December 28, 2011

የድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መዝባሪዎች እጃቸውን ከደብሩ እና ከሀገረ ስብከቱ ላይ እንዲያነሡ ተጠየቀ


 • የደብሩ አስተዳዳሪ የአጥቢያውን ልማት የመምራት አቅም የላቸውም::
 • ፖሊስ ሁለት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችንና አንድ ምእመን ይዞ አስሯል::
 • ተዋንያኑ ፋንቱ ማንዶዬ እና ችሮታው ከልካይ በቁሉቢ ለአኵስም ጽዮን ሙዚዬም ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ያካሂዳሉ::
 (ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 18/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 28/2011. READ IN PDF)፦ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የሚገኙ የስምንት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች እናምእመናን በሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ የተፈጸመው ሙስና ተጣርቶ በሙሰኞቹ ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ፣የደብሩን አስተዳደር በመምራት ረገድ የከፋ የአቅም ማነስታይቶባቸዋል፤በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው የተተለሙ የልማት ዕቅዶች ተፈጻሚ እንዳይሆኑ ዕንቅፋት ፈጥረዋልየተባሉት የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ኀይል ቆሞስ አባ ገብረ እግዚአብሔር ቸኮል ከሓላፊነታቸው እንዲወገዱ በተቃውሞ ትዕይንት ጠየቁ፡፡

December 27, 2011

የእነ መ/ር ዘመድኩን የፍርድ ቤት ውሎ


 • READ IN PDF.
 • “የስብከተ ወንጌል ሓላፊ ነኝ” ያሉት የበጋሻው ምስክር ስለ ሕገ ወጥ ሰባክያን የወጣውን መመሪያ “አላውቀውም፤ አልደረሰኝም” አሉ፤
 • በጋሻው በ”አርማጌዶን” ቪሲዲ “አሮጊቷ ሣራ” በሚለው ንግግር “በኑፋቄያቸው ተወግዘው ከወጡት ጋራ መነጻጸሬ አግባብ አይደለም” ቢልም ምስክሩ ታሪኩ አበራ ደግሞ “አነጋገሩ ቤተ ክርስቲያንን የማክበር እንጂ የማዋረድ አይደለም” ሲል መስክሯል፤
 • “አጉራ ዘለል ሰባክያን” ማለት “ፈቃድ የሌላቸውና ሳይማሩ የሚያስተምሩ ግለሰቦች” ማለት እንደ ሆነ ያስረዳው ታሪኩ አጉራ ዘለልነት በጋሻውን እንደማይመለከትና “መጋቤ ሐዲስ መባሉም ትክክለኛ ነው” ብሏል፤
 • ዲ/ን ደስታ ጌታሁን ያቀረቧቸው የመከላከያ ምስክሮች ተከሳሹ ያሳተሙት “የሰባኪው ሕጸጽ” መጽሐፍ “ሳይማሩ ተምረናል ሳይላኩ ተልከናል በማለት ያለፈቃድ እንሰብካለን እናስተምራለን የሚሉ ሕገ ወጥ ግለሰቦችን መቆጣጠር” በሚለው የቃለ ዐዋዲው መመሪያ መሠረት መጻፉን መስክረዋል፤
 •  “ባልማርም በአደባባይ የሐዲስ ኪዳን መጋቢ ተብዬአለሁ”/በጋሻው ደሳለኝ/፤

December 22, 2011

የጽላተ ጽዮን ነገር - የደጀ ሰላም ሪፖርታዥ


አቡነ ጳውሎስ ከጽላተ ጽዮን ማደሪያ እድሳት ይልቅ ለሙዚዬሙ ግንባታ ትኩረት ሰጥተዋል
 (ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 12/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 22/2011. READ IN PDF)
 •  የርእሰ ገዳማት ወአድባራት አኵስም ጽዮን ማርያም ሰበካ ጉባኤ 1.8 ሚሊዮን  ብር ወጪ የጽላተ ጽዮን ማደሪያ እድሳት ያካሂዳል፤ በሰበካ ጉባኤው ሥር የሚካሄደው እድሳት አቡነ ጳውሎስ “በተለየ ጥረትና አመራር ሰጭነት” ከሚቆጣጠሩት ሙዚዬም ግንባታ ፕሮጀክት ጋራ የሚያገናኘው ነገር የለም
 • የጽላተ ጽዮንን ማደሪያ በገንዘባቸው በማደስ ስማቸውን ለማስጠራት የመጡ ባለሀብቶች ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም፤ ይልቁንስ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠባቂ እና መድኃኒት ለሆነችው ጽሌ-ኦሪት-ጽዮን ማደሪያ እድሳት እያንዳንዱ ምእመን የአቅሙን እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ ተደርጓል
 •  ለተቸገሩ አብያተ ክርስቲያን የሚሰበሰበውን ርዳታ ጨምሮ የመንበረ ፓትርያርኩ የገንዘብ ምንጮች/አቅሞች በሕዳሴው ግድብ አምሳል ቅስቅሳ ወደሚደረግለት የሙዚዬም ግንባታ ፕሮጀክት እንዲዘዋወሩ ጫና በመደረጉ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ሠራተኞች ኑሮ እያቃወሰው ነው፤ በአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳደርና በካህናቱ መካከልም ፍጥጫ ፈጥሯል

