November 29, 2011

የአፍሪካ ግብረ ሰዶማውያን በአዲስ አበባ ለማካሄድ ያቀዱትን ስብሰባ “የኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ” ተቃወመ!!  • የግብረ ሰዶማውያኑ ስብሰባ የ(ICASA)ን ኮንፈረንስ አሉታዊ ትርጉም እንዳያሰጠው ተሰግቷል
  • “Claim, Scale-up and Sustain”(የራስ ማድረግ፣ ማሳደግ እና ቀጣይነት) የግብረ ሰዶማውያኑ ውይይት መሪ ቃል ሲሆን አዲስ አበባ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ መዲና መሆኗን በመጠቀም በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር ዕቅድ ተይዟል፤
  • እስከ አሁን ደቡብ አፍሪካ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ሕጋዊ ያደረገች ሲሆን በተቃራኒው የናይጄሪያ ፓርላማ ግብረ ሰዶማዊነትን ሕገ ወጥ ያደረገ ሲሆን በኬንያ እና በዑጋንዳ የግብረ ሰዶማውያን መብት በሚል ለፓርላማዎቻቸው ጥያቄ ቢቀርብም ውድቅ አድርገውታል።
  • ዝምባቡዌ ግብረ ሰዶማውያን “ውሾች ናቸው” በሚል ከሀገር ታባርራለች
 (ደጀ ሰላም፤ ኅዳር 19/2004 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 29/2011 PDF):- የውጭ አገር ዜጎች፣ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ወደ ውጭ አገር ለንግድ አብዝተው የሚመላለሱ ኢትዮጵያውያን ግብረ ሰዶማዊነትን እንደ ዘመናዊነት/ሥልጣኔ ቆጥሮ በማስፋፋት ረገድ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን በአብዛኛው የሚጠራሩበት ስም “ዜጋ” የሚል ነው፤ አንዳንዴ ይኸው ስያሜ “ኦፔራ፣ ወገን፣ ጅራሬ፣ ብርታሉ (ቁምጬ)፣ ጀሲካ ሞናሊዛ፣ ቆሚታ፣ መክተብ” በሚባሉ ስያሜዎች እንደሚተካ ተገልጧል፡፡

ግብረ ሰዶማዊነት በሁሉም እምነቶች ዘንድ ኀጢአት፣ በኢትዮጵያ ሕግም ወንጀል ነው፤ መንግሥት በግብረ ሰዶማዊነት ላይ የተለየ ትኩረት በመስጠት ሕጉን በተግባር ላይ እንዲያውል የተጠየቀ ሲሆን 97 በመቶ ኢትዮጵያውያን ግብረ ሰዶማዊነት አጸያፊ እና ኢ-ሞራላዊ እንደ ሆነ ያምናሉ፤ ኅብረተሰቡ ግብረ ሰዶማዊነትን አጥብቆ በመቃወም ባላቸው ጠንካራ አቋም (anti-gay sentiment) በዓለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። /የአ.አ.ዩ የ1996 ዓ.ም ጥናት/ “በግብረ ሰዶማውያኑ የታቀደው የቅድመ የ(ICASA) ኮንፈረንስ ስብሰባ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን ሞራል ክብር ያልሰጠ፣ ፀያፍ፣ ከሥነ ምግባር ውጭ እና ባህላችንን የሚያቆሽሽ አጀንዳ ለማስፈጸም የተነሣ የአንድ ቡድን እንቅስቃሴ ነው” /የኢ.ሃ.ጉ መግለጫ/

“በአገራችን ግብረ ሰዶማዊነት በድኻ አደግ ሕፃናትና ጎዳና ተዳዳሪዎች ላይ በሚደረግ ወሲባዊ ጥቃት ሥር እየሰደደ ያለና እንደ ፋሽን ሊነሣ ያለ ጉዳይ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ግብረ ሰዶማውያንና ግብረ ሰዶማዊነትን የሚደግፉ የውጭ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በኢትዮጵያ ያሉትን ጥቂት ግብረ ሰዶማያውያን ቁጥር በማጋነን ጎልተው እንዲታዩና ለ‹መብታቸው› ሰልፍ እንዲወጡ፣ በ1949 ፍትሐ ብሔር ሕግ የጋብቻ ትርጉም ‹በአንድ ወንድ እና ሴት መካከል የሚደረግ ኪዳን› በሚል ፈንታ ‹በሁለት ሰዎች መካከል የሚደረግ ኪዳን› ተብሎ እንዲሻሻልና ግብረ ሰዶማዊነት በሕግ እንዲፈቀድ መገፋፋታቸው ኅብረተሰቡን በከፍተኛ ሁኔታ እያሳሰበው ይገኛል፡፡

