December 13, 2011

16ኛው የ(ICASA) ጉባኤ ሪፖርታዥ


  • READ IN PDF.   
  • የተ.መ.ድ ኤድስ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ሰዶማውያን ማኅበራዊ ድጋፍ የሚያገኙበትን አጀንዳ ለማበረታታትና ለማስፋፋት የአቶ መለስ ዜናዊን የመሪነት እገዛ ጠይቀዋል፤
  • የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና “ገሞራውያን” የሚላቸው ሰዶማውያን እና ሰዶማውያት ከቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲለዩ፣ የመጸጸታቸው እና የቀና ኅሊናቸው ንጽሕና እስኪታወቅ ድረስም ንስሓቸው የዕድሜ ልክ እንደሚሆን ደንግጓል - “ገሞራውያን ይንበሩ በኵሉ ሕይወቶሙ ምስለ መስተብቋዕያን” /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 48÷17-56/፤
  •  በ16ው የ(ICASA) ጉባኤ የምሥራቅ አፍሪቃ መንግሥታት በብሔራዊ የጤና ፖሊሲ ክለሳዎቻቸው፣ በጤና ሁኔታዎች አመልካቾቻቸው፣ በጤና መርሐ ግብር ዝግጅቶቻቸውና ሳይንሳዊ ምርምሮቻቸው የግብረ ሰዶማውያንን ተሳትፎ እንዲያረጋግጡ የሚጠይቅ የቅስቀሳ ውይይት(Oral Poster Discussion) ተካሂዷል፤

