December 3, 2011

የግብረ ሰዶማውያኑ ስብሰባ በተ.መ.ድ የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ ነው

READ IN PDF.
  • ከ40 - 45 የሚደርሱ ግብረ ሰዶማውያን ከደቡብ አፍሪካ የመጡ ናቸው፤ ያረፉበት ቦታ በምሥጢር ተይዟል::
  • የጁፒተር ዓለም አቀፍ ሆቴሎች አስተዳደር የግብረ ሰዶማውያኑ ስብሰባ በሆቴሉ እንደሚካሄድ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን ደንበኞቹ እና አጠቃላይ ሕዝቡ እንዲገነዘቡለት አስታውቋል::
  • የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሠራተኞች በኢትዮጵያ ሕግ ወንጀል በሆነው ግብረ ሰዶማዊነት ላይ ለሚሰበሰቡ ግለሰቦች ፈቃድ መሰጠቱ ግራ እንዳጋባቸው ገልጸዋል፤ ሚኒስቴር መሥ/ቤቱ ምን እየሠራ እንደ ሆነ በቁጣ ላቀረቡት ጥያቄ ‹‹መፍትሔ መስጠት የሚችሉት የበላይ የመንግሥት አካላት ብቻ እንደሆኑ›› ተገልጦላቸዋል::
  •  መንግሥት በ‹ዝምታ ዲፕሎማሲ› የግብረ ሰዶማውያኑን የቅድመ (ICASA) ስብሰባ ከመከላከል ሲቆጠብ የስብሰባው የኮሚዩኒኬሽን ሓላፊዎች በበኩላቸው በተ.መ.ድ የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ ስለሚገኘው ‹ሥልጠና› እና ልምድ ልውውጥ የተካተተበት የግብረ ሰዶማውያኑ ቅድመ ጉባኤ የማነቃቂያ ስብሰባ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በመናገር እያደናገሩ ይገኛሉ::
 
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 23/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 3/2011):- አምሸር - AMSHeR/The African Men for Sexual Health and Rights/ የተባለ መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገ ድርጅት ከ16“ዓለም አቀፍ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና አባላዘር በሽታዎች በአፍሪካ” ቀደም ብሎ “Claim, Scale-up and Sustain” (የራስ ማድረግ፣ ማሳደግ እና ቀጣይነት) በሚል መሪ ቃል ያቀደው የ”MSM and HIV(Men who have sex with Men)” ስብሰባ በተባበሩት መንግሥታት የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ነገ ቅዳሜ፣ ኅዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም 200 ያህል ተሳታፊዎች በተገኙበት ይደረጋል የተባለው ስብሰባም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በውሎ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል፡፡

ቡድኑ ለዚሁ ስብሰባ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንሥቶ ግብረ ሰዶማዊ ተሳታፊዎችን ሲያፈላልግ የቆየ ሲሆን በአዲስ አበባም በመጀመሪያ ከ40 - 45 ለሚሆኑ ሰዎች፣ በቀጣይም እስከ 180 ለሚደርሱ እንግዶች መኝታ፣ መስተንግዶ እና መሰብሰቢያ አዳራሽ የሚሆኑ ሆቴሎችን ሲያጠያይቅ መቆየቱ ታውቋል፡፡ በመጨረሻም ድርጅቱ ከኖቨምበር መጨረሻ እስከ ዲሴምበር ሁለት ድረስ ከ40 - 45 ተሳታፊዎች፣ ዲሴምበር 3(ነገ ኅዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም) ደግሞ ከ25 አገሮች የተውጣጡ 200 ግብረ ሰዶማዊ ተሳታፊዎች እንዲሁም በጤና እና ሰብአዊ መብት ላይ ጥናት የሚያቀርቡ ከ15 አገሮች የተውጣጡ ባለሞያዎች(Experts on the health and human rights sexual minorities) የሚገኙበት የቅድመ (ICASA) ስብሰባ ቦሌ ሚሌኒየም አዳራሽ አቅራቢያ በሚገኘው ጁፒተር ዓለም አቀፍ ሆቴል እንደሚካሄድ በድረ ገጹ አስታውቆ ነበር፡፡