በበርካታ ሥነ ምግባራዊ ባህሏ የምትታወቀው ኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋን ከማን መድባው ይሆን?  ሥልጣኔ ይግባ ሥነ ምግባር የጎደለው ባህልና ልምድ ግን እዚያው ይቅር ትላለችን? ወይስ እንደሌላው ሥልጣኔውን ከእኵይ ሥነ ምግባሩ ጋራ ታግብሰብስ ይሆን? ይህን ዕድል ፈንታ የሚመርጥላት ትውልድ/ሕዝብ/ መሪ አስተሳሰብስ ወዴት አመዝኖ ይሆን?”/ዩናይትድ ፎር ላይፍ ኢትዮጵያ “ግብረ ሰዶማዊነት” በሚል ርእስ የአዘጋጀው መጽሐፍ/

ዜናውን መስማት በርግጥም ያስደነግጣል - ኢትዮጵያ ከምታስተናግደው 16ው “ዓለም አቀፍ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የአባላዘር በሽታዎች ጉባኤ በአፍሪካ” (16th International Conference on AIDS and STLs in Africa – ICASA) አንድ ቀን ቀደም ብሎ ለማካሄድ የታቀደው የአፍሪካ ግብረ ሰዶማውያን የቅድመ ኮንፈረንስ ማነቃቂያ ስብሰባ ከፍተኛ ትችት እና ተቃውሞ እየገጠመው ነው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንንና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤትን ጨምሮ የበርካታ አብያተ እምነት መሪዎችን በአባልነት የያዘው “የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ጉባኤ” የግብረ ሰዶማያኑን ስብሰባ በመቃወም ዛሬ ወሎ ሰፈር በሚገኘው የኖርዌ ቤተ ክርስቲያን ሊሰጠው ያዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ከመንግሥት በተላለፈ ሳይሆን እንዳልቀረ በተገመተ መመሪያ ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ተገልጧል፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫው ከመጀመሩ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት በድንገት የተገኙት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም የ‹ጉባኤው› አባላት ከሆኑት የአብያተ እምነት መሪዎቹ ጋራ ጊዜ ወስደው በዝግ በር ተነጋግረዋል። በመግለጫው ላይ እንዲገኙ ጥሪ የተደረገላቸው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ብዙኀን መገናኛ ጋዜጠኞችም ከአዳራሽ እንዲወጡ በመደረጉ በኮሪዶር ላይ ለመጠበቅ ተገደዋል፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም (Middle)

ጋዜጠኞቹ በቆይታቸው ኢትዮጵያ ከኅዳር 24 እስከ 28 ቀን 2004 ዓ.ም የሚካሄደውን 16ኛውን “ዓለም አቀፍ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የአባላዘር በሽታዎች ጉባኤ በአፍሪካ” (ICASA) ማስተናገዷ የሀገርን ገጽታ በዓለም አቀፍ መድረክ ለመገንባት እና እያንዳንዱ ተሳታፊ በጉባኤው ላይ ለመታደም ይችል ዘንድ ለምዝገባ ከከፈለው በመቶዎች የሚቆጠር ዶላር ጀምሮ ከሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አኳያ ከፍተኛ ሽር ጉድ እየተደረገበት ቢሆንም መንግሥት ከልምድ በሚታወቀው የዚህ ዐይነቱ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ተሳታፊዎች ግብራዊ ጠባይዕ ላይ ጥንቃቄ አለማድረጉ ከሚያስከትለው “የባህል መበረዝ/ወረርሽኝ ጠንቅ” አንጻር ክፉኛ አስተችቶታል፤

