December 4, 2011

የግብረ ሰዶማውያኑን ስብሰባ የተቃወሙ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ታስረው ተለቀቁ

  • ወጣቶቹ ከካዛንቺስ እና አካባቢው የተሰባሰቡ ናቸው ተብሏል
  • ተቃዋሚዎቹ በመፈክር መልክ ከያዟቸው ኀይለ ቃሎች መካከል “ግብረ ሰዶም ኀጢአት ነው!”፤ “ግብረ ሰዶም የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው!”፤ “ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በግብረ ሰዶማውያን አትረክስም!”፤ “[የወንጀል ሕጉ] አንቀጽ 629 ይከበር!” የሚሉ ይገኙበታል
  • ግብረ ሰዶማዊነት ለረጅም ጊዜ ከአእምሮ በሽታ ዝርዝር ተደምሮ የቆየ ነው
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 23/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 3/2011):- የዓለም ኤድስ ቀንን ምክንያት በማድረግ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና አባላዘር በሽታዎች ላይ አተኩሮ ከሚካሄደውና ኢትዮጵያ ከነገ ኅዳር 24 - 28 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ ከምታስታናግደው 16ው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ቀደም ብሎ ዛሬ ኅዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም የተካሄደውን የግብረ ሰዶማውያኑን ስብሰባ የተቃወሙ ወጣቶች ለአንድ ሰዓት ያህል ታስረው መለቀቃቸው ተሰማ፡፡