በካዛንቺስ አፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን - ተ.መ.ድ የስብሰባ አዳራሽ አጠገብ እና በቦሌ ሚሌኒየም አዳራሽ አቅራቢያ ዓለም አቀፍ እና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት የሚሰጡ ሆቴሎች እንዳሉት የገለጸው የጁፒተር ዓለም አቀፍ ሆቴሎች አስተዳደር በበኩሉ ኅዳር 21 ቀን 2004 ዓ.ም ለብዙኀን መገናኛ ባሰራጨው መግለጫ፣ በሆቴሉ የተጠቀሰው ስብሰባ የማይካሄድ ከመሆኑም ባሻገር በተጠቀሰው ቀን የስብሰባ አዳራሾች በሙሉ በሌሎች ተሰብሳቢዎች የተያዘ መሆኑን ገልጧል፤ በተለያዩ የመገናኛ መንገዶች እየተሰራጩ ያሉትን መረጃዎች ደንበኞቹ እና አጠቃላይ ሕዝቡ ሐሰት መሆኑን እንዲገነዘቡለትም በሆቴሉ የሰው ሀብት እና አስተዳደር መምሪያ ሓላፊ አቶ ኢሳይያስ ወልዱ ፊርማ የወጣው ደብዳቤ አሳስቧል፡፡

የዜናው ምንጮች እንደሚያስረዱት፣ ጁፒተር ዓለም አቀፍ ሆቴል፣ ሀገራችን ከኅዳር 24 - 28 ቀን 2004 ዓ.ም ለምታስተናግደው የ(ICASA) ስብሰባ እየመጡ ያሉ እንግዶችን እያስተናገደ ነው፤ መስተንግዶውም በሚስተናገደው ግለሰብ/አካል ሕጋዊነት ላይ እንጂ በመጣበት አጀንዳ ላይ የሚመሠረት እንዳልሆነ፣ በዚህም መሠረት በኦክቶበር ወር አምሸር ለሆቴሉ ጥያቄ ማቅረቡን፣ ይሁንና የጠየቀው ቦታ የተያዘ መሆኑ ሲገለጽለት ዓላማው የሚታወቅ እንዳልነበር፣ ነገር ግን ለግብረ ሰዶማዊ አጀንዳ መሆኑ ቢታወቅ ግን ጉዳዩ በሀገሪቱ ሕግ ወንጀል በመሆኑ ስብሰባው ከተጀመረም በኋላ ቢሆን የመሰረዝ ዕጣ ይገጥመው እንደነበር የሆቴሉ ሓላፊዎች አስረድተዋል ተብሏል፤ አምሸር ከሆቴሉ የጠየቀውን ቦታ ባላገኘበት ሁኔታ ስብሰባው እንደሚካሄድበት በድረ ገጹ ማስታወቁ አግባብ አለመሆኑም ተመልክቷል፡፡

በተያያዘ ዜና የግብረ ሰዶማውያኑ ቅድመ ኮንፈረንስ ስብሰባ እንደሚካሄድ በብዙኀን መገናኛ ከተገለጸ በኋላ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚሰነዘረው የተቃውሞ ድምፅ እየበረታ መጥቷል፡፡ ነጋድራስ ጋዜጣ በኅዳር 22 ቀን 2004 ዓ.ም እትሙ እንደዘገበው የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሠራተኞች የግብረ ሰዶማውያኑን ስብሰባ አጥብቀው እንደሚቃወሙት ገልጸዋል፡፡ የዓለም ኤድስ ቀንን ምክንያት በማድረግ ባለፈው ረቡዕ በብሔራዊ ቴአር አዳራሽ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ የሚኒስቴሩ ሠራተኞች ከዕለቱ የውይይት ርእስ ይልቅ የግብረ ሰዶማውያኑ ጉባኤ በአዲስ አበባ መደረግ እንዳሳሰባቸውና ጉዳዩ የሚመለከተው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በመሆኑ “ምን እየሠራ እንደሆነ እንዲነግረን እንፈልጋለን” ሲሉ ቁጣ በተሞላበት ሁኔታ ጠይቀዋል፡፡

ስለ ኤች.አይ ቪ/ኤድስ የውይይት መነሻ ሓሳብ ለመስጠት መድረክ ላይ የወጡት ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርቲ የተወከሉ ግለሰብ በሠራተኞቹ ቁጣ አዘል ጥያቄ ግራ ተጋብተው የተስተዋሉ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ደፍሮ ምላሽ ለመስጠት የፈቀደ ሰው ጠፍቶ ነበር፡፡ ቆይቶም ማንነታቸውንና የሥራ ሓላፊነታቸውን ያልገለ ተሳታፊ በመረጃ ደረጃ ሚኒስቴሩ ስለጉዳዩ እንደሚያውቅ ይሁንና ነገሩን የበላይ የመንግሥት አካላት ብቻ እንደሚፈቱት ገልጸዋል፡፡ “ግብረ ሰዶማዊነት በሀገራችን ወንጀል ነው፤ በወንጀል ዙሪያ ለሚሰበሰቡ ፈቃድ መስጠት ግራ ያጋባል፤” ብለዋል ሠራተኞቹ፡፡