የአብያተ እምነት መሪዎቹም በግብረ ሰዶማያውያኑ የቅድመ ኮንፈረንስ ማነቃቂያ ስብሰባ ላይ ያላቸውን የተቃውሞ መግለጫ እስከ ዛሬ በማዘግየታቸው በጋዜጠኞቹ እንዲብጠለጠሉ አድርጓቸዋል፡፡ አንዳንዶቹም ቅዳሜ፣ ኅዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም በጁፒተር ሆቴል የሚካሄደው የግብረ ሰዶማያውያኑ ውይይት የሕዝቡን ቁጣ በማነሣሣት ከፍተኛ ተቃውሞ ሊቀሰቅስ እንደሚችል በማመልከት መንግሥት የሆነ የማስታገሥ ርምጃ ሊወስድበት እንደሚገባ አስተያየት ሲሰጡ ተሰምተዋል፡፡

የጋዜጠኞቹ ቁም ነገር እና ቀልድ የተቀላቀለበት ጭውውት በቀጠለበት ሁኔታ በድንገት ከአዳራሹ ብቅ ያሉት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ መሪ ቄስ ኢተፋ ጎበና፣ “መግለጫው ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፤ መቼ እንደሆነ በትክክል አላውቀውም፤ ከጉባኤው በፊት ወይም በኋላ ሊሆን ይችላል” በማለት አጭር ማስታወቂያ ተናግረው ወደ አዳራሹ በር ፊታቸውን መልሰዋል፡፡ “ጉዳዩ ሀገራዊም ሃይማኖታዊም ጭምር በመሆኑ የአቋም መግለጫችሁን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፉ አግባብ ነው ወይ? ከሚ/ሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሓኖም ጋራ ስለተወያያችሁበት ጉዳይ ሊነግሩን ይችላሉን?” የሚሉ ጥያቄዎች ተከታትለው ቢቀርቡላቸውም “አላውቅም፤ አልተሰጠኝም” ከሚል በቀር ቀጥተኛ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ እርሳቸው በዚህ መልክ ተናግረው ወደ አዳራሹ ተመልሰው ከገቡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ሁሉም የአብያተ እምነት መሪዎች አዳራሹን ለቀው ሲወጡ በፊታቸው ላይ ብስጭት እና ሐዘን ይነበብ እንደነበር ተዘግቧል።

እየተከታተሉ በጥያቄ ያጣደፏቸውን ጋዜጠኞች የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤቱ ተወካይ “አቦ/እባካችሁ ተዉኝ” ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ብስጭት በሚነበብበት ዝምታ ወደ መኪናቸው መግባትን መርጠዋል፤ የአዳራሹ በር በተከፈተበት አጋጣሚ ፎቶ ግራፍ ያነሡ ጋዜጠኞች ካሜራም በጸጥታ ኀይሎች እየተቀማ ፊልሙ ከፎቶ ካሜራው ላይ እንዲሰረዝ ተደርጓል፡፡
ኅዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል የሚካሄደው የቅድመ ICASA የአፍሪካ ግብረ ሰዶማውያን የማነቃቂያ ኮንፈረንስ ራሱን አምሸር - AMSHeR(The African Men for Sexual Health and Rights) ብሎ በሚጠራ ቡድን የተዘጋጀ ፕሮግራም ሲሆን ከ25 አገሮች የተውጣጡ 200 ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሏል፤ የውይይቱ መሪ ቃልም “Claim, Scale-up and Sustain” (የራስ ማድረግ፣ ማሳደግ እና ቀጣይነት) የሚል እንደሆነ ተገልጧል፡፡

