November 19, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን ለአዲሱ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ አቀባበል አደረገ


  • READ IN PDF.
  •  “የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የበለጠ ለመደራጀት፣ ብዙ ሥራ ለመሥራት ይፈልጋሉ፤ ርኵስ መንፈስ ግን እያሰነፈ ሥራዎች እንዲቋረጡ እያደረገ ነው፤ የመናገር ሀብት የመሥራት ስንፍና አለብን፤ አድምጡኝ ብቻ ሳይሆን የማድመጥ፣ የመደማመጥ ነገር መኖር አለበት፡፡ እኛ ስንለያይ ንፋስ እየገባ ቤቱን ያውከዋል፤ ለክፉ ነገር ዝግ፣ ለበጎ ነገር ክፍት መሆን አለብን፤ የሚለዋወጥ ኅሊና ጥቅም የለውም፤ . . . ነገ የሚሆነውን አላውቅም እንጂ ሐቅና እውነት እንዳልዎት [መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይን] ዐውቃለሁ፤ እግዚአብሔር የሥራ ጊዜዎን፣ አእምሮዎን ይባርክልዎ:: (ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ)
  • “ለሁሉም መንገዱ አንድ ከሆነ፣ ለሁሉም ፍቅር ካለው ከራስ አልፎ ለሌላው የሚተርፍ ሥራ መሥራት ይቻላል፤ የምንኖረው፣ የምንተዋወቀው፣ የምንሠራው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለቤተ ክርስቲያን ነው (መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ)
  • [የማደራጃ] መምሪያውን በማንኛውም ነገር እናግዛለን፤ በበጎ ፈቃድ ቤተ ክርስቲያናችንን በሞያችን፣ በዕውቀታችን፣ በገንዘባችን ከማገልገል በቀር ሌላ ዓላማ የለንም፤ አባታዊ መመሪያዎንና ምክርዎን እንሻለን” /የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ/::
  • “Who is he, after all? እርሱ መንግሥት ነው እንዴ ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀመጠው፤ የተመደበበት ቦታ ቢሠራ ይሻለዋል፤ ከአቅሜ በላይ ነው ብያለሁ፤” (አቡነ ጳውሎስ ለአባ ሰረቀ ሎቢስቶች የተናገሩት)::
(ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 8/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 18/2011)፦ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሥር ተዋቅሮ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን ለአዲሱ የማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ መሸሻ አቀባበል አደረገ፤ በአቀባበሉ መርሐ ግብር ላይ የማኅበሩ ሥራ አመራር ጉባኤ እና ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት እንዲሁም የክፍል ሓላፊዎች ስማቸውን፣ ሞያቸውንና የሥራ ድርሻቸውን ለዋና ሓላፊው በመግለጽ ራሳቸውን ያስተዋወቁ ሲሆን የቤተ ክርስቲያንን ሕግ እና ሥርዐት አክብሮና አስከብሮ፣ መዋቅርንና የሥራ ተዋረድን ጠብቆ በፍቅር፣ በመደማመጥ መሥራት ከሁሉም አካላት እንደሚጠበቅ በአጽንዖት ተገልጧል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን “ሕፃናት፣ ወጣቶች እና ማኅበረ ቅዱሳንን ጭምር አስተባብሮ በመምራት” ረገድ በታየባቸው የአቅም ማነስ እንዲሁም ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ጋራ ባላቸው ግንኙነት ሳቢያ በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከዋና ሓላፊነታቸው ተወግደው ምርመራ እንዲካሄድባቸው ውሳኔ በተላለፋባቸው ቆሞስ አባ ሰረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል ምትክ የተሾሙት መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ በውጭ ሀገር ከ12 ዓመታት በላይ መኖራቸውን፣ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ እና በብፁዓን አባቶች ጥሪ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ቤታቸው እንጂ የማንም አለመሆኑን የገለጹት መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ፣ “እንደ መልካችን የተለያየ ሐሳብ እና ጠባይ ቢኖረንም ቤተ ክርስቲያን ሁሉንም በደካማነቱ ሳታርቅ አቅፋ የያዘች ናት፤” ብለዋል፡፡