200 ተሳታፊዎች እንደተገኙበት የተገለጸውና ቅዳሜ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን - የተባበሩት መንግሥታት የስብሰባ አዳራሽ ሲካሄድ የዋለው ይኸው ስብሰባ አምሸር - AMSHeR (The African Men for Sexual Health and Rights) የተባለ ከ13 የአፍሪካ አገሮች በተውጣጡና ግብረ ሰዶምን በግለሰብ ሰብአዊ መብት ላይ የተመሠረተ በጎ ምግባር አድርገው በሚወስዱ 15 ድርጅቶች የተቋቋመ ቡድን የተዘጋጀ ነው፡፡ የዛሬው ስብሰባ 200 ያህል ግብረ ሰዶማውያን በጋራ የተሳተፉበትና ለሦስተኛ ቀን የተካሄደ የማሳረጊያ ስብሰባ ሲሆን ኅዳር 21 እና 22 ቀን 2004 ዓ.ም በተለያየ ደረጃ ተመሳሳይ ስብሰባዎች በዚያው የኢ.ሲ.ኤ - ተ.መ.ድ የስብሰባ አዳራሽ ሲካሄዱ መቆየታቸው ታውቋል፡፡ 
“ለግብረ ሰዶማውያኑ አዲስ ትብብር ለመፍጠር እና ለማቀናጀት፣ ልምድን ለማዳበር፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስፋፋት እና ለሚቀጥለው ትውልድ ይህንኑ ዘይቤ ለማስተላለፍ” የሚል ዓላማ የያዘውን ይህን ስብሰባ ዛሬ የተቃወሙት ወጣቶች ቁጥራቸው 15 ያህል እንደሚደርስ ተገልጧል፡፡ ተቃዋሚዎቹ ዛሬ ጠዋት 2፡00 ላይ በመጀመሪያ ያመሩት ቀደም ሲል ስብሰባው ይካሄድበታል ወደተባለውና ቅርንጫፉ ካዛንቺስ ወደሚገኘው ጁፒተር ዓለም አቀፍ ሆቴል ነበር፡፡ ይሁንና የሆቴሉ አስተዳደር የተጠቀሰው ስብሰባ በሆቴሉ እንደማይካሄድ ለአንዳንድ የሚዲያ አካላት በመግለጹ ይህንኑ ዘግይተው የተረዱት ተቃዋሚዎቹ በአቅራቢያው ወዳለው ኢ.ሲ.ኤ - ተ.መ.ድ አቅንተዋል፡፡
ወጣቶቹ በኀይለ ቃል ያሰሟቸው ከነበሩት መፈክሮች ውስጥ “ግብረ ሰዶም ኀጢአት ነው!”፤ “ግብረ ሰዶም የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው!”፤ “ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በግብረ ሰዶማውያን አትረክስም!”፤ “[የወንጀል ሕጉ] አንቀጽ 629 ይከበር!” የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ይሁንና ከቀኑ 5፡30 ላይ ከ15 ተቃዋሚዎች መካከል “በዋናነት አስተባረዋል” የተባሉ ሰባት ወጣቶች ሲቪል በለበሱ የጸጥታ ኀይሎች ተለይተው ካዛንቺስ ቶታል አካባቢ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰዱ በኋላ 7፡50 ላይ መለቀቃቸው ታውቋል፡፡ ወጣቶቹ በጣቢያ ቆይታቸው ያለፈቃድ የተቃውሞ ሰልፉን ለምን እንዳደረጉ፣ ስለ ስብሰባው መረጃውን ከየት እንዳገኙ መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡
ስለ ስብሰባው በሚዲያ መስማታቸውንና ተሳታፊዎቹ ባሉበት ወይም በሚሰሙበት አኳኋን ተቃውሟቸውን ማሰማት እንደሚሹ ወጣቶቹ ላቀረቡት ጥያቄም “ከጀርባ ሌላ ዓላማ ከሌላችሁ በቀር ፈቃድ አውጥታችሁ መቃወም ትችላላችሁ፤ ይሁንና ይህን ስብሰባ እንኳን እናንተ እኛም እንድናውቀው አልተፈቀደም” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው አመልክተዋል፡፡ በዘመነ መሳፍንት እስራኤላውያን ግብረ ሰዶማዊነትንና ግብረ ሰዶማውያንን ለመከላከል ባሳዩት ቁርጠኝነትና በከፈሉት መሥዋዕት ችግሩን ከኅብረተሰቡ ማጥራታቸው ይታወሳል/መሳ.19፣ 22 - 28፤ 1ኛነገሥ. 14፣ 22 - 24፣ 46፤ 15፣10/፡፡
በሌላ በኩል በዓለም አቀፍ የበሽታዎች ዝርዝር መግለጫ /International Classification of Diseases 1 - 9/ICD ላይ ግብረ ሰዶማዊነት እንደ በሽታ ተቆጥሮ ለብዙ ዓመታት ሰፍሮ እንደ ኖረ ዩናይትድ ፎር ላይፍ ኢትዮጵያ “ግብረ ሰዶማዊነት - ተፈጥሮ? የምኞት ሸለቆ? መብት? የዝሙት ከፍታ ጫፍ?” በሚል ርእስ ያሳተመው መጽሐፍ ገልጧል፡፡ መጽሐፉ ጨምሮ እንዳተተው በአሜሪካ በአእምሮ ሕክምና ማኅበር “ግብረ ሰዶማዊነት ከአእምሮ መዛባት የተነሣ የሚፈጠር በሽታ ነው” ተብሎ ስለሚቆጠር በአእምሮ በሽታዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝግቦ እንደነበር አመልክቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከሁለቱም ስፍራዎች ከበሽታዎች ዝርዝር ውስጥ እንዲሰረዝ መደረጉን፣ ይህም በመስኩ የበርካታ ሊቃውንትን ተቃውሞ ቀስቅሶ እንደነበር አትቷል፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት ከአእምሮ በሽታ ዝርዝር ውስጥ ሲሰረዝ የቀረበው ምክንያት፡- “አንድ ሰው ግብረ ሰዶማዊ መሆን ወይም አለመሆን የራሱ መብት ነው” በሚል “Right Based Approach” እንደነበር ጨምሮ ጠቅሷል፡፡
ለግብረ ሰዶማዊነት ጥብቅና የቆሙ ወገኖች “እንደዚህ ተወልደናል” (Born that way) የሚለውን የግብረ ሰዶማውያን ኀልዮት በመጥቀስ ግብረ ሰዶማዊነትን ጄኔቲካዊ ውርስ ለማድረግ ቢጥሩም በርካታ ሳይንሳዊ ጥናቶች በአእምሮ ጤና መዛባት እና በግብረ ሰዶማውያን መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዳለ አረጋግጠዋል፡፡  (Neil Whitehead, Ph.D. & Briar Whitehead) የተባሉ ተመራማሪዎች በጻፉት My Genes Made Me Do It! - A Scientific Look At Sexual Orientation በተሰኘ መጽሐፋቸው እንደገለጹት ራስን ማጥፋት፣ ግራ የመጋባት፣ የጠባይዕ ተለዋዋጭነት፣ የአደንዛዥ ዕፆች እና የአልኮል ሱሰኝነት፣ ማኅበራዊ ሕይወትን መፃረር እና ከፍተኛ ወንጀሎችን በተደጋጋሚ መፈጸም የመሳሰሉት ብዙ ችግሮች በግብረ ሰዶማውያን ላይ ጎልተው የሚታዩ ችግሮች ናቸው፡፡ ሳይንሱ ይህን ቢልም ገና ጥንት በቅዱስ መጽሐፍ ግብረ ሰዶማዊነት በተፈጥሯዊ እውነት ላይ የማመፅ ተግባር መሆኑንና ውጤቱም ሰዎች እርስ በርስ በፍትወት ለሚቃጠሉበት ለማይረባ እእምሮ ተላልፎ መሰጠት መሆኑ ተገልጧል፡፡/ሮሜ 1፣18፤ ዘሌዋ 20፣13፤ 18፣ 22-23፤ 24 - 28/።

 