ስብሰባው “ለግብረ ሰዶማውያኑ አዲስ ትብብር ለመፍጠር እና ለማቀናጀት፣ ልምድን ለማዳበር፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስፋፋት እና ለሚቀጥለው ትውልድ ይህንኑ ዘይቤ ለማስተላለፍ ለየት ያለ ዕድል እንደሚፈጥር ይታመንበታል” ይላል ለስብሰባው ቅድመ ዝግጅት የወጣው የቡድኑ መግለጫ፡፡ “ግብረ ሰዶማዊነት ሕጋዊ እንዲሆን ከማስቻል አኳያ አፍሪካዊ ምላሽና ነጸብራቅ ማሳየት፤ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ ግብረ ሰዶማዊነትን ሕጋዊ ማድረግ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ በመለየት ለተግባራዊነቱ አቅጣጫን መቀየስ፣ በአፍሪካ የወንድ ለወንድ ግብረ ሰዶማዊ ግንኙነቶችን - MSM and HIV(Men who have sex with Men) እውን የማስደረግ ጉዳይ ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት አስተዋፅኦ ስለሚያደርግ ትኩረት እንዲያገኝ ማስቻል” በመግለጫው ላይ የተጠቀሱ የውይይቱ ዓላማዎች ናቸው፡፡ በውይይቱ ላይ የ (ICASA)ን ተወካይ ጨምሮ አምስት ታዋቂ ሰዎች የዕለቱ ተጋባዥ ተናጋሪዎች እንደሚሆኑ ተመልክቷል፡፡
የግብረ ሰዶማውያኑ ስብሰባ ከ(ICASA) ኮንፈረንስ ቀድሞ እንዲካሄድ መታቀዱ ለጉባኤው አሉታዊ ትርጉም እንደሚያሰጠው ያሳሰቡት “የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ጉባኤ” አባላት በበኩላቸው ግብረ ሰዶማዊነት በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ወንጀል እንደሆነ በግልጽ ተቀምጦ ሳለና ከ97 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን እንደ አጸያፊ እና ኢ-ሞራላዊ አድርገው የሚቆጥሩት መሆኑ እየታወቀ አምሸር ይህን ስብሰባ ለማድረግ ማቀዱ “ለኢትዮጵያ ሕግ እና ለኢትዮጵያውያን ሞራል ቦታ ያልሰጠ መሆኑን ያሳያል” ብሏል፡፡

የመንግሥት ተወካዮች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የሃይማኖት መሪዎች ታኅሣሥ 13 ቀን 2001 ዓ.ም “ግብረ ሰዶማዊነት - ተፈጥሮ ወይስ የሥነ ምግባር ውድቀት” በሚል ርእስ ከሳይንስ፣ ሥነ ምግባር እና ባህል አኳያ ውይይት በማድረግ ባለ10 ነጥብ የአቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን ለዘመናት የቆዩ የሀገራችን አኩሪ የሃይማኖት፣ ባህል፣ እና የታሪክ ዕሴቶች ከአገሪቱ ሕጎች ቀስ በቀስ የሚሸረሸሩበት ሁኔታ እንዲገታ፣ ከውጭ ሀገር በሚገቡ ፊልሞች፣ መጽሔት እና ጽሑፎች በኢንተርኔት ስለሆነ በአጠቃቀም እና ዝውውር ላይ መንግሥት አፋጣኝ ጥናት በማድረግ የሕግ ማዕቀብ እንዲዘረጋ. ርምጃም እንዲወስድ ጠይቀዋል፤ በግብረ ሰዶማዊነት ችግር ለገቡት ዜጎችም የሥነ ልቡና ሕክምና እና የምክር አገልግሎት አግኝተው ከችግሩ እንዲወጡ የተለየ ማእከልና ጉዳዩን የሚከታተል የጋራ ምክር ቤት እንዲቋቋም ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡
ሰዶማውያን የሚለው ስያሜ በቅዱስ መጽሐፍ ርኵሰትና ዝሙት ይፈጽምባቸው ከነበሩና በኋላም በእሳትና ዲን ከጠፉ ሁለት የጥንት ከተሞች የተገኘ ግብራዊ ስያሜ እንደሆነ ይወቃል፡፡

ዛሬ በ”የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ጉባኤ” ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “ብርቱ ማሳሰቢያ” በሚል ርእስ የተሰራጨውን መግለጫ ሙሉ ቃል ቀጥሎ መመልከት ይችላሉ፡፡
                            