ስለ ጉዳዩ በተለያዩ ብዙኀን መገናኛዎች የወጡት የ(ICASA) ስብሰባ ኮሚዩኒኬሽን ሓላፊዎች ምላሽ እንደሚያስረዳው፣ በአንድ በኩል ስለ ስብሰባው ሂደት እንጂ ለስብሰባው የሚመጡት ሰዎች ማንነት እንደማያስጨንቃቸው እየገለጹ በሌላ በኩል ደግሞ በ(ICASA) ስብሰባ ስም ወደ አገሪቱ የገቡ ግለሰቦች በግብረ ሰዶማዊ አጀንዳ ዙሪያ በጠራራ ፀይ/በግላጭ ስለሚያካሂዱት ስብሰባ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በመናገር ሕዝቡን እያምታቱ ይገኛሉ፡፡ ቀደም ሲል መሰል ስብሰባዎች የተካሄዱባቸው አገሮች ከሕዝባቸው ባህል እና እሴት እንዲሁም ከብሔራዊ ሕጎቻቸው ጋራ የማይጣጣሙ ድርጊቶች ፈጽመው በመሄዳቸው በእንግዳ ልማዶች ዘላቂ ጉዳት እንዳገኛቸው እየተዘገበ ይገኛል፡፡
በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ 37፣ በዓለም በአጠቃላይ 80 ያህል አገሮች ግብረ ሰዶማዊነትን በሕጎቻቸው በወንጀል ድርጊትነት ፈርጀው የደነገጉ ቢሆንም ከድርጊቱ ጋራ በተያያዘ እንደ ብሪታኒያ ያሉ ለጋሽ አገሮች የርዳታቸው ቅድመ ሁኔታ በማድረግ ግብረ ሰዶማዊነትን ከግለሰብ ሰብአዊ መብት ጋራ በማያያዝ ጫና በመፍጠር ላይ ናቸው፡፡17 comments:

Kidist Ethiopia said...

በተለያየ ነገር እርስ በእርሳችን ከምንነቃቀፍ በማስተዋል እጅ ለእጅ ተያይዘን በፍቅር በእውነት የምንልይበት ግዜ አሁን ነው።
መንግስት ስለፖለቲካ ጉዳይ እንጂ ስከኢትዮጽያ ጉዳይ አይመለከተውም።

Anonymous said...

እውነትም የመጨረሻ ዘመን ደርሰናል በሌላ ሃገር የሚደረገው ሲገርመን ጭራሽ በሃገራችን ላይ በጣም ያሳዝናል

Anonymous said...

ይሄኮ ግልፅ ነው!
ወያኔ ለ20 አመት ብቀላው አልበቃው ብሎት ምን እንደሚያደርገን ግራ ሲገባው ይሄን እርኩስ ነገር አምጥቶ እኛን ሰዶም ሊያደርገን ነው ያሰበው ምን ያህል ጥላቻው የበረታ ቢሆን ነው ለዚህ ያሰበን? እንገዲህ የት እንኑር? የት እንሂድ?
እገዚአብሄር ሆይ በቃችሁ በለን!!!!

Anonymous said...

It is a very very sad thing just to hear that homosexuality is going to be accepted (it feels so) in our country where people die for its religion and culture. From my little knowledge,Orthodox has a solid and clear position on homosexuality. Given the Orthodox understanding of the Old and New Testament scriptures as expressed in the Church's liturgical worship, sacramental rites, canonical regulations and lives and teachings of the saints, it is clear that the Orthodox Church identifies solidly with those Christians, homosexual and heterosexual, who consider homosexual orientation as a disorder and disease, and who therefore consider homosexual actions as sinful and destructive.

" If a man lies with a male as with a woman, both of them have committed an abomination . . . (Leviticus 20:13)"

And this disgusting homosexual thing should be banned for once and for all in our beloved home.
inde sedo ena gemora yemetfat melektu eyemeta yemeslal ena betselot inberta.

May God bless and keep our country.
Amennn

ምስክር said...