በግብረ ሰዶማውያኑ ስብሰባ ላይ የሚሰነዘረው ተቃውሞ እየተጠናከረ የመጣ ሲሆን ዛሬ ታትመው የወጡት ፍትሕ እና አዲስ አድማስ ጋዜጦች የአገሪቱን ሕግ በማጣቀስ፡- ግብረ ሰዶም በኢትዮጵያ መቼም ሕጋዊ እንደማይሆን፣ የሃይማኖት ተቋማት ብዙ ሥራ እንደሚጠበቅባቸው መንግሥትም የሕዝቡን ሞራላዊ ክብር የማስጠበቅ ሕገ መንግሥታዊ ግዴታ እንዳለበት የሚያሳስቡ ጽሑፎችን ይዘው ወጥተዋል፡፡
                       
የግብረ ሰዶማዊነት ነገር
(አዲስ አድማስ፤ ኅዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም)
/አበባየሁ ለገሠ/
ግብረ ሰዶማዊነት ኢትዮጵያ ውስጥ መቼም ቢሆን ሕጋዊ አይሆንም፡፡ በዚህ ድርጊት ውስጥ ያሉ ማረፊያ ስለሚፈልጉ ቢስፋፋላቸው ይወዳሉ፡፡ አንድ ሰው ጤናው ሲጓደል ከሕመሙ ለመፈወስ ጥረት ያደርጋል እንጂ ለሌሎቹም ይዳረስ አይባልም፡፡ ለዚህም የአገሪቱን መንግሥታዊ የጸጥታ እና የፍትሕ ተቋማት እንዲሁም ሀብት ጥቅም ላይ አያውልም፡፡
ባለፈው ማክሰኞ ይህን ድርጊት በመቃወም መግለጫ ለመስጠት የተሰባሰቡ የሃይማኖት ተቋማት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩን መገኘት ምክንያት አድርጎ በተፈጸመ ውይይት መግለጫው ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ከግል ሚዲያዎች ዜና ለመረዳት ተችሏል፡፡ ዋናው ጉዳይ የሃይማኖት ተቋማቱም ሆኑ ሌሎች የሚመለከታቸው ሁሉ ድርጊቱን ተቃውመው አቋም እንዲይዙ ነው የሚጠበቀው፡፡
የግብረ ሰዶማዊነትን ነገር ከጤና ክፍተት ጋራ መመልከቱ የተሻለ ነው፡፡ ከመብት አንጻር የሚጠየቀው የሌሎችን ጤናማ መብት ለመጣስ የሚመች በመሆኑ ነው፡፡ ከፍተኛ የሆነ የጠባይዕ ለውጥ የሚያስከትል ስለመሆኑ በርካታ ጥናቶች ያረጋገጡ ሲሆን መብት ይሁን ቢባል ተዘርዝረው የማያልቁ ቀውሶች እንደሚከሠቱ ላፍታም መጠራጠር አያስፈልግም፡፡ ግብረ ሰዶማዊነትን የማስፋፋት አካሄድ በገንዘብ እና የፖሊቲካ ሥልጣንን በሽፋንነት በመጠቀም፣ እንዲሁም የድርጊቱን ተቃዋሚዎች ደግሞ በማዋከብ እና የሰላማዊ ኑሮ ዋስትና በማሳጣት በተግባር የሚደገፍ ስለመሆኑ እየታወቀ መጥቷል፡፡
ከውጭ የሚመጡ የተወሰኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የሌሎች አገሮች ዜጎች በዚህ ችግር ውስጥ ነው ያሉት፡፡ ገንዘብ ይዘው የሚንቀሳቀሱት በተለይ በየጎዳናው ካሉ ኢትዮጵያውያን የተወሰኑትን ማግኘት ስለሚችሉ ነው፡፡ ሀብቷን መጠቀም ያልቻለች ሀገር ለባሕር ማዶ ርዳታ እና ፖሊቲካዊ ግንኙነት ሲባል ዜጎቿ እንዲቸበቸቡ መፍቀድ የለባትም፡፡ “ሳይቃጠል በቅጠል”ን መተረት እንጂ ለተወሰኑ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እጇን ለመስጠት እየከጀለች ከሆነ፣ እንዲስፋፋ ምክንያት የሆኑት ምግባረ ብልሹ ዜጎች፣ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች አካላት ሊያስቡበት ግድ ይላል፡፡