                                ብርቱ ማሳሰቢያ
ከጥቂት ቀናት በኋላ ሊከናወን ላለው የ16ው የዓለም አቀፍ የፀረ-ኤች.አይ.ቪ እና የአባላዘር መቆጣጠር(ICASA) ስብሰባ ኢትዮጵያ በታላቅ ዝግጅት ላይ ትገኛለች፡፡
የ(ICASA) ኮንፈረንስ የአፍሪካ አገሮች እያደረጉት ላሉት ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን የመከላከልና ሕዝቡን የማስተማር ሂደት ታላቅ ሚና ያለው አህጉራዊ ኮንፈረንስ ነው፡፡
በመዲናችን አዲስ አበባ ከኅዳር 24 - 28 ቀን 2004 ዓ.ም ሊካሄድ የታቀደው 16ው ኮንፈረንስም ከሚሌኒየሙ የዕድገት ግቦች ዋነኛው በሆነው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን የመከላከል እንዲሁም ሁሉም የበሽታው ተጠቂዎች የሕክምና ሽፋንና ክብካቤ ሊያገኙ የሚችሉበትን መንገድ እንዲቀይሱ እና ልምድ እንዲካፈሉ 10,000/ዐሥር ሺሕ/ ለሚሆኑ የአፍሪካ አገሮች ተወካዮች እና እንግዶች መድረክ አመቻችቷል፡፡
ኢትዮጵያውያን የዚህ ታላቅ መድረክ አዘጋጆች መሆናችን ታላቅ ኩራት እንዲሰማን ያደርገናል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህን የማሳሰቢያ ጥሪ እንድናሰማ ያነሣሣን የ16ው የ(ICASA) ጉባኤ በማስታከክ በአገራችን ፀያፍ፣ ከሥበ ምግባር ውጭና ባሕላችንን የሚያቆሽሽ አጀንዳ ለማስፈጸም የተነሣ የአንድ ቡድን እንቅስቃሴ ነው፡፡
ይህ ቡድን ራሱን AMSHeR(The African Men for Sexual Health and Rights) ብሎ የሚጠራ ሲሆን ዋነኛ ዓላማውም በአፍሪካ የሚገኙ ግብረ ሰዶማዊ ወንዶች የተሻለ ሕይወት እና ተቀባይነት የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡ ይህ ድርጅት በ13 የአፍሪካ አገሮች መቀመጫቸውን ያደረጉ 15 ግብረ ሰዶማዊነትን እንደ በጎ ምግባር የሚያንፀባርቁ ድርጅቶች ያዋቀሩት የጋራ ድርጅት ነው፡፡
AMSHeR ከ(ICASA) ኮንፈረንስ ጋራ አስታኮ ‹ቅድመ ኮንፈረንስ› በሚል ርእስ ቅዳሜ ኅዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ከ25 አገሮች ለተውጣጡ ታዳሚዎች MSM and HIV(Men who have sex with Men) በሚል አጀንዳ ላይ ውይይት ለማካሄድ ዐቅዷል፡፡
የውይይቱ መሪ ቃልም “Claim, Scale-up and Sustain” የሚል ሲሆን ቀጥተኛ የአማርኛ ትርጉሙ “የራስ ማድረግ፣ ማሳደግ እና ቀጣይነት” የሚል ነው፡፡
AMSHeR በዕለቱ (ICASA) ከሚያነሣቸው የውይይት ነጥቦች ጋራ ተመሳሳይነት ያላቸው ነገር ግን ግብረ ሰዶማዊነት እና ግብረ ሰዶማዊ የመሆን መብትን በአዎንታዊ መልኩ የሚያንፀባርቁ የውይይት እና የልምድ ልውውጥ መድረኮችን ለማካሄድ ዐቅዷል፡፡
በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ግብረ ሰዶማዊነት ወንጀል እንደሆነ በግልጽ ተቀምጦ ሳለና ከ97 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን እንደ አፀያፊ እና ኢ-ሞራላዊ አድርገው የሚቆጥሩት መሆኑ እየታወቀ ይህን ስብሰባ ለማድረግ AMSHeR ማቀዱ ለኢትዮጵያ ሕግ እና ለኢትዮጵያውያን ሞራል ቦታ ያልሰጠ መሆኑን ያሳያል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የዚህ ኢ-ሞራላዊ ስብሰባ በቅድመ ኮንፈረንስ ስም ከ16ው የ(ICASA) ኮንፈረንስ በፊት መደረግ በኮንፈረንሱ ላይ አሉታዊ አንድምታ እንዲያጠላበት ያደርጋል ብለን እናምናለን፡፡
                       
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!

27 comments:

Anonymous said...