ዋና ሓላፊው ቁጥብነትና ጥንቃቄ ጎልቶ ታይቶበታል በተባለው አጭር ንግግራቸው፣ የእርስ በርስ ትውውቁ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለቤተ ክርስቲያን ለሚከናወነው የጋራ አገልግሎት በመሆኑ የቤተ ክርስቲያንን ሕግ እና ሥርዐት በማክበር ሁሉም በአንድ መንገድና በፍቅር ካገለገለ ከራስ አልፎ ለሌላም የሚተርፍ ሥራ መሥራት እንደሚቻል አመልክተዋል፤ ስለተደረገላቸው አቀባበል በማመስገን እግዚአብሔር ይረዳቸው ዘንድ አባቶች በጸሎት እንዲያስቧቸው ጠይቀዋል፡፡

ሕግ እና ሥርዐት ያላት ቤተ ክርስቲያናችን ሁለመናዋ ያማረ መሆኑን በመግለጽ ንግግራቸውን የጀመሩት የማደራጃ መምሪያው ሊቀ ጳጳስ በበኩላቸው፡- በአባቶቻችን ቦታ የተገኘን እንደመሆኑ መጠን አባቶቻችንን በስምም በግብርም ተቀርጸን፣ መስለን ሥርዐቷን ልናከበር ብቻ ሳይሆን ልናስከብር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ሰውን ሰው የሚያሰኘው ቁም ነገሩ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው፣ ክርስቲያኖችን ከዓለም የሚለያቸው ቁም ነገር ከሰው አልፎ አራዊትን የሚያለምድው ውስጣዊ ፍቅራቸው፣ ቅድስናቸው፣ ታዛዥነታቸው፣ ሐቀኝነታቸው፣ ታማኝነታቸው በመሆኑ ለክፉ ነገር ኅሊናችን ዝግ፣ ለበጎ ነገር ደግሞ ክፍት መሆን እንደሚገባው መክረዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ከግለሰብ የተነሣ የሚመጡ ችግሮች እንደሚታዩ በመጠቆም ሁሉም ግን ቤተ ክርስቲያንን እንደማይወክሉ አስረድተዋል፡፡የመናገር ሀብት የመሥራት ስንፍና አለብን” በማለት የተቹት ብፁዕነታቸው፣ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ‹አድምጡኝ› ብቻ ሳይሆን የማድመጥ እና የመደማመጥ ነገር መኖር እንዳለበት፣ በአፈጻጸም ረገድ የሚታዩት ችግሮችም ስሕተቶችን በወቅቱ በማረም፣ በመወያየትና በመነጋገር፣ እንደ ሰውነታችን አካል/ ሕዋሳት ተባብሮ በመሥራት እንደሚፈቱ ገልጸዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
ሰይፍ ዘክልኤ አፉሁ” እንደሚባለው ወጣቱን በመንፈሳዊ ሕይወቱ ማጎልመስ/ማሳደግ፣ በማኅበራዊ ሕይወቱ እንዳይቀጭጭም መደገፍ እንደሚገባ ብፁዕነታቸው አሳስበው፣ የአዲስ አበባ ወጣቶችን በምሳሌነት በመጥቀስ ዛሬ ኦርቶዶክሳዊው ወጣት የበለጠ መደራጀት፣ ብዙ መሥራት እንደሚሻ፣ ርኵስ መንፈስ ግን እያሰነፈ ሥራዎች እንዲቋረጥ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ከማደራጃ መምሪያው ጋራ የከምባታ ሐድያና ጉራጌ አህጉረ ስብከትን ሊቀ ጳጳስነት ደርበው የያዙት ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ [የምሥራቅ ሐረርጌ እና ኦጋዴን አህጉረ ስብከት እያሉ]፡- የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ ጎልቶ በሚታይበት በጉርሱም፣ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ጫፍ እስከ ዋርዴር ቅዱስ ገብርኤል፣ ቀብሪደኃር፣ ጎዴ ድረስ በመከላከያ ሠራዊት ኮንቮይ ታጅበው በሄዱበት ወቅት የማኅበረ ቅዱሳንን አባላትና አገልግሎት (የኅትመት ውጤቶች) ማግኘታቸውን ገልጸው፣ ይኸው የማኅበሩ ሐዋርያዊ አገልግሎት ገና ያላያቸው፣ ሊናቸው የሚገቡ አካባቢዎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

እርሳቸው ማዕርገ ጵጵስና ከመሾማቸው በፊት በ1983 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ስብከተ ወንጌል ክፍል ሓላፊ እንደነበሩ ያስታወሱት ብፁዕነታቸው፣ በወቅቱ ወጣቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን በብዛት ይጎርፍ የነበረ ቢሆንም በቂ የመምህራን ቁጥር እንዳልነበር፣ የማኅበሩ ቀደምት አባላትም በአዲስ አበባ ዙሪያ በ40 ኪ.ሜ ክልል ስምሪት በማድረግ ይሰጡት የነበረውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎት አዘክረዋል - ዛሬ ከዚያ በተሻለ ደረጃ ላይ ብንገኝም ገና ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅበት፣ ለዚህም አንዱ ሌላውን በመናቅና በማዋረድ ሁከት ውስጥ በመግባት ሳይሆን ተከባብሮና ተስማምቶ ማገልገል እንደሚኖርበት አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

