December 14, 2011

በአርማጌዶን ቪሲዲ በጋሻው መ/ር ዘመድኩንን ከሰሰ


  • በጋሻው በጠ/ቤ/ክህነቱ ጥያቄ የተዘጋውን መዝገብ ለማንቀሳቀስ እየጣረ ነው::
  • “የተሻረው ደብዳቤ” - ወንጀለኛነት መያዣ የሆነበት የበጋሻው ድራማ::
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 4/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 14/2011/ READ IN PDF)፦:- መ/ር ዘመድኩን በቀለ አርማጌዶን ቁጥር አንድ ቪሲዲ ጋራ በተያያዘ በፌዴራል ዐቃቤ ሕግ የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ ቀረበበት፡፡ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩ በልዩ ሁኔታ ታይቶ መ/ር ዘመድኩን የዋስትና መብት ተነፍጎት ክሱን በማረፊያ ቤት ሆኖ እንዲከታተል ጠይቆ ነበር፡፡ የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው፣ በቪሲዲው ውስጥ የተዘረዘሩት ነገሮች በይዘታቸው ሃይማኖታዊ በመሆናቸውና ቪሲዲው ከፍ ላለ ሃይማኖታዊ ፋይዳ የተሠራ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን የማየት ሥልጣን እንደሌለውና በስም ማጥፋት ወንጀል ሊያስከስስ እንደማይችል በማስረዳት በክሱ ላይ መቃወሚያ አቅርበዋል፤ ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን መከራከሪያ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠትና ክሱ የሚቀጥል ከሆነ የምስክሮችን ቃል ለማዳመጥ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ታኅሣሥ ሦስት ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረበው የፌዴራል ዐቃቤ ሕጉ ቤተ ማርያም ዓለማየሁ የክስ ጽሕፈት እንደሚያስረዳው፣ “ተከሳሽ መ/ር ዘመድኩን በቀለ በግል ተበዳይ [በጋሻው ደሳለኝ] ክብር እና መልካም ስም ላይ ከባድ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ በአራዳ ክ/ከ ቀበሌ 03/09 በሚገኘው ጌልጌላ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት በተከሳሽ ተዘጋጅቶ ለሽያጭ በቀረበው ‹አርማጌዶን ቁጥር አንድ› ቪሲዲ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች፡- አጉራ ዘለል ሰባኪ ነው፤ ተሐድሶ ነው፤ የክሕደት ስብከት ነው የሚሰብከው፤ በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ላይ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ትምህርት ያስተምራል፤ ራሱን በራሱ በመሾም የቤተ ክርስቲያን መምህር መሆኑን ለማሳየት የሚጥር ነው፤ እና ሌሎችንም ቀደም ሲል በወጣው አርማጌዶን የቴፕ ካሴት ውስጥ የግል ተበዳይን መልካም ሰብእና የሚያጎድፉ ንግግሮችን ለሦስተኛ ወገኖች አሳትሞ ያቀረበ በመሆኑ በፈጸመው የስም ማጥፋት ወንጀል ተከሷል፤” ይላል፡፡
የተከሳሽ ጠበቃ አቶ ጌትነት የሻነህ ክሱ የደረሳቸው ከሦስት ቀናት በፊት ዘግይቶ በመሆኑ መከላከያ ምስክሮቻቸውን ለማሳወቅ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፤ በክሱ ላይ ያላቸውንም መቃወሚያ በአራት ነጥቦች ለይተው አስረድተዋል፡፡ ስሜ ጠፍቷል ለሚል የግል ተበዳይ ዐቃቤ ሕግ ሊቆምለት የሚችለው ተበዳዩ ሕግ አውጪና የመንግሥት ባለሥልጣን ሲሆን እንጂ ከዚህ በቀር ግለሰቦችና ድርጅቶች በግላቸው ጠበቃ ማቆም እንደሚገባቸው፤ በክሱም ይሁን በቪሲዲው የተዘረዘሩት ነገሮች ሃይማኖታዊ በመሆናቸው ፍ/ቤቱ ጉዳዩን የማየት ሥልጣን እንደሌለው፤ በቪሲዲው ውስጥ አዘጋጁ የግል ተበዳይን ተችተው እንጂ ፈርደው/ወስነው እንዳልተናገሩ፤ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 547 መሠረት ለሕዝብ የላቀ ፋይዳ ላሏቸው ጥቅሞች ሲባል በቪሲዲው እንደቀረቡት ዐይነት ሥራዎች ሊሠሩ እንደሚችሉ ጠበቃው ገልጸዋል፡፡
ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ በተከሳሽ የተፈጸመው ከፍተኛ የስም ማጥፋት በደል መሆኑን፣ “ከቅዱስ ሲኖዶስ የተላከላቸው” ሁለት ገጽ ደብዳቤ/የሃይማኖት ሕጸጽ አለባቸው የሚባሉ ግለሰቦችን ቅዱስ ሲኖዶስ አረጋግጦ ሳይወስንና አውግዞ ሳይለይ ማንም ሰው በይፋ መቃወም እንደማይችል የሚያዝዘው የፓትርያሪኩ ደብዳቤ ማለታቸው ነው/ መኖሩን ቪሲዲውን እያሠራጨ መሆኑን በመጥቀስ ክሱ እንዲቀጥል ተከራክሯል፤ ከዚህም አልፎ የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ ዋስትና የማያስከለክል ቢሆንም ተከሳሽ “በጀመርኹት ተግባር እቀጥልበታለሁ” በማለት የግል ተበዳይ የበለጠ ተቀባይነት እንዲያጡ ስላደረገ በማረፊያ ቤት ቆይቶ ጉዳዩን እንዲከታተል ችሎቱን ጠይቀዋል፡፡
ዋስትና ሕገ መንግሥታዊ መብት መሆኑን ያስረዱት ዳኛው ገና ለገና ሊያደርጉት ነው በሚልና ባልተፈጸመ ወንጀል ተከሳሽን የዋስትና መብት ለመንፈግ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ተከሳሽ የብር 3000 ዋስ አቅርበው እንዲወጡ ትእዛዝ ሰጥቷል፤ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 613/3/ የተመለከተውን ክስ በመተላለፍ ስለተመሠረተው ክስ አግባብነት በቀረቡት የግራ ቀኝ ሙግቶች ላይ ውሳኔ ለመስጠትና ክሱ የሚቀጥል ከሆነ የምስክሮችን ቃል ለማድመጥ ለታኅሣሥ ዘጠኝ ቀን 2004 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በዐቃቤ ሕግ ክስ የማስረጃ ዝርዝር ውስጥ የሰው ምስክር ሆነው የቀረቡት፡- ራሱ በጋሻው ደሳለኝ“ተሐድሶ የለም” በሚለው ንግግሩ የሚታወቀው፣ ምስጢረ ተዋሕዶን በማኪያቶ መስሎ ‹ያስተማረው›፣ በመጨረሻም ሕገ ወጥ ቡድኑን የተቀላቀለው ታሪኩ አበራ“ተሐድሶ ማለት እኔ ነኝ” ብሎ ያወጀው አሰግድ ሳህሉያሬድ በቀለ እና የአንድ ፕሮቴስታንት ፓስተርን መጽሐፍ በራሱ ስም ከማሳተም አልፎ “ዛሬ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋራ እናስተዋውቃችኋለን” በሚል ንግግሩ የሚታወቀው ናትናኤል ታምራት - እንደ ቅደም ተከተላቸው ናቸው፡፡ ፖሊስ ከመ/ር ዘመድኩን መኖሪያ ቤትና መዝሙር ቤት የሰበሰባቸው 114 አርማጌዶን ቪሲዲ እና 386 አርማጌዶን ካሴት በኤግዚቢትነት መያዛቸውን በክስ ጽሕፈቱ ላይ ተገልጧል፡፡
በሌላ በኩል በጋሻው ደሳለኝ - መ/ር ዘመድኩን በቀለ ለማራኪ መጽሔት ከሰጠው ቃለ ምልልስ፣ ዲያቆን ደስታ ጌታሁን “የሰባኪው ሕጸጽ” በሚል ርእስ ካሳተመው መጽሐፍ ጋራ በተያያዘ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት የተመሠረተባቸውንና ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለፍትሕ ሚ/ር ባቀረበው ጥያቄ የተቋረጠውን ክስ ዳግመኛ ለማንቀሳቀስ እየጣረ ነው፡፡ ከዚሁ ጋራ በተያያዘም ሁለቱ ተከሳሾች በክፍለ ከተማው ፖሊስ በተደረገላቸው ጥሪ ነገ ታኅሣሥ አራት ቀን ጠዋት ቦሌ ምድብ ችሎት እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡
መ/ር ዘመድኩንና ዲያቆን ደስታ ኅዳር አንድ ቀን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት የዋና ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ባቀረቡት ማመልከቻ፡- በዐቃቤ ሕግ የተመሠረተባቸው ክስ ሃይማኖታዊ ይዘት ስላለው፣ በሌላም በኩል የግል ተበዳይ የተባለው ግለሰብና መሰሎቹ ሃይማኖታዊ አቋም በቅዱስ ሲኖዶስ እየታየ በመሆኑ ክሱ እንዲቋረጥ በጠየቁት መሠረት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለፍትሕ ሚ/ር በቀን 1/02/2004 ዓ.ም በቁጥር 1/218/2004 በጻፈው ደብዳቤ ክሱ ተቋርጦ መዝገቡ እንዲላክለት ጠይቋል፡፡ በዚህ መሠረት በሚ/ር ዴኤታው ብርሃኑ ጸጋዬ ስም በወጣ ደብዳቤ ክሱ ተቋርጦ መዝገቡ መመለሱ በቀን 4/03/2004 በቁጥር 02/ደህ-8021/04 የተጻፈው ደብዳቤ ያመለክታል፡፡