  • የአገሮች ባህላዊ እሴት እና ሃይማኖታዊ ትውፊት ምንም ይሁን ምን የግብረ ገሞራ(ሰዶማውያንና ሰዶማውያት) መብት ከሰብአዊ መብቶች አንዱ እንደሆነና የመብቱ መከበር ወይም አለመከበር የአሜሪካንን ርዳታና የጥገኝነት አሰጣጥ ሥርዐት እንደሚወስን ወ/ሮ ሂላሪ ክሊንተን አስታውቀዋል፤ የወ/ሮዋ ዕወጃ የቀጣይ ዓመት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን እንጂ እንደተባለው ርዳታን በቀጥታ እንደማይመለከት የተናገሩ ተንታኞች በበኩላቸው፣ የኦባማ አስተዳደር በአፍሪቃ የሰዶማውያንን አኗኗር ‹ለማሻሻል› እና ለሰዶማውያን መብት የቆሙ ቡድኖችን በማጠናከር በአህጉሩ እየገነገነ ነው የሚባለውን የቀኝ ክንፍ ‹ወንጌላውያን› እንቅስቃሴ ለመቋቋም ያለመ እንደሆነ ጠቁመዋል፤
  • የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን በልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በኩል በ (ICASA) ጉባኤ ላይ ተካፍላለች፤ ኮሚሽኑ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን በመከላከል እና በመቆጣጠር ያስመዘገባቸውን ውጤቶችና ቀጣይ ፕሮጀክቶች በፖስተር ዐውደ ርእይ(Poster Exhibition) መልክ አቅርቧል፤ ዐውደ ርእዩ ኮሚሽኑ ከዓለም አቀፍ ርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ጋር በማስተዋወቅ ተጨማሪ ድጋፍ የሚያገኝበትን አዲስ የትብብር መሥመር እንዳመቻቸለት ተገልጧል፤
  • “ሰዶማውያንን ካልተቃወምን፣ ርኵሰታቸውን ካላወገዝን፣ ለጥያቄአቸው መልስ ካልሰጠን የነገዋ ቤተ ክርስቲያን በእነዚህ ውዥንብሮች ትናወጣለች” /አባ ሳሙኤል፣ “ሰዶማውያንና የኀጢአት ደመወዝ” መጽሐፍ/፤
  • “ሰዶማውያን ሊጠይቁት የሚገባቸው መብት ንስሓ መግባትን ብቻ ነው”/ሊቃውንት ጉባኤ፣ “ከሰዶማውያን ርኵሰት ተጠበቁ” መጽሐፍ/፤
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 3/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 12/2011)፦ 16ው ዓለም አቀፍ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና አባላዘር በሽታዎች ጉባኤ በአፍሪካ /ICASA/ ኅዳር 28 ቀን 2004 ዓ.ም ማምሻውን ተጠናቋል፡፡ ከ103 አገሮች የመጡ የመንግሥታትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መሪዎችና ተወካዮች፣ ሳይንቲስቶች፣ ፖሊሲ አውጭዎችና የማኅበረሰብ መሪዎች የተካተቱበት ጉባኤው 10,361 ያህል ተሳታፊዎች እንደተገኙበት፤ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፣ ወባ እና ቲቢ ላይ ያተኮሩ ከ1000 ያላነሱ ጥናታዊ ጽሑፎች፣ መረጃ እና የልምድ ልውውጥ የተደረገባቸው የቃል ጥናቶች (Oral Presentation and Poster Discussion) እና የፖስተር ዐውደ ርእይ (Poster Exhibition) እንደቀረቡበት ተገልጧል፡፡
“ገንዘብ ማድረግ፣ ማሳደግ እና ማዝለቅ”/Own, Scale-up and Sustain/ በሚል መሪ ቃል በሚሌኒየም አዳራሽ የተካሄደው ጉባኤው በሥራ ላይ በቆየባቸው አምስት ቀናት፣ እ.አ.አ በ2015 ኤች.አይ.ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በመግታት ከኤድስ ነጻ የሆነ ትውልድ ለማፍራት/Getting to Zero and Ending AIDS/ የተቀመጠው ግብ ጥረቱን በዋናነት የሚደግፈው ግሎባል ፈንድ በዓለም አቀፉ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ቀውስ የተነሣ በገጠመው የበጀት እጥረት/cut and cancellation/ እንዳይስተጓጎል የተፈጠረው ስጋት ቀዳሚ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ ከስጋቱ በተፃራሪ በጉባኤው ሁለተኛ ቀን ቁጥራቸው ከ1000 ያላነሱ የ57 ሲቪል ማኅበራት ተወካዮች ከዓለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶች የሚሰጠው የኤድስ ፈንድ በአግባቡ ጥቅም ላይ አለመዋሉን በማስመልከት ገንዘቡ የት እንደደረሰ የሚጠይቅ ሰልፍ በቅጽሩ አካሂደዋል፡፡
የዓለም ባንክ፣ ዩኒሴፍ እና የተ.መ.ድ ኤድስ ፕሮግራም በጋር ካወጡት ሪፖርት ለመረዳት እንደተቻለው ባለፈው ዐሥር ዓመት በኤድስና ተያያዥ በሽታዎች ሳቢያ የሚከሠተው የሞት መጠን 25 በመቶ ቀንሷል፤ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገሮች 6.65 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የፀረ-ኤድስ መድኃኒት ተጠቃሚ ሆነዋል፤ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ውስጥ ካለ ነፍሰ ጡር ሴቶች መካከል 50 ከመቶ ያህሉ ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ የሚከላከለውን ሕክምና አግኝተዋል፡፡
የተ.መ.ድ ኤድስ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ሚሼል ስዲቤ ባለፈው ሳምንት እሑድ፣ ኅዳር 24 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀትር በኋላ በተከናወነው የ(ICASA) ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ “ለጋሽ አገሮች በገጠማቸው የገንዘብና ኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ የፀረ-ኤድስ መድኃኒቱን ወጪ 70 በመቶ የሚሸፍነው የግሎባል ፈንድ ቦርድ ለቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የተከታይ 11 ዙር የበጀት ድጋፍ እንደማያሰባስብ መወሰኑ በዝቅተኛና መካከለኛ አገሮች በሚገኙ የፀረ-ኤድስ መድኃኒቱን የሚጠቀሙ ዘጠኝ ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት አደጋ ላይ የሚጥል፣ በውጤቱም ብዙዎችን አሳዳጊ አልባ በማድረግና ለቫይረሱ መስፋፋት በማጋለጥ ቀደም ሲል የተገኙ ውጤቶችን ወደ ኋላ የሚመልስ በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው ነው፤” ሲሉ ገልጸዋል፡፡
አፍሪካውያን መንግሥታት አገራዊ የሀብት ምንጮችን በማጠናከር፣ የፀረ-ኤድስ መድኃኒቱ በአፍሪካ ምድር የሚመረትበትንና የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚደረግበትን ሁኔታ በማመቻቸት ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መኖሩ ከታወቀበት ከ30 ዓመትና በሽታው 24 ሚሊዮን አፍሪካውያንን ከገደለ በኋላ የተገኙ ውጤቶችን የራሳቸው የሚያደርጉበትን አዲስ የልማት አስተሳሰብና አቅጣጫ እንዲቀይሱም ጠይቀዋል፡፡ ለዚህም የኤች.አይ.ቪ ሥርጭትና በኤድስ ሳቢያ የሚከሠተው ሞት በ25 በመቶ ከቀነሰባቸው 22 የአፍሪካ አገሮች አንዷ ለሆነችው ኢትዮጵያ “ልዩ የአመራር ልቅና በመስጠት ውጤታማ ሆነዋል” ያሏቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን አፍሪካውያን በአፍሪካ መር “አዲስ አስተሳሰብና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ያተኮረ የኢኮኖሚ ፖሊሲ” በመቀየስ በኤድስ ላይ የተገኘውን ውጤት አስጠብቀው ይራመዱ ዘንድ ከ”መሪነት ልቅናቸው” ረድኤት እንዲያደርጉላቸው ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል፡፡
ሚ/ር ሚሼል ሲዲቤ የአቶ መለስን የመሪነት በረከት የተማፀኑበት ጥያቄ በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ በንግግራቸው መሀል በአፍሪካ የሚካሄደው ፀረ-ኤድስ ንቅናቄ የማኅበረሰቡን ስሑት አመለካከቶች ተጋፍጠው መብቶቻቸውን የጨበጡ ሰዎች አነቃቂ ታሪክ መሆኑን ያመለከቱት ሚ/ር ሲዲቤ በንግግራቸው ማብቂያ ላይ፣ በማኅበራዊ ኑሮ የኤድስን ምላሽ ይወስናሉ ያሏቸውን ሁኔታዎች/social determinants/ በመጠቃቀስ አቋማቸውን ወደ መግለጽ ዘልቀዋል - “በሴቶች/ልጃገረዶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት ማስቆም አለብን” - ማለፊያ! ለጥቀውም “በበሽታው በከፍተኛ ደረጃ በሚጠቁ/ተጋላጭ የሆኑ ወገኖች ላይ የሚፈጸመውን መድልዎ ማስቆም አለብን፤” አሉ፤ እነዚህንም ወገኖች ሲዘረዝሩ፡- ስደተኞች፣ እስረኞች፣ የዕፅ ሱሰኞችና በግብረ ዝሙት አዳሪዎች መሆናቸውን ጠቀሱ፡፡ መልካም! ነገር የተበላሸው ከወንዶች ጋር ጾታዊ ግንኙነት የሚፈጽሙ ወንዶችም (Men who have sex with Men - MSM) ከእነርሱ መካከል እንደሆኑ ሲናገሩ ነው፤ እነዚያም እነዚህም ጥበቃና የሕይወት አድን አገልግሎት እንደሚያሻቸው በማሳሰብም አቶ መለስ ማኅበራዊ ድጋፍ፣ ተቀባይነትና ዘለቄታ ያለው አጀንዳ/socially sustainable agenda/ በማስተዋወቅ፣ በመደገፍና በማበረታታት የመሪነት ሚና እንዲኖራቸው ጠይቀዋል፡፡
የዋና ዳይሬክተሩን ንግግር ተከትሎ የተናገሩት አቶ መለስ፣ አህጉሪቱ እስከ አሁን ያስመዘገበቻቸውን መልካም ተመክሮዎች ማሳደግና ዘላቂነታቸውን ማረጋገጥ ታላቅ ተግዳሮት ቢሆንም አዲስ በሆነ አፍሪቃ መር አቀራረብ በሽታውን ለመዋጋትና ለማጥፋት በቀጣይ ዓመታት ተግቶ መሥራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡ ከዚህም ጋር ለሕክምናው ሁሉን አቀፍ ተደራሽነት ለማስፋት ዓለም አቀፍ አጋርነት ወሳኝ መሆኑን፣  በአህጉሪቱ አገሮች መካከል ልምዶችን መለዋወጥና ሳይንሳዊ ዕውቀቶችን ማሳደግም ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ከመናገር በቀር ለሚ/ር ሚሼል ሲዲቤ ጥያቄ የሰጡት ቀጥተኛ ምላሽ የለም፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእንግሊዝኛው ክፍል “Meet ETv” ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ለግብረ ሰዶማውያን ጥበቃ ስለማድረግና የሚደርስባቸውን መድልዎ መከላከል እንደሚገባ ስለተናገሩት ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፤ በሰጡት ምላሽም ጥሪያቸው ለሰዶማውያኑ ‹መብት› ሕጋዊነት/Legalisation/ ወይም ግብረ ሰዶምን በማይቀበሉ ሃይማኖታዊ ቡድኖች ላይ ለመጫን ሳይሆን ሰዶማውያኑ ለማንኛውም አገልግሎት ተደራሽነት ይኖራቸው ዘንድ ከፍ ያለ ርኅራኄ/Compassion/ እንዲደረግላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ሰዶማውያን በሁሉም ቦታ መኖራቸውን የተናገሩት ሚ/ር ሲዲቤ፣ “አንድ ሰው [ሰዶማዊ] በመሆኑ ብቻ ከተለያዩ አገልግሎቶች መገለል የለበትም” በማለት ገሞራዊነትን ወንጀል ያደረጉ 80 የዓለም አገሮችን “homophobic” ከማለት አልታቀቡም፡፡
ይገርማል! ሚ/ር ሚሼል ሲዲቤ በትውልዳቸው ከአፍሪቃ - ማሊ ናቸው፡፡ መቀመጫው ዋሽንግተን ዲሲ በሆነው “Pew Research Center” እ.አ.አ በ2007 በግብረ ገሞራ ላይ በሰበሰበው ዓለም አቀፍ የአመለካከት ቅኝት/Global Attitudes Survey/ 98 ከመቶ ማሊያውያን ሰዶማዊነት ማኅበረሰቡ ሊጸየፈውና ሊያወግዘው የሚገባ ወራዳ ተግባር መሆኑን እንደሚያምኑ ታውቋል፡፡ ከማሊ ሕዝብ 90 በመቶ የሱኒ እስልምና አማኒ ሲሆን አንድ በመቶው ክርስቲያን /ካቶሊክና ፕሮቴስንታንት/ የተቀረው ዘጠኝ በመቶ ደግሞ የልማድ እምነቶች ተከታይ ነው፡፡ ማሊ ተፈጥሯዊ ያልሆነውን ግብረ ገሞራን ወንጀል የሚያደርግ ሕግ ገና ለማውጣት እየሠራች ሲሆን ሕዝቡ ድርጊቱን ያጸየፈው ሃይማኖቱና ባህሉ በፈጠረለት አስተሳሰብ እንደሆነ ተገልጧል፡፡
የአሜሪካንንና የተቀረውን ዓለም አስተሳሰብ በሚያንፁ ጉዳዮች፣ አመለካከቶችና አዝማሚያዎች ላይ ድጋፍ የሚሰጡ መረጃዎችን በማውጣት የሚታወቀው ይኸው ድርጅት ባካሄደው በዚሁ ቅኝት 97 በመቶ ኢትዮጵያውያን ባላቸው ፀረ-ገሞራዊነት ከዓለም በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ 43.5 ከመቶ (በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ሰበካ ጉባኤ መምሪያ መረጃ 45 ሚሊዮን) ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ 33.9 የእስልምና፣ 18.6 የፕሮቴስንታንት እምነት ተከታይ የሆነባት ኢትዮጵያ ግብረ ሰዶማዊነትን “ለንጽሕና ክብር ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆኑ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች” በማለት ድርጊቱን ወንጀል የሚያደርግ ሕግ ያላት ሲሆን እንደ ወንጀሉ አፈጻጸም ከ3 - 15 ዓመት ሊያስቀጣ እንደሚችል በአንቀጽ 629 ላይ ተደንግጓል፡፡
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ሊቃውንት ጉባኤ “ከሰዶማውያን ርኵሰት ተጠበቁ” በሚል ርእስ በ2002 ዓ.ም ባሳተመው መጽሐፍ፣ ግብረ ሰዶማውያን በሽተኞች መሆናቸውን፣ በሽታቸውም አእምሮታዊ እና አካላዊ መሆኑን፣ አእምሮታዊው እብደት ሲሆን አካላዊው በሽታ ደግሞ ኤድስ፣ የፊንጢጣና የአንጀት መቁሰል እንደሆነ የሕክምና ባለሞያዎች ማረጋገጣቸውን ይገልጻል፡፡ “ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንደ ብሉይ ኪዳን በሰዶማውያንና ሰዶማውያት ላይ ቀጥተኛ የሞት ፍርድ ይፈርዳል፤” ያለው መጽሐፉ ይሁንና ለሰዶማውያኑና ሰዶማውያቱ መንፈሳዊ ቅጣት በመስጠት ከነፍሳዊ ቅጣት ለመታደግ ጥረት መደረጉን አስረድቷል፡፡ በ314 ዓ.ም በዕንቈራ /ዛሬ አንካራ/ የተደረገው የአብያተ ክርስቲያን ጉባኤ በ16ው ቀኖና፣ ሰዶማውያንና ሰዶማውያት የመጸጸታቸውና የቀና ኅሊናቸው ንጽሕና እስኪታወቅ ድረስ መላ ዘመናቸውን በንስሓ እንዲኖሩ፣ ከንዑሰ ክርስቲኖች ጋርም እንዲጸልዩ አዝዟል፤ የዕድሜ ልክ ንስሓው የበደሉን ክብደት እንደሚያሳይ በመጽሐፉ ላይ ተብራርቷል፡፡