አዲሱን ዋና ሓላፊ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይንም በሚመለከት “ነገ የሚሆነውን አላውቅም እንጂ ሐቅና እውነት እንዳልዎት ዐውቃለሁ” በማለት ምስክርነታቸውን የሰጡት ብፁዕነታቸው፣ በዋና ሓላፊነታቸው በሚቆዩበት ወቅት ተጠሪነታቸው ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት መሆኑን በመገንዘብ መዋቅርን አክብሮ፣ በማይለዋወጥ ኅሊና ሥራን መፈጸም እንደሚገባ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል፤እግዚአብሔር ሥራዎን፣ አእምሮዎን ይባርክልዎ፤ እግዚአብሔር ያስችልዎ፤ ይርዳዎ” በማለትም ቡራኬያቸውን ሰጥዋቸዋል፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም በ12 ነጥቦች የተዘረዘሩ የማኅበሩን ዓላማዎች ከመተዳደሪያ ደንቡ ጋራ በማመሳከር ያስረዱ ሲሆን ማኅበሩ ከ20 ዓመት በፊት፣ “መመሪያ ይሰጠን፤ መዋቅር ይበጅልን” በሚል ወደ አባቶች ቀርቦ በጠየቀው መሠረት በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ሥር እንዲዋቀር መደረጉን አውስተዋል፡፡ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ አያይዘውም የማኅበሩ ዓላማ የተማረው ትውልድ በሞያው፣ በዕውቀቱ እና በገንዘቡ ቤተ ክርስቲያንን በመንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ዘርፎች በበጎ ፈቃድ ማገልገል እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ተናግረዋል፤ በማደራጃ መምሪያው ሥር እንደመዋቀሩም መጠን በየስድስት ወሩና በዓመት ዕቅዱንና ክንውኑን ለመመሪያው በሚያቀርበው ሪፖርት እንደሚያሳውቅ፣ መምሪያውን በሚፈለገው መንገድ ለማገዝና ለማጠናከርም ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ አስታውቀዋል፡፡

ይህም አዲሱ ዋና ሓላፊ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ በቀጣይ የማኅበሩን ሥራዎች ተዘዋወረው በመጎብኘት፣ በማኅበሩ ጉባኤያትና የተለያዩ ዝግጅቶች ላይ እየተገኙ አባታዊ ምክር፣ አስተያየትና መምሪያ በመስጠት የበለጠ እንደሚጠናከር ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ያላቸውን ተስፋ በመግለጽ ዋና ሓላፊውን “እንኳን ደኅና መጡ” ብለዋቸዋል፡፡ ትንት ኅዳር 7 ቀን 2004 ዓ.ም ማምሻውን በተከናወነው በዚሁ የአቀባበል እና የእርስ በርስ ትውውቅ መርሐ ግብር ላይ የማደራጃ መምሪያው ምክትል ሓላፊ መ/ር ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ የተገኙ ሲሆን የመምሪያውን ጸሐፊ ጨምሮ የአባ ሰረቀን ከዋና ሓላፊነት መነሣትና በፓትርያኩ ተሰጥቷቸው ከነበረው የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅነት መሻር ተቃውመዋል የተባሉት ሌሎች ሦስት የመምሪያው ሓላፊዎች አለመገኘታቸው ተዘግቧል፡፡

ለአባ ሰረቀ በፓትርያርኩ የተሰጣቸው የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተሽሮ የሌላ መምሪያ ሓላፊ መደረግ እንደማይገባቸው፣ የቀረበባቸው ክስም ለምንኵናቸው እንደማይመጥንና ሥራቸውን ለመቀጠል እንደማያስችላቸው፣ ለፓትርያኩም ቢሆን በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅነታቸው ሓላፊነት ከሚበዛባቸው ንቡረ ድ ኤልያስ ይልቅ የጠቅ/ቤ/ክ/ጽ/ቤትን በቅርበት የሚቆጣጠሩላቸው ታማኛቸው አባ ሰረቀ በምክትል ሥራ አስኪያጅነት መቆየታቸው እንደሚጠቅማቸው በመጥቀስ ወደ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያኩ በተደጋጋሚ በመግባት አቤቱታ እና ውትወታ /ሎቢ/ ላቀረቡላቸው ለእኒህ ሦስት የልዩ ልዩ ዴስክ ሓላፊዎች ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ “ውሳኔው አባቶች የወሰኑት ነው፤ ከአቅሜ በላይ ነው፤ ምንም ማድረግ አልችልም፤” በማለት መልሰዋቸው ተብሏል፡፡

