንን ተቃውሞ የሚያበርድ” ያሉትን አዲስ ቪሲዲ እያዘጋጁ ነው...
- እነሆ 19 ዓመት ሆነ
- አባ ሰረቀ ፍ/ቤት ቀረቡ
- (ታሪክ በዚህ ሳምንት) - “መስለህ አስተምር በሚለው የመናፍቃን የማስተማር ዘ...
- የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ሕገ ወጥ ሰባክያንን አ...
- የማ/ቅዱሳን ዋና ፀሐፊ መምህር ሙሉጌታ ኃ/ማርያም፤ ከ“ዕንቁ” መጽሔት ጋር ያ...
- “ጳጳሶቹ አይረቡም … (ቤተ ክህነቱ) ወደ ሞት አፋፍ እየሄደ ነው” (አቦይ ስብ...
- ሁለት ሊነበቡ የሚገባቸው ቃለ ምልልሶች
- በ“ሰባት ወይራ ሆቴል” አስተዳደር ጉዳይ የቅዱስ ላሊበላ ደብር እና ጠቅላይ ቤ...
-
▼
July
(19)