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዕንባ ተሸኙ


(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 11/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 21/2011/ READ IN PDF)፦ ቀደም ብሎ ለኒውዮርክ ቀጥሎም ለዋሺንግተን እና አካባቢው ሀ/ስብከት በሊቀ ጳጳስነት ተመድበው ሲያገለግሉ ቆዩትና በጥቅምቱ የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ወደ መዕራብ ሐረርጌ እና ጅጅጋ አህጉረ ስብከት የተዘዋወሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዕንባ ተሸኙ።
 ባለፈው ቅዳሜ ታኅሣሥ 7/2004 ዓ.ም (12/17/2011) በቨርጂኒያ ግዛት በተደረገላቸው የመሸኛ ዝግጅት ላይ ስንብት የተደረገላቸው ብፁዕነታቸው በምድረ አሜሪካ ቆይታቸው ስለነበረው ሁኔታ ማብራሪያ ከመስጠታቸውም በተጨማሪ በእርሳቸው መሔድ የተጀመረው አገልግሎት እንዳይቀዛቀዝ አባታዊ አደራ ሰጥተዋል።

December 17, 2011

በስልጢ ወረዳ የቆቶ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን መቃኞ ጉልላት እና ጣሪያ በወረዳው ፖሊስ ተነቅሎ ከተወሰደ በኋላ የግድግዳው ዕንጨት በሙስሊም ተማሪዎች ተቃጥሎ ተቀበረREAD IN PDF.
  • 200 የወረዳው ምእመናን ተወካዮች ወደ ሐዋሳ በማምራት ለክልሉ ርእሰ መስተዳድር ረዳት ጽ/ቤት አቤቱታቸውን አቅርበዋል፤ በሁኔታው ያነቡት የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በስፍራው በመገኘት ምእመናንን አጽናንተዋል፤ በጉዳዩ ላይም ከወረዳ አስተዳደር እና ፖሊስ እንዲሁም ከክልሉ የፍትሕ እና ጸጥታ ዘርፍ ሓላፊዎች ጋራ እየመከሩበት ነው
  • መቃኞው የተሠራበት ቦታ የቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥምቀት ይዞታ ስለ መሆኑ የደቡብ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መስተዳድር ጽ/ቤት፣ በክልሉ ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ የተፈጥሮ ሀብትና የገጠር መሬት አስተዳደር ዘርፍ፣ የስልጢ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት እና የወረዳው ፍ/ቤት እንዲሁም የቆቶ ባሎሶ ቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት በየደረጃው በሰጧቸው ውሳኔዎች አረጋግጠው ነበር
  • በውድቅት ሌሊት የተወሰደው የወረዳው ፖሊስ አፍራሽ ግብረ ኀይል ሕገ ወጥ ርምጃ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር በፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ይግባኝ በጠየቀበትና የአፈጻጸም መመሪያ ባልተሰጠበት የተፈጸመ ሲሆን፣ ዛሬ ጠዋት ግድግዳውን በማፈራረስ ያቃጠሉት ሙስሊም ተማሪዎች ደግሞ በወረዳው ክርስቲያኖች ላይ ጅሃድ ባወጀው ጀማል ሽኩሪ በተባለ ጽንፈኛ የተቀሰቀሱ ናቸው

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አወዛጋቢ ስብሰባ ጠርተዋል፤ ለአቡነ አብርሃም ሽኝት ተዘጋጅቷል

(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 6/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 16/2011. READ IN PDF)፦ ባለፈው ጥቅምት በተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ለዲሰና አካባቢው እንዲሁም ለካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት በሊቀ ጳጳስነት የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በዲሲ ሀ/ስብከት ስም የጠሩት ስብሰባ ነገ ቅዳሜ በዋሺንግተን ዲሲው የቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

