December 22, 2011

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዕንባ ተሸኙ


(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 11/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 21/2011/ READ IN PDF)፦ ቀደም ብሎ ለኒውዮርክ ቀጥሎም ለዋሺንግተን እና አካባቢው ሀ/ስብከት በሊቀ ጳጳስነት ተመድበው ሲያገለግሉ ቆዩትና በጥቅምቱ የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ወደ መዕራብ ሐረርጌ እና ጅጅጋ አህጉረ ስብከት የተዘዋወሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዕንባ ተሸኙ።
 ባለፈው ቅዳሜ ታኅሣሥ 7/2004 ዓ.ም (12/17/2011) በቨርጂኒያ ግዛት በተደረገላቸው የመሸኛ ዝግጅት ላይ ስንብት የተደረገላቸው ብፁዕነታቸው በምድረ አሜሪካ ቆይታቸው ስለነበረው ሁኔታ ማብራሪያ ከመስጠታቸውም በተጨማሪ በእርሳቸው መሔድ የተጀመረው አገልግሎት እንዳይቀዛቀዝ አባታዊ አደራ ሰጥተዋል።
በሀገሩ መንግሥት የሚታወቅ ሀ/ስብከት መመስረታቸውን፣ መንበረ ጵጵስና በሀገሩ አሠራር መሠረት መገዛቱን፣ ይህም ግዢ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሪፖርት መደረጉን፣ አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት መባረካቸውን፣ የአንድነት መንፈስ በምድረ አሜሪካ መፈጠሩን የዘረዘሩት ብፁዕነታቸው አሁንም ይኸው የአንዲት ቤተ ክርስቲያን መንፈስ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

በዕለቱ አስተያየታቸውን የሰጡ ከየአድባራቱ የመጡ አባቶች እና ምእመናን በዕንባና በሳግ በታፈነ ድምጽ ለብፁዕነታቸው ያላቸውን ፍቅር እና ለአገልግሎታቸው ያላቸውን ክብር አሳይተዋል። ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ከዋሺንግተን ዲሲ በተንቀሳቀሱበት በዛሬው ቀን ከአውሮፕላን ማረፊያ ሊሸኛቸው የመጣው ምእመን በፍቅር ዕንባ “ደህና ግቡ” ያላቸው ሲሆን በሐረር እና ጅጅጋ አህጉረ ስብከት ያለው አገልግሎት እንደ አቡነ አብርሃም ያለ አባት እንደሚአስፈልገው እግዚአብሔር ባወቀ የሆነ እንደሆነም በመሸኛ በዓሉ ላይ በተለያዩ ተናጋሪዎች ተወስቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በብፁዕ አቡነ አብርሃም ምትክ ለዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ተመድበው የመጡት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በበዓሉ ላይ ያልተገኙ ሲሆን ምንጮቻችን እንዳስረዱንም ከሀ/ስብከቱ አካላት ጋር በጋራ ሥራ አለመጀመራቸውም ታውቋል። ይልቁንም ‘ገለልተኛ’ የሚባሉ አብያተ ክርስቲያናትን እና አንዳንድ ካህናትን በግል በመጥራት “አብረን እንሥራ” ለማለት በመሞከር ላይ መሆናቸው ታውቋል።


16 comments:

abi said...

አይ ፍቅር አባታችን እግዚአብሔር ይጠብቅዎ “ደህና ግቡ”

yesu said...

Here you go true orthodoxawian.we have to learn............Abatachen Egziabher bemnegedwo hulu yitbekot.
Did you invite Abune fanuel?........WHY YOU SAID HE DIDN'T
COME.PLS....PLS..

Anonymous said...

It is East Harerge, not West harerge

Emuye said...