ይሁንና እነበጋሻው ደሳለኝ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አንድ መምሪያ ውስጥ በሓላፊነት የተቀመጠን ሙሰኛ ግለሰብ በጥቅም አግባብተውና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአንድ ክፍል ሓላፊ የሆነና በሌላ ከባድ ወንጀል የሚፈለግን ግለሰብ በፈጸመው ወንጀል አስፈራርተው ክሱ እንዲቋረጥ ለፍትሕ ሚ/ር በጽሑፍ ጥያቄ ያቀረቡትን ብፁዕ አቡነ ፊልጶስን የተሳሳተ ተግባር እንዲፈጽሙ ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡ እንደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ጥቆማ እነ በጋሻው የተጠቀሙት ግለሰቡ ለዋና ሥራ አስኪያጁ አለው የሚባለውን የመንፈሳዊ ልጅነት ቀረቤታ ነው፡፡ ግለሰቡ በዚህ ቀረቤታው ብፁዕነታቸው በፊርማቸው አጽድቀው ያወጡትን ደብዳቤ “አላውቀውም” ብለው እንዲናገሩ በማግባባት ይህንንም በድምፅ በመቅረጽ፣ የተቀረጸው ቃል በነበጋሻው አማካይነት ለሚኒስትር ዴኤታው እንዲቀርብላቸው ተደርጓል፡፡
ሚ/ር ዴኤታው ብፁዕነታቸውን በስልክ ባነጋገሯቸው ጊዜም ተመሳሳይ ምላሽ በመሰጠቱ ሚኒስቴሩ ኅዳር አንድ ቀን የተጻፈውን ደብዳቤ እውነታነት የሚያጣራ ልኡክ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መላኩ ታውቋል፤ ልዑኩም የተከሳሽ አመልካቾች ደብዳቤ ገቢ የሆነበትንና የዋና ሥራ አስኪያጁ ደብዳቤ ወጪ የሆነበትን የመዝገብ ቤት ፋይሎች ሂደት በማረጋገጥ ክሱ እንዲቋረጥ ለሚኒስቴሩ ጥያቄ የቀረበበት መንገድ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጧል ተብሏል፡፡ ይህም ሆኖ ሚ/ር ዴኤታው ክሱ እንዲቀጥል ለቦሌ ምድብ ችሎት ትእዛዝ የሰጡበት መንገድ ግልጽ አለመሆኑን ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት፡፡
ይህንን ጉዳይ የተመለከቱ ዶኩመንቶችን ከPDF ይመልከቱ

5 comments:

Anonymous said...

SAMAETENATE NAWE KATAHADESO GARA MATAGALE.AMELAKA GIORGEIS WAGACHEHONE YABEZALACHOHE.YAORTODOX TEWAHEDO LEJOCHE

Anonymous said...

ahunis wushet ayiselechachihum beshitegnoch nachihu. pls erefit situn yeenaniten yewushet tarik mesimat selichitonal. zemedikun enidehone wagawun yagegnal atiterateru. yeegiziabiher kal degimo hulem hiyawu new.

Anonymous said...

so what is wrong if he said that let us introduce Jesus. you guys are out of the line, our lord Jesus is the road to take us to the Almighty of God.

Anonymous said...

alemawokihin satawuk asiteyayet batiset tiru new, mejemeriya erasihin ashenif, degimos man anibib aleh yihen website, erefit bemidir layi yelem, maref kefelek nisiha giba, kebalebetu belayi yawoke buda new alu, yewushetu kuncho erasih honeh atiwashu tilaleh endie, anten bilo mekari, yeliji sira atisira, yemenafik website hedeh eziya asiteyayet sit, yemayimeleketihin atizebarik, zzebaraki neger neh

Anonymous said...

ያበጣም ያሳዝናል!!!!!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)