Lezemenat tafrana tekebra yenorech hagerin bemanalebigninet yihin hulu gif mefetsem betam yasazinal. minim enkuan zemenawinet ena legenzeb bilo tarik ena tiwilid yemayresaw tebasa tilo malef askefi new. lelaw yikir yihinin enkuan endayhon ebakachihu anid belulin. yehich hager mekerawa beztoal. Abetu Amlak hoy Libona sitachew

Anonymous said...

ayee anchi hager....lezih bekash...????????????????..amilak hoy minew tewuken..???...leminis lekifuwoch asalifeh setehen..?
sirachin befiteh yihen yahil kefa..siraw kifu yehone hizeb yeweledew yemeretew meri........

Anonymous said...

ኦሪት ዘፍጥረት

ምዕራፍ 19:

24፤ እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤

25፤ እነዚያንም ከተሞች፥ በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ፥ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ፥ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ።

26፤ የሎጥም ሚስት ወደ ኋላዋ ተመለከተች፥ የጨው ሐውልትም ሆነች

Anonymous said...

i knew that one of the students of addis ababa university, master of public health,conducted a research on this issue in addis ababa and identified many things. he indicated that the practice was very common in addis ababa, jimma, hawassa, gondar and other tourist distination areas. particularly in addis, he indicated that there were bars for this practice. of course, my surprise while reading the research was knowing the fact that known religious persons, high profile persons, muscicians and others were involved. whatever the case we have to know that the end of the world is approaching, let God helps all of us

Anonymous said...

Oh my God this is morally,culturally and religiously unacceptable. What a mess is going on there in Ethiopia.
The religious alliance and the people at large have to reject whatever the dictators direct them. This, the so called gov't officials are crazy. Really they are so stupid.

Anonymous said...

ይህ ስብሰባ በይፋ በዚህች አገር ከተከናወነ ወይም እንዲከናወን ከተፈቀደ መንግስት ለሕዝቡ ያለው ንቀትና ድፍረት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ውርደትን፣ ንቀትንና ድፍረትን መሸከም የለመደ ትከሻችንና ሁሉን በዝምታ የሚችል ሰፊ ሆዳችን ይህንንም መታገስና መሸከም ከቻለ እውነትም የለንም፡፡ ኢትዮጵያም ሆነች ኢትዮጵያዊነት የለም፡፡ ቢያንስ በዚህ እንኳን መንግስት የሰውነትና የእምነት ክብራችንን ቢጠብቅልን ምናለበት?

kesis Sintayehu said...

Dear Dejeselam, thank you for the information. We the Ethiopian have to condemn this evil event together. This is what angers God and makes Him to punish the generation. For us the poverty,plagues, drought,HIV, and other disaters those we are experiencing are more than enough. Homosexulity is not what we seek for. We are seeking to creat a generation that proud of his good culture,history, and faith. We are in need of good generation who works for his country development. We are working much to stop any unethical movements those target on our generation and the future. This is against our faith. It is not the matter of politics. Though we are supporting the government's development and transformartion agendas, we also strugle any evil issues that distort our commiunity. What the eligious sectors are trying is not enough alone. The whole religious people have to comme together soon and condemn it. Beside this we have to pray to God that He may save us and our beloved children from this evil movment that angers Him.
May God be with us through his beloved mother's intercesion.
Blessings.
Kesis Sintayehu Abate.

Anonymous said...

YOU GUYS I mean those who need Ethiopia to get involved in this kind of immoral
discussion should be condemned.

1. Most of the Ethiopian culture and religion do not allow this agenda , we do not have big problems ,we do have so many big issues where we may need help and share experiences like good technology .Do not dump you rubbish ideas in to us.

2. You assume as if you are modern but in our definition , modern means following the mind' hilina' ,nature does not push many people to be gay.
if there are some problems,this guys should be treated.The solution for the problem is solving,not disseminating and more people sick. we know how this kind of gays are created, if you think and want to help gays , help them to reverse to natural ways and get treated.

3. We developing countries,please be aware and struggle to change our work culture, system of work flow , to be hard worker and so on ,do not grab rubbish agendas from others.

4. It is our right we have to say no to agendas which do not build our generation.

There are many disadvantage in to it.
-teaching other people including children to be involved.
-demoralizing people.
-economic burden
-decrease continuity of life
-and involve people to use drugs and much more to avoid mind regret

5.we strongly disagree and condemn the agenda.

Anonymous said...