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ይህን ድርጊት አይቀበለውም፡፡ ሕገ መንግሥቱ የበላይ ሕግ ነው፡፡ ማንኛውም የመንግሥት ባለሥልጣን ይሁን አካል፣ ልማዳዊ አሠራር ከዚህ ሕገ መንግሥት ጋራ የሚቃረን ከሆነ ተፈጻሚነት እንደሌለው በአንቀጽ 9(1) ላይ ተመልክቷል፡፡ ይህ ግን አልተፈጸመም፡፡ “ማንኛውም ዜጋ፣ የመንግሥት አካል፣ የፖሊቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማኅበራት እንዲሁም ባለሥልጣኖቻቸው ሕገ መንግሥቱን የማስከበርና ለዚሁ ሰነድ ተገዢ መሆን አለበት፤” ይላል በአንቀጽ 9(2)፡፡ እውነታው ይህ ነው?
. . . ግብረ ሰዶማዊነትን መቃወም የኅብረተሰቡን ጤንነት መጠበቅ ነው፡፡ ደኅንነት ነው፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 91(1) መሠረት መሠረታዊ መብቶችንና ሰብአዊ ክብርን፣ ዴሞክራሲንና ሕገ መንግሥቱን የማይቃረኑ ባህሎችና ልማዶች በእኩልነት እንዲጎለብቱና እንዲያድጉ የመርዳት ሓላፊነቱ የመንግሥት ነው፡፡
የጋብቻ ሥርዐትም ቢሆን በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 34(1 መሠረት በወንዶች እና በሴቶች መካከል የሚፈጸም ነው እንጂ በተመሳሳይ ጾታ መካከል አይደለም፡፡ ቤተሰብ መመሥረት የሚቻለው በወንድ እና በሴት መካከል ካለው ግንኙነት መነሻነት በመሆኑ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 34(3) መሠረት ከኅብረተሰቡና ከመንግሥት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው፡፡
በ1992 ዓ.ም የፌዴራል የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግም ቢሆን ከአንቀጽ 1 - 4 ድረስ የብሔራዊ፣ የሃይማኖት እና የባህል ሥርዐትን መሠረት ያደረጉ ጋብቻዎች በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት መካከል የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ የተፈጸመው ጋብቻ ከኢትዮጵያ ውጭ ቢሆን እንኳ የሕዝብን ሞራል የሚቃረን ከሆነ በዚህ ዐዋጅ ቁጥር 213/92 ዓ.ም አንቀጽ 5 መሠረት ተቀባይነት የለውም፡፡ ግብረ ሰዶማዊነትን መሠረት ያደረገ ጋብቻ ደግሞ በኢትዮጵያ የቤተሰብ ሕግ ውስጥ ቦታ የለውም፡፡
ግብረ ሰዶማውያን(ሁሉም ባይሆኑም) የተወሰኑት ድርጊቱን ለማቀበል በመልካም አስተሳሰብ የላቸውም፡፡ ይህንንም በተለያዩ መንገዶች ለመግለጽ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ መልካም መንገዶችን ለመግፋት ሞክረዋል፡፡ ከሕገ መንግስቱ በተጨማሪ ግብረ ሰዶማዊነት በግልጽ በኢትዮጵያ የተከለከለ መሆኑን ተሻሽሎ እንዲደነገግ ማድረግ፣ የወንጀል ሕጉ በቂ ሆኖ ካልተገኘ ራሱን የቻለ ዐዋጅ ማዘጋጀት፣ ይህን ጥፋት ለማስፋፋት የሚሞክር ማንኛውም የባለሥልጣን ሓላፊነቱን እንዲያስረክብ፣ ማንኛውም ተቋም በዚህ ድርጊት ውስጥ ከተገኘ እንዲዘጋ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የሃይማኖት ተቋማትም ብዙ ሥራ መሥራት ይጠብቃቸዋል፡፡