ብፁዕ አባታችን
በመንገድዎት ሁሉ እግዚአብሔር ይከተልዎት
አንድ ነገር ቃል እገባልዎታለሁ
በልቤ ዉስጥ የጫሩት የሐይማኖት ፍቅር መቸም ስለማይጠፋ፣ በማገለግልበት ቦታ ሁሉ እዉነተኛ የአብረሃም ልጅ ሆኜ አገለግላለሁ፡፡

ቡራኬዎት ይድረሰን!!!!!!!!

Haq tenagare said...

He should have been the arch bishop of all EOTC here in USA irrespective of the disagreement,not division, regarding mentioning aba paulos's name; since the only difference among the Churces, excluding those under 'sidetegna sinodos', is this matter. However, he exaggerated the problem as if it were being outside of the Church's unity or as if some sort of canonical and/or dogmatic differences exist. So, his assignment elsewhere could be better to find a lasting solution to this issue. And,I believe, Abune Fanuel's approach may bring about a change to the desired goal. So far what we have seen was just splitting Churches which, in my view, aggravated the problem, not addressing the issue properly. We wish him all the best in his future service. He is a hard working father,though. I like his quality of being relentless.

j said...

“በሌላዉ ሰዉ መሠረት ላይ እንዳልሠራ የክርስቶስ ስም በተጠራበት ስፍራ ሳይሆን ወንጌልን ለመስበክ ተጣጣርሁ፤....” ሮሜ 14፡20
አባ አብርሀም ሌሎች ባልሠሩበት መሠረት ላይ ለመሥራት የተጣጣሩ ብቻ ሳይሆኑ የሠሩ አባት ናቸዉ። በሰሜን አሜሪካ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት የሠራ አባት የለምና። ግማሹ ገለልተኛ ሌላዉ ስደተኛ በሚል ስም አንድ ሁለት አሥርት ዓመታት አስቆጥሯል።
በዚህ ላይ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት የተናገረን እየረገሙ ነበር የሰነበቱት። አባ አብርሀም ግን በቆዩባቸዉ ጥቂት ዓመታት መሠረትን መጣል ብቻ ሳይሆን አንጸዉ ነዉ ያለፉት። በተለይ በዚህ ዘመን እንዲህ ትጉህ ታላቅ ሐዋርያ ለቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል።
ይህ መልእክት መታሰቢያነቱ ለአባ አብርሃም ይሁን። በአበዉ ስም ተሰይመዉ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ለሠሩ በቆይታቸዉ ወቅት ቀና አገልግሎታቸዉን ተረድተዉ ላልተለዩአቸዉ ሁሉ ይሁን። በዚህ ዘመን መደማመጥ በራሱ ታላቅ ጸጋ ነዉ። አባ አብርሃምን የተጠጋ ጥሩ አድማጭ ይወጣዋል። ለሊቅ ለደቂቁ እኩል ጀሮ አላቸዉ ። በተለይ የዘወትር ትምህርታቸዉ የማትረሳ ፣ሁሉም ተቀብሎ ቢሠራ ዉጤት ያላት ከግብረ ሐዋርያት መዕራፍ 4፡32 “ ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸዉ....”። አባ አብርሃም ወደ ቅድስት ሀገር በመሄዳቸዉ ታድለዋል። የምሥራቅ ሐረርጌ ምእመናን እንዲህ አይነት ታላቅ አባት በማግኘታቸዉ ተመርጠዋል።
ብዕሩ ዘ-አትላንታ

ብዕሩ ዘ-አትላንታ said...