December 16, 2011

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚካሄዱ ግንባታዎች ከፍተኛ የሙስና ምንጭ እየሆኑ ነውአርእስተ ነጥቦችዶኩመንቶች
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 6/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 16/2011. READ IN PDF.)፦

 • ለድሬዳዋ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ ከጅምሩ አንሥቶ በሀገር ውስጥና በውጭ ከሚገኙ ምእመናን ከተሰበሰበው ብር 11.3 ሚሊዮን ውስጥ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ጉድለት መገኘቱን በምእመናን ምርጫ የተዋቀረው “የባለሞያዎች ተሟጋች ቡድን” እና የሰበካ ጉባኤው አባላት እየተናገሩ ነው

December 14, 2011

በጋሻው በመ/ር ዘመድኩን ላይ የመሠረተው ክስ የፀረ-ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶውን ጥምረት እያጠናከረው ነው


 • “የአዲስ አበባ ጥምቀት ተመላሽ ወጣቶች ኅብረት”፣ ኦርቶዶክሳውያን ፖሊሶች እና የችሎት ተከታታዮች ለመ/ር ዘመድኩን ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል::
 • በድብደባ ሙከራ ወንጀል ክስ እንዲመሠረትበት የተወሰነበት መናፍቁ አሰግድ ሣህሉ መ/ር ዘመድኩን ከሕገ ወጡ ቡድን ጋራ ዕርቅ እንዲያወርድ ተማፀነ::
 • በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጥያቄ የተቋረጠው የክስ መዝገብ እንዲቀጥል ተደርጓል::
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 4/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 14/2011/ READ IN PDF)፦ በጋሻው ደሳለኝ በመ/ር ዘመድኩን በቀለ እና ዲያቆን ደስታ ጌታሁን ላይ በስም ማጥፋት ወንጀል መሥርቶት የነበረውና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ጥያቄ ተቋርጦ የነበረው የክስ መዝገብ ዳግመኛ ተከፍቶ እንዲንቀሳቀስ በፍትሕ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ መመሪያ ከተሰጠ በኋላ ሁለቱ ተከሳሾች ዛሬ፣ ታኅሣሥ አት ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡

በአርማጌዶን ቪሲዲ በጋሻው መ/ር ዘመድኩንን ከሰሰ


 • በጋሻው በጠ/ቤ/ክህነቱ ጥያቄ የተዘጋውን መዝገብ ለማንቀሳቀስ እየጣረ ነው::
 • “የተሻረው ደብዳቤ” - ወንጀለኛነት መያዣ የሆነበት የበጋሻው ድራማ::
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 4/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 14/2011/ READ IN PDF)፦:- መ/ር ዘመድኩን በቀለ አርማጌዶን ቁጥር አንድ ቪሲዲ ጋራ በተያያዘ በፌዴራል ዐቃቤ ሕግ የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ ቀረበበት፡፡ ዐቃቤ ሕግ ጉዳዩ በልዩ ሁኔታ ታይቶ መ/ር ዘመድኩን የዋስትና መብት ተነፍጎት ክሱን በማረፊያ ቤት ሆኖ እንዲከታተል ጠይቆ ነበር፡፡ የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው፣ በቪሲዲው ውስጥ የተዘረዘሩት ነገሮች በይዘታቸው ሃይማኖታዊ በመሆናቸውና ቪሲዲው ከፍ ላለ ሃይማኖታዊ ፋይዳ የተሠራ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን የማየት ሥልጣን እንደሌለውና በስም ማጥፋት ወንጀል ሊያስከስስ እንደማይችል በማስረዳት በክሱ ላይ መቃወሚያ አቅርበዋል፤ ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን መከራከሪያ መርምሮ ውሳኔ ለመስጠትና ክሱ የሚቀጥል ከሆነ የምስክሮችን ቃል ለማዳመጥ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