በተፃራሪ የ“Pew Global Attitudes Project” ያወጣው የአመለካከት ቅኝት ጥናት ከምንም ያልቆጠሩ የሚመስሉት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወ/ሮ ሂላሪ ክሊንተን የበርካታ አገሮች ፀረ-ግብረ ሰዶማዊ ሕግ፣ ሃይማኖታዊ ሥርዐትና ባህላዊ እሴት ምንም ይሁን ምን “ሰብአዊ መብት ነው” ያሉትን ገሞራዊነትን /ሰዶማዊነትን አስመልክቶ ማሻሻያዎች ይደረጉ ዘንድ አሜሪካ የውጭ ርዳታና ዲፕሎማሲ አቅሟን እንደምትጠቀም አስታውቀዋል፡፡ ወይዘሮዋ በጄኔቭ ለዲፕሎማቶች ሲናገሩ፣ “የማይታዩ ሕዳጣን”/Invisible Minorities/ ያሏቸው ሰዶማውያንና ሰዶማውያት፣ “ከሕዝቡ ውስጥ የተገኙ የእያንዳንዱ ማኅበረሰብ አካል ናቸው፤ ሰዶማዊነትም ሰብአዊ እውነት እንጂ ምዕራባዊ ፈጠራ አይደለም” በማለት መንግሥታት የሚደርስባቸውን ጥቃት፣ እስርና ግድያ ለመከላከል ቸል ከማለት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡ ወ/ሮ ክሊንተን ንግግራቸውን እንደጨረሱ ዲፕሎማቶቹ በፍጥነት አዳራሹን ለቀው በመውጣት ተቃውሟቸውን ማሳየታቸውን አሶሽዬትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ይኸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዕወጃ የአሜሪካ ጥብቅ አጋር ከሆኑትና ሰዶማዊነት በሕግ ወንጀል፣ በሃይማኖት ኀጢአት በባህልም አጸያፊ ከሆኑባቸው እንደ ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ግብጽ፣ አፍጋኒስታን፣ ቦትስዋና፣ ዩጋንዳ፣ ጋና እና ናይጄሪያ አገሮች ጋር ግንኙነቷን አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ተነግሯል፡፡ የወ/ሮዋ ዕወጃ የቀጣይ ዓመት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫን እንጂ እንደተባለው ርዳታን በቀጥታ እንደማይመለከት የተናገሩ ተንታኞች በበኩላቸው፣ የኦባማ አስተዳደር በአፍሪቃ የሰዶማውያንን አኗኗርለማሻሻልእና ለሰዶማውያን መብት የቆሙ ቡድኖችን በማጠናከር በአህጉሩ እየገነገነ ነው የሚባለውን የቀኝ ክንፍወንጌላውያንእንቅስቃሴ/American evangelical Christian groups/ ለመቋቋም ያለመ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
ዘ ኦብዘርቨር” እንደዘገበው ከአሜሪካ ቀደም ሲል የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን የሰዶማውያን መብትን በማይቀበሉ አገሮች ላይ መንግሥታቸው የሚሰጠውን የአጠቃላይ በጀት ድጋፍ የማቀብ ርምጃ እንደሚወስድ መግለጻቸውን ተከትሎ እንደ ናይጄሪያ እና ዑጋንዳ ያሉ አገሮች የፀረ-ገሞራ ሕጋቸውን/anti-gay legislation/ የሚያጠበቅ ጠጣር ርምጃ እየወሰዱ ነው፡፡
የናይጄሪያ ሴኔት በግብረ ሰዶማዊነት ድርጊት የተሰማራ ግለሰብ ላይ እስከ 14 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ግብረ ሰዶማውያንን የተባበረ ወይም የተመሳሳይ ጾታ ጥምረትን የደገፈና ያበረታታ ደግሞ የ10 ዓመት እስራት ይጠብቀዋል፡፡ ውሳኔው በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጉድላክ ጆናታን ሲጸድቅ የሀገሪቱ ሕግ ሆኖ ተፈጻሚነት የሚኖረው ሲሆን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ ቤተሰቦችና ጓደኞች ለተመሳሳይ ሴቴና ወንድ ተጋቢዎች፣ የሁለቱም ጾታ ተራክቦ ፈጻሚዎችና ቀያሪዎች ሁሉ ድርጊታቸው ወንጀል በመሆኑ ጥብቅ ርምጃ የሚወሰድባቸው ይሆናሉ፡፡ የዚምባቡዌው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ የዴቪድ ካሜሮንን ዛቻ “ሰይጣናዊ” በማለት በይፋ የዘለፉ ሲሆን በሰዶማዊነት ተግባር የተገኙ ዜጎቻቸው ሁሉ አይቀጡ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቀዋል፡፡ የዑጋንዳ መንግሥት ቃል አቀባይ በበኩላቸው የካሜሮን ማስጠንቀቂያ የቅኝ ግዛት አቀንቃኝነታቸውን እንዳሳበቀባቸው ገልጸው “ባህላችንና እሴታችን ግብረ ሰዶማዊነትን አይቀበልም” በማለት አገራቸው ከርዳታ ጥገኝነት ለመላቀቅ የነዳጅ ዘርፏን እንደምታስፋፋ ተናግረዋል፡፡ እ.አ.አ በ2009 የዑጋንዳ ፓርላማ ግብረ ሰዶማውያንን በሞት የሚቀጣ ሕግ ለማውጣት ትልመ ሐሳብ ማቅረቡ ለለጋሽ አገሮች ዛቻ ዳርጎታል፡፡
“ርዳታ ይጠቅመናል፤” ያሉት የጋናው ፕሬዝዳንት ጆን አታ ሚልስ፣ ለርዳታ ሲባል ግን የአገራቸውን ፍላጎት የሚፃረር ተግባር ተቀባይነት እንደማያገኝ አሳስበዋል፡፡ በሕዝባዊ መነሣሣት እና በምርጫ መካከል እየተናጠች በምትገኘው ግብጽ የቢቢሲ ዘጋቢ የሆነችው ራንያህ ሳብሪ፣ የአሜሪካ መግለጫም ይሁን የእንግሊዝ ማስጠንቀቂያ በየትኛውም የግብጽ ፖሊቲካ ፓርቲዎች(liberals, secularists and Islamists) ይሁን መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ዘንድ ጨርሶ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ፈጽሞ ቢተዉት መልካም እንደሆነ መክራለች፡፡
የወ/ሮ ሂላሪ ክሊንተን መግለጫ ሂዩማን ራይትስ ዎችን ጨምሮ ስም ያወጡ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ድጋፋቸውን ሲቸሩት ለቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዕጩ ሆኖ ለመቅረብ የሚፎካከሩት የሪፓብሊካን ፓርቲ ተወዳዳሪዎች ደግሞ የኦባማን አስተዳደር ውሳኔ ተችተውታል፡፡ የቴክሳሱ ገዥ ሪክ ፔሪ “በውጭ አገሮች የሰዶማውያንን ልዩ መብት አስከብራለሁ” የሚለው የአስተዳደሩ ውሳኔ የአሜሪካንን ጥቅም እንደማያስጠብቅ ተናግረዋል፡፡
አልያ ኤልማሃዲ የተባለች የኻያ ዓመት ግብጻዊ “Rebel's Diary” በተባለው መጦመሪያዋና ፌስቡኳ ላይ የገዛ ራስዋን ዕርቃን ሥዕለ ገጽ በመለጠፍ በግብጽ ግለሰባዊ ምርጫዎችን የሚያስከብር የማሻሻያ ርምጃ እንዲወሰድ በመጠየቋ በታህሪር ተቃዋሚዎች ተደብድባ ከአደባባዩ እንድትባረር ተደርጋለች፡፡ የግብረ ሰዶም ነገር የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን፣ የየአገሩን ተቃዋሚ ፖሊቲካ ፓርቲዎችንና ድርጊቱን የሚያነውረውን የየአገሩን አብዛኛውን ማኅበረሰብ በተለያየ መድረክ አቁሞ እርስበርስ ማናተፉ ያልተዋጠላቸው የሚመስሉት ኢትዮጵያዊቷ ጦማሪት ማሕሌት ሰሎሞን በአንፃሩ እንደ ሕዝብ ያለፍርሃት መኖርና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ማእከላዊ ጉዳይ መሆኑ መዘንጋት እንደሌለበት መክረዋል፡፡
የእሚ (http://www.mahletzesolomon.com/) በተሰኘ መጦመሪያ መድረካቸው የሚታወቁት ማሕሌት “So Gay Activists are not Terrorist” በሚል ርእስ ባሰፈሩት ጦማራቸው፡- በቅድመ (ICASA) ጉባኤ አምሸር የተሰኘው  የሰዶማዊነት አቀንቃኝ ቡድን የኢያእምሮ ስሑት ምግባር/insanely wrongful deed/ ስለሆነው ሰዶማዊነት በአዲስ አበባ ስብሰባ እንዲያካሄድ መፈቀዱ፣ መንግሥት የሕዝቡ ግዕዘ ኅሊና የማይፈቅደውን ነውር ባለመከላከል የብዙኀኑን ትኩረት ለማስቀየስ አልያም የሊበራል አቀንቃኞችን ጸጥ ለማሰኘት የተጠቀመበት አጀንዳና ስልት አድርገው እንደሚወስዱት ገልጸዋል፡፡ ስብሰባውን ለመቃወም ያዘጋጁትን ጋዜጣዊ መግለጫ ከመስጠት በተከለከሉትና ለሚያገለግሉት ሕዝብ ማኅበራዊና ሰብአዊ እክል የመድረስ ሓላፊነት ያለባቸው “የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ጉባኤ” አባላት በሚታይባቸው ተደጋጋሚ ድክመት አመኔታ እንዳጡባቸው የጻፉት ጦማሪቷ፣ በተከለከለው ጋዜጣዊ ጉባኤያቸው ወቅት ለተሰራጨው ጽሑፋዊ መግለጫቸው ግን ዋጋ እንደሚሰጡት አልሸሸጉም፡፡
የግብረ ሰዶማውያኑ የቅድመ (ICASA) ስብሰባ እንደሚካሄድ ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ ፀረ ሰዶማዊ ጭብጦች በአዲስ አበባ የሚገኙ ሰባክያነ ወንጌል ዋነኛ ርእሰ ጉዳይ ሆኖ የሰነበተ ሲሆን አንዳንዶቹም በፌስቡክ ማኅበራዊ ዓምዳቸው በመንግሥት እና በሃይማኖት አባቶች ግልጽ ትችቶችን ሰንዝረዋል፡፡
የፀረ ተሐድሶ ሰባክያን ጥምረት አባል የሆኑት መ/ር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴ “ኢትዮጵያዊ” በሚል ርእስ ባሰፈሩት ሐተታ፣ “ስለዚህ ጉዳይ ለምን ዝም አላችሁ? ይህን ማስቆም ካልቻላችሁ አባትነታችሁ ምኑ ላይ ነው?” በማለት አባቶችን ወቅሰዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ2002 ዓ.ም ምርጫ ማግሥት፣ “ይህ ሕዝብ ክብሩን ጠብቆ የሚራብ ሕዝብ ነው” በማለት የተናገሩትን በማስታወስም “መንግሥት ለዜጎቹ ሰብእና ከቆመ፣ መቀሌ ላይ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል እየተከበረ በአዲስ አበባ ብሔር ብሔረሰቦችን ሁሉ የሚያዋርድ [የትኛውም ብሔረሰብ የዚህ ደጋፊ አይደለምና] ስብሰባ ለምን ፈቀደ? ርዳታቸው ቀርቶብን ክብራችንን ጠብቀን እንድንራብ ያልተወሰነውስ ለምንድን ነው?” በማለት ጠይቀዋል፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት አንድነትን የሚያፈርስ፤ የሕዝቡን ጀግንነት፣ ማኅበራዊ እሴትና መተማመን የሚያጠፋ እንዲሁም ትውልድን የሚቀንስ፣ ሕገ ተፈጥሮን የሚፃረር ተግባር መሆኑን ያስረዱት መምህሩ፣ “የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ጉባኤ” አባላት ሊያወግዙት ነበር በተባለው ስብሰባ በታዳሚነት መገኘታቸው “አሳፋሪ ታሪካችን ነው” ሲሉ ነቅፈዋል፡፡
መልእክታቸውን ሲያጠቃልሉም የሚከተለውን ብለዋል፡- “ርግጥ ነው፤ ኢትዮጵያዊ ይሞታል እንጂ መልኩን አይቀይርም፤ ክብራችንን ጠብቀን እንሙት!! ክብራችንን ጠብቀን እንሙት!! ሞት ላይቀር እየኖሩ ከመሞት ሞቶ መክበር ይሻላልና፡፡ ያመጡትን ዳቦ ይዘውልን ከነ ርኵሰታቸው ይሂዱልን!!...መንግሥት ሕዝቡን አዋርዶታል፤ መንፈሳዊ እና ባህላዊ ማንነታችንን ገደል የሚከት ነገር አድርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት ሃይማኖቱንና አገሩን የሚያከብር ሁሉ አዝኗል፡፡ በዚህ እግዚአብሔር ተቆጥቶ የሚያመጣብንን መመለስ የምንችልበት አቅም የለንምና ቁጣውን በትዕግሥት መዐቱን በምሕረት እንዲመልስልን ሁላችንም በያለንበት እናልቅስ፡፡ ወላጆች ለወለዷቸው፣ ካህናት ለንስሓ ልጆቻቸው፣ [የሥነ ጥበብ ሰዎች] ለሞያ አክባሪዎቻቸው፣ ጸሐፍት እና ገጣምያን ለአንባቢዎቻቸው፣ ሰባክያን  ለምእመናን ሁሉም ወደ እግዚአብሔር ያለቅስ ዘንድ ያሳስቡ፤ ባሕታውያን መነኮሳትም ይጸልዩ፤ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር እንዲያርቅልን፤ ለመሪዎቻችንም ልብ እንዲሰጥ፡፡”
እንደ መምህር ጳውሎስ ሁሉ በርካታ ዜጎች የግብረ ሰዶማውያኑን ስብሰባ እና የ(ICASA)ን ጉባኤ አንድ በማድረግ ክፉኛ ቢያብጠለጥሉትም ጉባኤው በዝግጅቱ የተዋጣለት ከመሆኑም በላይ ለቀጣይ ጉባኤያት “ደረጃን ያስቀመጠ” እንደነበር የመንግሥት መገናኛ ብዙኀን ያናገሯቸው የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም እና የጉባኤው ዝግጅት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይገረሙ አበበ ገልጸዋል፡፡ እንደዘገባው 7361 ተሳታፊዎች ከ1000 ያላነሱ ጥናቶች በቀረቡበት ጉባኤ የተሳተፉ ሲሆን ቀሪዎቹ 3000 ያህል ተሳታፊዎች ደግሞ መረጃ እና የልምድ ልውውጥ የተደረገባቸው የቃል ጥናቶች /Oral Presentation and Poster Discussion/ እና የፖስተር ዐወደ ርእይ /Poster Exhibition/ በቀረበባቸው የሲቪል ማኅበረሰብ መንደር ተስተናግደዋል፡፡ በአንድ ጊዜ 14 ስብሰባዎችን እንዲያስተናግድ ሆኖ ለጉባኤው የተሰናዳው የሚሌኒየም አዳራሽ “አክሱም፣ ዐባይ፣ ተከዜ፣ ኦሞ፣ ሶፍ ዑመር፣ ነጭ ሣር፣ ኒያላ፣ ዋሊያ፣ ሻላ፣ አብያታ፣ አዋሽ፣ ላሊበላ፣ ስሜን፣ ፋሲለደስ” በተሰኙ የኢትዮጵያ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስሕቦች በተሠየሙ አዳራሾች የተከፋፈለ ሲሆን ለዝግጅቱ አራት ሚሊዮን ዩሮ ወጭ መደረጉ ተገልጧል፡፡
የደጀ ሰላም ታዛቢዎች እንደተናገሩት በማኅበረሰብ መንደር በተስተናገዱት የፖስተር ዐውደ ርእይና የቃላዊ ውይይት 320 ክዋኔዎች፡- በብዙዎቹ የአፍሪቃ አገሮች (በተለይም በናይጄሪያ፣ ዩጋንዳ፣ ዛንዚባር ኬኒያ፣ ቡሩንዲ፣ ግብጽ፣ ቱኒዝያ እና ሞሮኮ) ወንድ ግብረ ዝሙት አዳሪዎችን ጨምሮ ሰዶማውያኑና ሰዶማውያቱ ኅቡአን ከመሆናቸው የተነሣ ኤፒዲሞሎጂያዊ መረጃዎችን ማግኘት ማዳገቱን፣ ከየአገሮች የሕግ፣ ባህልና ሃይማኖታዊ አቋም የተነሣ ለጤና አገልግሎቶች ተደራሽ ባለመሆናቸው በአባላዘርና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ክፉኛ መጠቃታቸውን የሚያወሱቱ ጥቂት የሚባሉ አልነበሩም፤ የክዋኔዎቹ አቅራቢዎችም ከየአገሮቹ የመጡ የሰዶማያንና ሰዶማውያት ቅንጅቶች/ጥምረቶች እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡
ለአብነት ያህል ከኬኒያ እና ቡሩንዲ በመጡት የጥምረቶቹ ተወካዮች/የፕሮግራም ሓላፊዎች/ “Sexual Minorities Navigating Restrictive Legal Spaces around HIV and Health; Community Driven Ownership of the HIV and STI Response within East Africa” በሚል ርእስ የቀረበው የውይይት ርእሰ ጉዳይ፣ ሰዶማውያን በክፍለ አህጉሩ የውንጀላ፣ ማግለል እና አድልዎ /criminalization, stigma and discrimination/ ሰለባ መሆናቸውን ያትታል፤ ሰዶማውያኑ ራሳቸው በሕዝብ ጤና መድረኮች/ ክርክሮች ወቅት በመብት ላይ የተመረኮዙ የመርሐ ግብር ዕቅዶች/Right Based Programming/ ቀዳሚ አጀንዳ ለማድረግ እንዲታገሉም ይወተውታል፡፡ ከዚህም አልፎ የምሥራቅ አፍሪቃ መንግሥታት በብሔራዊ የጤና ፖሊሲ ክለሳዎቻቸው፣ በጤና ሁኔታዎች አመልካቾቻቸው፣ በጤና መርሐ ግብር ግምገማዎቻቸውና ዝግጅቶቻቸው እንዲሁም ሳይንሳዊ ምርምሮቻቸው የግብረ ሰዶማውያንን ተሳትፎ እንዲያረጋግጡ ጠይቋል፡፡ የሰዶማውያኑን ስብሰባ በተ.መ.ድ የስብሰባ አዳራሽ ያካሄደው አምሸር የክዋኔ ወለል/ፓቪልዮን የተሰጠው ሲሆን ወለሉም በተ.ቁ 208 የተሠየመ ነበር፡፡