“በሌላዉ ሰዉ መሠረት ላይ እንዳልሠራ የክርስቶስ ስም በተጠራበት ስፍራ ሳይሆን ወንጌልን ለመስበክ ተጣጣርሁ፤....” ሮሜ 14፡20
አባ አብርሃም ሌሎች ባልሠሩበት መሠረት ላይ ለመሥራት የተጣጣሩ ብቻ ሳይሆኑ የሠሩ አባት ናቸዉ። በሰሜን አሜሪካ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት የሠራ አባት የለምና። ግማሹ ገለልተኛ ሌላዉ ስደተኛ በሚል ስም አንድ ሁለት አሥርት ዓመታት አስቆጥሯል።
በዚህ ላይ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት የተናገረን እየረገሙ ነበር የሰነበቱት። አባ አብርሃም ግን በቆዩባቸዉ ጥቂት ዓመታት መሠረትን መጣል ብቻ ሳይሆን አንጸዉ ነዉ ያለፉት። በተለይ በዚህ ዘመን እንዲህ ትጉህ ታላቅ ሐዋርያ ለቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል።
ይህ መልእክት መታሰቢያነቱ ለአባ አብርሃም ይሁን። በአበዉ ስም ተሰይመዉ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ለሠሩ በቆይታቸዉ ወቅት ቀና አገልግሎታቸዉን ተረድተዉ ላልተለዩአቸዉ ሁሉ ይሁን። በዚህ ዘመን መደማመጥ በራሱ ታላቅ ጸጋ ነዉ። አባ አብርሃምን የተጠጋ ጥሩ አድማጭ ይወጣዋል። ለሊቅ ለደቂቁ እኩል ጀሮ አላቸዉ ። በተለይ የዘወትር ትምህርታቸዉ የማትረሳ ፣ሁሉም ተቀብሎ ቢሠራ ዉጤት ያላት ከግብረ ሐዋርያት መዕራፍ 4፡32 “ ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸዉ....”። አባ አብርሃም ወደ ቅድስት ሀገር በመሄዳቸዉ ታድለዋል። የምሥራቅ ሐረርጌ ምእመናን እንዲህ አይነት ታላቅ አባት በማግኘታቸዉ ተመርጠዋል።
ብዕሩ ዘ-አትላንታ

Anonymous said...

Abatachen burakwote kalnbet yedersene endezeh yalu abatochene amelke kidusan abzeto yestene enate betekerstyane endenzeh yalu abatoche yasfelgwatalena Harrer memenane endet yalachu edelegochu nachu ega balenbet hager endet techegeren betekerstyane endemnehede ersu amelkachen yawekalen becha amelkae kidusane hulachenem leseha heywote yabekane.

Anonymous said...

በእውነት የአባታችንን ቀና ግብር ከምዕመኑ ፍቅር እና እንባ ማየት ይቻላል፣ ብጹዕ አባታችን በሄዱበት እግዚአብሄር ይምራዎ የዲሲ ምዕመናንና አጋልጋዮችም በታነጻችሁበት መሰረት ጽኑ አምላክ ያበርታችሁ!

Anonymous said...

ብፁዕ አቡነ አብርሃም እንባ ብቻ ሳይሆን ሌላም ቢደረግላቸው ምንም አይደለም፡ እርሳቸው ለአንዲት የተዋሕዶ ሀይማኖት ከሀገረ ሀገረ እየተዘዋወሩ የሰበኩ፣ ያስተማሩ ትጉህ እውነተኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሐዋርያ ነበሩ በመሄዳቸው ከልብ ብናዝንም የጀመሩትን ሕልማቸውን እውን ማድረግ ደሞ ከኛ ከመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ይጠበቅብናል ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳን።
ለብፁ አባታችን ለትጉሁ እረኛ
እንመሰክራለን ለተከሉት የአንድነት መሠረት ሁልጊዜ እኛ
ለቅድስት እናታችን እንዲሆኗት አለኝታና ዳኛ
እናውቃለን እኛ እንደሆኑ ታዛዥ ጸሎተኛ
ዘወትር እንመኛለን እንዲሰጦት እድሜውን ከጤና
እንዲጠብቋት ቤተክርስቲያንን ከችግር ፈተና
ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ሞያሌ ቦረና

እግዚአብሔር መረጦት እንዲሆኑ የሰላም ሰባኪ
ንገሩልን ለዓለም ብለው ሰላም ለኪ
አምላክ ይጠብቆት እንዲሰሩ ሥራ
የሐረር ሕዝብም ይሁን የሚራራ
እንዲተክሉ ሰላምን ከድሬደዋ እስከ ካራማራ
በጸሎትዎ አስቡን አብዝተው ዘውትር
የጀመሩትን ጅምር ለመፈጸም የምር

ቡራኬዎ አይለየን ዘወትር እንወድዎታለን መቼም እንደ እርስዎ ያለ አባት መቼም የምናገኝ አይመስለንም።
የዘወትር ልጆችዎ ከዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት

Anonymous said...

