December 17, 2011

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አወዛጋቢ ስብሰባ ጠርተዋል፤ ለአቡነ አብርሃም ሽኝት ተዘጋጅቷል

(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 6/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 16/2011. READ IN PDF)፦ ባለፈው ጥቅምት በተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ለዲሰና አካባቢው እንዲሁም ለካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት በሊቀ ጳጳስነት የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በዲሲ ሀ/ስብከት ስም የጠሩት ስብሰባ ነገ ቅዳሜ በዋሺንግተን ዲሲው የቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
ብፁዕነታቸው የቅ/ሲኖዶስን ተልዕኮ ለማስፈጸም ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ቢላኩም በሀ/ስብከቱ ሥር ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ጋር ተግባራዊ ግንኙነት ካለመመሥረታቸውም በላይ በተለምዶ “ገለልተኛ” ከሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት ጋር “በጋራ እንሥራ” በሚል ፈሊጥ መቀመጫቸውን ከገለልተኛው እና ራሳቸው ከመሠረቱት ቤተ ክርስቲያን አድርገዋል። “ሁሉም ልጆቼ ናቸው” ያሉት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በነገ ቅዳሜው የታኅሣሥ 7/2004 ዓ.ም ስብሰባ በሀ/ስብከቱ ሥር ያሉ አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት እንደማይገኙ የታወቀ ሲሆን ብፁዕነታቸው በግል ደብዳቤ ጭምር የጠሯቸው ከሀ/ስብከቱ አስተዳደር ውጪ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት እና አንዳንድ አገልጋይ ካህናት ይሳተፉ ይሆናል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። (የመጥሪያውን ደብዳቤ ሙሉ ቃል ከዚህ ጽሑፍ መጨረሻ ይመልከቱ)።

የጥሪው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የስብሰባው ዓላማ “ሃይማኖት እንዳይበረዝና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዳይፋለስ ለመጠበቅ አብረን በመመካከር እንድናገለግል” ለመወያየት የሚል ሲሆን አሳዛኝ በሆነ መልኩ ቀኖና እንዳይፈርስ ጥሪ የሚያደርጉት ብፁዕነታቸው ራሳቸው አስተዳደራዊ አንድነቷ የተጠበቀ ቤተ ክርስቲያንን በማገልገል በኩል ጥያቄ የሚነሣባቸው መሆኑ ነው። ለታላቁ የአበው ክብር ማለትም ለጵጵስና ሲበቁ ራሳቸው የመሠረቱትን ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር እንዲመራ ማድረጋቸውን ተናግረው፣ አስጨብጭበው፣ “ይደልዎ" አስብለው ቢሆንም ቃላቸውን ሳይጠብቁ ቀርተዋል። ታዲያ በጥቂቱ ሳይታመኑ በትልቁ እንዴት ሊታመኑ ይችላሉ? ይህንን ባለማድረጋቸው ቢወቀሱስ ቅር ሊላቸው ይገባልን? ምእመኑ የሚወቅሳቸው ስለሚጠላቸው ሳይሆን የሚከተሉት መንገድ የተሳሳተ መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባ ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የተተኩትን እና የምዕራብ ሐረርጌና ጂጂጋ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተመደቡትን ብፁዕ አብርሃምን ለመሸኘት የመሰናበቻ መርሐ ግብር መዘጋጀቱ ታውቋል። በምእመኑ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ቀኖና ጠበቃ ተደርገው የሚወሰዱት አቡነ አብርሃም መቀየራቸው ብቻ ሳይሆን የተተኩት ደግሞ ብፁዕነታቸው ለማስጠበቅ ይሞክሩ የነበሩትን የቤተ ክርስቲያን አንድነት በማይቀበሉ አባት መሆኑ ሐዘን መፍጠሩ ይታወቃል። (መጥሪያውን በመጨረሻ ያገኙታል)

15 comments:

Anonymous said...

This illegal "gubae" designed by aba Fanuel should be denounced by the true christians. This dived and rule system of aba fanuel was started in Awasa,however it was totally disqualified by the Awasa "miemenan". If aba fanuel sided to the right of our orthodox tewahido church, he would include all churches in his discussion forum.Therefore, we should be careful about his propaganda and secret agenda.

Anonymous said...

አባታችን "መታዘዝ ከመስዋዕትነት ይበልጣል" መታዘዞት መልካም ነው:: ግን ግልገሎቾን ጠቦቶቾን በጎቾን አይን ላወጣ ለምድ ላለበሰ ክፉ ተኩላ ዜግነት አምላኩ ለሆን በትነው አይሂዱ በእግዝትነ ማርያም እባክዎት በዚህ ኢጣሊያን ተመሳሳይ ችግር ተፈጥሮብን የነ በሩን አባት በግድ ሕዝቡ ሳይፈልግ ተጠርተው ሄደው በ2006 የተረበሸ ቤተ ክርስቲያናችን በነጻ ተሰጥቶን ስንገለገልበት የነበረ ከ2009 / 2011 አጋማሽ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተደጋጋሚ በተነሳ ግጭት ተዘግቶብን በችግር አሳልፈና ከዚህም የተመለሱት አባት አገር ቤት ሄደው በመከራና በችግር ላይ ናቸው ሰበካ ጉባኤ ሰንበት ተማሪዎች ለቤተ ክርስቲያ የምትቆረቆሩ ከእጃችሁ ሳይወጡ አስቡበት ጸልዩበት እግዚአብሔር በቃችሁ የሚለን መቼ ይሆን?