        ሕገ መንግሥቱ ይከበር፤ ሞራላችንም ይጠበቅ
/ፍትሕ፣ ኅዳር 22 ቀን 2004 ዓ.ም/
(አንተነህ ደረሰ)

ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኀን ለመረዳት እንደቻልነው ኢትዮጵያ በኡች.አይ.ቪ/ኤድስ ላይ የሚካሄደውን 16ው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡ ከዚህ ኮንፈረንስ ቀደም ብሎ ግን ወንድ ግብረ ሰዶማውያን በአፍሪካ ሕጋዊ ዕውቅናና ከለላ እንዲያገኝ የሚሠሩ ግለሰቦችና ዓለም አቀፍ ተቋማት በመጪው ቅዳሜ(ዛሬ፣ ኅዳር 23 ቀን) በመዲናችን አዲስ አበባ ጉባኤያቸውን ለማካሄድ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡
ጉባኤው ከአገሪቱ ሕግ አንጻር እንዴት ይታያል? ግብረ ሰዶማዊነት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ምን ማለት ነው? ጉባኤው በሀገራችን መካሄዱ ምን አንድምታ አለው? የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሣታችን አይቀርም፡፡ የመጨረሻውን ጥያቄ ለአንባብያን ልተውና የቀሩት ላይ ጥቂት ልበል፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 5 ላይ በግልጽ እንደተመለከተው ምንም እንኳን ማንኛውም ሰው የአመለካከት ነጻነት ቢኖረውም የያዘው አመለካከት ለሕዝብ የሞራል ሁኔታ ተፃራሪ ከሆነ አመለካከቱን ከመግለጽ በሕግ ሊገደብ እንደሚችል ደንግጓል፡፡ በሕገ መንግሥቱ መሠረት የወጣው የወንጀል ሕግም በአንቀጽ 643 በግልፅ እንዳስቀመጠው ከግብረ ገብ/ሞራል/ ውጭ የሆኑ ነገሮችን፣ ምርቶችንና ሥራዎችን ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ማቅረብ ወይም መግለጽ ወንጀል መሆኑን ይደነግጋል፡፡
መቼም ጉባኤው በግል የሚካሄድ አለመሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በጉባኤው ላይም ወንድ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚመለከቱ ንግግሮች፣ ጥናታዊ ጽሑፎች፣ በራሪ ወረቀቶችና የመሳሰሉት ሥራዎች መቅረባቸው አይቀርም፡፡ የወንጀል ሕጉ ግብረ ሰዶማዊነት ከሞራል ውጭ መሆኑን፣ በአንቀጽ 629 - 631 ባሉ ድንጋጌዎች የሕዝብን ሞራል በመፃረር የሚፈጸሙ ወንጅሎች በተዘረዘሩበት ምዕራፍ ሥር አስፍሮትና ቅጣትም ጥሎበት ይገኛል፡፡ ሕገ መንግሥቱ ይሁን የወንጀል ሕጉ በጋራ ኢትዮጵያ ውስጥ ግብረ ሰዶምን መፈጸም ብቻ ሳይሆን ግብረ ሰዶምን የሚያበረታቱ አመለካከቶችን ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ መግለጽ በሕግ የተከለከለ ሆኖ እንገኘዋለን፡፡
ሕጉ ይህን ቢልም ሕግ አስፈጻሚው ወዶና ፈቅዶ የወንድ ግብረ ሰዶማዊነት የሕግ ከለላ ያገኝ ዘንድ የሚታገሉ አካላት ጉባኤያቸውን አመለካከታቸውን መግለጽ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ በሆነበት አገራችን ሊያካሂዱ ነው፡፡
ግብረ ሰዶማዊነት በባህላችንም በሃይማኖታችንም የተወገዘ ተግባር ነው፡፡ የትኛውም የኢትዮጵያ ባህል ወይም ሃይማኖት ግብረ ሰዶማዊነትን ይጠየፋል፡፡ ይህን የማይጠየፍ ባህል ወይም ሃይማኖት አለን የሚል አካል ቢኖር እንኳን ከላይ የተጠቀሰውን የሕግ ድንጋጌ ስለሚፃረር ከተጠያቂነት የሚድን አይሆንም፡፡
በጉዳዩ ላይ ከማንም በፊት ድምፃቸውን ያሰሙ ዘንድ የሃይማኖት አባቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የሃይማኖት አባቶች ማክሰኞ፣ ኅዳር 19 ቀን 2004 ዓ.ም መግለጫ ለመስጠት የተገናኙ ቢሆንም የጤና ጥበቃ ሚ/ሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም በቦታው በመገኘት የሃይማኖት አባቶችን በማነጋገር መግለጫው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ በማድረጋቸው የሃይማኖት አባቶች በጉዳዩ ላይ አንድም ቃል ሳይናገሩ ወደ መጡበት ተመልሰዋል፡፡
ይህ ብዙ ጥያቄዎችን የሚያጭር ተግባር ነው፡፡ የሃይማኖት አባቶች ምን ነካቸው? ለሃይማኖታዊው አስተምህሮ፣ ለነፍሳቸው ያደሩ አይደሉምን? መንግሥት ሌላ ሃይማኖት ሌላ፡፡ ሃይማኖታችን ግብረ ሰዶማዊነትን አይፈቅድም ብለው ጉባኤውን ቢያወግዙ ምናለበት? ዶ/ሩስ ምን ነክቷቸዋል፡፡ ማድረግ ያለባቸው ሕገ መንግሥቱን ማክበርና ማስከበር፣ የሕዝብን ሞራል መጠበቅና ጉባኤው እንዳይካሄድ ማድረግ ነው ወይስ የሃይማኖት አባቶች ጉባኤውን እንዳያወግዙ ማድረግ?...መንግሥት ጉባኤውን ከፈቀደ፣ የሃይማኖት አባቶችም መንግሥትን ፈርተው ዝም ካሉ የሕዝቡን መብት ማን ያስከብር? ድምፁንስ ማን ያሰማለት? ሞራሉንስ ማን ይጠበቅለት?
በመጨረሻ ይህ እላለሁ - ይህ ጉባኤ በአገራችን እንዲካሄድ የፈቀደ አካል አንድ ቀን በሕግ ተጠያቂ፣ በታሪክም ተወቃሽ መሆኑ አይቀርም፡፡ መንግሥት ደጋግሞ እንደሚለው እኔም መንግሥትን እላለሁ፡- “ሕገ መንግሥቱ ይከበር፤ ሞራላችንም ይጠበቅ” ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡


20 comments:

ብስራተ ገብርኤል said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጅያን ይጠብቅልን፡፡
ይህ የግብረሰዶም በሽታ በሰለጠኑት ዓለም የተስፋፋው የመንፈሳዊ ምግብ አጦት በመሆኑ በትዳር ያለመፅናታቸው ማህበራዊ ባህላዊ ትወፊት ስለሌላቸው በገንዘብ የታሰረ ህሊና ብቻ ስለሚመራቸው የአእምሮ ዝቅጠት ስለገጠማቸው ይህን ሽንፈት ያመለጡ እየመሰላቸው የተዘፈቁበት ማጥ ሲሆን፣ይህን በሽታቸውን በየሐገሩ ማዛመት እነሱ ብቻ የሚጠየቁበት ችግር ሆኖ እንዲነገር አይፈልጉም፡፡
ታዲያ የኛ መሪዎች ለእናት ሐገር ጥሪ፣ለጦርነት፣ለአባይ ግንባታ ወይም ለምርጫ ብቻ ነው ሕዝብ የሚፈለገው፤ይህን እንዳትረሱ ያስፈልጋል፡፡ያመጣችሁት ኃጢያት ለድሀ ብቻ የሚተርፍ እንዳይመስላችሁ፡፡የናንተንም ልጆች ይመለከታል፡፡በናንተ ቢደርስ ምን ይሰማችኃል?እግዚአብሔረ ብድራቱን ይክፈላችሁ፡፡እናንተም አባቶች ከሰማይ ሆኖ የሚያያችሁን አምላክ አሁን እንኳን አስቡት፡፡
የቅዱሳን አምላክ አገራችንን ሕዝባችችንን ይጠብቅልን-አሜን፡፡

ዘ ሐመረ ኖህ said...

እስከ ዛሬ መንግስት ሃገርን ሕዝብን ቅርስን ሃይማኖትን እየሸጠ ነው ሕገ መንግስቱን መንግስት አክብሮ አያውቅም ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ ይህን አሳፋሪና አሳዛኝ ተግባር ፈፀመ የሃይማኖት አባት ተብዬዎቹ ለገንዘብና ለሥልጣን ያደሩ በመሆናቸው ማናቸውንም ዓይነት የመንግስት እኩይ ተግባር ገፍተው አይቃወሙም ምንአልባት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሓኖም ሆነ ዶከተር ይገረሙ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የዚሁ የግብረ ሰዶም ሰለባ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል ሕዝቡ ለተቃዎሞ መነሳት አለበት አለብን አይናችን እያየ በቁማችን በሥጋም በነፍስም ከምንሞትና ተተኪ ትውልድ ከማጣት በክብር ለመሞት መነሳት አለብን ሃገራችን ቢሏት ቢሏት አልጠፋ ስላለቻቸው ደሞ በዚህ መጡባት እግዚአብሔር ሃገራችንን ይጠብቃታል እኛም የድርሻችንን መወጣት አለብን

Hailemariam said...

የኢትዮጵያ መንግስት ሆይ? አሁን የመውደቂያህን ወጥመድ ያዘጋጀህ ትመስላለህ።
ማን፣ ማንንም ይሁን ለዚሁ በጣም አጸያፊ ስራን ለማከናወን ስብሰባን እንዲካሄድ የፈቀዱ አካላት በሕግ ፊት ቀርበው ዋጋቸውን እንዲያገኙ ማድረግ ጊዜ የማይሰጥ አንገብጋቢ ስራችን መሆን አለበት ምክንያቱ ይህ መሬታዊውን ሕገ መንግስትን መናድ ብቻ ሳይሆን ሰማያዊው ሕግና ሰብአዊ ፍጡርን በቁሙ ማፍረስ ስለሆነ አባ-ፓስተርና ሼኩን ዝም ቢሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደወትሮህ ሳትዘናጋ ተነሳ!
እኔ በበኩሌ ነገሮችን በማጣራት ላይ እገኛለሁ።

Anonymous said...

I am living united States of America homesexuality is widely practiced officially some states and condemn most of the states . Now a days devil attacking everyone , guys becareful , our mother land Ethiopia is God's land , now devil concentrate on Ethiopia . Be unite for praying to oppose this bad practice.

Anonymous said...

I am living united States of America homesexuality is widely practiced officially some states and condemn most of the states . Now a days devil attacking everyone , guys becareful , our mother land Ethiopia is God's land , now devil concentrate on Ethiopia . Be unite for praying to oppose this bad practice.

lamelame europe said...

ayete motone setesha heda tashetalache yademate afenecha.wenate manegesetenena hezeben lamatalate nawe?wayes manegesete nawe yehane yaragawe?pls yametako anebabewane kamaseraja gara negarone

Anonymous said...

are zendiro gud new egiziabher Ethiopia yitebik enilalen gin endet bilo new egna esu yalen sansema egna yalinew yemisema gin lehatian yemeta letsadikan yiterfal new negeru ena tetenkeku abirachunkan atibilu kendezih aynet sew mikiniyatu kenesu gar metifat alifeligm abetu maren getaye

Anonymous said...