እንግዲህ ሰሞኑን የኦባማ አስተዳደር ፀረ-ሰዶማዊ ሕጎቻቸውን ለማጥበቅ የሚንቀሳቀሱ አገሮችን በመኰነን በወ/ሮ ሒላሪ በኩል ያወጣው መግለጫ በአንድ ገጹ እንዲህ ያሉ ጥምረቶችንና ቅንጅቶችን ለማበረታታትና ለመደገፍ ፍላጎቶች እንዳሉበት ተንታኞች አመልክተዋል፡፡ እ.አ.አ በ2015 አንድም ሰው በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እንዳይያዝ፣ እንዳይገለል እና እንዳይሞት/Zero new HIV infections. Zero discrimination. Zero AIDS-related deaths/ ዐቅዶ ለሚሠራው የተ.መ.ድ ኤድስ ፕሮግራም ከፍተኛውን የበጀት ድጋፍ (54.2 በመቶ) የምትሰጠው አሜሪካ መሆኗ ከመግለጫው አኳያ ከፍተኛ ስጋት የሚያጭር ነው፡፡
በኅዳር ወር መጨረሻ ላይ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ “ዓለም አቀፍ የጤና ትብብር”/Global Health Intiative - GHI/ በተሰኘ ዕቅዳቸው እ.አ.አ በ2013 ስድስት ሚሊዮን ሰዎችን የፀረ-ኤድስ መድኃኒት ተጠቃሚ ለማድረግ፣ 1.5 ሚሊዮን ለሚሆኑ ነፍሰ ጡሮች ቫይረሱ ከእናት ወደ ፅንስ እንዳይተላለፍ ለመርዳት ቃል ገብተዋል፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትን ዶናልድ ቡዝን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ “የእናቶችንና ሕፃናትን ሞት መቀነስ፣ የቲቢ፣ ወባ እና የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታዎችን መከላከል” በሚል ዓላማ ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ አሁንም በቀጠለው “የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ አስቸኳይ ጊዜ ዕቅድ”/PEPFAR/ 39 ቢሊዮን ዶላር የተለገሠ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ኢትዮጵያ 1.4 ቢሊዮን ዶላር ተረድታለች፡፡
ከርዳታው በተፈጠረ አቅም ሩብ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የፀረ-ኤድስ መድኃኒት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ የኤች፣አይ.ቪ የምክክርና ምርመራ አገልግሎትም በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል፡፡ ከ1995 - 1999 ዓ.ም በአዲስ አበባ ውስጥ ብቻ በበሽታው ሳቢያ የሚከሠተው ሞት በ70 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡ አሳዳጊ አልባ የሆኑ 493 ሺሕ ሕፃናትን ጨምሮ 1.1 ሚሊዮን ሰዎች ክብካቤና ድጋፍ እያገኙ መሆኑም ተነግሯል፡፡ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በግሎባል ፈንድ እና ዓለም አቀፍ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በጎ አድራጊዎች /IOCC/ በኩል ርዳታውን የሚያገኝ ሲሆን ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከል በርካታ ሥራዎችን ያከናወነና በማከናወን ላይ መሆኑን የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ባለፈው ዓመት ግንቦት ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ያቀረቡት የአምስት ዓመት የሥራ ክንውን ሪፖርት ያስረዳል፡፡
ቤተ ክርስቲያን ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር መታቀብ፣ መታመን እና አለማግለል የሚሉ መርሖች ያሏት ሲሆን የፕሮግራሙ ዋና ዋና ተግባራት፡- የአቅም ግንባታ ሥልጠና፣ የምክክር ጉባኤ፣ የልምድ ልውውጥ፤ በጠባይ ለውጥ ላይ ያተኮረ ትምህርትና መረጃ ለሕዝቡ መስጠት፤ አሳዳጊ አጥ የሆኑትንና ለችግር የተጋለጡ ሕፃናትን መከባከብ፤ ኤች.አይ.ቪ በደማቸው የሚገኝባቸውን ወገኖች መደገፍና መከባከብ፤ የገቢ ማግኛ ምንጭ ለመፍጠር የሚያስችል የክህሎት ሥልጠና መስጠት መሆኑ ተገልጧል፡፡ እንደ ብፁዕነታቸው ሪፖርት፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በቅዱስ ፓትርያሪኩና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ሐዋርያዊ ጉዞ/Patriarch and Arch Bishops AIDS Rallies/ ተካሂዷል፤ ሰባክያነ ወንጌልና ካህናት ሠልጠነዋል፤ የማኅበረሰብ ውይይት ተከናውኗል፤ ከ330 በላይ ለሆኑ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የአቻ ለአቻ ሥልጠናዎች ተሰጥቷል፡፡
በ44 አህጉረ ስብከት፣ 36 ቅርንጫፎች ይዞ የሚንቀሳቀሰው የኮሚሽኑ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ መምሪያ እ.አ.አ በ2010 ከግሎባል ፈንድ ሰባተኛ ዙር ፕሮጀክት ባገኘው ብር 26 ሚሊዮን ርዳታ ለ107 ሺሕ ሕፃናት የምግብ፣ መጠለያ፣ አልባሳት፣ የት/ቤት ቁሳቁስ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ በበሽታው ተጎድተው አልጋ ላይ ለዋሉና ረዳት ለሌላቸው ሰዎች የቤት ለቤት ክብካቤ በማድረግ የምግብ፣ መጠለያ፣ አልባሳት ርዳታ በማድረግ እንደሚገኝ የኮሚሽኑ ሰነዶች ያስረዳል፡፡ በ25 አህጉረ ስብከት የሚገኙ የ42 ወረዳ ሕፃናት የድጋፍና ክብካቤ እንዲሁም በ198 ወረዳዎች በ826 አመቻቾችና በ100 ማኅበረሰብ መካከል የማኅበረሰብ ውይይት ተደርጓል፡፡ ለ10,174 ካህናት የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ጠበልንና የፀረ-ኤድስ መድኃኒቱን አንድ ላይ መጠቀም የእግዚአብሔርን ማዳን ኃይል እንደመጠራጠር ተደርጎ ይተረጎም የነበረው የተዛባ አመለካከት ተወግዶ ሁለቱንም መጠቀም እንደሚቻል የማሳመን ሥራ ተሠርቷል፡፡
የተ.መ.ድ ኤድስ ፕሮግራም ከሚያስተባብረው አንዱ የሆነው የተ.መ.ድ የሕዝብ ፈንድ (UNFPA) በተገኘ ድጋፍ መጽሐፈ ግጻዌን መሠረት ያደረገ “የልማት ወንጌል” የተባለ መጽሐፍ በቤተ ክርስቲያን የዕለት ተዕለት አስተምህሮ ጋር ተካትቶ ተዘጋጅቷል፤ በስምንት የካህናት ማሠልጠኛና በሦስቱ የነገረ መለኮት ኮሌጆች ሥርዐተ ትምህርት ውስጥም እንዲጣጣም መደረጉ ተገልጧል፡፡ “የልማት ወንጌል” መጽሐፍ በይዘቱ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን የመከላከል፣ የሥነ ተዋልዶና ጤናማ እናትነትን እንዲሁም የጾታ እኩልነትን የተመለከቱ መልእክቶችን መያዙ ተዘግቧል፡፡
ኮሚሽኑ በ16ው የ(ICASA) ጉባኤ ላይ “Developmental Bible:Theology and Public Health Working Hand in Hand in the Ethiopian Orthodox Church” በሚል ርእስ ልማትን አስመልክቶ በሰባት አህጉረ ስብከት በተመረጡ አህጉረ ስብከት በሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ስለ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፣ ሥነ ተዋልዶ ጤና፣ ጎጂ ልምዶችና የሴት ልጆች ግርዛትን በተመለከተ 3303 ካህናት፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ሴቶች የመንፈሳውያን ማኅበራት አባላትን ዕውቀት፣ አመለካከትና ልምድ የፈተሸበትን ጥናት ውጤት አቅርቧል፡፡
በጥናቱ ውጤት መሠረት ኅብረተሰቡ የኤች.አይ.ቪ ምርመራና ምክር አገልግሎት (ቅድመ ጋብቻ ጭምር) ተጠቃሚ እንዲሆን በማስተማርና በመቀስቀስ፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች የቅድመ ወሊድ ክትትል፣ የኤች.አይ.ቪ ምርመራና ምክር አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ በአጭር ጊዜ በማሳመንና ግንዛቤ በማስጨበጥ፣ ያለዕድሜ ጋብቻን በማዘግየትና የሴት ልጅ ግርዛትን በማስቀረት በኩል በ”ልማት ወንጌል” የሠለጠኑ ካህናት አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ የሚገልጸው የጥናቱ ክፍል ይገኝበታል፡፡ ሴቶች በባሎቻቸው የሚደርስባቸውን ድብደባ አስመልክቶ ከተጠየቁት የሚበዙት(የሰንበት ት/ቤት ሴቶች ወጣቶች ሳይቀር) በአዎንታ እንደሚመለከቱት የሚገልጸው ጥናቱ የሴቶችን አቅም ለማጎልበት ብዙ መሠራት እንዳለበት ይጠቁማል፡፡
በጥናቱ ዳራ ላይ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባሻገር የሕዝቡን አመለካከት የሚያንፁ፣ ለትምህርት እና መረጃ ምንጭነት/ተቋምነት ምቹ የሚያደርጓት 45,000 ገዳማትና አድባራት፣ 500,000 ካህናትና ዲያቆናት፣ ሰባት ሚሊዮን የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ በመንፈሳውያን ማኅበራት የታቀፉ 10 ሚሊዮን ሴቶች እንዳሏት ተመልክቷል፡፡
የኮሚሽኑን ሊቀ ጳጳስ ጨምሮ ስድስት ልኡካን የተሳተፉበት ጉባኤው በፖስተር ዐውደ ርእይ ክፍል የኮሚሽኑን ክንውኖችና ዕቅዶች የሚገልጹ ፖስተሮች፣ ብሮሸሮች እና የፕሮጀክት ሰነዶች አቅርቧል፡፡ ይህም ኮሚሽኑን ከዓለም አቀፍ ርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ጋር የበለጠ በማስተዋወቅ ተጨማሪ ባለሞያዎችን በማሠልጠን አገልግሎቱን ለማስፋፋት የሚችልበትን ድጋፍ የሚያገኝበትን አዲስ የትብብር መሥመር እንዳመቻቸለት ተገልጧል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኮሚሽኑን በ30 አህጉረ ስብከት በመንቀሳቀስ ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሕሙማን የድጋፍና ክብካቤ ሥራ ለመሥራት ያስቻለው የዓለም አቀፍ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በጎ አድራጊዎች/IOCC/ ፕሮጀክት ተጠናቋል፤ ቀሪው የፕሮጀክቱ ክፍል በሆነውና ከሌሎች ምንጮች/የኢትዮጵያ የእምነት ተቋማት የልማት ፎረም፣ ፖፑሌሽን ካውንስል፣ ክርስቲያን ኤይድ ኢትዮጵያ፣ አውሮፓ ኅብረት፣ ዴንማርክ ቤተ ክርስቲያን/ በተገኙ ድጋፎች ለምእተ ዓመቱ የልማት ግብ ወሳኝ ተደርጎ በሚታየው ቫይረሱ ከእናቶች ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ የሚከላከለውንና ሌሎችንም ፕሮጀክት እየተገበረ ይገኛል፡፡
የ16ው /ICASA/ ጉባኤ ተሳታፊዎች ለጋሾች የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ብቻ ሳይሆን “ከለጋሾች የተሰጠው የኤድስ ፈንድ ሁሉ የት ገባ? ምን ላይ ዋለ?” ብለው ባካሄዱት ሰልፍ መነሻነት የአፍሪካ መንግሥታት አስተማማኝ የጤና ሥርዐትና መልካም አስተዳደር መዘርጋት እንዳለባቸው ተጠይቋል፡፡ ተመሳሳይ ጥያቄ በልማት ኮሚሽኑ የበጀት አጠቃቀም ላይ ሊነሣ እንደሚገባ የሚጠይቁ የኮሚሽኑና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሠራተኞች ቁጥርም በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ኮሚሽኑ በቀደሙት ጊዜያት ለጋሾችን በማሳመን ያገኘው የፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ገንዘብ በፓትርያርኩ ትእዛዝ አላግባብ ወጪ ሲደረግ መቆየቱንና አሁንም ያለ ኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ዕውቅና ኮሚሽነሩን ዶ/ር አግደው ረዴን በቀጥታ የማዘዝ ሙከራዎች መኖራቸው ተነግሯል፡፡
ይህም “ሁሉም ኢትዮጵያዊ የተሻለ ኑሮ ተፈጥሮለት ማየት” በሚል ርእይ ከ40 ዓመት በፊት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የተቋቋመው ኮሚሽን ተልእኮውን ያሳካ ዘንድ፣ “ብቁ አመራር መስጠት በሚችል የሰው ኀይል መጠናከር ይኖርበታል” በሚሉት በብፁዕ ሊቀ ጳጳሱና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ መካከል የውስጥ ለውስጥ ውዝግቡን እንዳባባሰው ነው የተዘገበው፡፡ ሆኖም የሊቀ ጳጳሱ አቋም ኮሚሽኑ ከለጋሾች ጋር ያለው ግንኙነት እንዳይበላሽ፣ የፕሮጀክቶች ቀጣይነትም እንዳይደናቀፍ ለመከላከል ማገዙ ተጠቁሟል፡፡
16ኛው የ/ICASA/ ጉባኤ ተጠናቋል፡፡ ይህን በማስመልከት ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ዶ/ር ቴዎድሮስ ቀጣዩ ሕዝቡ ስለ ነበረው የእንግዶች አቀባበል አመስግነዋል፡፡ ሕዝቡ ስለተከፋበት የሰዶማውያኑ ስብሰባ ግን ያሉት ነገር የለም፡፡ ቀጣዩ 17ው የ/ICASA/ ጉባኤ ግብረ ሰዶምን ሕጋዊ ባደረገችውና እነ/AMSHeR/ በከተሙባት ደቡብ አፍሪካ ይካሄዳል፡፡ አገራችን ከ10,000 በላይ እንግዶች(አንዳንድ ሚዲያዎች ቁጥሩን በግማሽ ይቀንሱታል) የተገኙበትንና ለሁለት ዓመት የተዘጋጀችበትን የ/ICASA/ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ከማሰናዳት አልፋ ለቀጣይ አዘጋጅ አገሮች “ደረጃ ያስቀመጠችው” አዲስ አበባ በቅርቡ ከ3000 - 7000 እንግዶች የሚገኙበት ሌላ የጤና ጉባኤ እንደምታስተናግድ ተጠቁሟል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኤድስ ማኅበር(SAS) ያስቀመጠውን የጤና ሥርዐት አፈጻጸም፣ የሰላም ሁኔታና የጸጥታ አጠባበቅ፣ የሆቴል፣ ትራንስፖርትና መሰብሰቢያ አዳራሽ የማሟላት አቅም መስፈርቶች መሠረት ታምኖባት መመረጧ ብዙም አከራካሪ ላይሆን ይችላል፤ “የአፍሪካ ኅብረት የጤና ቻርተር የፈረመ” የሚለውም እንዲሁ፡፡ ይሁንና ብዙዎች ምፀታዊ/ድርብ መለኪያ/ እንደሆነ የተቹት “ሰብአዊ መብቶችን ስለ ማክበር” የተመለከተው መመዘኛ ከአገሪቱ ሕግ፣ የባህልና ሃይማኖታዊ እሴት አኳያ ተጣጥሞ መሄድ እንዳለበት ደጀ ሰላም ታምናለች፡፡ የኮንፈረንስ ቱሪዝሙ፣ የገጽታ ግንባታው ተጠናክሮ የቀጠለውን ያህል እንደ አገር ለብዙኀን መልካም ጠባይ ተቃራኒ ስለሆነ ተግባር/የቡድን መብቶች/ና በግለሰብ መብቶች ዙሪያ መወያየትም የሚጠላ አይሆንም፡፡ እስከዚያው ግን የሚያስማማን ቁም ነገር ሰዶማዊነት ሕገ መንግሥታዊ እገዳ እንዲጣልበት የጠየቁ የሃይማኖት አባቶች ባሉባት ኢትዮጵያ ግብረ ሰዶማዊነት እንደ መብት ሊራመድ እንደማይገባው ነው፡፡  
++++