እንዲህ የሚይደርገውን መንግስታችንን፡ ህዝቡ አንድ ሊለው ይገባል። ህዝቡን የማያደምጥ መንግስት ከደርግ ሊማር ይገባዋል። ሌላው ቢቀር ምርጫ ሲመጣ ህዝቡ ይህንን ነገር አይረሳውም።

የሃይማኖት መሪዎችስ መግለጫ ለመስጠት ምን አስፈራቸው፤ ሃላፊነታቸውን የማይወጡ ከወነ እነሱም ስልጣን ለምን ለሚገባው አያስረክቡም።

ze gascha' said...

This is really the beginning of the end of the world. It is really, the time that we have to wake up from our deep sleep and pray to Almighty God.It is awfull to invite sodomites to our holy land. This is a a demoral action that is performed by the Goverment on Ethiopian people. Unless we co-operate to denounce such act early, our next generation will inherit the sodomite ethiopia.

Anonymous said...

ውግዘት የሚገባው ተግባር
http://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=1:2011-12-02-08-19-57&catid=2:-&Itemid=2

Anonymous said...

wayyii gezeeeee yegrmal

Anonymous said...

Yeferie diniberi yideferali yeferie ageri yiwererali. Ferewochi silehonini hagerachini hayimanotachini inkuani lemekelakeli iniferaleni. Ferie keigzeyabiheri adelemi. Gena seyitani amilakewochi metitewi silassie katederali yamelikalu.
Ferewochi silehonini besewimi be Igizeyabiherimi feti yetenakini neni.

Anonymous said...

ERE EBAKACHEHU MIN YEBALAL EWENET YEH BEHAGERACHEN TEFETSEME /TEDEREGE WERDET NEW
ABATOCHACHENENA AYATOCHACHEN YEHENEN ENDAYSEMU DEBKU TASTAWESU ENDEHON SET LEDG ENKWAN SETAREGEZ GUD TEBLO YEDEBEK NEBER YEHE DEMO YEBASE NEW
CHELA ANBEL ZEMETA SIBEZA GUD YAMETAL
MELAKAM ENGEDIH ENASEBEBET

Anonymous said...

የሃይማኖት መሪዎችስ መግለጫ ለመስጠት ምን አስፈራቸው፤ ሃላፊነታቸውን የማይወጡ ከወነ እነሱም ስልጣን ለምን ለሚገባው አያስረክቡም።
ምስክር በትክክል አስቀምጠኈዋል
አባ ጳውሎስ መግለጫ ለመስጠት ምን አስፈራቸው፤ ሃላፊነታቸውን የማይወጡ ከወነ እርሳቸውም ስልጣን ለምን ለሚገባው አያስረክቡም። ሀጥያትን መቃወም ወያኔን መቃወም እንደሆነ ቢታወቅም ይሄ ግን የሞራል ብቻ ሳይሆን የአባ ጳውሎስን
ሀይማኖት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ጉዳይ ነው::በመሆኑም የሃይማኖት መሪዎች ጊዜ ሳይወስዱ በስልጣን ላይ ያለውን ህውሀት ወያኔን ሊያወግዙ ይገባል::

Anonymous said...

yeha nagare kateta yamanegeste sera nawe deje selamoche pls katachala bazeh laye yalawen akome manegeste yagalasabate kala betetakomone,
enetsaleye ebakachohe

Anonymous said...

ይሄኮ ግልፅ ነው!
ወያኔ ለ20 አመት ብቀላው አልበቃው ብሎት ምን እንደሚያደርገን ግራ ሲገባው ይሄን እርኩስ ነገር አምጥቶ እኛን ሰዶም ሊያደርገን ነው ያሰበው ምን ያህል ጥላቻው የበረታ ቢሆን ነው ለዚህ ያሰበን? እንገዲህ የት እንኑር? የት እንሂድ?
እገዚአብሄር ሆይ በቃችሁ በለን!!!!

Anonymous said...

ERE EBAKACHEHU DEJESELAMOCH YALETECHEBETE NEGER EYTSAFACHEHU MESKINUN HEZEB ATADENAGERU KIFUM ATANAGERUT MIN AYENET GUD NEW ZENDERO LIB YESTACHEHU

Anonymous said...

I am willy confused about this thing.Please all the only thing we can do is just pray from our heart to Gods mother and she will give us the answer.Otherwise we don not know our religion leader and our government will do next.May be they will officially amend a constitution in favor of gay community.

Anonymous said...

Betam yasazinal egzer yikir yibelachew

Anonymous said...

EBAKACHIW KIRSTIANOCH YEMSKINOCHIN EMBA WEDE MIABIS AMLAKACHIN ENCHU ERSUM CHUHETACHININ SEMTO LEMEFRED YIMETAL AYIKERIM

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)