Please all the Ethiopian people do not forget this meeting and the theme of the meeting of this evil action and the donor like England. I am sorry to say, this could be one of their best strategy to weep out the African people and get bare land in Africa. This is a genocide action and they are supporting. This long term plan, otherwise, is it really rights of the homosexual people concern them? If so at this moment, how many people are there in Ethiopia who are practicing this evil action? Are they really greater than the number of people in political prisons different part of the country? They kept silent for those prisoners. Since King Haileselassie, those western countries they are helping us (Africa) but we all know the outcome (they divided us with ethnically). Please all innocent Ethiopian, despite of our religion difference, wake up and united to condemn the meeting at any time, place and event. Not only this year, until we will depart of this world. Please I am not saying let us hurt/kill our incent Ethiopian let help them to take out from this evil practice

Anonymous said...

please our Government,meles try to do another history like Abay Dam by talking strong action on Homosexuality. You know the aim, desire and long term plan of the western country more than your people.

Anonymous said...

Ethiopia Ejochwean Wed EGZIABHER Tezrgalche Yetblwe Auien Mehoen Albet, EGZIABHER Ejien Ke ETHIOPIA Ezbe Gear Adrglien Ebake!

Anonymous said...

Ethiopia Ejochwean Wed EGZIABHER Tezrgalche Yetblwe Auien Mehoen Albet, EGZIABHER Ejien Ke ETHIOPIA Ezbe Gear Adrglien Ebake!

Anonymous said...

Oh. Mengst selamawi self hulu meseretun yeminekenkbet eyemeselew bahlachnn, enganetachnn hagerachnn liyatefat new. Egna kemekawem betechemari entsely! Emamlak yebarekechat ager bemanm balega atreksm! Le esu yemisanew yelem. Talalakochachn kelay tewu kalalu egna metegnat yelebnm. E/R ETHIOPIAN YTEBK!

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ደጀ ሰላምን ከሚያነቡ አንዱ ነኝ ። ዘወትር ማለት ይቻላል ኮምፒዩተር በከፈትኩ ቁጥር መቅድመ ኩሉ የአይኔ ማረፊያ ነው ።ማለት እችላለሁ ። እናም ብዙ ስለ ቤተ ክርስቲያንም ስለ ሀገርም የሚጻፉትን ነገሮች ሳነብ ምንም አስተያየት ለመጻፍ ህሊናየ ባይወስንም ነገር ግን መደስትም መበሳጨትም አልቀረልኝም ። እናም ዛሬ ግን ለመጻፍ ልምዱ ባይኖረኝም እንድጽፍ ነገሩ አስገደደኝ ።በማንነታችን ላይ እየተቃጣ እና እየተፈጸም ያለው ነገር እርር ድብን ኩምትር የሚያደርግ ነው ። ከምን የተነሳ ነው ብየ ላንዳፍታ ሳስብ መሥራት ያለብንን ነገር ባለመሥራታችን ወደሚለው ውሳኔ ደርሻለሁ። መቸውም ቢሆን የምናመልከው አምላክ አይተወንም አያሳፍረንም ነገር ግን መሥራት ያለብንን ነገር የኛን ግዴታ ካልተወጣን ደግሞ በንሮአችን ላይ ችግር መፍጠሩ አይቀሬ ነው። ብዙ ግዜ መሆን የሌለባቸው ነገሮች ሆነው ስናገኛቸው ብቸኛ አማራጭ እያደረግን ያለነው ጸሎትን ነው ። የሁሉም ኮሜንት እንጸልይ እንጸልይ ነው ። በጸሎት አስፈላጊነት ምንም ጥርጥር ባይኖረኝም ነገር ግን ጸሎት ከተግባር ጋር ነው ግብ ሊመታ የሚችለው የሚል እምነት አለኝ ። ጸሎት በሥራችን ላይ የእግዚአብሔርን አብሮነት ፤ፈቃድ፤ ኃይል፤ ጸጋ ፤ ወዘት ማግኛ ነው ።እንጂ ያለሥራ ዝም ብሎ መጸለይ አይመስለኝም ።አንድ ምሳሌ ባስቀምጥ ሃሳቤን የበለጠ ግልጽ የሚያደርገው ይመስለኛል ።
ዳዊትንና ጎልያድን ተመልከቱ ። ዳዊት ያለ እግዚአብሔር አብሮነትና ፈቃድ ቢሆን ጎልያድን መግደል ይቻለው ነበር ? በጎልያድ መሞት የግዚአብሔር ፈቅድ ቢሆንም ዳሩ ግን ዳዊት ደንጋዩን ባይወረውር ሞቱ ይከናወን ነበር ? የዳዊት ደንጋዩን መወርውር ግድ ነበር ለጎልያድ መሞት ። አዉቃለሁ እግዛብሔር ሁሉን አድራጊ ነው ። ነገር ግን በንሮአችን ውስጥ እኛ እንድንሥራው ግዴታችን የሆነ ነገር አለ ። ጸሎት ከዛ ሥራ ጋር ሲተባበር ነው ዋጋው ግልጽ ሆኖ የሚታየው። ይህን ስል ቤተክርስቲያናችንንም ይሁን ሀገራችንን በሚመለከት በሚከሰቱ ነገሮች ሆ ብለን በስሜት ደንጋይ መወርውር አስፈላጊ ነው እያልኩ አይደለም። ግን ከጸሎት ጋር በጥበብና በእውነት እንደግዜው አስፈላጊነት እያስብንበት መሥራት ያለብን ነገር እንዳለ ደግሞ ይታሰበኛል። እርግጥ ነው መታሰር መደብደብ መሰድድ መገደል መገለል ሊያጋጥም ይችላል ። ሆኖም ግን የጸሎት ኃይሉ ያኔ ነው የሚታወቀው ።ሃስቤን እዚህ ላይ ገታ ላደረገው ግድ አለኝ ።ከጸሎት ጋር የሚጠበቅብንን ለመስራት እራሳችንን ማዘጋጀት አለብን የሚለውን አመለካከት ለመግለጽ ብየ ነው ። አስተያየት ጽፌ ስለማላቅ ከተሳሳትኩ በልባችሁ እንደበጎ አስባችሁ እርምት አድርጉበት ።
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ሀገርን ይጠብቅ