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ላይ ያላት ጽኑዕ ተቃውሞ
(ከሰዶማውያን ርኵሰት ተጠበቁ፤ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ሊቃውንት ጉባኤ፤ 2002 ዓ.ም)

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን በጥብቅ ትቃወማለች፤ ታወግዛለችም፤ የምትቃወመውም ድርጊቱ፡-
·         በቅዱስ መጽሐፍ በብሉይና በሐዲስ ኪዳን ያልተፈቀደና የተወገዘ፤
·         በቀኖና ቤተ ክርስቲያን በጥብቅ የተወገዘ፤
·         በሕገ ተፈጥሮ ያልተፈቀደ፤
·         በእንስሳት የማይፈጸም አስጸያፊ ተግባር፤
·         ኢ-ሰብኣዊ እና ኢ-ግብረ ገባዊ ተግባር፤
·         በተለይ በአሁኑ ጊዜ ይህ ድርጊት ለጤና ጠንቅ የሚዳርግ፤
·         ቀደም ሲል የሰው ልጅ በአጠቃላይ ዕልቂት የተቀጣበት ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት በመሆኑ ነው፡፡

ስለሆነም
1.          በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰውን ወንድና ሴት አድርጎ ስለ ፈጠረ፣ ጋብቻ ወይም የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም የሚገባው በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ነው፡፡ ይህም በቅዱስ ጋብቻ ነው፡፡(ዘፍ.1÷27)
2.         ከዚህ ውጭ በተመሳሳይ ጾታ መካከል የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንዳይፈጸም ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ሲል ይደነግጋል፡- “ከሴት ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ይህ ጸያፍ ነገር ነውና፡፡”(ዘሌዋ.18÷22) “ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው፡፡”(ዘሌዋ.20÷13)
3.         በሐዲስ ኪዳንም ይህ ድርጊት ፈጽሞ የተወገዘ ድርጊት ነው፡፡ “ሴቶቻቸው ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባቸውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ፡፡”(ሮሜ 1÷27) “. . .ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ….የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፤”(1ቆሮ.6÷9-10)
ከዚህ በላይ በብሉይና በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንደተገለጸው በተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና በተመሳሳይ ጾታ መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በእግዚአብሔር ቃል በጥብቅ የተከለከለ ስለሆነ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ድርጊቱን አጥብቃ ታወግዛለች፡፡
የሰዶምና የገሞራ ሰዎችና በዙሪያቸው የነበሩት ከተሞች ሁሉ ፈጽመው የጠፉት በተመሳሳይ ጾታ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሠሩት ኀጢአት እንደሆነ ቅዱስ መጽሐፍ ያስረዳል፤ ያም አጠቃላይ ጥፋትን አድርሶባቸዋል፡፡ ይህም ተመሳሳይ ግብርን በሚፈጽሙ ሁሉ ላይ ሊደርስ እንደሚችል በቅዱስ መጽሐፍ እንደሚከተለው ተገልጦአል፤ “እንዲሁም እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው የነበሩ ከተማዎች በዘለዓለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል፡፡”(ይሁዳ ቁ.7)
ይህ ድርጊት በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተወገዘው ሁሉ በቀኖና ቤተ ክርስቲያንም “ይገብርዎ ኵነኔሆሙ (ሰይፍ ግብረ ገሞራን)”፤ “የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያደርጉ አድራጊውም ተደራጊውም በሞት ይቀጡ”(የሐዋርያት ቀኖና 71) “ግብረ ሰዶምን የሚፈጽሙ በንስሓ ቢመለሱ ዕድሜ ልካቸውን በንስሓ ይኑሩ፡፡”(ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 48)
ስለዚህ ይህ ድርጊት ማለት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ወይም በተመሳሳይ ጾታ መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት፡-
ሀ)ኢ-ክርስቲያናዊ ብቻ ሳይሆን ኢ-ሰብአዊ በመሆኑ፤
ለ)የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የሚፃረር
ሐ)በሕገ ተፈጥሮ በሕግ መጽሐፋዊ የተፈቀደውን በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚፈጸመውን ቅዱስ ጋብቻ የሚያስቀር፤
መ) እንደ ሰዶምና ገሞራ ሰዎች ታላቅ ጥፋትን የሚያመጣ፤
ረ) ለደዌ ሥጋና ለደዌ ነፍስ የሚዳርግ ስለሆነ ምንጊዜም አጥብቃ የምትቃወመው መሆኑን በድጋሚ ታረጋግጣለች፡፡
ይህን ድርጊት በመፈጸም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከዚህ ድርጊት በንስሓ እንዲመለሱና ለሰው ልጅ ከእግዚአብሔር በተሰጠው የአንድ ወንድና የአንዲት ሴት የተቀደሰ ጋብቻ ጸንተው እንዲኖሩ ቤተ ክርስቲያናችን አዘውትራ ትጸልያለች፡፡


