November 5, 2011

አባ ሰረቀ ከሹመት ታግደው ይቆያሉ፤ ንቡረ እድ አባ ገ/ማርያም የትምህርት እና ማሠልጠኛ መምሪያ ሓላፊ ሆነው እንደተሾሙ እየተነገረ ነው


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 25/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 5/2011/ PDF)፦ አባ ሰረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል ከተጠረጠሩበት የሃይማኖት ሕጸጽ ነጻ መሆናቸው እስኪረጋገጥ ድረስ በማንኛውም ቦታ በሓላፊነት እንዳይመደቡ ዛሬ የተጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንደወሰነ ዘግይተው የደረሱን የመረጃ ምንጮች በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሆኑ ደብዳቤ ደርሷቸው የነበሩት ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም ገብረ ሥላሴ የትምህርት እና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊ እንዲሆኑ መወሰኑን እነዚሁ ምንጮች ጨምረው አመልክተዋል፡፡ ርግጡን ቆይተን እናየዋለን፡፡


ትናንት የማደራጃ መምሪያው ዋና ሓላፊ እንዲሆኑ ‹በፓትርያሪኩ እና በጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ስምምነት ተመርጠዋል› የተባሉት አባ ኅሩይ መሸሻ መምሪያውን በሲኖዶሱ ከተላለፉት ውሳኔዎች አኳያ አስተባብሮ የመምራት ጉዳይ ጥያቄ ቢነሣባቸውም ለጊዜው የተሰማባቸው ለውጥ እንደሌለ ተጠቁሟል፡፡

ዛሬ ከቀትር በፊት በነበረው የስብሰባው ማጠናቀቂያ ላይ በተላለፈው በዚሁ ውሳኔ የፓትርያርኩ የምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅነት ሹመት ሐሳብ በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት በቋሚ ሲኖዶስ ተመርጦ እስኪቀርብ ድረስ እንዲቆይ፣ የቀድሞው ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ ግን ቀደም ሲል እንደተገለጸው ወደ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት በሥራ አስኪያጅነት የመዘዋወራቸው ጉዳይ አይቀሬ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

4 comments:

yemelaku bariya said...

በሙስና ላይ ጠንካራ አቋም ላላቸው ለንቡረዕድ ይህን አቋማቸውን እግዚአብሔር ከሳቸው ጋ እንዲያጸናው እንጸልይላቸው:: እንድህ አይነቶቹን አባቶች ላላሳጣን ላልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይገባዋል:: እሳቸውንም በክብር በሞገስ ይጠብቅልን:: ተስፋ አሳይተውናልና::

MESERAK said...

በቅድሚያ ምስጋና ለደጀሰላምአ
ተስፋ በቆረጥንበት ሰኣትህ እንደዚ አይነት ዜና መስማት በጣምነው ደስየተኝሁት
አሁንማ አባቶችንለይ ተስፋ ቆረጪ ነበር ግን ትንሽደግሞ ነፍሴልትመለስ ነው
በጣም የታዘብኲቸው ባለፈው ሰሞን ዲሲ ላይ” በእንተስማ ለማርያም” የሚል አውደርእይ
በማህበረ ቅዱሳን ተዘጋጅቶ ሳይ መቹም እንባዩን ዘርቺ ነው የወጣሁት ፣አሁን በውነት ከሆነ
ቅዱስሲኖዶስ ስንትቀን ሙሉ ስለማሕበረ ቅዱሳን ይወያይ ነበር? እያልኩኝ …….ታዘብኲቸው
አሁንመቺም ይሄ አይጠፋችውም እነሱናቸው የመጀመሪያ ተጠቃሚዎቸች ለሹመት ና ለማእረግ ያበቃቻቸው
ይህችው ቤተክርስቲያን ነበረች ?ታዲያ እንዴት ይረሳል? ለማንኛውም የቤተክርስቲያን አምለክ ይታደገን
ደጀስላም ተስፋበናንተላይ ጥለናልና በርቱ

ቸርወሬያሰማን አሜን

Orthodoxawi said...

Dear Dejeselam, thanks for your usual well supplemented reports about the Holy Synod meeting.

In summary:-
1. Most of the decisions during the meeting are satisfactory.

2. In particular, I am happy to see that our fathers have reached on a common understanding about the danger of Tehadso. That is why they deprived of Aba Sereke (the Tehadso-Horn) from any official post.

They have also decided to take actions on the other Tehadso-protestant missionaries (Begashaw's group).

2. What I am not happy about is the case of Aba Fanuel. Now, much is expected from the real Tewahedos in North America. They should defend our church. They should not accept Aba Fanuel...otherwise he will do the same as he did in Awassa. He is already planning to take the Tehadso-gangs with him.

Take care North Americans.

Egzer Yirdachihu.
Long live Tewahedo!

ZeTewahedo said...

Selam Wegenoche,

Endemitayewu abatochachin le betekrstiyan be selamawiw tornet eyetewadequ yigegnalu. Chersewu bayaswegdutim be Aba Paulos le betekrstiyan yetedegesewun tifat mekenes chilewal.
Gin meche yihon enihn sewu (Aba Paulos) tewegdewu yemnayachewu ... erefte zemen bigetachewu melkam neber...yikrta yihn silalku ... gin betam abezut? Hulie Yetfat sira? Betekrstiyan lekbr abekachachewu enji min atefach? Lemin yihon endih bekfat yetenesubat? Ye alama guday ayimeslachihum?

Ewnetegnoch Abatochin Egziabher Amlak Be Edme ena Be tsega Yitebkilin. Amen!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)