ዳን said...
This comment has been removed by a blog administrator.
Anonymous said...

+++

የሚስተካከሉ ስላልሆኑ መቀበል አልነበረባችሁም ነበር:: ትልቅ ፈተና ይሆኑባችኋል::

እግዚአብሔር ይርዳችሁ;

desa said...

Ke Abune Fanuel gena bizu gud eintebikalen.

Anonymous said...

mk why you criticize abune fanuel ? I think he is not accept you

Anonymous said...

I get a question?? our church had been in a great problems since its debut. Surprisingly almost all the problems are emanated from the top(fathers) not from the follower. Every time when the fathers go right we follow them when they move to the wrong direction we do so. But I am not sure if this is inscribed in the teaching of the church. What we have seen now a days is the same thing what we are used to see. When our religions fathers divided in to two major parts we, the members, do as we act before. when we see even "minor" division we can't ask and retrospect for awhile but we try to make it much wider,I do not know which principle's we are respecting,the rule of God or that of devil? I don't know who looted our mind? fear, power ignorance, money, or/and lack of knowledge? what ever the case is , in as far as we are departed from the truth and the source of the major problem we are going to face the same and the worst persistent destruction we are to face, leave alone to solve it. And it may not surprise to see tenth and hundredth of division in our church.this may be good news for the enemy of the church who works day and night for the demise of the church and a historical and moral corruption for some others.In which group do we belong. it is our choice!

Anonymous said...

Abune Fanueal is a hero. Btam turu
Abatna krestian nachew. lemne frisawiyanen aldegefum newu? woyis
seytanawi kinat newu? Ahune enanete
krstiyan nachehu? Egziabehare yikir
yebelachehu.

whether you like it or not a lot of Tewahedo Christiyans' Love Abune
Fanueale. What you can do about it?
Davil?

Anonymous said...

አይ ደጄ ሰላም የምታወሩት ሁሉ የጠላትና የቅናት ወሬ ነው። እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ።

Anonymous said...

Abune Abreham is deserve a lot of rewards from the church congregations. I am sorry to say Abune Fanuel has to be fired from our church. He is a source of antiorthodox...we don't need him!!!!!!!!! He is money minded and corrupted .. I have no power but I do believe God will disclose everything behind him. I know him very well at Awassa...God please help us and give us mercy.

Anonymous said...

እግዚአብሄር አንደሰው አድርጏ ፈጥራቸው አነርሱ ግን እራሳቸውን አያሳቱ ህሊና እንደሌለዉ አራዊት በመሆን የአባታቸውን የዲያቢሎስን ፍቃድ የሚፈዽሙት መሀመድዉያን ድርጊት በጣም ቢያሳዝነኝም በጣም ልቤን የነካኝና የደነቀኝ ነገር ቢኖር ግን ይሕ ሁሉ ሲፈፀም የሕግ አስከባሪ አካላት የአሸባሪዎችን ድርጊት አይተዉ እንዳላዩ በመሆን በወቅቱ እርምጃ አለመውሰዳቸዉ ነዉ ነገር ግን ይህ ለምን ይሆን??? ለመሆኑ አገራችን ዉስጥ ህግ አለ?? መንግስትስ?

በጎቼን ጠብቁ ብሎ ቅዱስ እግዚአብሄር አደራ የሰጣቸው አባቶችስ ቅዱስ ስጋዉና ክቡር ደሙ የሚፈተትበት እና የ ቅዱስ እግዚአብሄር ማደርያ የሆነዉ ቤቱ በወንበዴዎች ሲቃጠል ለምን ከልጆቻቸዉ ጋር በመሆን ጩኸታቸዉን አንሰማም?? ወይስ ከ እግዚአብሄር በላይ የሚፈሩትና ፍቃዱን የሚፈጵሙለት አካል አለ?

አሕዛብ ሆይ በከንቱ አትድከሙ ቤተክርስትያን እንደ ሆነ በክርስቶስ አለትነት ነዉና የተመሰረተችዉ አትጠፋም ከመውግያውም ጋ ለሚጣሉ በእነርሱ ይብሳል ይላል ቅዱሱ መፅሃፋችን

Gere3025

Anonymous said...

tbarku

Anonymous said...

tebarku

Anonymous said...

Dejeselam,please write about Abuna Fanuel's contribution for orthdox tewahido church. Therefore,every person knows, decides and confusion become neat.

Anonymous said...

pleas let's watch our mouth, there is a lot of things to do If we want to support our church. Protesting member of senodos is not good idea.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)