ግብረ ሰዶምን በሚመለከት የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ድምፅ

የግብረ ሰዶም ፈጻሚዎችና ደጋፊዎች ቁጥር እጅግ በጣም ከላቀ ደረጃ ላይ በደረሰበት በአሁኑ ጊዜ በግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ስም ታትሞ የወጣው “Homosexuality” የተሰኘ መጽሐፍ የቤተ ክርስቲያኗን አቋም እንደሚከተለው ያስቀምጣል፤
3.ሀ) በዚህ ትምህርት ትንተና ግብረ ሰዶም ሕገ ተፈጥሮን የሚቃረን ድርጊት ስለሆነ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን የሚፈጽሙ ወንዶችንና ሴቶችን ምንነት በቃላት ለመግለጽ የሚያስችል ቋንቋ የለም፡፡ “ወንድና ሴት፤ ባልና ሚስት” የሚለው ቃል እስከ አሁን ሲነገር የኖረው በተፈጥሮ የወንድነትና የሴትነት መለያ አካል ላላቸውና በዚህም አካል የአባትነትንና የእናትነትን ተግባር በመፈጸም የሰው ዘር ቀጣይነት እንዲኖረው ለሚያደርጉ የአዳምና የሔዋን ዝርያ ላላቸው ፍጥረታት ነው፡፡ አሁን ግን በተመሳሳይ ጾታ መካከል ግንኙነት ወይም ጋብቻ የሚፈጸም ከሆነ “ሴት፣ ወንድ” የሚለው የተፈጥሮ ጾታ ልዩነት፣ ልጅ መውለድ፣ ዘር መተካት፣ አባት፣ እናት ተብሎ መጠራት ላይኖር ነው፡፡ ወንድ ራሱ ባልም ሚስትም ልሁን ካለ፣ ሴትም ራስዋ ሚስትም ባልም ልሁን ካለች፣ ሰው ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ ሆነ ማለት አይደለምን? ይህስ ድርጊት የሰውን ዘር ለመተካት የሚያስችል ይሆናል?
3.ለ) ግብረ ሰዶም ፈጻሚዎች እስከ ጋብቻ ድረስ በመሄድ ይህን ተግባር የሚፈጽሙት ወንድ እና ሴትን ማለት ባልና ሚስትን ለሕጋዊ ግንኙነት በሚያነሣሣ የተፈጥሮ ፍቅር ስሕበት አይደለም፡፡ በተፈጥሮ የታዘዘ አማራጭ መንገድ ሆኖም አይደለም፡፡ የቅዱስ መጽሐፍ ፈቃድ ያለበት ተግባር ሆኖም አይደለም፡፡ በመሆኑም ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ግብረ ሰዶም ፈጻሚዎችን ለአባልነት አትቀበላቸውም፡፡ ምስጢረ ቍርባንን እንዲሳተፉ አትፈቅድም፡፡ በዚህ ኃጢአት የሚኖር ማንም ሰው በአስቸኳይ ራሱን ከኃ ጢአቱ ማውጣት ይኖርበታል፡፡
3.ሐ) ግብረ ሰዶም ፈጻሚዎች ግብረ ሰዶምን እንደ ሰብኣዊ መብት በመቁጠር ግብረ ሰዶምን የሚቃወሙ አብያተ ክርስቲያን የሚያደርጉትን የሰብኣዊ መብት ጥሰት አድርገው ያስባሉ፤ ሐሳባቸውን ለውጠውም ለግብረ ሰዶም ሕጋዊ ዕውቅና እንዲሰጠው ይማጠናሉ፡፡ ግብረ ሰዶምን የሚያወግዘው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃልም “የዚያን ጊዜውን ሕዝብ እንጂ የዘመኑን ዓለም አይመለከትም” በማለት ለመሞገት ይሞክራሉ፡፡ ከሕገ ተፈጥሮም ሆነ ከሕገ መጽሐፋዊ አንጻር የግብረ ሰዶምን አስከፊ ኃጢአትነት ገልጸው የሚያስተምሩ አብያተ ክርስቲያናት ግን፡-
. የእግዚአብሔር ቃል ከሚያልፍ የሰማይና ምድር ማለፍ እንደሚቀል በተጻፈው የወንጌል ቃል መሠረት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ለማሻሻል፣ ለማሳጠርም ሆነ ለማስረዘም ሥልጣን ስለሌለው ለግብረ ሰዶም ፈጽሞ ሕጋዊ ዕውቅና መስጠት እንደማይቻል፤
. ግብረ ሰዶም ፈጻሚዎች ያላቸው መብት ንስሓ መግባት ብቻ ስለሆነ የዚህ እኩይ ተግባር ፈጻሚዎች የሚጓዙበት ይህ የኑሮ መንገድ መጨረሻው ገደል መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በመገንዘብ በአስቸኳይ ወደ ንስሓ እንዲመለሱና ከዚህ ዐይነቱ ኢ-ሰብኣዊ እና ኢ-መጽሐፋዊ ሕይወት በመውጣት በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በቅዱስ መጽሐፍ በተፈቀደው የሕይወት መንገድ መጓዝ እንዲጀምሩ ጥሪ ከማድረግ በቀር ሌላ የሚያደርጉት አማራጭ የለም፡፡

የሰዶማዊነት ውግዘት በቀኖና ቤተ ክርስቲያን
ሰዶማዊነት ወይም ግብረ ሰዶም በብሉይ እና ሐዲስ ኪዳናት የተነቀፈውንና የተወገዘውን ያህል በቀኖና ቤተ ክርስቲያንና በቀደምት አበው መጻሕፍትም እጅግ የተጸየፈ፣ የረከሰ እና የተወገዘ ነው፡፡ ሐዲስ ኪዳን እንደ ብሉይ ኪዳን በሰዶማውያንና ሰዶማውያት ላይ በሥጋቸው የሞት ቅጣት ፍርድ እንደሚገባቸው ባይበይንም በዐጸደ ነፍስ ዘለዓለማዊ የነፍስ ሞት እንደሚጠብቃቸው አረጋግጦ ይናገራል(1ቆሮ.6÷9-12)፡፡ ይህም ቅጣት ከጊዜያዊው የሥጋ ሞት ቅጣት እጅግ ይከፋል፡፡
የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ግን እንደ ብሉይ ኪዳን በሰዶማውያንና ሰዶማውያት ላይ ቀጥተኛ የሞት ፍርድ ይፈርዳል፤ ሆኖም የአድራጊውንና የተደራጊውን ዕድሜያዊ መጠን በማመጣጠን የሁለቱን ፍርድ ለይቶ ያስቀምጣል፡፡ የተደራጊው ዕድሜ ከ12 ዓመት በታች ቢሆን ከሞት ቅጣት እንዲድን ሲወስን አድራጊው ግን ከ12 ዓመት በላይ ከሆነ በሞት እንዲቀጣ በግልጽ ያስረዳል፤ ቀኖናውም የሚከተለው ነው፡-
“እለ ይገብሩ ግብረ ገሞራ፣ ለገባሪኒ ወለዘይገብርዎ ኵነኔሆሙ ሰይፍ፡፡ ሶበሰ ኮነ ዘይገብርዎ ሕፁፀ መዋዕሊሁ እም ዐሠርቱ ወክልኤቱ ሕፀፀ መዋዕሊሁ ያድኅኖ እምኵነኔ፡፡”
ትርጉም፡- “የገሞራውያንን/የሰዶማውያንን/ ሥራ የሚሠሩ ቢኖሩ ለአድራጊውም ለተደራጊውም ቅጣታቸው ሰይፍ/ሞት/ ነው፤ ነገር ግን ተደራጊው ዕድሜው ከ12 ዓመት በታች ቢሆን የዕድሜው አናሳነት ከሞት ቅጣት ያድነዋል፡፡”/እል አብ ጥሊስ፤ የሐዋርያት ትእዛዝ 71/
ከ12 ዓመት በታች የሆነው ተደራጊ ከቅጣት እንዲድን የተበየነበት ምክንያት ድርጊቱን የሚፈጽመው ፈቅዶ ሳይሆን ተገዶ ስለሚሆን ነው፡፡
“አድራጊውና ተደራጊው ሁለቱ በሰይፍ ይቀጡ” የሚለው ትእዛዝ ፍርድ በቀጥታ ከኦሪት ዘሌዋውያን 20÷13 የተወሰደ ነው፤ ዘዳግም ሕግም ይህን ድርጊት የሚፈጽሙ በሀገር ውስጥ መኖር እንደሌለባቸው ከመናገሩ ባሻገር ከውሻ ጋር መድቦ ይገልጣቸዋል(ዘዳግ.23÷17-18)
ከዚህም በላይ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ፍርድ ከመጻሕፍተ ነገሥት ፍርድ ጋር ይተባበራል፤ ንጉሥ አሳና ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ሰዶማውያንንና ሰዶማውያትን አጥፍተዋቸዋልና፡፡ ይህም ከሀገር በማባረር ሳይሆን በሞት ቅጣት የተፈጸመ ማጥፋት እንደሆነ ግልጽ ነው(1ነገሥ. 15÷11-12፤ 1ነገሥ.22÷46)፡፡
ከዚህም ሌላ የቤተ ክርስቲያን ቀኖናዎች እንደ ሐዲስ ኪዳን መንፈሳዊ ቅጣት እንጂ ሥጋዊ ቅጣት/የሞት ቅጣት/ ከመስጠት እንደራሩ ይታያል፤ መንፈሳዊ ቅጣት በመስጠትም ሰዶማውያኑን ከነፍሳዊ ቅጣት ለመታደግ ጥረት አድርገዋል፡፡ ይህም ማለት ሰዶማውያኑና ሰዶማውያቱ በንስሓ ተመልሰው በዚህ ዓለም በቤተ ክርስቲያን ከምእመናን ጋር ሱታፌ እንዲኖራቸው፣ በወዲያኛውም ዓለም መንግሥተ እግዚአብሔር ከሚገባቸው ምእመናን ጋር የመንግሥቱ ወራሾች እንዲሆኑ ማብቃት ነው፡፡
በ314 ዓ.ም በዕንቈራ/ዛሬ አንካራ/ የተደረገው የአብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ በ16ው ቀኖና ሰዶማውያንንና ሰዶማውያትን በተመለከተ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፡-
“ለኵሎሙ እለ የሐውሩ ተባዕተ ይኴንኖሙ እግዚአብሔር እስመ እሉ ኮኑ እኩያነ ወለእመ ነስሑ ወገብኡ እምኔሁ ይጸልዩ ምስለ ንኡሰ ክርስቲያን ለዓለም፡፡” ትርጉም፡- “በግብረ ሰዶም ወደ ወንዶች የሚሄዱትን ሁሉ እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል፤ እነዚህ ክፉዎች ሆነዋል፤ ንስሓ ቢገቡና ከክፉ ሥራቸው ቢመለሱ ግን ለዘለዓለም/መላው የሕይወት ዘመናቸውን/ ከንኡሰ ክርስቲያን ጋር ይጸልዩ፡፡”
ከዚህ በላይ በግልጥ እንደሚስተዋለው የዕንቈራው ጉባኤ ቀኖና ሰዶማውያኑን በሞተ ሥጋ ከመቅጣት ራርቶላቸዋል፡፡ ኾኖም ሰዶማዊ ድርጊት ወይም ግብረ ሰዶም በእግዚአብሔር ሕግና ትእዛዝ ላይ ከፍተኛ ማመፅና፣ ሕገ ተፈጥሮን መለወጥ፣ ሰብኣዊ ክብርን ማዋረድ፣ የወንድና የሴት ማንነትንም መቀየር ስለሆነ በዕድሜ ልክ ንስሓ መንፈሳዊ ቅጣትን ወስኖአል፡፡
ከዚህም ጋር በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 48÷17 - 56፣ “ገሞራውያን ይንበሩ በኵሉ ሕይወቶሙ ምስለ መስተብቋዕያን” ትርጉም፡- “ግብረ ሰዶምን የሚሠሩ መላ ዘመናቸውን ከተነሳሕያን ጋር ይኑሩ” በማለት ከዕንቈራው ጉባኤ ቀኖና ጋር በተመሳሳይ የንስሓ ቅጣት ሰዶማውያኑንና ሰዶማውያቱን ይቀጣል፡፡ የዕድሜ ልክ ንስሓ የበደሉን ክብደት ያመለክታል፤ ምክንያቱም ግብረ ሰዶም የሚፈጸመው በድንገት ሳይሆን በብዙ ጊዜ ልምምድ፤ በአለማወቅ ሳይሆን በማወቅ፤ በስሕተት ሳይሆን በድፍረት፤ በግድ ሳይሆን በፈቃድ እና በመሻት ነውና፡፡
ብዙ ጊዜ የዝሙት ኀጢአት መንሥኤ ምኞት ነው፤ ከዚያም ምኞትን ለመፈጸም መዳራት ይቀጥላል፤ ከመዳራት የተነሣም በገቢር ኀጢአት መውደቅ ይከተላል፡፡
ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ እንዲህ ይላል፡- “…እያንዳንዱ ሰው በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል፤ ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች፡፡”(ያዕ.1÷14) የዕንቈራው ጉባኤ ይህን በመገንዘብ ከገቢር አስቀድሞ የሚፈጸመውን መዳራትን በማውገዝ ስለ ሰዶማውያንና ሰዶማውያት የሚከተለውን ቀኖናዊ ብያኔ ሰጥቶአል፤ ቀኖናውም የሚከተለው ነው፡- “እመቦ ብእሲት ውስብት እንተ ትዜሙ በብእሲ አው ትመርዕ በብአእሲት እንተ ከማሃ፣ አው ብእሲ ውሱብ ዘይዜሙ በብእሲተ ካልእ አው ይፈቱ ተባዕተ ዘይመርዕ ይክል እዎሙ ሱታፌ እስከ ሰብዐቱ ዓመት ምስለ እለ ዪኔስሑ በከመ ነገርነ በቀዳሚ ትእዛዝ ወለእመ ተዐውቀ ንጽሕ ንስሓሆሙ ወኅሊናሆሙ ርቱዕ ይሳተፉ እምድኅሬሁ ቍርባነ፡፡” ትርጉም፡- “ባል ያላት ከሌላ ወንድ ጋር የምትዘሙት ወይም እንደ እርስዋ ካለች ሴት ጋር የምትዳራ ሴት ብትኖር ወይም ሚስት ያለችው በሌላ ወንድ ሚስት የሚዘሙት ወይም የሚዳራ ወንድን የሚፈልግ እስከ ሰባት ዓመት ከምእመናን አንድነት ይከልክሏቸው፤ ከዚያ በኋላ ግን በመጀመሪያው ትእዛዝ እንደተናገርን ከተነሳሕያን ጋር ይጸልዩ፤ የመጸጸታቸውና የቀና ኅሊናቸው ንጽሕና ከታወቀ ግን ከዚያ በኋላ በቍርባን ይሳተፉ ዘንድ ይገባል፡፡”(ቀኖና ዘዕንቈራ 19)
መመኘት ወይም ሴት ከሴት ጋር ወይም ወንድ ከወንድ ጋር መዳራት ከገቢር ያላነሰ የረከሰ ኃጢአት ቢሆንም የዕንቈራ ጉባኤ ቀኖና ከተግባራዊ ግብረ ሰዶም የቅጣት ቀኖና ዝቅ በማድረግ የሰባት ዓመት የንስሓ ጊዜ ሰጥቶአል፡፡
በእርግጥ ይህም ሊሆን የቻለው በትክክል በመጥፎ ድርጊታቸው መጸጸታቸው ሲረጋገጥ መሆኑን ቀኖናው ያስረዳል፡፡ ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያም “በወንዶች ልጆች ፍቅር የሚቃጠሉ፣ በርኵሰት የሚወድቁና አሳፋሪ ዝሙትን የሚፈጽሙ ከቅጣት አያመልጡም፤ እግዚአብሔር ዐይኑን ይጥልባቸዋልና፡፡” ትርጉም፡- “በወንዶች ልጆች ፍቅር የሚቃጠሉ፣ በርኵሰት የሚወድቁና አሳፋሪ ዝሙትን የሚፈጽሙ ከቅጣት አያመልጡም፤ እግዚአብሔር ዐይኑን ይጥልባቸዋልና፡፡” በማለት ሰዶማውያንና ሰዶማውያት እግዚአብሔር እንደሚቀጣቸው ተናግሮአል፡፡
ፍርዱ ሥጋዊና ነፍሳዊ ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ዛሬ ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙትን እንደ ቀደሙት የሰዶምና የገሞራ ሰዎች በሥጋቸው ይቀጣቸዋል፡፡ ይኸውም በአካላቸው ላይ በሽታ ይከሥትባቸዋል፤ በነፍሳቸውም እንደሚቀጡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በ1ቆሮ.6÷9-12 ላይ ያረጋግጣል፡፡
ከዚህም ጋር ሰዶማውያንና ሰዶማውያት በሚፈጽሙት አስጸያፊና አስነዋሪ ግብረ ሰዶም በኅብረተሰቡ ዘንድ የተጠሉ፣ የተወገዙና የተለዩ ይሆናሉ፡፡ ይህም የሞራል ውድቀትንና ኀፍረትን ስለሚያስከትልባቸው ሌላው ተጨማሪ ቅጣት ነው፡፡
ይሁን እንጂ ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንደተገለጠው በንስሓ ቢመለሱ ከሥጋዊና መንፈሳዊ ከሞራላዊ ቅጣት ይድናሉ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም በሥርዐታቸው “ሰዶማዊውን በቤተ ክርስቲያን አይቀበሉት፤ ከባድ ኀጢአት ነውና፤ ነገር ግን ተግባሩን ቢተውና ቢመለስ ይቀበሉት፤ ሰዶማዊ ተግባሩን ለመተው ባይፈቅድ ግን የተለየ ይሁን፡፡”(የቅዱሳን ሐዋርያት ሥርዐት/ሕግ/ መጽሐፍ 8÷32)
ሰዶማዊነት በጣም አስጸያፊና አስነዋሪ፣ ወራዳና ርካሽ ተግባር ነው፤ ጤናማ አእምሮና አስተዋይ ኅሊና ያለው ወንድ የወንድነት ጠባዩን ቀይሮ የሴትነት ጠባይን ለራሱ መውሰዱ ወደ ወንድ የሚሄደውም ወደ ሴት በመሄድ ፈንታ ወደ ወንድ መሄዱ ምን ያህል ወራዳነት እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡ እንዲህ የሚያደርጉ ሁሉ አእምሮ የጎደላቸው በሽተኞች መሆናቸው አያጠራጥርም፤ በሽታውም አእምሮታዊና አካላዊ ነው፤ አእምሮታዊው እብደት ሲሆን አካላዊው በሽታ ደግሞ ኤድስ፣ የፊንጢጣና የአንጀት መቁሰል እንደሆነ የሕክምና ባለሞያዎች ያረጋገጡት ጉዳይ ነው፡፡
ስለዚህ ሰዶማውያንና ሰዶማውያት ሁሉ ከዚህ አስነዋሪና አስጸያፊ ተግባር በንስሓ እንዲመለሱና ከአእምሯዊ እና አካላዊ በሽታ እንዲፈወሱ፣ ከርኵሰታቸው እንዲቀደሱ ቤተ ክርስቲያን ትመክራለች፤ የማይመለሱትንና እንቢተኞችን ግን በጽኑዕ ታወግዛለች፤ ከአንድነትዋም ትለያለች፡፡