ይሁንና በአባ ሰረቀ ጉዳይ፣ “ከብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ጎን ቆመዋል፤ በፓትርያኩ ላይ አሢረዋል” ያሏቸውን አንዳንድ የቤተ ክህነቱን ሓላፊዎች በመክሰስ ውትወታቸውን የቀጠሉት ሎቢስቶች ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ፓትርያኩ በመግባት፣ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች እስካልተመለሱ ድረስ አባ ሰረቀ በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ውሳኔ በተመደቡበት የትምህርት እና ማሠልጠኛ መምሪያ ሓላፊነት ለመሥራት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ይነግሯቸዋል፡፡ በወትዋቾቹ ውትወታም ነው ቢሉ በአባ ሰረቀ እምቢታም ነው ቢሉ ያዘኑት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያክ አቡነ ጳውሎስም፡- “Who is he, after all? እርሱ መንግሥት ነው እንዴ ቅድመ ሁኔታ የሚያስቀመጠው፤ የተመደበበት ቦታ ቢሠራ ይሻለዋል፤ ከአቅሜ በላይ ነው ብያለሁ፤” ብለው እንደመለሱላቸውና በምላሻቸውም ሎቢስቶቹ ከቢሯቸው ተደናግጠው መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡


16 comments:

Anonymous said...

Bego Yemegbabate Ye fiker Ye sira zemen yadirgilin

bante views said...

“ የቤተክርስቲያንን ስርአት ማክበር ብቻሳይሆን ማስከበርም አለብን ”..አውነትነው

Anonymous said...

rejim idime ina tena le wudu abatachin le ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ .

Haile Zemariam said...

Amlak hoy! Ebakeh fekren, metesaseben, kin helinana netsuh lebonan seten!
Lehulachenem ye agelgelot zemenachenen barkelen!
Ye Tenbit mefetsemia atadergen!
Amen.

Haile Zemariam

Anonymous said...

1."አዲሱ ዋና ሓላፊ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ በቀጣይ የማኅበሩን ሥራዎች ተዘዋወረው በመጎብኘት፣ በማኅበሩ ጉባኤያትና የተለያዩ ዝግጅቶች ላይ እየተገኙ አባታዊ ምክር፣ አስተያየትና መምሪያ በመስጠት የበለጠ እንደሚጠናከር ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ያላቸውን ተስፋ በመግለጽ ዋና ሓላፊውን “እንኳን ደኅና መጡ” ብለዋቸዋል፡፡"

2."ማኅበረ ቅዱሳን ለአዲሱ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ አቀባበል አደረገ"
አባ ኅሩይ ዋና ሓላፊ ናቸው ወይንስ የሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ሓላፊ?

አቀባበል የተደረገው ለጳጳሱ ነው ላባህሩይ?

lele said...

tamasegan tero abate agegetane abatocheme egame badaseta yamenagalagelebate barakata sega ena nafese yamenagagebate yaderegelen.bamawakem balamawekem yatafote tamalesawe eske dabelose yameyaferebate zeman yaderegelen

Anonymous said...

መልካም፡ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ሌሎችን የተሐድሶ ሰርጎ ገቦች ገብተዋቸዋል ብሎ እንደሚያሳስበው፤ ራሱንም ገብተውኝ ይሆን እንዴ ብሎ ለአፍታ ቢመረምር መልካም ነው፤ የሚጠረጠሩትንም ስም እየጠሩ ከማሳደድ አቅርቦ ለመመለስ ሙከራ ቢደረግ መልካም ነው። አረመኔን ለመስበክ የተዘጋጀ፤ የተጠራጠረን በሁለት እግሩ ለማቆም ቢጥር ክፉ የለውም። ሐዋርያው የቆመ የሚመስለው ቢኖር እርሱ ይጠንቀቅ ይላልና።

Anonymous said...