“በሌላዉ ሰዉ መሠረት ላይ እንዳልሠራ የክርስቶስ ስም በተጠራበት ስፍራ ሳይሆን ወንጌልን ለመስበክ ተጣጣርሁ፤....” ሮሜ 14፡20
አባ አብርሀም ሌሎች ባልሠሩበት መሠረት ላይ ለመሥራት የተጣጣሩ ብቻ ሳይሆኑ የሠሩ አባት ናቸዉ።

ብእሩ ዘ አትላንታ
for your information you you should visit
http://en.wikipedia.org/wiki/Abuna_Yesehaq
Abuna Yesehaq, born Laike Maryam Mandefro in Adwa, Ethiopia, 1933; died 29 December 2005 Newark, New Jersey, was a leader of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in the Western hemisphere.

Mandefro was born to an Orthodox Christian family, attended Christian school, and joined the priesthood. He was one of the clerics fortunate enough to be tutored personally by Emperor Haile Selassie I, the titular head of the Church.

In October 1959, the Ethiopian Orthodox Church officially established a branch in New York; Abba Laike Mandefro, as he was then known, was sent there in 1963 and was given the task of finding a more suitable building for the Church, which was purchased in 1966. Mandefro then returned to Ethiopia to seek assistance for renovations; unfortunately the building was taken by the New York City authorities in his absence.

With the assistance of Emperor Haile Selassie, and the Ethiopian consulate in New York, Mandefro returned to New York City and purchased another site for the Church in 1969.

In 1970 he was sent to Jamaica where he began to minister specifically to the Rastafari community, at the official invitation of Rasta elders including Joseph Hibbert, who was in turn named as a "Spiritual Organizer" by Mandefro. Many government officials and others in Jamaica were deeply disappointed that Abba Mandefro defended the Rastafarians' faith on many occasions, and that he baptised thousands of them, pointedly refusing to denounce their faith in Haile Selassie as the returned Christ. On the other hand, a large number of other Rastas were likewise disappointed because he would not baptise them in the name of the Emperor, but only in the name of Jesus Christ. This however did not disturb those Rastas who viewed Christ and Haile Selassie as one and the same, and readily underwent baptism at the hands of this man who had been sent from Ethiopia by their living God. Only after the Marxist Derg Revolution that toppled Haile Selassie and appointed their own Patriarch over the Church, did the requirement become enforced for prospective baptisees in Jamaica to renounce his divinity and cut their dreadlocks.

Abba Mandefro also founded many Orthodox Churches throughout the Caribbean and elsewhere, and received the title "Archbishop Yesehaq of the Western Hemisphere and South Africa" in 1979.

In the 1990s, a schism happened in the Orthodox Church when the new government of the EPRDF took power in Ethiopia and appointed their own Patriarch, Abuna Paulos. Abuna Yesehaq refused to recognise this political change, pointing out that according to the ancient Church canons, the Church leaders are to remain in office until they pass away, and cannot be dismissed or reappointed by any secular government. However, the New York City authorities took the side of the newly-appointed Patriarch, and police interrupted a Church service on 9 August 1998 with guns drawn, using profanity, handcuffed children, and took possession of the Church in the name of Abuna Paulos.
አላስፈላጊ ውዳሴ ከንቱ ጥሩ አይደለም
ካላወቁም ይወቁ ያንብቡ
ቃለ እግዚአብሄርን በአግባቡ እንጠቀም

Anonymous said...

abatachenen emeberehan edeme tena tesetachew esekahun baderegut melekam negeroch hulu kelebachen enamesegenalen behedubet hulu selame egzeabher ke abatachen gar yehun;;

Anonymous said...

abatachen burakewot balehubet yederesegn beselam gebu

Anonymous said...

