December 16, 2011

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚካሄዱ ግንባታዎች ከፍተኛ የሙስና ምንጭ እየሆኑ ነውአርእስተ ነጥቦችዶኩመንቶች
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 6/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 16/2011. READ IN PDF.)፦

  • ለድሬዳዋ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ ከጅምሩ አንሥቶ በሀገር ውስጥና በውጭ ከሚገኙ ምእመናን ከተሰበሰበው ብር 11.3 ሚሊዮን ውስጥ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ጉድለት መገኘቱን በምእመናን ምርጫ የተዋቀረው “የባለሞያዎች ተሟጋች ቡድን” እና የሰበካ ጉባኤው አባላት እየተናገሩ ነው
  •  ከሕንፃ አሠሪው ኮሚቴ ራሳቸውን ባገለሉ አባላት በቀረበ ጥያቄ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ቁጥጥር አገልግሎት ኦዲተሮች ባደረጉት ማጣራት ከብር 1.8 ሚሊዮን በላይ ለሕንፃ ሥራ ተቋራጩ አላግባብ መከፈሉን አረጋግጠዋል፤ “ተጠሪነቴ ለፓትርያርኩ ነው” በሚል ለሰበካ ጉባኤው የማይታዘዘው የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ክፍያው ከፓትርያርኩ በተሰጠ ትእዛዝ እንደተፈጸመ ገልጧል፤ ይኸው ሳይበቃ ሰሞኑን ወደ ድሬዳዋ ያመሩት የጠ/ቤ/ክህነቱ መሐንዲስ ለተቋራጩ ተጨማሪ ብር 900,000 እንዲከፈል ማዘዛቸው ተሰምቷል፤ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ በበኩሉ የነበረው ሒሳብ በተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ተመርምሮ ግኝቱ በይፋ እስኪገለጽ ድረስ የታዘዘውን ተጨማሪ ክፍያ በቀድሞው አሠራር መፈጸም ሕጋዊነት እንደማይኖረው አስታውቋል
  • ·         ምእመናን እና ካህናት የሕንፃ ግንባታውን ወጪ የሚያጣሩ ገለልተኛ ባለሞያዎችን ከመምረጣቸውም በላይ ምእመኑን በዐውደ ምሕረት ወሬኞች እና ዐመፀኞች” በማለት የዘለፉት የደብሩ አስተዳዳሪ፣ ጸሐፊና የስብከተ ወንጌል ሓላፊው ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ጠይቀዋል
  • የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት በበኩሉ የሕንፃ ግንባታውንና የደብሩን አጠቃላይ የሒሳብ ሪፖርት ለምእመናን አቅርበው አዲስ ምርጫ በማካሄድ ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ ያቀዱትን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት፣ “በቃለ ዐዋዲው የተወሰነውን የሥራ ዘመናችሁን አሳልፋችኋል” በሚል ከታኅሣሥ ሦስት ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ከሓላፊነታቸው አግዷል
  • የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ፣ የጠ/ቤ/ክህነቱ መሐንዲስ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ፣ የሕንፃ አሠሪው ኮሚቴ ሊቀ መንበር፣ የሕንፃው ተቋራጭ መሐንዲስና ሌሎች ግለሰቦች አላግባብ ከወጣው ወጪ የጥቅም ተጋሪዎች እንደሆኑ እየተነገረ ነው
  • የሕንፃው ግንባታው ከታቀደው ጊዜ ከአራት ዓመት በላይ ተጓቷል፤ በፓትርያርኩ ልዩ ትእዛዝ አላግባብ በሚፈጸም ክፍያ በውለታ ከተቀመጠው ገንዘብ በዕጥፍ ያህል ወጪ ቢሆንም የተጠናቀቀው የግንባታው 65 በመቶ ብቻ ነው፤ የሕንፃው ሥራም ከዲዛየኑ ውጭ የሆኑ ብልሹ ገጽታዎች ይታዩበታል፤ የሕንፃ ተቋራጩ ከሀገር መውጣቱ ተነግሯል
  • የአጥቢያው ካህናትና ምእመናን፣ የሀ/ስብከቱ ስምንት ሰንበት ት/ቤቶች በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ቸልተኝነት ማዘናቸውን ገልጸዋል፤ የድሬዳዋ ፍትሕ እና ጸጥታ ዘርፍ እንዲሁም ፖሊስ ኮሚሽን የደብሩን አስተዳደር ከምእመኑ ጋ ለማስማማት ጥረት እያደረጉ ነው
  • “ከዚህ በላይ ልንታገሥ አንችልም፤ ችግሩ ተባብሶ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ከማምራቱ በፊት የመረጥናቸው ባለሞያዎች የሕንፃውን ወጪ የማጣራቱን ሥራ ይጀምሩልን፤ የአቅም ማነስ ያለባቸውና የሰበካ ጉባኤውን ሥራ ሆነ ብለው እያደናቀፉ የመከፋፈል ተግባር የሚፈጽሙት የደብሩ አስተዳዳሪ[መልአከ ኀይል ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ቸኮል]፣ ጸሐፊው እና የስብከተ ወንጌል ሓላፊው በየመድረኩ የሚናገሩትን ዘለፋ አቁመው በአስቸኳይ ይነሡልን፤ የሕንፃ አሠሪው ኮሚቴ ምእመኑ በሚመርጣቸው አባላት ይተኩልን፤ ይህ ካልሆነ ለሚፈጠረው ችግር ሓላፊነቱን አንወስድም!!” /የደብሩ ሰበካ ጉባኤ፣ ሰንበት ት/ቤት እና ስብከተ ወንጌል አባላት በጋራ የተፈራረሙበት አቤቱታ/::
ከዚህ በታች ዶኩመንቶቹን ተመልከቱ።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)