Anonymous said...

These kids are better than so called 'religious/spiritual fathers'. It is so sad that these Church fathers did not officially condemn the so called 'government' which allowed those people who practice this condemn act or curse to officially summon in the birth place of SAINT TEKILEHAIMANOT.
'Balebetun kalinaku, atirun ayinekeniku'. The next step is going to be to order everbody to be gay and lesbian; if he/she says no,then the government executes him or her. I think, everybody will say okay! Because all are now scary cats!

Anonymous said...

new york times,
Published:
December 6, 2011
U.S. to Aid Gay Rights Abroad, Obama and Clinton Say
GENEVA — The Obama administration announced on Tuesday that the United States would use all the tools of American diplomacy, including the potent enticement of foreign aid, to promote gay rights around the world.

http://www.nytimes.com/2011/12/07/world/united-states-to-use-aid-to-promote-gay-rights-abroad.html?pagewanted=all

Anonymous said...

The Obama administration announced on Tuesday that the United States would use all the tools of American diplomacy, including the potent enticement of foreign aid, to promote gay rights around the world.
Let's see.What is going on in the US.
1) Unemployment is imploding in the U.S.A. with 15 million workers without jobs.

2) Our national debt is $15 TRILLION, $4 TRILLION of which was piled on in only three years by Obama and his administration.

2) Our housing market is on the verge of collapsing again, with all the foreclosures coming in 2012.

3) Obama brags about creating 120,000 jobs in one year when 360,000 are needed to keep pace with the number of Americans entering the job market.

4) Our southern border is a sieve. Obama brags that the number of illegals picked up is at an all-time low -- meaning illegals are coming in unabated.

5) Attorney General Holder, Director of Homeland Security Napolitano and their agencies are allowing federal employees to violate state, U.S. and international law by letting weapons of all types "walk" into Mexico. They called the illegal exercise, "Fast and Furious." It was more like "Fraudulent and Fallacious" -- they lied about it to Congress. Often.

6) Some of those thugs killed U.S. Border Patrol Agent Brian Terry using those illegal weapons. Of course, Holder (Obama's favorite) did not have time to visit Terry's parents -- or to even phone them. Then he lied to Congress. Often.

So, since everything is going super here, we have plenty of time and money to meddle in other nations' business. Wrong.

This independent is working hard to make 2012 the year of the "ABO" election....

.... the "Anybody But Obama" election.

Anonymous said...

Ferie besewimi be Egzabiherimi feti yetenaker newi. Lelawi kerito yezarewochi Ethiopiawian hayimanotachinini mekelakeli sayihoni tikatini mekawemi iniferaleni. Gini isikemechie.

mitu said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጅያን ይጠብቅልን፡፡
እጅግ በጣም ዘግና ነገር ነው

Anonymous said...

ወይ ጉድ ወይ ጉድ በዚህ ይሉኝታ ቢስ ዘረኛ አንድ ነገር መደረግ አለበት የተዋህዶ ልጆች ምን እየጠበቃችሁ ነው? ሰዶማውያን ከመሆን በሰማእትነት መሞት ይሻላል ይህን ባለጌ በቃ እንበል እንነሳ ተነስ አትፍዘዝ ተነስ አትፍዘዝ ተነስ አትፍዘዝ
በቃ በቃ በቃ!!!!!!!!!!!!!!በል::

Anonymous said...

Eijeg yemiyasazene tegebare neaw. Zeme lene ayegebaneme. hulachenem yedershachenne mewetate aleben. Yen Meles menegest yewedeme.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)