ግብረ ሰዶም በዓለም አብያተ ክርስቲያን ማኅበር ውስጥ አስከትሎት የነበረው ችግር
. . . ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ኾኖ ኀጢአተኛውን ዓለም ለማዳን ወደዚህ የሰዎች ዓለም ሲመጣ የሰውን ልጅ የማዳን ሥራውን የጀመረው ትምህርተ ወንጌልን በማስቀደም ነው፡፡ በዚህም ቃለ ወንጌል የሰው ልጅ ማድረግና አለማድረግ፣ መሆንና አለመሆን ያለበትን ግዴታ ለሰው ልጅ ግልጽ ስላደረገ በተለይ የክርስትናው ዓለም በስሕተት ከሚሠራው ኀጢአት ይልቅ የሚበዛው ዐውቆ በድፍረት የሚሠራው ኀጢአት ነው፡፡
እንደሚታወቀው እስከ አሁን ድረስ የክርስትናው ዓለም ክብር የቀነሰው የእምነት ትምህርት ልዩነት ነው፡፡ አሁን ደግሞ “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ ከአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በተከሠተው የእምነት ትምህርት ልዩነት ምክንያት እርስ በርሱ ሲወዛገብ የኖረው የክርስትናው ዓለም አሁን ደግሞ በሥነ ምግባር ትምህርት ልዩነት ምክንያት እጅግ ወደ ከፋ ውዝግብ ውስጥ እየገባ ነው፡፡ ለዚህም ልዩነትና ውዝግብ ምክንያት የሆነው የግብረ ሰዶም ድጋፍና ተቃውሞ ነው፡፡
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በክርስትናው ዓለም የእምነት ትምህርት ልዩነት ቢኖርም የግብረ ሰዶም አስከፊ ተግባርነትን በማስተማር በኩል የነበረው አንድነት እንከን ያለው አልነበረም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በምዕራቡ ክፍለ ዓለም “ግብረ ሰዶምን መፈጸም ኃጢአት አይደለም” የሚል አቋም መያዝ ለወንድና ለወንድ፣ ለሴትና ለሴት ጋብቻ ሕጋዊ ዕውቅና ሲሰጥ፣ የክፍለ ዓለሙ አብዛኛው ሕዝበ ክርስቲያን ደግሞ በአብያተ ክርስቲያናት ደረጃ ሳይቀር ውሳኔ በማሳለፍ ለዚህ ዕውቅናና ድጋፍ በመስጠቱ በዘመኑ የክርስትናው ዓለም ላይ እንኳን ክርስቲያን፣ ሰው ነኝ ለማለት የማያስደፍር የእምነትና የምግባር ኪሳራ እያደረሰ ነው፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ይህም በምዕራቡ ክፍለ ዓለም አብያተ ክርስቲያን ጭምር ሲነገር የኖረ ምስክርነት ቃል ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የእግዚአብሔር ቃል እንደ መሆኑ መጠን ከእግዚአብሔር ቃል አንዷ ከምትወድቅ ሰማይና ምድር ቢያልፍ እንደሚቀል የተናገረውን ቃለ ወንጌል የምዕራቡ ክፍለ ዓለም ሕዝበ ክርስቲያን ያውቃል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ፓርላማ ሕግ በድምፅ ብልጫ ለመሻርም ሆነ ለማሻሻል ፈጽሞ እንደማይቻል የክርስትናው ዓለም ያውቃል፡፡ እንዲህ ከሆነ የምዕራቡ ክፍለ ዓለም ሕዝበ ክርስቲያን ምን ሥልጣን ኑሮት ነው የእግዚአብሔርን ቃል በማሻሻል ለግብረ ሰዶም እና ለተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ሕጋዊ ዕውቅና የሰጠው፤ የክርስትና እምነትን ሕግ የሻረ ሕዝብስ በክርስትና ስም መጠራት ይችላል ወይ? ለዚህ ጥያቄ ምንም ዐይነት አዎንታዊ አሳማኝ መልስ አይኖርም፡፡
ይህ በመሆኑም በዚህ ጽሑፍ መግቢያ ላይ እንደተገለጠው የክርስትናው ዓለም እንደገና በሌላ ከፋፋይ ትምህርት አንድነቱ ከአደጋ ላይ እየወደቀ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ መላው የክርስትናው ዓለም የግብረ ሰዶምን ኀጢአትነት ዐውቆ ፀረ ግብረ ሰዶም ትምህርት በመስጠት በኩል የነበረው አንድነት ጽኑዕ ነበር፡፡ ለዚህም ትምህርታዊ አንድነት መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ነበር፡፡ ለምሳሌ ሮሜ ምዕ. አንድ፡፡ አሁን ግን ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ እምነት ተከታይ ሕዝብ መካከል የተወሰነው ግብረ ሰዶም ፈጻሚ፣ የተወሰነው ደግሞ የዚህ ግብረ ኃጢአት ደጋፊ ሲሆን ሌላው ግን የዚህ ግብረ ኃጢአት ፍጹም ተቃዋሚ ስለሆነ በዚህ ድጋፍና ተቃውሞ ምክንያት የክርስትናው ዓለም ለሁለት ከተከፈለ ውሎ አድሯል፡፡ ይህ ልዩነት ሊወገድ የሚችለውም ሁሉም የእግዚአብሔርን ቃል በመከተል ግብረ ሰዶምን ማውገዝ ሲችል ነው፡፡
በአብዛኛው ግብረ ሰዶምን ከመደገፍ አልፎ ተርፎ በአብያተ ክርስቲያናት ደረጃ ሳይቀር ለድርጊቱ ሕጋዊ ዕውቅና የሰጠው በምዕራቡ ክፍለ ዓለም የሚገኘው በርካታ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሕዝብ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህን ድርጊት በዓለም አቀፍ ደረጃ በመቃወም ለእግዚአብሔር ቃል ያላቸውን ታማኝነት በሐዋርያው ትምህርት በመግለጽ ላይ የሚገኙት የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትና ሌሎችም ናቸው፡፡
የምዕራቡ ክፍለ ዓለም በርካታ አብያተ ክርስቲያን ለግብረ ሰዶም ፈጻሚዎች ሕጋዊ ዕውቅና ከመስጠት አልፈው ተርፈው ለእነዚህ ወገኖች “የግብረ ሰዶም ፈጻሚዎች ሕዳጣን ክርስቲያን ኅብረተሰብ”(Christian Homosexual Minority) የሚል ስያሜ በመስጠት የዓለም አብያተ ክርስቲያን ማኅበር አባል እንዲሆኑ ጠይቀው ነበር፤ ጥያቄው የቀረበውም እ.አ.አ በ1998 ዝምባቡዌ ላይ በተካሄደው የዓለም አብያተ ክርስቲያን ማኅበር ስምንተኛ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ነበር፡፡ ሆኖም የማኅበሩ አባላት የሆኑት የኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያን ተወካዮች ባቀረቡት ጠንካራ ተቃውሞ ጥያቄው ውድቅ ሆኗል፡፡
“ክርስቲያን” ተብለው መጠራት የማይገባቸው እኒህ ግብረ ሰዶም ፈጻሚዎች ወደፊትም የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማኅበር አባል ለመሆን የሚፈቀድላቸው ከሆነ ከማኅበሩ አባልነት እንደሚወጡ መላው የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በጉባኤው ላይ አስጠንቅቀዋል፡፡ ግብረ ሰዶማውያኑ የማኅበሩ አባል እንዲሆኑ ቢፈቀድ ኖሮ ማኅበሩ የዓለም አብያተ ክርስቲያን ማኅበር በሚለው ስያሜ መጠራት የሚገባው ባልሆነ ነበር፡፡ ይህ ስም እንዲቀጥል ያደረጉት የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን ናቸው፡፡ በዚህም የእነርሱ መኖር ለዓለም አብያተ ክርስቲያን ማኅበር እጅግ ጠቃሚ መኾኑን አረጋግጠዋል፡፡
ግብረ ሰዶማውያንን የሚቃወሙት ኦርቶዶክሳውያን ብቻ አይደሉም፡፡ ቫቲካንም የዚህ ግብረ ኃጢአት ተቃዋሚ እንደሆነች ልዩ ልዩ ሰነዶች ያረጋግጣሉ፡፡ ቫቲካን ለግብረ ሰዶም ፈጻሚዎች መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳይፈጸም ለካህናቷ ዓለም አቀፋዊ መመሪያ እንደሰጠች የዓለም አብያተ ክርስቲያን ማኅበር መጽሔት(ኦገስት፣ ቍ.19፣ 1999) ያረጋግጣል፡፡ የምዕራቡ ክፍለ ዓለም አብያተ ክርስቲያን ተከታዮችም ቢሆኑ ሁሉም ግብረ ሰዶምን ይደግፋሉ ማለት አይደለም፡፡ እነዚህ የግብረ ሰዶም ተቃዋሚ ክርስቲያኖች እያሉ እንደሌሉ የተቈጠሩት ህልውናቸው በድምፅ ብልጫ ስለተዋጠ ነው፡፡ አብያተ ክርስቲያናቱ ውሳኔውን የሚያሳልፉት በድምፅ ብልጫ ስለሆነ ተቃውሟቸው በድምፅ ብልጫ ውድቅ ቢሆንም እነርሱ ውሳኔውን ይቀበሉታል ማለት አይደለም፡፡ አሁንም ግብረ ሰዶምን የሚቃወሙ ምዕራባውያን ክርስቲያኖች ቁጥር ብዙ ነው፡፡