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ሰው በሌለበት ሀገር ሰው ሆነው የተገኙ አባት...

“እኛ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ግን ቅዱስ አትናቴዎስ አርዮስን የረታባትን፣ ቅዱስ ቄርሎስ ተዋሕዶን ያብራራባትን ንጽሕት ቅድስት ሃይማኖት እስከ ሞት ድረስ ለመጠበቅ የታመንን እንሆናለን” ...

ብዕሩ ዘ-አትላንታ said...

December 22,2011 ስለ አባ አብርሃም በሰጠሁት አስተያየት ላይ "አላስፈላጊ ዉዳሴ ከንቱ ጥሩ አይደለም" ስላሉኝ
ከጅምሩ ማን ብዬ ለመጀመር ብቸገርም እንደርስዎ የታሪክ አዋቂነት ጠለቅ ብለዉ ሳያነቡ ስለሰጡት አስተያየት ግን የምለዉ ይኖረኛል
ስለ አባ አብርሃም የተገለጸዉ ጽሑፍ በመሠረቱ ወቅቱን ተንተርሶ የቀረበ ነዉ። “ በተለይ በዚህ ዘመን በማለት” ፤ በተጨማሪም “በአበዉ ስም ተሰይመዉ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ለሠሩ” የሚል ይገኝበታል ከዚህ በዘለቀ ግን ጸሐፊዉ በጎ ሥራ ስለሠሩ አባቶች ሳያዉቅ ወይም ደግሞ የሉም በማለት የደመደመዉ ነገር የለዉም። ጎበዝ ትችት ወይም ደግሞ አስተያየት መስጠት የሰፋ በጎ ጎን ቢኖረዉም ማጤን ጥበብ ነዉ። እዚህ ላይ አንድ ሰዉ ስለራሱ ዝና ሲደሰኩር ቢዉል ነዉ የሚያሳፍረዉ፤ መልካም የሠሩትን ሰዎች ማድነቅ ማበረታታት ግን አያስነቅፍም። ለሁለት አሥርት ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን ያቆሰሉ ያደሙ በእርሳቸዉ ዕድሜ ያሉ ከዚያም በላይ ያስቆጠሩ ያልሠሩትን ሠርተዋልና ሊመሰገኑ ይገባል። እንዲህ ማለት ደግሞ ስለ እዉነት እንደ ሻማ በርተዉ መልካሙን ዘመን እየናፈቁ ሞት የቀደማቸዉን መርሳት አይሆንብኝም።
በስደት ስም ቤተ ክርስቲያንን ያኮረፉ፣ በፍኖቱ ተከትበዉ ገለልተኛ የተባለዉን ተቋም የመሠረቱ እያሉ በዚህ መሀል ስለ አንድነትና ሰላም የሚያነባ አባት ማግኘት ምንኛ ድንቅ ነዉ። አባ አብርሃም እኮ ከዉስጥም ከዉጭም ሲጎሸሙ የሰነበቱ አባት ናቸዉ። ቢባልላቸዉ ምን ያስገርማል? መቻቻልን ከማ መማር እንዳለብን ሰይረዱ አይቀሩም፣ይቅር መባባልን በሕይወት ሆኖ ለማስተማር ከሃይማኖት አባቶች የበለጠ ማን? ስለ ፍቅር ለመሰዋትስ ከእነርሱ የበለጠ ማን ምሳሌ እንዲሆነን ነዉ?
ወደ አነሱበት ርዕሰ ጉዳይ ልመለስና የተኣፈዉ አጭር መልዕክት አሁን በአካል ካሉት ጋራ በንጽጽር ለማሳየት እንጂ ስለ ቀደሙት ለመተረክ አይደለም። ምክንያቱም የተተበተቡበት ገመድ ባይታወቅም ሊፈታ የሚችለዉን ችግር በማክረር የጸቡን ግድግዳ እየገነቡ ላሉት በሦስቱም ወገን ሰላለዉ ችግር ለመግለጽ ነዉ። ምናልባት ሳያጤኑ አይቀሩም። ፖለቲካ ሌላ ሃይማኖትና ቤተ ክርስቲያን ሌላ። ያኮረፈዉ በማን እና በምን እንደሆነ ለምእመኑ ግልጽ ባልሆነበት መንገድ ምእመኑ ሲተራመስ እና ተስፋ ሲያጣ እነርሱ አባት ተብዬዎቹ ተደላድለዉ ሲኖሩ ይስተዋላል። ሀገር ቤት ያለዉ የዉጭዉ እያሉ። በመሀል ግን የዓላዉያን ነገሥታትና የመናፍቃን እርስዎን ባለዉቅም መዘባበቻ የሆነችዉ ግን ቤተ ክርስቲያን ናት። ምናልባት ከተሰማዎትን ከተረዱት ……….
ለእኔ እንዳየሁትና እንደታዘብኩት በተመደቡበት ቦታ ተገቢዉን ሥራ የሠሩ እዉነተኛ ሐዋርያ ናቸዉ። ናቸዉ። ሊመሰገኑ ይገባል። ለእርሶ የምመክሮት ምናልባት ከተቀበሉኝ ሰዉን ባለበት በሕይወት ዘመኑ ስለሠራዉ በጎ ነገር ማመስገን ፤ ደካማ ጎኑን መንቀፍና አስተያየት መስጠት ቢለመድ መልካም ነዉ። ሲሠሩ በዉዳሴ ከንቱ ስም ፣ሲያጠፉ በዝምድና እያድበሰበስን የተጓዝንበት ዘመን ከእንግዲህ መብቃት አለበት። ከተግባባን የብዕሩ ምልከታ ይህ ነዉ። ቸር ይሰንብቱ….” የሐቅ ብዕር ሲመዘዝ ገንዘብ ተበድረህ መስታወት ግዛበት የሰዉን ተዉና የራስህ እይበት “ በዚህ ይቆዩኝ