እሪ በይ ሀገሬ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

ይህንን ያሳየን ያሰማን!እንደጥንቱ አባቶቻችን እግዚኦ እንበላ!ሱባኤ እንግባ!በዚህች የእግዚአብሔር ፍርሃት አለባት በምትባል ሀገር በአደባባይ ወንድና ወንድ ሴትና ሴት ሊጋባ!!!!!!!!!!!!!!ጉድ በሉ በሉ እርስ በርስ መበላላት ትተን ሕዝበ ክርስቲያኑን ቀስቅሱና ጩኸታችንን ለእግዚአብሔርም! ለመንግሥትም እናሰማ!
ዮሴፍ ነኝ

Anonymous said...

ዘመናችን እየከፋ መጥቷልና የምቆምበትን እናስተውል።
በቅርቡ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ግብረ ሰዶማውያንን ለማያከብሩ አሕጉር (አገሮች) ምንም ዓይነት የኢኮኖሚ እርዳታ እንደማያደርጉ ግልጥ አድርገዋል። በዚህም ጉዳይ የዚምባቡዌው ጠቅላይ ሚኒስትር [የተቃዋሚው MDC ፓርቲ ሊቀመንበር] ቅሌት ጉድ አሰኝቷል። ይኸውም ውጉዝ ከመ አርዮስ ሲሏቸው የነበሩትን ሰዶማውያን ወዳጆች ለማለት ተገድደዋል። ለተጨማሪ ዜና ይኸንን ይመልከቱ። http://news.pinkpaper.com/NewsStory/6310/30/10/2011/Prime-Minister-tells-leaders-aid-is-dependent-on-changing-anti-gay-policy-.aspx፤ http://www.newzimbabwe.com/news-6437-Tsvangirai%20gay%20push%20doomed%20Ncube/news.aspx
ለመሆኑ የውጪ አገር ዜጎች፣ በውጪ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ወደ ውጪ ለንግድ የሚመላለሱ ኢትዮጵያውያን ብቻ ናቸው በዚህ ጉዳይ ተዋናዮች? ጉዳዩ ከተነሳ አይቀር የግብረ ሰዶም ዋንኛ ተዋናዮች የሐገራችን ቱባ ቱባ ባለሥልጣናት ናቸው።
የኛስ ጠቅላይ ሚኒስቴር እንደ ዚምባቡዌው ይቀለበሱ ይሆን፤ ወይንስ በሐገራችን ሕግ ይጸኑ ይሆን? ጊዜ ይፈታዋል።
አባታችን የክብር ፕሬዚዳንት የሆኑበትስ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማኅበር ከ፶ ከ፻ የማያንሱቱ አባላት ሰዶማውያን እንደሆኑ ጠፍቷቸው ይሆንን የዛሬው ብስጭታቸው።
ሰዶማውያን ጳጳሳትን የምትሾመው አንግሊካን ቤተክርስቲያን፤ የአባላቷ ብዛት ከሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንና ከምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ቀጥላ በሦስተኛ ደረጃ ይገኛል።

Anonymous said...

batam yasazenale AMELAKE HOY ESEKA MACHE NAWE ZEME YAMETELACHAWE......

Anonymous said...

Yegna bedelina ametsa ejig bikefa enji yihichi lealem temsalet yehonech hager endih yale bsigawim bemenfesawim hig wenjelna hatiat mehonu yetregagetwun guday sijemer wedmedrk lemakreb dirdir wusit yemigebabet gudaye alneberem. Ahunim Lehayemanot abatochim hone lemengist balsiltanat gudayu yetiwlid tifat kemasketelu befit sayiderk bertibu meftihe endiyabejulet mastwalina tibebin yistilin legnam kehatiyatachin temelisen beniseha endinimeles Egziabherim hgerachin Ethiopian ena hayimanotachin orthodox tewahedon keminsemaw kifu neger hulu yitebikilin! Amen!

Ye dingil baria said...

This comment fully conveys my sentiment... may the Almighty God give us his mercy at this critical time! Amen!!!!
ይህ ስብሰባ በይፋ በዚህች አገር ከተከናወነ ወይም እንዲከናወን ከተፈቀደ መንግስት ለሕዝቡ ያለው ንቀትና ድፍረት የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ውርደትን፣ ንቀትንና ድፍረትን መሸከም የለመደ ትከሻችንና ሁሉን በዝምታ የሚችል ሰፊ ሆዳችን ይህንንም መታገስና መሸከም ከቻለ እውነትም የለንም፡፡ ኢትዮጵያም ሆነች ኢትዮጵያዊነት የለም፡፡ ቢያንስ በዚህ እንኳን መንግስት የሰውነትና የእምነት ክብራችንን ቢጠብቅልን ምናለበት?