/ ሚሼል ሲዲቤ ለግብረ ሰዶማውያን ማኅበራዊ ተቀባይነት ድጋፍ የጠየቁበትን ዐረፍተ ነገር ተናግረው ሳይጨርሱ ከአዳራሹ የይበልታም የአሉታም ቃና ያላቸው ሆታዎች /buzzes and hisses/ ተደምጠዋል፡፡ ከአዳራሹ ውጭ በጥቂት ወጣት ሰልፈኞች አንደበት የተስተጋቡት የብዙኀን ኀይለ ቃሎች ይዘት ግን አንድና አንድ ነው - ! አገራችንን ከመጥፎ ባህል እንጠብቅ!”ግብረ ሰዶም ኀጢአት ነውአንቀጽ 629 ይከበርቅድስት አገራችን በግብረ ሰዶማውያን አትደፍርምግብረ ሰዶም ወራዳ ምግባር ነውግብረ ሰዶም አሳፋሪ ነው፤ እንቃወመለንግብረ ሰዶም የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው”!!


15 comments:

Anonymous said...

+++
Why Our Holy Church is still a member of the so called "World Churches council"?. Please, our fathers santify yourself, stand against the evil! Tell the truth and separate! We cannot be children of God if we stand with the enemies of His Commandments!!!

Kinfe-Michael said...

The end for this world is approaching faster than ever. Can't you people see it? Everything we see and hear proves that the scripture is unfolding right before our very eyes. This is not a fight of the flesh and the blood. This is the end of times and Satan is paving the way for the coming of the False Messiah. Please read the bible and what is going on around the world. Try to learn how the current political and economic turmoils around the whole world are just the beginning of the welcoming feast for the beast. Atheist Meles and actor 'Abune' Paulos are hurrying to bring these changes to our country. They are just loyal employees for the Devil as are their western bosses. Dear Ethiopians: the changes are inevitable. They are written and will come. "He who has ears, let him hear." The first thing is to hold on to our faith. We, ourselves, need to stand firm. This is a time when anyone who thinks is standing should be careful not to fall. After that, we need to help our family, friends, neighbors and other people to keep their true faith, Orthodox Tewahido. We are so lucky that we were born in Ethiopia, a land of our great fathers who fought hard during their times to hand over the only true faith to us. Let's not waste this gift. This gift from our fathers is our only shield during times of challenges like the one we are facing now and for much more to come in the future. "Tezekerene Egzio Bewste Mengistke."

Anonymous said...

even though i one of the supporter of Mahiber Kidusan what are they doing on this issue this is more that Tehadiso we have to fight this and they have to make some kind arrangement to request Government to give Permission for demonstration. the history will judge us if we don't speak on this and we try to on miner think please don't be silent on this because everyone looking on you guys. because we thinking that Mahiber kidusan are a public figures be part of it and let as fight this together those who have bad thought on Mahiber kidusan will know that you guys are doing aways right please please please this is not something we have to give a time about. history will judge you if are not speaking on this matter and God will determine if we are true christians DEJE SELAME PLEASE POST THIS COMMENT IF NOT PLEASE SHARE MY IDEA TO THE PEOPLE concern to thank you MY GOD BLESS MY religion, my county and my people!!!

Yigemal ! said...

Is Abune Paulos president of world council of churches which has member Churches that accept and support THIS CURSE??? If so, this man does not deserve any respect!
The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church has taken part in ICASA conference which also had agenda as to how to protect the rights of homosexuals? Those of you, who support aba paulos and mention his name, are also equallly judged by God. WHERE IS THE CONDEMNATION OF OUR CHURCH IN THE STRONGEST POSSIBLE TERMS AGAINST THIS EVIL DEED AND THIS EVIL 'GOVERNMENT' ? OH! MY GOD!!!

Anonymous said...

This is the time that our country and religion are under serious temptation. Please, please, please look at/listen to the first News of this link and start to pray strong at this Holy fasting season
http://www.ethsat.com/2011/12/12/esat-tv-news-dec-12-2011-video/
Igziabher Kematu Yisewren. Ines Ferahu

Anonymous said...

Thank you Dejeselam yesew neger - yesew hatsiat - yesew newr - yesew bedel - yesew gebena kemezerzer lehager-lewgen -lesew-yemitsekim neger mejemersh asdestogal Dejeselam Metarekiya -Memegebiya-Mewyaya-Mesebisebia-marefiya neberch Addistu Dejeselam zeke yellebat sew yemisedebbat-yemwaredbat -sim yemtsefabat hona nebere hulum bedelaga -behonebet alem sewn masadedi titen mastemar -mastarek makerareb- mesebseb yibejal ye Dejeselam azegajoc ke D Daneil Kibret temaru bertu tsenkiru kifun bekifu atashenfu dihina hunu

Anonymous said...

Thank you Dejeselam yesew neger - yesew hatsiat - yesew newr - yesew bedel - yesew gebena kemezerzer lehager-lewgen -lesew-yemitsekim neger mejemersh asdestogal Dejeselam Metarekiya -Memegebiya-Mewyaya-Mesebisebia-marefiya neberch Addistu Dejeselam zeke yellebat sew yemisedebbat-yemwaredbat -sim yemtsefabat hona nebere hulum bedelaga -behonebet alem sewn masadedi titen mastemar -mastarek makerareb- mesebseb yibejal ye Dejeselam azegajoc ke D Daneil Kibret temaru bertu tsenkiru kifun bekifu atashenfu dihina hunu

Abebaw said...

Dear Dejeselamawyan,
You have done the right and the best job Many thanks to your efoort.
Gibre sedom is not a human right. The natural and the ligal right is sex between opposite sexes. SEDOMAWINET YEQNTOT HATIAT NEW.
Please consentrate on such important isues to help us and our Church.
Be objective and imprcial in your writtings and we all will benefit.Stop the polemics between you.
Many of us are indebted to this document. Thank you again.

Abebaw said...

Dear Dejeselamawyan,
You have done the right and the best job Many thanks to your efoort.
Gibre sedom is not a human right. The natural and the ligal right is sex between opposite sexes. SEDOMAWINET yEQNTOT HATIAT NEW.
Please consentrate on such important isues to help us and our Church.
Be objective and imprcial in your writtings and we all will benefit.Stop the polemics between you.
Many of us are indebted to this document. Thank you again.

Anonymous said...

እናታችን መመኪያችን ታቦተ ጽዮን አደጋ ላይ ናት ደግሞ ብለው ብለው በእርሷ መጡ ?????ጆሮን ጭው የሚያደርግ አሳዛኝ ዜና
የሚከተለውን ሊንክ ልብ ብለው ያድምጡ
http://www.ethsat.com/2011/12/12/esat-tv-news-dec-12-2011-video/

Anonymous said...

እናታችን መመኪያችን ታቦተ ጽዮን አደጋ ላይ ናት ደግሞ ብለው ብለው በእርሷ መጡ ?????ጆሮን ጭው የሚያደርግ አሳዛኝ ዜና
የሚከተለውን ሊንክ ልብ ብለው ያድምጡ
http://www.ethsat.com/2011/12/12/esat-tv-news-dec-12-2011-video/

Anonymous said...

እናታችን መመኪያችን ታቦተ ጽዮን አደጋ ላይ ናት ደግሞ ብለው ብለው በእርሷ መጡ ?????ጆሮን ጭው የሚያደርግ አሳዛኝ ዜና
የሚከተለውን ሊንክ ልብ ብለው ያድምጡ
http://www.ethsat.com/2011/12/12/esat-tv-news-dec-12-2011-video/

Anonymous said...

Thanks so much Deje Selam for sharing all our country's and church's issues for us who are living outside. Its good to know what is going on to do our parts.
Plase God be with us in this pessimistic time

Anonymous said...

No one of us are brave enough to say no to any thing which comes agains our country, our poeple, our church and even ourselves. Look to Mehaberekidusan they choose to keepquiet when this gay meeting was held in ADDis because if they say any thing the goverment will round all of them. But look our fathers didn't keep the country, the church and our relegion simply by fear and passiveness when danger is coming. As you all know they dead when the need comes let alone being in jail for some time.
Ferie besewmi beigzabiherimi feti yetenake newi.
So we all are fearful useless generation( yeingidielijochi neni)

Unknown said...

Last annonym, here are two articles Mahibere Kidusan posted. What are you talking about?
1. "የሎጥ ዘመን በዚች ቅድስት ሀገርና ሕዝብ ላይ አይደገምም!!" (Mahibere Kidusan, http://www.eotcmk.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=809:2011-12-10-14-27-12&catid=22:-&Itemid=26

2. "ውግዘት የሚገባው ተግባር"
http://www.eotcmk.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=1:2011-12-02-08-19-57&catid=2:-&Itemid=2

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)