Anonymous said...

Dear Haq Tenagare, "Haq" means truth does it not...then why do you speak in double tongues. Let the readers be aware. Bitsue Abune Abrham seems exaggerated only to those treat the current disunity of the church LIGHTLY. Regarding your comments "aggravated the problem", its your opinion so I will respect it, but my question is when you form these conclusions do you realize you may sound extremely ignorant? Bitsue Abune Abrham did not come to DC seeking a following to cause divisions my friend. We, those who were tired of seeing the E.O.T.C. being exploited by individuals, political and tribal groups, went to him in seeking his opinion and it so happened his vision and objective matched ours and many others in the area; hence three years later, 17 plus churches following the proper sereat. True divisions is of satan but let me remind you, it was the churches who chose to be outside the mother church of Ethiopia, ie outside synods, and geleltegna's who cause this divisions. There are problems with our mother church, but two wrongs don't make a right my friend. What Bitsue Abbatachin did was bless our church so we can follow the right sereat, our alama happened to be the same preserving the true image of the Church. So you think Abune Fanuel will do a better job??? Sorry I will disagree, why? Because he has already broken so many seratoch, and he has not even started his work as the archbishop of dc & ca. i will not detail them here. so please, don't say things you know little about...has abune fanuel pumped his vision into you??? sounds like it, you are praising his grace before seeing the work? We have see the work of Bitsue Abba Abrham, it speaks for itself, it was work of righteousness, it was work of unity, it was work of peace, it was true apostolic work...we have seen it, heard it, touched it and tasted it, we can confess that it was righteous. no one can knock the work His grace has done, so please dont be so quick to try discredit Bitsue Abba Abraham and give credit to Bitsue Abba Fanuel before BA Fanuel starts working...

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)