December 13, 2011

16ኛው የ(ICASA) ጉባኤ ሪፖርታዥ


 • READ IN PDF.   
 • የተ.መ.ድ ኤድስ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ሰዶማውያን ማኅበራዊ ድጋፍ የሚያገኙበትን አጀንዳ ለማበረታታትና ለማስፋፋት የአቶ መለስ ዜናዊን የመሪነት እገዛ ጠይቀዋል፤
 • የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና “ገሞራውያን” የሚላቸው ሰዶማውያን እና ሰዶማውያት ከቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲለዩ፣ የመጸጸታቸው እና የቀና ኅሊናቸው ንጽሕና እስኪታወቅ ድረስም ንስሓቸው የዕድሜ ልክ እንደሚሆን ደንግጓል - “ገሞራውያን ይንበሩ በኵሉ ሕይወቶሙ ምስለ መስተብቋዕያን” /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 48÷17-56/፤
 •  በ16ው የ(ICASA) ጉባኤ የምሥራቅ አፍሪቃ መንግሥታት በብሔራዊ የጤና ፖሊሲ ክለሳዎቻቸው፣ በጤና ሁኔታዎች አመልካቾቻቸው፣ በጤና መርሐ ግብር ዝግጅቶቻቸውና ሳይንሳዊ ምርምሮቻቸው የግብረ ሰዶማውያንን ተሳትፎ እንዲያረጋግጡ የሚጠይቅ የቅስቀሳ ውይይት(Oral Poster Discussion) ተካሂዷል፤

December 4, 2011

የግብረ ሰዶማውያኑን ስብሰባ የተቃወሙ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ታስረው ተለቀቁ

 • ወጣቶቹ ከካዛንቺስ እና አካባቢው የተሰባሰቡ ናቸው ተብሏል
 • ተቃዋሚዎቹ በመፈክር መልክ ከያዟቸው ኀይለ ቃሎች መካከል “ግብረ ሰዶም ኀጢአት ነው!”፤ “ግብረ ሰዶም የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው!”፤ “ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በግብረ ሰዶማውያን አትረክስም!”፤ “[የወንጀል ሕጉ] አንቀጽ 629 ይከበር!” የሚሉ ይገኙበታል
 • ግብረ ሰዶማዊነት ለረጅም ጊዜ ከአእምሮ በሽታ ዝርዝር ተደምሮ የቆየ ነው
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 23/2004 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 3/2011):- የዓለም ኤድስ ቀንን ምክንያት በማድረግ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና አባላዘር በሽታዎች ላይ አተኩሮ ከሚካሄደውና ኢትዮጵያ ከነገ ኅዳር 24 - 28 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ ከምታስታናግደው 16ው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ቀደም ብሎ ዛሬ ኅዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም የተካሄደውን የግብረ ሰዶማውያኑን ስብሰባ የተቃወሙ ወጣቶች ለአንድ ሰዓት ያህል ታስረው መለቀቃቸው ተሰማ፡፡

December 3, 2011

የግብረ ሰዶማውያኑ ስብሰባ በተ.መ.ድ የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ ነው

READ IN PDF.
 • ከ40 - 45 የሚደርሱ ግብረ ሰዶማውያን ከደቡብ አፍሪካ የመጡ ናቸው፤ ያረፉበት ቦታ በምሥጢር ተይዟል::
 • የጁፒተር ዓለም አቀፍ ሆቴሎች አስተዳደር የግብረ ሰዶማውያኑ ስብሰባ በሆቴሉ እንደሚካሄድ የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን ደንበኞቹ እና አጠቃላይ ሕዝቡ እንዲገነዘቡለት አስታውቋል::
 • የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሠራተኞች በኢትዮጵያ ሕግ ወንጀል በሆነው ግብረ ሰዶማዊነት ላይ ለሚሰበሰቡ ግለሰቦች ፈቃድ መሰጠቱ ግራ እንዳጋባቸው ገልጸዋል፤ ሚኒስቴር መሥ/ቤቱ ምን እየሠራ እንደ ሆነ በቁጣ ላቀረቡት ጥያቄ ‹‹መፍትሔ መስጠት የሚችሉት የበላይ የመንግሥት አካላት ብቻ እንደሆኑ›› ተገልጦላቸዋል::
 •  መንግሥት በ‹ዝምታ ዲፕሎማሲ› የግብረ ሰዶማውያኑን የቅድመ (ICASA) ስብሰባ ከመከላከል ሲቆጠብ የስብሰባው የኮሚዩኒኬሽን ሓላፊዎች በበኩላቸው በተ.መ.ድ የስብሰባ አዳራሽ እየተካሄደ ስለሚገኘው ‹ሥልጠና› እና ልምድ ልውውጥ የተካተተበት የግብረ ሰዶማውያኑ ቅድመ ጉባኤ የማነቃቂያ ስብሰባ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በመናገር እያደናገሩ ይገኛሉ::

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)