መልካም፡ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ሌሎችን የተሐድሶ ሰርጎ ገቦች ገብተዋቸዋል ብሎ እንደሚያሳስበው፤ ራሱንም ገብተውኝ ይሆን እንዴ ብሎ ለአፍታ ቢመረምር መልካም ነው፤ የሚጠረጠሩትንም ስም እየጠሩ ከማሳደድ አቅርቦ ለመመለስ ሙከራ ቢደረግ መልካም ነው። አረመኔን ለመስበክ የተዘጋጀ፤ የተጠራጠረን በሁለት እግሩ ለማቆም ቢጥር ክፉ የለውም። ሐዋርያው የቆመ የሚመስለው ቢኖር እርሱ ይጠንቀቅ ይላልና።

Anonymous said...

we hope God is working and heard abune paulos saying ''it is above my capacity. Our true spiritual fathers had prayed and will be praying a lot.

1. May God help him to repent for all what he did.

2.May God give us strength and prayer to stand for our church.

3. May God return those who are lost from our church due to bureaucratic administration, corruption and be hurt by service givers.

4.May God help us to know our orthodox church well and be practical person.

5. May this year be a year of repentance, love, work and clearing the church from corrupter, bad administrators, non-spiritual persons and make place of spirituality.


6. please all orthodox people be researcher on our church to know our church, our properties and above all our people life to be lead in a better spiritual as well as cultural integrity.

7.God bless all of us and help us to pray for our church ,people and country on our everyday's prayer.

Anonymous said...

Cher yaseman. It is good to hear this.

Orthodoxawi said...

Egzer yetemesegene yihun.
Eski addisun halafim ke kfuwoch mikir yitebkachew.

Amen!

Orthodoxawi said...

Who is he after all? -> He is a fanatic, extremist coordinator of tehadso-protestantism.

ZeTewahedo said...

Dear MK, congrats! God is with you.
Now try to treat the new Manager with love and great care as far as he is truly from Tewahedo.

Also help him with whatever you can, to lead and take the Sunday schools one step ahead.

Egziabher Yirdachihu!

ብዕሩ ዘ-አትላንታ said...

መልካም ነዉ። መቼም ከትላንቱ ጥፋት የማይማር የለም። ለአባቶቻችን በማደራጃ መምሪያዉ ለተመደቡት ከባድ ፈተና እንደሚገጥማቸዉ እርግጠኛ ነኝ። ለማለት የተፈለገዉ አባ ሰረቀ(ሠረቀ) የተከሉትን ሰንኮፍ ነቅሎ ለማዉጣት ቀላል አይሆንም ለማለት ነዉ። አባ ሰረቀ ወጣቱን ከአባቶች የለያዩ፣ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ለማጋጨት ብዙ የጣሩ፣ኑፋቄን በቤተ ክርስቲያናችን ዉስጥ የዘሩ ጸረ ተዋህዶ ናቸዉና ነዉ። አሁን የተሰጣቸዉ ቦታም ቢሆን ቤተ ክርስቲያንን ከመጠበቅና ከማስጠበቅ አንጻር ተገቢ ቦታ አይደለም እላለሁ። ለእርሳቸዉ የሚገባዉ ቀኖናና ትምህርት ነዉ። አሁን እንዳይሠሩ የሚያግዳቸዉ ተሰነዘረብኝ የሚሉት ዉንጀላ ሳይሆን የፈጸሙት ግፍና በኑፋቄ የተመረዘ ማንነታቸዉ ነዉ። ስለዚህ አባ ሰረቀ በሐሰት ፈርጥመዉ መፈራገጡን አቁመዉ የበደሉአትን ቤተ ክርስቲያን ይቅርታ ቢጠይቁ የሻላል። ለእኛ፣ በዚህ ዘመን በሃይማኖት ለመኖር ለምንናፍቅ የተዋህዶ ልጆች ጥሩ አባት፣መምህርና የሚያጸና እንጂ የሌላ እጄታ ሆኖ የሚያናቁር፡ መሥራት በሚገባን ዘመን በንትርክና ጭቅጭቅ ጊዜአችንን የሚያባክን አይደለም። ለቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መከበር ለሚማስኑ አባቶቻችን ረጅም እድሜና መልካም የሥራ ዘመን እመኛለሁ። ብዕሩ ዘ-አትላንታ

Anonymous said...

Who is he, after all? Wasn't he witchcraft practitioner while he was in Gondar? Who is? Wasn't he the would be mastermind of Tehadiso conspiracy?

Tell him that he is UNFIT for all positions and take him away the Church's leadership and clerical servitude as well. You, Brood of viper.

Anonymous said...

ነገ የሚሆነውን አላውቅም እንጂ ሐቅና እውነት እንዳልዎት ዐውቃለሁ”

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)