Mosad said...

Gobez anishewed yehe tata yemetabin Ato Melese Dolar lemagegnet silu yametubin eda new ...mekneyatum be HIV sem yemikebelew Dolar likelekelut selemichelu homosexualitin yekawemal yemil yewah lib yelegnim !

ጆሮ ያለው ይስማ said...

የቀበጠች አይጥ የድመትን አፍንጫ ታሸታለች !

Anonymous said...

ደጀሰላሞች
እባካችሁ ጨጓራችን አትላጡት:: ባንሰማው ይሻላል መሰል :: የምታወሩት ሁሉ ውሸት ስለሚመስለኝ ምንም አይሰማኝም ነበር :: አንዳንድ ሁኔታዎችን ሳረጋግጥ ዛሬ ደግሞ ምኑን ይጽፉ ይሆን በማለት ደጀሰላምን እየፈራኋት መጣሁ :: እባካችሁ ኢትዮጵያውያን ሁላችን አንድ አድርጎ በጋራ የምንጸልይበት ሁኔታ የሚያመቻች ጹሑፍ ጀምሩ ::

ፈጣሪ አገራችንና ቤተ ክርስቲያናችን ይጠብቅልን

Anonymous said...

BOYCOT-BOYCOTT- BOYCOTT

"JUPITER INTERNATIONAL HOTELS"

( both locations in Addis Ababa)

Please spread the news in every way possible to all Ethiopians so it will be a lesson for other hotels.

Anonymous said...

weche yamenenore mene marage alaben ebakachohe hasabe akafelone

Anonymous said...

gena bezu neger yemetabenal tebeku ers be eresachen mesmamat aketon beand betekereseteyan west kuch belen senbelala andun andun lematefat senrot egziabher lela meksefet lakebin abezen mefaker alebin kemetechachet wegen eski abatochen mesadeb enakum

Anonymous said...

IT IS BE A SHAME TO "T.P.L.F".LEZEMENAT TEKEBERA YENORECHEH HAGER.

Anonymous said...

.... እነዚህ ቤተክርስቲያን የሚያቃጥሉ ሙስሊም ነን የሚለዉ ምነዉ እዚህ ላይ በርትተዉ እርምጃ ቢወስዱ!!!

Anonymous said...

Everything against nature is digusting. being gay which includes Lesbian is something not natural in a way that cuts the root God ordered us keep it alive. May God be with us!!

Anonymous said...

The hipocracy of all of you makes me sick. I am not condoning homosexual behavior. GOD will be the judge.

But, all of you to look so hurt , as if the country;s immorality just began, shows how myopic and closed minded you are.

Where were you when prostitution is rampant in the country and young girls are sold on the street for pennies? Where where you when such behavior is lead to escourage of AIDS which made our coutry the fast growing HIV case in the world.

STOP your selective outrage. immorality is immorality is immorality. IT is not for you to list sins in order of importance.

Anonymous said...

http://www.newsdire.com/news/2331-gay-conference-in-ethiopia-may-face-ban.html

Anonymous said...

ezmen fethame selehon bezu negr yesmal. Egziabher lemenanenti neger aselefu endaysethn metheye egbanal.

ማህበረ፡ክርስቲያን said...

ቸሩ፡አምላክ፡ከዚህ፡ሁሉ፡ይሰውረን፡፡እነዚህን፡የዲያቢሎስን፡ግብር፡የሚያራምዱትን፡በሙሉ፡ካገራችን፡ነቅሎ፡ያውጣልን፡፡ኢትዮጵያ፡አገራችንን፡ይጠብቅልን፡፡
እባካችሁ፡የተቃውሞ፡ድምጻችንን፡የምናሰማበት፡መንገድ፡ካለ፡ብትገልጹልን፡፡
እመቤታችን፡ተራጂን!!!

Anonymous said...

Please Ethiopian Orthodox preachers Put aside your differences and be together in this regard.You should say something for the people with out fear when you be on a stage to preach people.

Above all please God and Merry be with us!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)